YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዊ ብሔ/አስ/ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ ፡፡

ከእንጅባራ ከተማ ወጣ ብሎ በአካይታ ቀበሌ በቀን 26/1/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ስዓት አካባቢ ከእንጅባራ አምበላ ተሳፋሪ ጭኖ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-13645 አማ ታርጋ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ እንጅባራ አቅጣጫ ከሚመጣ ሎቤድ ኮድ 3-84604 ኢት ጋር በመጋጨቱ ወዲያውኑ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎቹ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በእንጅባራ አጠቃላይ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢ/ር አስማረ ገብረኪዳን ተናግረው እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች መረጃዎችን ተከታትለን የምናደረስ ይሆናል ብሏል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa