YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"የሐረማያ ዮንቨርስቲ ማስተማር ካቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው የዩኒቨርስቲዉ ሠራተኛ እና ተማሪዎች አስታወቁ።" -የጀርመን ድምፅ ራዲዮ

«ከተመዘገብን አንስቶ እስካሁን በአግባቡ የተማርነው አንድ ሳምንት ቢሆን ነው» የሚለው አንድ የዩንቨርስቲው ተማሪ በዚሁ መስተጓጎል ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ አንድ ወር እንደሆነው ገልፆልናል። በስልክ ያነጋገርናቸዉ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዩንቨርስቲው ባልደረባ እንደገለፁልን ደግሞ ትምህርት መልሶ ከተጀመረ 10 ቀን ገደማ ቢሆነውም ክፍል የሚገባው ተማሪ ቁጥር በጣም ውስን ነው። ለዚህም ባልደረባው በምክንያትነት የጠቀሱት አንዳንድ ተማሪዎች በድብቅ በሚያሰራጩት የማስፈራሪያ እና የአድማ ወረቀቶች ምክንያት ነው።

«በሐሮማያ ዩንቨርስቲ ግጭት ከተቀሰቀሰ አንስቶ የከፋ ችግር እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ የሰፈረዉ የፌደራል ፖሊስ ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል ፣መከላከያም ገብቷል። የኦሮሚያ አድማ በታኝ እና የዩንቨርስቲው ጥበቃም በግቢው ይገኛሉ» ተብሏል። በሐረማያ ዮንቨርስቲ ግጭት የተጀመረው ጥቅምት መጨረሻ ወልዲያ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች ከመገደላቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነው። የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ሰልፍ በመውጣት ወለጋ ላይ የተደነገገዉ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ይነሳ፣ መከላከያ ሠራዊት ከኦሮሚያ ይውጣ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ይውረዱ በሚል የፖለቲካ ጥያቄዎች አንስተው መንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ብለው ትምህርት አቁመው እንደነበር የዩንቨርስቲው ባልደረባ ተናግረዋል።

« በካፍቴሪያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ከሚመገቡት 13000 ገደማ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት 5000 ተማሪዎች ብቻ የሚገኙበት ሁኔታ አለ» ብለዋል የዮንቨርስቲው ባልደረባ። የተለያዩ የዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት እና ዛሬ በጋራ በተለያዩ ዮንቨርስቲዎች የተነሱትን ግጭቶች ተከትሎ በቀጣይ ሂደቱ ላይ በመምከር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።

ዘገባው የዶይቸ ቨሌ ነው
@YeneTube @FikerAssefa
ነገ ታህሳስ 02 ቀን/2012 ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ሲሆን ፡-አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

📌 ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ
📌 ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፤ ከፍል ውኃ ፤ ከለገሀር ፤ከካሳንችስ፤ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት ፤ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች በሥራላይ ያሉ የፀጥታ አካላት የመንገድ መረጃን በመጠየቅና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት እና መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥሮች ፡-
በ011-1-11- 01-11
፣011-5-52-40-77
፣011-5-52-63-02
፣011-5-52-63-03 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዛሬ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት በሁሉም ካንፓሶች ከምሽቱ 2:00 ብኃላ ከግቢው መውጣትም ሆነ መግባት የማይቻል መሆኑን በጥብቅ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጥምቀት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ከዓለም የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ።

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ ጥር 11 ቀን የሚከበረው ጥምቀት ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ የዓለም ባህላዊ ቅርሶች አራተኛው ሆኗል።ገዳ–የኦሮሞ የአስተዳደር ሥርዓት በ2016፣ ፊቼ ጨምበላላ–የሲዳማ የአዲስ አመት ክብረ በዓል በ2015 እንዲሁም የመስቀል በዓል በ2013 የማይዳሰሱ የዓለም ባህላዊ ቅርሶች ተብለው ተመዝግበዋል።

የዓለም የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ጉባኤ ጥምቀትን ጨምሮ አምስት ባህላዊ ቅርሶችን የመዘገበው በካምቦዲያ ዋና ከተማ በመካሔድ ላይ በሚገኘው ስብሰባው ነው። ምዝገባው ነገም ይቀጥላል።ዛሬ ረቡዕ በነበረው ስብሰባ ባቻታ የተባለ የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ማኅበረሰባዊ ሙዚቃ እና ዳንስ፣ አልፒኒዝም የተባለ በፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስዊትዘርላንድ ተራራ የመውጣት ማኅበረሰባዊ ባህል፣ በኢራን ዶታር የተባለ ማኅበረሰባዊ የሙዚቃ መሳሪያ የመስራት እና የመጫወት ባህል፣ በሜክሲኮ ውብ እና በአይነቱ ልዩ የሆነ ሸክላ የመስራት ጥበብ (artisanal talavera) ተመዝግበዋል።

Via Sheger Tribune
@YeneTube @FikerAssefa
የጠ/ሚ አብይ አህመድ አቀባበል በፎቶ!

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከአሜሪካው አቻቸው ማይክ ፖምፔዎ ትናንት ተገናኝተዋል። ፖምፔዎ ከሁለት ቀናት በፊት ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ መክረው ነበር።

ምንጭ: በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ዲሲ በአሜሪካ መንግስት እና በአለም ባንክ ታዛቢነት የተካሄደው ውይይት ተጠናቋል ይህን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ መግለጫ ሰጥተዋል።

Via Selam Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የባህርዳር ዩንቨርስቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ በአግባቡ እየተካሄደባቸው ባልሆኑ ጊቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሁለት የመንግስት ተቋማት ውዝግብ ምክንያት አገልግሎት ሊሰጥ ያልቻለው የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አሸማጋይነት ውሳኔ አግኝቷል፡፡

ሸገር ከመረጃ አቀባዮቹ እንደሰማው በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢው መስሪያ ቤት መካከል በነበረ እሰጣገባ ኃይል ባለማግኘቱ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያልቻለው ይህ የባቡር መንገድ ለቀሪ ስራው መሸፈኛ የሚሆን ወጪ ከመንግስት ግምጃ ቤት እንዲሰጠውና ለኃይል ማገናኛ መስመሮቹ የሚውል በፍጥነት የግዢ ጨረታ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ወጥቶ ስራው እንዲጀመር ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ከገንዘብ ሚኒስቴር ለዚሁ ግዢ የሚውል ገንዘብ ወጪ ከተደረገ በኋላ እዳውን የሚከፍለው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ነው ተብሏል፡፡ከአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሃራ ገበያ ለተገነባው የባቡር መስመር የኃይል ማስተላለፊያ ከፍተኛ መስመሮች የሚፈጀው ገንዘብ 37.5 ሚሊዮን ዶላር ይጠጋል መባሉን ሸገር ዘግቧል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መንገድ በኡራኤል አካባቢ ባለው መስመር አጥር ጥሶ የገባ ተሽከርካሪ ከአጥሮቹ መሰባበር በቀር ያደረሰው ጉዳት የለም ተብሏል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
"ፍቅርና ክብር የገባዉን ሕዝብ ማገልገል ኩራትም ዕድልም ነዉ።

አመሰግናለሁ
Galatoomaa
Thank You!
"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለተደረገላቸው አቀባበል ያቀረቡት ምስጋና

@YeneTube @FikerAssefa
በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ባለፈው ጊዜ ከጊቢ ውጭ ጉዳት ደርሶበት አንድ ተማሪ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል። በትናንትናው ዕለት ዋና የችግሩ ፈጣሪና ግብረ አበሮቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመነሻ 30 ብር ሂሳብ ቢዛ የተባለ አዲስ ሜትር ታክሲ ስራ ጀመር።

የቀድሞው የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በሀላፊነት የሚመሩት "ቢዛ ራይድ" የተባለ የታክሲ አገልግሎት በ248 መኪኖች ስራ የጀመረ ሲሆን በ6288 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎትን ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

Via:- Tesfay Getnet
@YeneTube @Fikerassefa
ዩኔስኮ የጥምቀት በአላችንን "የማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች" መዝገብ ውስጥ እንዳሰፈረ አስታውቋል!

እንኳን ደስ አለን!

@Yenetube @Fikerassefa
አዲሱ የማብራት ክፍያ ሲስተም ከመሀል አዲስ አበባ እስከ ክልል ከተሞች ነዋሪዎች እያማረረ ይገኛል።

ነዋሪዎች ከንጋት 12 ሰዐት ጀምሮ የወር እዳቸውን ለመግፈል ቢሰልፉም እዛው የክፍያ ጣቢያው ላይ ውሎ ከመመለስ በስተቀር ምንም አላተረፉም።

በሰበታ እና በአለም ገና ዛሬ ነዋሪዎች ለመክፈል ከንጋት ጀምሮ ቢሰለፉም በአግባቡ አለመስተናገዳቸውን እንዲሁም አቅመ ደካሞች እየተንገላቱ መሆናቸውን ተመልክተናል እና ማብራት ሀይል ሲስተም ከቀየረ ወዲህ የመጣው ይሄ ችግር ሊስተካከል እንደሚገባ ለማሳወቅ እንወዳለን።
@Yenetube @Fikerassefa