YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የዘንድሮው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ጥቅምት 3 ይከበራል፡፡

12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ “ሰንደቅ አላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ይከበራል፡፡ቀኑ ሲከበር መንግስት የሚተገብራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች፣ ስለ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች፣ ስለ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና በፌዴራል ስርዓቱ ውስጥ ስለህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት የጋራ መግባባት በሚፈጥር መልኩ በመወያየት እንደሚሆንም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡በሕገ-መንግሥቱም ሆነ በአዋጆች ዕውቅና ያገኘውን ሰንደቅ ዓላማ ማክበርና በጋራ ከፍ አድርጎ ማውለብለብ ተገቢ እንደሆነም ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ የአገራችን ሉዓላዊነትና የሕዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት መገለጫ ነው፡፡

-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 6000 የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃደኝነነት ለአንድ ወር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን ና ኮፒ በመያዝ ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ማእከል በአካል በመገኘት ከመስከረም 24 ቀን 2012 ጀምሮ በስራ ሰአት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

• አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች

• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው

• እድሜ ከ20- 45 አማት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ

• የስራ ልምድ አይጠይቅም. ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ አበል የሚከፍል ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

Via:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ከአዲስ አበባ ቀጥታ ጅቡቲ የነበረውን የጉዞ መስመር ሊቀይር ነው!

በሳምንት ሁለት ቀናት ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚመላለሰውን የባቡር ትራንስፖርት በማስቀረት አዲስ የጉዞ መስመር ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጨረሱን የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንድነት ፓርክ ተመረቀ!

በታላቁ ቤተመንግስት የተሰራው የአንድነት ፓርክ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ተመርቆ ተከፈተ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጥቂት መረጃ ስለ አንድነት ፓርክ!

ከትናንት በስቲያ ፓርኩን እና በግቢው ውስጥ የተከናወኑ መጠነ ሰፊ እድሳቶችን የውጭ ሚድያ ጋዜጠኞች ጎብኝተን ነበር። ከጉብኝቱ የወሰድኳቸውን የተወሰኑ መረጃዎች ላካፍላችሁ:

📌 አጠቃላይ የፓርኩ ስራ፣ የግቢው አጥር እና አዳዲስ ህንፃዎች ግንባታ፣ የድሮዎቹ ህንፃዎች እድሳት እና ጥገና በግምት 5 ቢልዮን ብር ገደማ ፈጅቷል።

📌 ለፓርኪንግ የሚሆን ሌላ ሰፊ ግንባታ ከግቢው ውጪ ተጀምሯል። ይህም ተጨማሪ 1.5 ቢልዮን ብር ይፈጃል ተብሎ ተገምቷል

📌 ሙሉ ወጪውን የሸፈነው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ነው

📌 ዘጠኝ ወር የፈጀው ግንባታ እየተከናወነ ባለበት የቁፋሮ ስራ ወቅት የሰው አፅምን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተሽከርካሪዎች ተቀብረው ተገኝተዋል።

📌 የቀድሞዎቹ ጠ/ሚሮች መለስ ዜናዊ እና ሀይለማርያም ደሳለኝ ይኖሩበት የነበረው ህንፃ የቤት እቃዎች ገብተውለት የእንግዳ መሪዎች ማረፊያ እንዲሆን ታስቧል።

📌 አንዳንድ ግንባታዎች ጥቃቅን ስራ ይቀራቸዋል፣ በተለይ የአንበሳ እና ሌሎች እንስሳት ማረፊያ ቦታ። የአንበሳ ስፍራው "ጥቁር አንበሳ" የተባለው ልዩ አንበሳ መኖርያ ይሆናል። በአጠቃላይ 300 ገደማ እንስሳቶች የፓርኩ የእንስሳት ክፍል ውስጥ ሆነው ለህዝብ እይታ ይውላሉ።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጽ ፓርላማ ለሕዳሴው ግድብ ጊዜያዊ ኮሚቴ እንደሚያቋቁም ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

ኮሚቴው መንግሥት ስለ ግድቡ ያቀረበለትን አቋም ይመረምራል፡፡ ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ ጥቅሟን ለማስጠበቅ መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች ይፈትሻል፡፡ ከውጭ፣ አፍሪካ ጉዳዮች፣ መከላከያና ብሄራዊ ደኅንነት የሚውጣጣውን ኮሚቴ፣ የፓርላማው ምክትል አፈ ጉባዔ ይመሩታል፡፡ ግብጽ የሦስትዮሹን Declaration of Principles ስምምነት ተንተርሳ፣ ገለልተኛ አሸማጋይ እንዲገባ አቋም እንደያዘች ጠቅላይ ሚንስትሩ ትናንት ለፓርላማው ገልጸዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በሐምሌ ኤርትራን ሲጎበኙ፣ የውጭ ሚንስቴር ምንም መረጃ እንዳልነበረው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ባለሥልጣኖቹ ጉብኝቱን እንደ ተራው ዜጋ ከኤርትራ ዜና ምንጮችና ከማኅበራዊ ሜዲያ ነው የሰሙት፡፡ የተቋሙ መገለል፣ የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም አደጋ ላይ ሊልው ይችላል- ብለዋል ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡ የዐለም ዐቀፉ ግጭት ተቋም (አይሲጄ) የአፍሪካ ሃላፊ በበኩላቸው፣ ዐቢይ የለውጥ አጀንዳቸውን በተቋማት ካልመሩት መሠረት ሊይዝላቸው አይችልም ሲሉ ተችተዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ይደረጋል ለተባለው ሰልፍ ዝግጅት መጨረሱን ‹‹የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት›› ተናገረ፡፡

የከተማዋ አስተዳደር በበኩሉ ጥያቄው ደርሶኛል፣ ለፀጥታና ለደኅንነት መዋቅሩም አሳውቄያለሁ ሲል ለአሐዱ ቴሌቪዥን አረጋግጧል፡፡የአዲስ አበባ ሕዝብ በርካታ የፖለቲካ፣ ምጣኔ ሀብትና ማኅበራዊ ጥያቄዎች አሉት፤ እነዚህንም ጥያቄዎች ይዤ እሰራለሁ ሲል መጋቢት 1/2011 የተቋቋመው ባለአደራ ምክር ቤቱ ለጥቅምት 2/2012 የጠራሁት ሰልፍ እውቅና አግኝቷል ብሏል፡፡በመስቀል አደባባይ ይደረጋል በተባለው ሰልፍም የዴሞክራሲና የሰላም መልዕክቶች ይተላለፋሉ ሲል የባለአደራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ ተናግሯል፡፡

በሰልፉ የሚሳተፉ የመዲናዋ ነዋሪዎችም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የፖለቲካ፣ ምጣኔ ሃብትና ማኅበራዊ ጥያቄዎቻቸውን እንዲያቀረቡ ባልደራሱ የአደራ ጥሪ አቅርቧል፡፡የአደባባይ ሰልፍና ኹነቶች ላይ የተለያዩ አርማና ምልክቶች መታየትን ተከትሎ አሐዱ ባልደራሱን የጠየቀ ሲሆን፣ ‹‹ሰልፈኞቹን ይሔን ይዛችሁ ውጡ ያንን ተው ማለት አልችልም፤ ይልቁንም የመሰላቸውንና ይወክለኛል ያሉትን አርማ መያዝ ይችላሉ የሚል አቋም አለኝ›› ብሏል፡፡ዋናው ግን ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ መግለፅና የሌላውን ማክበር ነው ሲልም አፅንኦት ሰጥቷል፡፡

አሐዱ ስለ ሰልፉ እውቅና የጠየቃቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬተሪ ፌቨን ተሾመ ጥያቄው ለአስተዳደሩ እንደደረሰውና ለፌደራልና ለከተማው የደኅነትና የፀጥታ መዋቅር ማሳወቁን ተናግረዋል፡፡ባልደራሱ ከሚያነሳቸው ጥያቄዎች መካከል የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የካቢኔ ሥልጣን ዘመን አልቋል፣ ስለዚህም የባለ አደራ አስተዳደር መመስረት አለበት የሚለው ይገኝበታል፡፡ በተጓዳኝ የከተማዋ ነዋሪ መብቶች አልተከበሩም አስተዳዳሩም ለነዋሪው ትክክለኛ ወካይ አልሆነም ሲልም ይወቅሳል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በአንፃሩ የከተማዋን ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል እየሰራ እንደሆነ በመግለፅ የባለአደራ ምክር ቤትን እንደማይቀበል ምላሽ ሲሰጥና ሲያስጠነቅቅ ከርሟል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተናገሩት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች
• የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዝምድና ውክልና እስከመሰጣጠት የደረሰ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
• ባቀረብንላችሁ ጥሪ መሰረት የ5 ሚሊዮን ብሩን እራት የታደማችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እንኳን በሰላም መጣችሁ
• የ5 ሚሊዮን ብሩን እራት እንዲደገም በርካቶች ጥሪ ቢያቀርቡም እራቱ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገ በመሆኑ እንደማይደገም አረጋግጠዋል
• በፕሮጀክቱ ቀን ከለሊት በመስራት ማጠናቀቅ የቻሉ ኢትዮጵያውያንም እንኳን ደስ አላችሁ ተብሏል
• እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪክ አለን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ዱካችን በባህርም ሆነ በሰማይ ይታያል

• ስልጣኔ የተከማቸ የእውቀት ጥበብ ነው፣ ስልጣኔ ሳያቋርጥ እንደሚፈስ ጅረት ነው

• አባቶቻችን ጥፋት ቢሰሩም ከነሱ ጥፋት ተምረን አባቶቻችን አንድ አድርገው ያሳለፉልንን አገር አንድ አድርገን ማሻገር ግዴታ እንዳለብን ያሳያል

• ልጆቻችን ቤተመንግስት ፎቶ የማይነሳ የሚያስፈራ ስፍራ ሳይሆን፣ በመገዳደል ብቻ የሚገባበት ሳይሆን የሚጎበኝ ስፍራ መሆኑንም ለማሳየት የሚስችል ስፍራ ነው

• በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ትልቁን ፓርክ እንገነባለን

• ይህንን ለማሳካት የሚያቆመን አንዳችም ሀይል የለም

• በዚህ ቤተመንህግስት ርካታ አስደናቂ ግብዣዎች ተደርገዋል በርካቶችም አድንቀውት አልፈዋል

• ዛሬ ለመላ ኢትዮጵያውያን መናገር የምፈልገው እኛ እንቀጥላለን ታሪክን ከዛሬ ጋር ለነገ በሚበጅ መልኩ አስተሳስረን እንቀጥላለን

• የሚያግዘን ካገኘን የወሩን በሳምንት የሳምንቱንም በእለት እንጨርሳለን

• ጨርሰን ሪባን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
"ተስፋ የሚስቆርጡ ነገሮች በየሰከንዱ የሚታዩበት፣ በየዕለቱ በሚያስደምም ሁኔታ የተሰፋው የሚተረተርባት ሀገር ውስጥ ብንሆንም ተስፋ አንቆርጥም" -

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአንድነት ፓርክ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ካሰሙት ንግግር የተወሰደ

#Ethiopia
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from WaymoreBrands😎(Clothing) (Kal)
Best brand frames❤️ Gucci👌 Boss🤓 and many more....The price includes delivery to any destination in addis and it includes😁 photo solar and anti glare lenses😎 call +251912894364
Or inbox via @ZenachBrands1
Forwarded from YeneTube
Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ዘመናዊ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግንባታ እሁድ ይጀምራል!

የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ህንጻ ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡የግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓቱ እሁድ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ የከተማዋና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ይከናወናል፡፡ህንጻው ከመሬት ስር የሚገነቡ አራት ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፤ ከትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል በተጨማሪ መረጃ ማደራጃ ክፍሎች፣ የወንጀልና የአደጋ መከላከያ መረጃ ቢሮዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ያካትታል፡፡ፕሮጀክቱ ከመሬት ስር የሚጠናቀቅ ሲሆን ከመሬት በላይ ለአረንጓዴ ልማት እንደሚውል ተገልጿል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዪ የ2012 ዓ.ም አርአያ ሰው ሽልማት አሸናፊ ሆነች።

ጋዜጠኛ አስካለ መቀመጫውን አሜሪካ - ዳላስ ባደረገው አድዋ የባህልና ታሪክ ማህበር አዘጋጅነት የሚከናወነውን የ2012 አርአያ ሰው ሽልማት ነው ያሸነፈችው ።ከ22 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት ሙያ አገሯንና ህዝቧን እያገለገለች የምትገኘው ጋዜጠኛ አስካለ፣ለረጅም አመታት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዪ ታቀርባቸው በነበሩ ፕሮግራሞች ተወዳጅ ለመሆን የበቃች አንጋፋና ተወዳጅ ጋዜጠኛ ናት።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በ ኢቲቪ መዝናኛ ቻናል በሚተላለፈው ውሎ አዳር በተሰኘው ፕሮግራሟ የብዙ ተመልካቾችን ቀልብ ስባለች ተብሏል::

የዉሎ አዳር ኘሮግራም የኢትዮጵያዊያንን አኗኗር በተለይም ሰፊውን የገጠሩን ህብረተሰብ አኗኗር ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ኘሮግራም ነው። ስራን በተግባር፤ ሙያን በፍቅር ያስመሰከረች ጋዜጠኛ በሚልም ከፕሮግራሙ ጋር በበርካታ ተመልካቾች እየተመሰከረላት እንደሆነ በሽልማት ስነስርአቱ ላይ ተገልጧል፡፡በዚሁ ፕሮግራም ባሳየችው ሙያዊ ብቃት፣ የ2012 አርአያ ሰው ሽልማት አሸናፊ መሆኗ ተገልጧል፡፡

Via FM Addis 97.1
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል አሸነፉ!!

💚💛 እንኳን ደስ አለን💚💛
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸነፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡

ዘንድሮ ለዘርፉ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሪታ ተንበርግ በሰፊው ያሸንፋሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከ20 ዓመት በፊት ደም አፋሳሽ የነበረውንና በርካታ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ አድርገው ሰላም በማውረዳቸውና ምስራቅ አፍሪካ የትብብር ቀጠና እንዲሆን ያደረጉት ድፕሎማሲያዊ ጥረት የኖቤል ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡

በተለይም ወደ ደም መፋሰስ እየገባች የነበረችው የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ተደራድረው የስልጣን ክፍፍል በማድረግ ወደ ሰላም መመለሳቸውም ትልቅ ዋጋ የሚያሰጥ ስኬት ተደርጎም ተወስዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኝ ማስተከላቸውና በእርሳቸው አመራር የካቢኔያቸውን ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ማድረጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲቸራቸው ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ጠበብቶች ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተለያዩ መስኮች ጉልህ ተግባራቶችን ያከናወኑ ግለሰቦችን ተቋማት በየዓመቱ የሚሸለሙበት የኖቤል ሽልማት በአለማችን ከሚሰጡ ሽልማቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

የኖቤል የሰላም ሽልማት እስካሁን ለ133 ግለሰቦችና ተቋማቶች ተሰጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ 1938 ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ለኖቤል ሽልማት መታጨታቸው የቢቢሲ መረጃ ያሳያል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማትን በማሸነፋቸው 9 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 9 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ይበረከትላቸዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባን ከባህርዳርና ጎንደር የሚያገናኘው መንገድ ዛሬ ረፋድ ጀምሮ ጎሃ ጺዮን ከተማ ላይ ተዘግቷል።

ጎሃ ጺዮን በአባይ በርሃ አፋፋ ላይ የምትገኝ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች አዋሳኝ ከተማ ናት።
@YeneTube @Fikerassefa