በድሬደዋ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ።
ግጭቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ #ተደርጓል።
በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ጋራ ፣ደቻቱና አምስተኛ ተብለዉ በሚጠሩ ቦታዎች ትናንት ረፋድ ጀምሮ በአካባቢዉ ነዋሪዎች መካከል ማንነት ላይ ያነጣጠረ ግጭት ተቀስቅሷል።
ይህንን በመቃወምም በደቻቱ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች «መንግስት መፍትሄ ይስጠን» ሲሉ የከተማዋን አስተዳደር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።
ከሰልፈኞቹ መካከል ተመርጠው ከአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያካሄዱት ነዋሪዎች "ብሄርና ማነትታችንን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እየደረሱብን ነው። አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ እና መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።
ነዋሪዎቹ "የአካባቢ /መንደር ግጭትን መፍታት ለመንግስት እንዴት አንደተሳነው አልገባንም? ምላሽ ይሰጠን ?"ሲሉም ጠይቀዋል።እንደ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ "ከአስተዳደሩ አመራር አካላት ጭምር ችግሩን በየጊዜው የሚያባብስ አካል አለ ፤ አስተዳደሩም ሆነ የፀጥታ ኃይሉ ሰላማችንን እና ደህንነታችንን በተገቢው መንገድ ሊያስጠብቅ ባለመቻሉ የፌደራል መንግስት ጣልቃ ሊገባና ለችግራችን አንድ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል» ብለዋል።
በድሬደዋ ከአዲስ አመት ዋዜማ ጀምሮ የተቀሰቀሰው የደቻቱ አምስተኛ፣ ገንደጋራ እና አዲስ ከተማ አካባቢዎች ግጭት ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን በግጭቱ ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት፣ ለአካል መጉደል እንዲሁም ለንብረት ዉድመትና ዝርፊያ ምክንያት ሆኗል። የእነዚህ አካባቢዎች ትልቁ የገበያ ማዕከል ቀፊራም ተገቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄድ ተስኖታል።
ዛሬ ለአቤቱታና ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎችን ያነጋገሩት የአስተዳደ የድርጅት እና መንግስት ስራ ኃላፊዎች በበኩላቸዉ አስተዳደሩ በአካባቢው እየተፈጠሩ የሚገኙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፣የችግሩ ጠንሳሽ እና አባባሽ ያላቸውን አካላት ወንጀል በማጣራና በቁጥጥር በማዋል ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እየሰራን ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል ከህዝቡ ጋር ወርዶ በመወያየት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።
Via:-DW
@YeneTube @Fikerassefa