ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ይገኛል በጠዋቱ መረሀ ግብር ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪች ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ሲሆን ከሰዐት ላይ (7:30) ላይ ለማህበረሰብ ሳይንስ ኦሬንቴሽን ይሰጣል።
🎯ተማሪዎች ኦሬንቴሽን የሚሰጥበት አደራሽ መገኘት እንዲሁም መከታተል ግዴታችሁ ነው።
@YeneTube @Fikerassefa

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል።
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ይጀመራል።የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።ምክር ቤቱ በዚህ መደበኛ ስብሳበው የክልሉ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም በክልሉ ስራ አስፈፃሚ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ረቂቅ እድቅ ዙሪያ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ የዳኝነት የአገልግሎት ክፍያ፣ የዳኞች ጉባኤ ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን ተሻሽለው የወጡ ረቂቅ አዋጆችን ጨምሮ 5 የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa

በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል።
በቅርቡ የተከሰተው ግድያ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ለከተሞች እየተደረገ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
በቅርቡ የተከሰተው ግድያ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ለከተሞች እየተደረገ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተገባድቦ ዛሬ ተመርቋል፤ የመማር ማስተማር ሥራውንም ጀምሯል፡፡
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የሶፍኡመር ዋሻ በ‘UNESCO’ የአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ ለኦቢኤን እንደገልፁት በ ‘UNESCO’ በጊዚያዊ የአለም ቅርሰነት ተመዝግቦ የቆየውን የሶፍኡመር ዋሻ ሙሉ ለሙሉ ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ሁሉ ተሟልቷል፡፡ከድርጅቱ በተላኩ ባለሙያዎች ዋሻው ተጎብኝቶ ፤ አስፈላጊው ጥናት መደረጉን ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
Via OBN

ማረሚያ ቤቶች የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያቋቁሙ የሚፈቅድ ሕግ ተረቀቀ!
ባሳለፍነው ሳምንት መስከረም 29/2012 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የፌደራል ማሪሚያ ቤት ረቂቅ አዋጅ የማረሚያ ቤት አስተዳደርን ወደ ኮሚሽን እንዲያድግ እና ተጨማሪ ዘጠኝ ሥልጣኖች እንዲኖሩት ያቀረበ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ታራሚዎችን በሥራ ላይ ለማሰማራት የሚያስችሉ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያቋቁም ሥልጣን የሚሰጥ ነው።በተጨማሪም የማሰልጠኛ ተቋማት እንዲኖሩት፣ ለፖሊሶች የጋራ መኖሪያ ካምፖችን እንዲገነባ እና የውስጥ ገቢዎቹን ለመንግሥት ገቢ ማድረጉ ቀርቶ ከበጀት ውጪ ላሉ ሥራዎች እንዲያውል የሚሉት የተወሰኑት ናቸው።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

በጭልጋ ቁጥር 1 ወረዳ በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተፈጸመ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት እንደሆነ ተገለጸ፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ቁጥር 1 ወረዳ ‹ቡሆና› በተባለው አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሠራጨ ነው፡፡ አብመድ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ግን ‹‹ከመተማ ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ቡሆና አካባቢ በከባድ መሳሪያ ተመትቷል›› በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ከአካባቢው ባገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳኘው በለጠ ባለሙያዎችን ቦታው ድረስ በመላክ አረጋግጠናል በማለት ለአብመድ እንደገለጹት በአካባቢው መስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከተከሰተው ጥቃት ውጭ የተፈጸመ ሕገ ወጥ ድርጊት (ጥቃት) የለም፡፡
‹‹በአካባቢው አሁን አንጻራዊ ሠላም አለ፤ ጥምር የፀጥታ ኃይሉም ተቀናጅቶ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ የትናንቱ መግለጫ ደግሞ በኅብረተሰቡ ዘንድ መረጋጋት እንዲፈጠር አድርጓል›› ብለዋል አቶ ዳኘው፡፡ ትናንት ምሽት በተሰጠው መግለጫ ልክ የፀጥታ ኃይሉ አካባቢውን አስተማማኝ ሠላም የሠፈነበት ለማድረግ እንዲሰራ ነዋሪዎች እያሳሰቡ መሆኑንም ነው አቶ ዳኘው ያመለከቱት፡፡ኅብረተሰቡ ዛሬ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን አውቆ የተረጋጋ መደበኛ ሕይወቱን እንዲመራ ያሳሰቡት መምሪያ ኃላፊው በማኅበራዊ ሚዲያ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የቆዬ መረጃ እየለቀቁ ሕዝቡን ማደናገር እንደማይገባም አስገንዝበዋል፡፡

በመዲናዋ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ነው።
በአዲስ አበባ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ መሆናቸውን የከተማው ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተለይ ለኢቲቪ እንደተናገሩት በከተማዋ ካሉ 121 ወረዳዎች 62ቱ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ናቸው፡፡አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌኮም ኔትወርክ እገዛ እንደመሆኑ የዚህ መሰረተ ልማት ጥራትና ተደራሽነት ጉድለት የዲጂታል መታወቂያው በሁሉም የከተማዋ አስተዳደር እንዳይሰጥ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል አቶ ዮናስ፡፡ከዚህ ባሻገር የሰው ሀይል እጥረት፣ ስራውን ማስፈጸሚያ በቂ ቢሮ ያለመኖር እና ለሰራተኞች የሚከፈል ደመወዝ አናሳ መሆኑ አገልግሎቱን በመዲናዋ ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር ችግር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ: ኢቲቪ

አየር መንገዱ በጀመረው የኤሌከትሮኒክስ ቪዛ 200 ሺህ መንገደኞች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ 200 ሺህ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2017 ሰኔ ወር ላይ ጀምሮ ለደንበኞቹ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል።ይህን ተከትሎም የተለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች ከየትኛውም የአለም ክፍል ሆነው በአገልግሎቱ በመጠቀም በቀላሉ ወደ ሀገሪቱ መግባት ችለዋል።
በዚህ መሰረትም አግልግሎቱ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ከ217 ሀገሮች በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ 200 ሺህ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። አገልግሎቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ጥቅም ከማስገኘቱ ባለፈ ቱሪዝምን በማስተዋወቅ እና በንግድና ኢንቨስትመንት ሀገሪቱን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ተናግረዋል።ከዚህ ባለፈም በፍጥነት እያደገ ያለው የአየር መንገዱ ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነት በሀገሪቱ ካለው የሆቴል አገልግሎት ጋር ተቀናጅቶ ኢትዮጵያን ተመራጭ የኮንፈረንስ እና ቱሪዝም መናኸሪያ እንደሚያደርጋት ታምኖበታል።

ከአንድ ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ከመኪና ውስጥ ሰርቀው ለመማምለጥ ሙከራ ያደረጉ ሶስት ተጠርጣሪዎች በሕ/ሰቡ እና በፖሊስ ጥምረት ተያዙ ::
ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ/ም የግል ተበዳይ ሚስተር ፒን ላፊ ላንግ የተባሉ የሚንግ ሲያ ስትሮንግ ማሽነሪ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ የግ›ማህበር ባለቤት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ከሚገኘው አዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ 1.2 ሚሊየን ብር አውጥተው በኮድ 2 ቢ 23934 አ.አ ቪትዝ መኪናቸው ገንዘቡን ጭነው ሲሄዱ ተጠርጣሪዎቹ ደግሞ በኮድ 2 ቢ 01156 አ.አ ቪትዝ መኪና የግል ተበዳይ መኪናቸውን አቁመው ምሳ ለመብላት ወደ ሆቴል በገቡለት አጋጣሚ ተጠርጣሪዎቹ የመኪናውን መስታወት በመስበር መኪናው ውስጥ የነበረውን ሙሉ ሻንጣ ብር ይዘው በተሸከርካሪያቸው ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ የግል ተበዳይ ባሰሙት ይድረሱልኝ ጥሪ ተጠርጣሪዎቹ ከነ እግዝቢቱ በህ/ሰቡና በፖሊስ ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ረዋንዳ ጉሊት ቻይና ገበያ አካባቢ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን ተረፈ ይጥና ገልፀዋል ፡፡
የግል ተበዳዩ ንብረታቸው በቁጥጥር ስር በመዋሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ሕብረተሰቡና ፖሊስ ላደረገላቸው ከፍተኛ ትብብር ምስጋናቸው የላቀ መሆኑን ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል ፡፡በመጨረሻም መሰል ወንጀሎች በአ/አበባ ከተማ መበራከታቸውን የተናገሩት የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን ተረፈ ይጥና ሕብረተሰቡ ከፍተኛ መጠን ያሏቸውን ገንዘቦች በጥሬ ከመያዝ ይልቅ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በመጠቀም ከወንጀል ድርጊቶች አራሳቸውን መከላከል እንዳለባቸው መርማሪው በመልክታቸው ገልፀዋል ፡፡
Via Addis Ababa Police Commission

b47c-2c4b-4ea2-8747-8611a0441536.m4a
1.7 MB
መደበኛ ባልሆነ መንገድ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በራሳቸው የፖሊስን ስራ በመከወን የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን ከዚህ በኋላ እንደማይታገስ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተናገረ፡፡የፖለቲካ አመራሩም ለግጭት ምክንያት የሚሆኑ ንግግሮችን አቁሞ ህዝቡን ካረጋጋ ፖሊስ የዜጋውን ደህንነት ለመጠበቅ አይቸገረም ብሏል፡፡
Via sheger
@YeneTube @FikerAssefa
Via sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል መንግስት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአራት ተቃውሞ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸደቀ!
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በአራት ተቃውሞ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች በምክትል ርዕስ መስተዳድሩና ዘርፉን በሚመሩ የቢሮ ኃላፊዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ቀደም ሲል በክልሉ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የበጀት ዕጥረት መኖሩን ገልጸው በያዝነው በጀት ዓመት አዲስ ፕሮጀክት እንደማይኖርና የተጀመሩትን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረውዋል፡፡ለሰራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ለተጀመሩ የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ግንባታ ሀብት በማፈላለግ ይሰራል፡፡ ለሰራ ዕድል ፈጠራ ቁጠባን የሀብት ምንጭ በማደረግ መሰራት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡በትምህርቱ ዘርፉ የመምህራን ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራና አዳዲስ የመምህራን ቅጥር መፈጸም እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
Via SRTA

ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ከሦስተዮሹ መድረክ ውጭ ሌላ አማራጭ አትቀበልም ብለዋል- የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴትሩ ስለሺ በቀለ፡፡ ሚንስትሩ ይህን የተናገሩት ስለ ግድቡና ስለ ግብጽ አቋም ለሚንስትሮች ምክር ቤትና ባለድርሻዎች ገለጻ በደረጉበት ወቅት መሆኑን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ 💥
BLUE Brand Solutions
Blue Brand Solutions brought you the latest
📌Technologies(smartphones,Laptops)
📌 Men's and women's clothing👔
📌 Human hair 🙆♀
📌Musical instruments
📌Mens and Women's Perfume
Contact; @sherlockseller @Nah22
Call us
+251947896322&+251945421100
ቻናላቸውን ተቀላቅለሁ ይመልከቱ⬇️
https://tttttt.me/blueelec

ማስታወቂያ💥
Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
☎0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA
🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306

Macbook Pro😍 15.4" 256GB SSD Intel Core i7 9th Gen 2.60 GHz 16GB Touch Bar - Space
Call now🏃♂+251912894363
Or via ZenachBrands1
Join our channel 😍😍@ZenachBrands for more items

በሰመራ ከተማ ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ።
በሰመራ ብሔራዊ ስታዲየም በተካሔደው ሰልፍ ወደ 700 ገደማ ተሳታፊዎች የተለያዩ መፈክሮች ይዘው መገኘታቸውን በቦታው የነበሩ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
በሰልፉ የተሳተፉት አማር ሐቢብ «የኢሳ ማኅበረሰብ ከጅቡቲ መንግሥት ድጋፍ እያገኘ የአፋር ሕዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው። ኮንትሮባንዲስቶችም ኮንትሮባንዳቸው እንዳይቆምባቸው የአፋር ሕዝብ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጥቃት እያደረሱ ነው። ያንን የሚቃወም ተቃውሞ ነው እያሰማን ያለንው» ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
አቶ አልዛርቃዊ ሐቢብ የተባሉ ሌላ የሰመራ ነዋሪ «ዛሬ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነው በአፋር የተደረገው፤ የአፋር ሕዝብ በነቂስ ወጥቆ ነው ድምፁን ያሰማው» ብለዋል።
ባለፈው ቅዳሜ በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ኦብኖ ቀበሌ ታጣቂ ኃይሎች አደረሱት በተባለው ጥቃት ከ13 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 42 ሰዎች ቆስለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች በጅቡቲ መንግሥት የሚታገዙ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋል።
ይህንን ውንጀላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስተባብሏል። በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዦር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው «የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ የሚለው ወሬ ሐሰት ነው» ሲሉ ባለፈው ሰኞ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለት አደባባይ የወጡ የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ግን የመከላከያ ሚኒስቴርን ምላሽ አልተቀበሉም። አማር ሐቢብ «የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ በትናንትናው ዕለት የተለያዩ መረጃዎችን ይፋ አድርገው ነበር።
መከላከያ አሰሳ አድርጊያለሁ፤ እዚህ አካባቢ ምንም አይነት የውጭ ኃይል የለም። ብሎ ነበር። የክልሉ መንግሥት ደግሞ የዛን ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር። ያ ምላሽ ታርጋን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በአፋር ሚዲያ ይፋ አድርጎልናል። እኛ ደግሞ የክልላችንን ድምፅ በመደገፍ ነው የወጣንው» ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሚተላለፈው የአፋርኛ ቋንቋ የቴሌቭዥን ሥርጭት የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የሰጡት ማብራሪያ ለተቃውሞ አደባባይ ለወጡ ሰዎች አንዱ ገፊ ምክንያት ሆኗል። በብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ በተላለፈው ዘገባ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የጥቃት ፈፃሚዎቹን ማንነት ያረጋግጣሉ ያሏቸውን ሁለት አይነት ሰንደቅ ዓላማዎች፣ የፊት መሸፈኛ ጭንብል እና መታወቂያ ወረቀቶች አሳይተዋል።
በመታወቂያ ወረቀቶቹ ላይ «የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት የጸጥታ አስተዳደር እና ፍትኅ ቢሮ የልዩ ፖሊስ አባላት መታወቂያ ካርድ» የሚል ፅሁፍ ይነበባል። በአፋርኛ ቋንቋ የተላለፈውን ዘገባ የተመለከቱት አማር «ትናንትና ወረራ እየተካሔደብን እንደሆነ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ በእኛ ቋንቋ፤ በአፋርኛ የአየር ሰዓት ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበረ» ሲሉ አስረድተዋል።
Via:- DW