YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በተጨማሪ ⬇️

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት (ባልደራስ) #አግባብነት እና #ህጋዊነት የሌለው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ይህን የተናገሩት 'አዲስ ወግ' በተሰኘው የውይይት መድርክ የመዝጊያ ስነስርዐት ላይ ባሰሙት ንግግር ነው።

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት በማህበራት ማደራጃ አዋጅ መሰረት #እራሱን_እያደራጀና የቅድመ ምዝገባ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የምክርቤቱ ሰብሰባቢ ጋዜጠኛ #እስክንድር ነጋ ትናንት በኢሳት ቲቪ ተናግሮ ነበር። ምንም አይነት የህግ ጥሰት አለመፈጸሙንም ገልጿል።

-ElU
@Yenetube @Fikerassefa
እስክንድር ነጋ Vs ጀዋር መሐመድ ( # DW)

የአዲስ አበባ የባለቤትነት ዉዝግብ

«እኛ የምንለዉ ሕጉ የሚለዉን ነዉ።የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሕግ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ይላል።የፌደራሉ ሕገ መንግሥትም ኦሮሚያ (ከአዲስ አበባ) ልዩ ጥቅም እንዳለዉ ያስቀምጣል------»
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅና የመብት አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ
«የአዲስ አበባ ጉዳይ የዜግነት ጥያቄ ነዉ-----ሕገ መንግስቱ ከየት መጣ? ማን አወጣዉ? ምንስ አላማ ነበረዉ?------» ጋዜጠኛና የመብት አቀንቃኝ #እስክንድር_ነጋ

«እንዴ!! ምነዉ እባክሕ? እስክንድር ነጋ እኮ የመብት ታጋይ ነዉ----ልንቃወመዉ፣ ልንተቸዉ እንችላለን፣ ከዚያ ባለፈ ግን ዛሬ እስክንድርን ያስፈራሩ ነገ ጀዋርን ያስፈራራሉ-----እስክንድር ብቻዉን ሳይሆን ሁላችንም አብረነዉ ተሰልፈን እንታገላለን----» ጀዋር መሐመድ
ጀዋር ያለዉን «የምጠራጠርበት ምንም ምንም ምክንያት የለኝም።አመሰግነዋለሁ።-------» #እስክንድር_ነጋ

«በግሌ ከጠይቀከኝ ከእስክንዳር ጋር አይደለም ከማንም ጋር በማንኛዉም ሰዓት በዚሕ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም ጉዳይ ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነን----» #ጀዋር_መሐመድ

«ለመወያየት መቶ በመቶ ዝግጁ ነኝ። የምንፈታዉም በድርድርና ዉይይት ነዉ።----ብስለቱም አለን» እስክንድር ነጋ።
@YeneTube @FikerAssefa
የባላደራ ምክርቤቱ ሰብሳቢ

ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች #እስክንድር_ነጋ ጋዜጣዊ መግለጫውን ከሆቴሉ ውጭ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

@YeneTube @FikerAssefa