YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኢትዮጵያ_እና_ግብፅ

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገውን ድርድር እንደገና ለማስጀመር ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቅርቡ እንደሚገናኙ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት በአገራቸው ቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ጋር በሩሲያ እንደሚገናኙ አስታውቀዋል።

አል-ሲሲ ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጋር የሚገናኙበትን ትክክለኛ ቀን ባይገልጹም ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ጥቅምት 12 ቀን በሶቺ ከተማ የሚካሔደውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በተባባሪ ሊቀ-መንበርነት ይመራሉ።
ኢትዮጵያግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር ላይ ያደረጓቸው ድርድሮች ያለ ውጤት ተበትነዋል።

ባለፈው መስከረም በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የድርድሩ ፈቅ አለማለት ለቀጣናው መረጋጋት ሥጋት ሆኗል ያሉት ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ከፍትኃዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት ለመድረስ ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ «የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ» በማለት ውድቅ አድርጋለች።

Via:- Dw
@YeneTube @Fikeraseeda