“ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር አንስማማም ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ ይከታተለኝ ነበር፤ እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም፤ ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ለእርሱ ኦነግ ነህ ማለት ነው ” አቶ ጁነዲን ሳዶ
አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ ዘመን ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ መካከል የተወሰዱ ጥቂት ነጥቦች
📌 ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በነበሩበት ጊዜ ምንም የማያወላዳ የህወሃት የበላይነት አለ። ይህ በፖሊሲ ደረጃ ነው።
📌 በምርጫ 97 የኢህአዴግ ደረት ትንሽ አበጥ ያለበት ሁኔታ ነበርና ለተቃዋሚዎች ትኩረት አልተሰጠም።
📌 ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚነሱብኝ ጉዳዮች የፖለቲካ ሥራ ነው የተሰራባቸው። የፖለቲካ ሥራውን የሰሩት ሰዎች ደግሞ ከፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ ከኢህአዴግም ከኦህዴድም ውስጥ ናቸው።
📌 የደህንነት መስሪያ ቤቱ ነበር የተሳሳቱ መረጃዎችን በሕዝቡ መካከል ሲያሰራጭ የነበረው። በግል ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር አንስማማም።
📌 አሃበሽ የሚባል ባዕድ ሃይማኖት እንዲገባ ያደረገው እሱ ነው ይላሉ።
📌 መስኪድ አሰራ ስለሚባለው እኔ በሕይወቴ እስከአሁን ያሰራሁት አንድ መስኪድ ብቻ ነው። እናቴ ስታርፍ አርሲ የተወለድኩበት ቦታ ላይ በአርሲ ባህል «በጌጌሳ» ገንዘብ አሰባስቤ ነው የሰራሁት፤ በልመና።
📌 ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይከታተለኝ ነበር። እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ኦነግ ነህ ማለት ነው ለእርሱ።
📌 ኦነጎች በበኩላቸው መንግሥት ውስጥ በመሆኔ የሚቀሰቅስብን እና የሚያስቸግረን እሱ ነው ብለው እኔን የሚጠሉበት ሁኔታ አለ። ይሁንና አቶ ጌታቸው አሰፋ ኦነግ ነው ብሎ ፋይል ከፍቶብኝ ስልኬን እያስጠለፈ በርካታ ችግር አድርሶብኛል።
📌 እኔን ምክንያት አድርገው ባለቤቴን ስላሰሯት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገብቼ ነበር። የመጨረሻው ልጄ ከእናቱ ተለይቶ የማያውቅ ገና የአራት ዓመት ሕፃን ነበር። ባለቤቴን ፍቷትና እኔን እሰሩኝ ብል ማንም ሊሰማኝ አልቻለም።
📌 ለህክምና ታይላንድ ነው በቀጥታ የሄድኩት። ታይላንድ ለአንድ ወር በህክምና ቆየሁና ወደዱባይ አመራሁ። ዱባይ ሁለት ወር ቆይቻለሁ። እዚያ ተራ ሥራ እየሰራሁ ኑሮን ለመግፋት አስቤ ነበር ግን አልሆነም።
📌 በኬንያ 12 ወር ቆይቻለሁ። በወቅቱ ትንሽ ከተማ ውስጥ ተደብቄ ነበር። ኬንያ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። ታስረው መጥተውም ደብዛቸው የጠፉ አሉ። እኔ የት እንዳለሁ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቢያውቅ ስለሚያስረኝ የምጠቀመው ስልክ እንኳን ኢንተርኔት የሌለው ነበር።
📌 በኋላ ከኬንያ ወደአሜሪካ አቀናሁ። እናም እንኳን የደህንነት ሰዎች ሊደግፉኝ ቀርቶ ሲያሳድዱኝ የነበሩት እነሱ ነበሩ።
📌 አሜሪካ ስገባ ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለበጎ ነው በማለት እራሴን ወደሃይማኖቴ በመመለስ እንደገና ውስጤን ለማየት ቻልኩ፡፡ ለሰዎችም ይቅርታ ማድረግ ጀመርኩ።
📌 አሁን ጌታቸው አሰፋን ባገኘው ቀድሞ እንደምናደድበት አልናደድበትም፡፡ ይልቁንም ሰላም እለዋለሁ። እርሱም አሁን ችግር ውስጥ ነው።
📌 ከለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እና አቶ ለማ መገርሳ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት አግኝቻቸዋለሁ። ሀገሬ መመለስ እፈልጋለሁ ስላቸው ዶክተር ዐብይ ዝግጁ ከሆንክ አሁኑኑ እንድትመጣ ነበር ያለኝ።
📌 አሁን ገንዘብ ስለሌለኝ አቅም ካላቸው ሰዎች ጋር እየተባበርኩ ለመስራት ነው ሃሳቤ። ባለሀብቶችን ማሰባሰብ እና ማሳመን የሚጠይቅ ሥራ ላይ ተሰማርቻለሁ።
📌 ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ ግጭቶች ይጠበቃሉ። ግጭት ባይኖር ነበር ጤነኛ የማይሆነው። እዚህም እዚያም የሚፈነዳዱ ነገሮች በአግባቡ ከተያዙ ወደትክክለኛ መፍትሄ ይመጣሉ። ዋናው ነገር መንግሥት ጠንካራ መሆን መቻል አለበት።
📌 ጠንካራ የሚሊተሪ አቅም ወይም የፖሊስ አቅም ብቻ ሳይሆን የመንግሥት ጥንካሬ በንግግር ቃላት፣ በተግባር ማሳየት፣ በመዋቅር እና በፍትህ ይገለጻል።
📌 መንግሥት የሚችለውን እሰራለሁ የማይችለውን አልችልም ማለት አለበት። የሃሰት ቃል እየተገባ ከሄደ የሕዝብ አመኔታ እና አክብሮቱ ይታጣል።
📌 መንግሥት ቆፍጣና ሆኖ የእራሱን ሰዎች በአግባቡ ማሰማራት ካልቻለ ሕዝቡ አያከብረውም። ከዚህ ባለፈ ግን እንደ አጠቃላይ ሕግ የበላይነት ላይ ማወላዳት አያስፈልግም።
📌 ኢትዮጵያም ሙሉ የምትሆነው ከብሔር ብሔረሰቦቿ ጋር ነው። አንዱን በኢኮኖሚም ሆነ በማህበራዊ ጉዳይ አግልሎ ሌላው ሊያድግ አይችልም። በዚህ ረገድ አንዱ ለአንዱ ስጋት መሆን የለበትም።
📌 ሜቴክ ገንዘብ ስለዘረፈ የትግራይ ሕዝብ አብሮ መጨፍለቅ የለበትም የሚል አስተሳሰብ ይዘን መጓዘ ያስፈልጋል፡፡
📌 ጥቂት የኦዲፒ ባለሥልጣናት ካጠፉ ኦሮሞ ሕዝብን በአንድ ላይ መፈረጅ ኢትዮጵያዊነትን ያላላል። እናም ሁሉም አካታችነትን ሳይለቅ ሁሉም ተከባብሮ ሲኖር ነው ጥንካሬ የምናገኘው።
📌 ክልል መሆን ኢማዕከላዊነትን አያሳይም። ወደፊት እኮ ክልሎችም መልሰው ሊዋሃዱ /Re union/ ሊደረግ ይችላል።
ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa

#ኢሬቻ2012 በውቢቷ #ሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተከብሯል።
ከተለያዩ ኦሮምያ ክልል የመጡ ቄሮች እና አባገዳዎች ከሲዳማ ህዝብ ጋር ኢሬቻን በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አደራሽ አክብረዋል።
@YeneTube @Fikerassefa

በምዕራብ ጎንደር ዞን አማራና ቅማንት በሚዋሰኑባቸው አባቢዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት በተፈጸሙ ጥቃቶች በአማራ ልዩ ሀይል አባላት ላይ የሞትና የመቁሰል ጉዳቶች ደረሱ።
ዛሬ ከሽኸዲ ከተማ ወደ ነጋዴ ባህር በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ቅኝት በማድረግ ላይበነበሩ የልዩ ሀይሉ ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አንድ ፖሊስ ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል። በተመሳሳይ ዛሬ በጭልጋ ከተማ በታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት የአንድ የልዩ ሀይል ኣአባል ህይወት አልፏል።
ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ከአይከል ከተማ ወደ ዳንጉራ በማምራት ላይ በነበሩ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ላይ ጥቃት መፈጸሙና ጉዳት መድረሱም ይታወሳል።
በሌላ በኩል የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በቅማንት ብሔረሰብ አባላት ላይ ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑን አስታውቋል።
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ባወጡት ዘለግ ያለ ሀተታ ልዩ ሀይሉ ቅማንትን ጨምሮ በአማራ ክልል በሚኖሩ ንዑሳን ብሔረሰቦች ላይ እየፈጸመ ነው ያሉትን ጥቃት ኮንነዋል።
Via Ethiopia Live updates

በሴቶች 10,000 ሜትር ዉድድር ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሲፈን ሀሰን አንደኛ ሆና አጠናቃለች።ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ወጥታ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳልያ አስገኝታለች።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የቤንሻንጉል ክልል የ102 ባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ።
በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ 102 ባለሀብቶች ፈቃድ መሰረዙንና ይዘውት የነበሩትን 56ሺ ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ማስገባቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡በክልሉ የአካባቢ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ነፃነት ዘለቀ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ለእርሻ ሥራ ፈቃድ ወስደው ያላለሙ ባለሀብቶች እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በክልሉ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ 651 ባለሀብቶች መሆናቸውን ጠቅሰው እነዚህም 350ሺ ሄክታር መሬት ወስደዋል፡፡
ይሁንና መሬቱን የሚያለሙና ያላለሙ በሚል በተደረገ ልየታ 102 የሚሆኑት ሳያለሙ የቀሩ በመሆናቸው እርምጃው መወሰዱን ጠቅሰው በዚህም 56ሺ ሄክታር መሬት ተነጥቆ ለመሬት ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል፡፡የአስር ባለሀብቶች የተበላሸ ብድር መሰረዙን ያነሱት አቶ ነፃነት፤ ከባንክ መሬቱን አሲዘው ብድር የወሰዱ በመሆኑ ባንኩ ‹‹መሬቱን ይዘን ብድር ስለሰጠን የመሬቱ ባለቤቶች ነን›› በሚል ከቢሮው ጋር ያለመግባባት መፈጠሩን አንስተዋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም አዲስ የምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከመስከረም 27-29/2012 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርስቲው አሳውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ቀነኒሳ በቀለ የበርሊን ማራቶንን አሸነፈ።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የበርሊን ማራቶንን ቀነኒሳ በቀለ አሸነፈ፡፡ቀነኒሳ 2 ሰዓት ከ01 ደቂቃ 41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈው፡፡ቀነኒሳ የአለም የማራቶን ሪከርድን ለማሻሻል 2 ሰከንድ ብቻ እንደዘገየ ነው የተነገረው፡፡
ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የበርሊን ማራቶንን ቀነኒሳ በቀለ አሸነፈ፡፡ቀነኒሳ 2 ሰዓት ከ01 ደቂቃ 41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈው፡፡ቀነኒሳ የአለም የማራቶን ሪከርድን ለማሻሻል 2 ሰከንድ ብቻ እንደዘገየ ነው የተነገረው፡፡
ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
በርሊን ማራቶን ሴቶች
እሸቴ በከሪ 🇪🇹 2:20:14
ማሬ ዲባባ 🇪🇹 2:20:21
ሳሊ ቼፒዬጎ 🇰🇪 2:21:06
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
እሸቴ በከሪ 🇪🇹 2:20:14
ማሬ ዲባባ 🇪🇹 2:20:21
ሳሊ ቼፒዬጎ 🇰🇪 2:21:06
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋና አካባቢዋ በተፈጠረ የፀጥታ መደፍረስ ችግር የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
የአማራ ክልል የጸጥታና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደገለጹት በትናንትናው ዕለት አይከል ከተማ አቅራቢያ በሚኒባስ ሲጓዙ ከነበሩ ሰዎች መካከል 6 መንገደኞች "በማንነታቸው ምክንያት" ተመርጠው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኅላ ተገለዋል።
አቶ ተሻገር ለጥቃቱ "ጽንፈኛ" ያሏቸውን የቅማንት ኮሚቴ አባላት ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ኮሚቴው "ለውጡ" እንዲደናቀፍ በሚፈልጉ ሀይሎች 'ስፖንሰር' እንደሚደረግም ገልጸዋል።
Via:- EThiopian Live Update

ከአፋር ክልል የመጡ ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረዉ ባደረሱት ጥቃት በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን አፈደም ወረዳ አላሌ መንደር 15 ንፁሃን ዜጎች ሲሞቱ ፣ ሌሎች በርካታ ዜጎችም ቆስሏል።
ተመሳሳይ ጥቃቶች ላለፉት 2 ቀናት በሃሪሳ ወረዳ መንደሮች መከሰታቸዉና ከብቶችን በመዝረፍ ቤቶቹን ማቃጠላቸዉን ለማወቅ ችለናል። የፌደራል መንግስቱ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ እልባት ልያበጅለት እንደሚገባው የአካባቢው ነዋሪዎች አሳስበዋል።
በሁለቱ ወንድማማቾች ህዝቦች መካካል ግጭት የሚፈጥሩ አካላትም ለህግ ማቅረብ እንዳለበትም አክለው ገልጸዋል።የሶማሌ ክልል መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ በፍጥነት አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ እንዳለበት ለሚመለከተዉ የፌደራል ተቋምም ሪፖርት ማድረግ እንዳለበትም ጭምር።አላሌ ከአፋርና ሶማሌ ክልል በ60 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንደምትገኝ ለማወቅ ችለናል ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በቁጥጥር ስር ዋሉ!
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቤተሰባቸው ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ቢቢሲ ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን፤ ከቤተሰባቸው ጋር እንደሚገናኙና ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ለማወቅ ተችሏል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ለሳምንታት በክልሉ ሥራ አመራር ተቋም ውስጥ በስልጠናና በግምገማ ላይ እንደነበሩ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ ለቢቢሲ ገልጸዋል።እስሩ የተከሰተው ከዚሁ ስልጠናና ግምገማ ጋር ተያይዞ ሊሆን እንደሚችል እኚሁ ግለሰብ ያላቸውን ግምት ጠቅሰዋል።
ረዳት ኮሚሽነሩን ለእስር የዳረጋቸው ምክንያት ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት እንደማያውቁ አንድ የቤተሰብ አባል የተናገሩት ሲሆን፤ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አንዳንድ ሰዎች ግን ጉዳዩ ባለፈው ዓመት ሰኔ 15 ባህርዳር ውስጥ ከተከሰተው ችግር ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ ይገምታሉ።ቢቢሲ ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ ከጥቂት ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በተመለከተ ከአንድ የቤተሰብ አባላቸው ለማረጋገጥ ቢችልም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና የጸጥታ ኃላፊዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
Via BBC

የሳኡዲ አረቢያው ንጉሥ ጠባቂ በጥይት ተገደለ
የሳኡዲው ንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ የግል ጠባቂ የነበረው ግለሰብ ከጓደኞቹ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ተተኩሶበት መገደሉን ባለስልጣናት አስታወቁ።
ጀነራል አብደል አዚዝ አል ፋጋም ቅዳሜ ምሽት ላይ ነበር ጓደኛውን ለመጠየቅ በሄደበት ከሞሃመድ ቢን ሚሻል ሰል አሊ ጋር ግጭት ተፈጥሮ ለሞት የበቃው።
የፖሊስ መግለጫ እንደሚያመለክተው ሁለቱ ግለሰቦች ከተጋጩ በኋላ አሊ የተባለው ተጠርጣሪ ጅዳ ሁለቱ ከነበሩበት ቦታ ወጥቶ በመሄድ ሽጉጥ ይዞ በመመለስ ተኩስ ከፍቷል።
ተኳሹም ለፖሊስ እጁን እንዲሰጥ ቢጠየቅም እምቢ በማለት ተተኩሶበት መሞቱ ተገልጿል። ጀነራል ፋጋም በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምከንያት ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ አልፋለች።
በተጨማሪም ሌሎች ሰባት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለቱ የሟች ጀነራል ፋጋም ጓደኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን የደህንነት አባላት ናቸው ተብሏል።
ጀነራል ፋጋም በብዙ የሳኡዲ ዜጎች ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን ከንጉሥ ሳልማን ጋርም የቅርብ ግንኙነት ነበረው። ለብዙ ዓመታትም የንጉሡ ግል ጠባቂ ሆኖ አገልግሏል።
ብዙዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች 'ጀግና' ነበር እያሉ አሞካሽተውታል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

በደቡብ አፍሪካ አምስት ኢትዮጵያዊያን በሰው እገታ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ።
ኢትዮጵያዊያኑ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ተጠርጥረው የታሰሩት ሶስት እንስት ህጻናትን በማገት ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጻናት 50 ሺህ የደቡብ አፍሪካ ራንድ እንዲከፈላቸው የህጻናቱን ቤተሰቦች እንደጠየቁ ኒውስ24 የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።ተጠርጣሪዎቹ ያገቷቸው ህጻናት ወላጆች ኢትዮጵያያን መሆናቸው ደግሞ ነገሩን አስደንጋጭ እንዳደረገባቸው ዘገባው አስታውሷል።
ተጠርጣሪዎቹ ህጻናቱን ከአገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ አካባቢ ካገቱ በኋላ ወደ ጆሃንስበርግ እንዳጓጓዟቸውና ጉቴንግ በተሰኘ ከተማ አስቀምጠዋቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመደራደር ላይ እያሉ በፖሊስ መያዛቸው ተገልጿል። አጋቾቹም በህገወጥ ሰው ማዘዋወር፣በእገታ ወንጀልና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጆች ክስ እንደሚመሰረትባቸው በዘጋው ተጠቅሷል።በደቡብ አፍሪካ የአገሪቱ ዜጎች ባልሆኑ ዜጎች የሚፈጸሙ የእገታ እና ሰዎች ማዘዋወር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን ከቀናት በፊት ሁለት ህንዳዊያን አራት የባብግላዲሽ ዜጎችን ሲያዘዋውሩ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
Via Ethio FM

የቢሾፍቱ-ጨፌ ዶንሳ-ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።55 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመንገድ ፕሮጀክት በ3 ዓመታት ግዜ እንደሚጠናቀቅና ግንባታውም ከኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 914 ሚሊዮን ብር እንደሚከናወን ተገልጿል።
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
#ማስተካከያ ከአማራ ፓሊስ
ስለ ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ በህግ ጥላ ስር የመዋል ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያው የሚሰራጨው የተሳሳተ መረጃ መታረም ይገባዋል ።
ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ ሰራዊት የመምራትም ሆነ የማሰማራት ኃላፊነት የላቸውም በዚህም የልዩ ኃይል ፖሊስ ስምሪት አሰጣጥ ላይ ሃሳብ ሰጥተው ታሰሩ የሚለው ፍፁም የተሳሳተ ሃሳብ ነው ።
መኮንኑ በክልላችን ሰኔ 15ት ቀን በተከሰተው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ወንጀል ኃላፊነታቸውንና የአመራር ልምዳቸው በሚጠይቀው ልክ አለመወጣታቸውና በጉዳዩ ላይ ዕውቅና አላቸው የሚል ማስረጃ የቀረበባቸው በመሆኑ በህግ ቁጥጥር ስር ሁነው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ።
የተጠረጠሩበት ወንጀልም የኮሚሽኑ ሁሉም የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት በምርመራ ቡድኑ በግልፅ ተነግሯቸው እሳቸውም ኃላፊነታቸውን ያልተወጡበትን ምክንያት አቅርበዋል ።
ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው ፍትህ በሚሰጣቸው ውሳኔ ንፅናቸው የሚረጋገጥ ሁኖ እርስ በርሳችን የሚከፋፍሉ ዘጋባዎች መታረም ይገባቸዋል ።
ምንጭ ፦ አማራ ፓሊስ

የጊፋታ በዓል "አንድነትና ዘላቂ ልማት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ስታዲየም በድምቀት ተከበረ
የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል "አንድነትና ዘላቂ ልማት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ስታዲየም በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ ላይ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ የልዑካን ቡድኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳገቶ ኩምቤ የጊፋታ በዓል የአንድነትና የመቻቻል ተምሳሌት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ በዓሉን በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የወላይታ ዞን እምቅ የቱሪዝም ሀብቶች እና የተለያዩ ተፈላጊ ምርቶች ያሉት አካባቢ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የዞኑ መስተዳድርና ህዝብም የአካባቢውን የልማት እንቅስቃሴ በማጠናከር በመደመር እሳቤ የተጀመረውን ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ እንዲያስቀጥል አሳስበዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው "እኛ ኢትዮጵያውያን ቋንቋ፣ ባህል እና ሀይማኖት አይለያየንም፤ ባህላዊ ስርዓቶቻችንም የጋራ መገለጫዎቻችን ናቸው" ብለዋል፡፡
የጊፋታ በዓል መገለጫ ከሆኑት መካከል የሃያያ ሌኬ ባህላዊ ጨዋታም በስታዲየሙ ቀርቧል፡፡
Via:- ETV
@YeneTube @FIkerAssefa

Share of population aged below 14 years old.
Nigeria: 44%
#Ethiopia: 40%
Pakistan: 34%
Indonesia: 27%
India: 27%
Mexico: 26%
Saudi: 25%
Turkey: 25%
Brazil: 21%
US: 19%
France: 18%
UK: 17%
China: 17%
Russia: 17%
Canada: 16%
Germany: 13%
Italy: 13%
Japan: 12%
(World Bank)
@YeneTube @FikerAssefa
Nigeria: 44%
#Ethiopia: 40%
Pakistan: 34%
Indonesia: 27%
India: 27%
Mexico: 26%
Saudi: 25%
Turkey: 25%
Brazil: 21%
US: 19%
France: 18%
UK: 17%
China: 17%
Russia: 17%
Canada: 16%
Germany: 13%
Italy: 13%
Japan: 12%
(World Bank)
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ 19/2812 ዓ.ም 5:00 ሰዓት ጀምሮ የሩስያ ቤተ ክርስትያን ልዑካን ጎንደር ይገባሉ፡፡ ህብረተሰቡ አየር መንገድ ሄዶ እንዲቀበላቸው አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል ።
ለበለጠ መረጃ 0918150107/ 0940409494 ይደውሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ 0918150107/ 0940409494 ይደውሉ፡፡
ኦሮሚያ መስተዳድር ሻሸመኔ ከተማ የኮሌራ ወረርሸኝ መስፋፋቱ ተነገረ።
በኦሮሚያ አስተዳድር ሻሸመኔ ከተማ ነዋሪ የነበሩ አንድ ሰው ትናንት በበሽታው መሞታቸው ተዘግቧል። የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ወረርሽኙን ለመግታት እየጣረ መሆኑን አስታውቋል።በኦሮሚያ ክልል በተለይ በምዕራብ አርሲ ዞን የሻሸመኔ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች የወረርሽኝ ሥጋት አይሎ መስተዋሉን የሚናገሩት የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ደረጀ ምንም እንኳ በጥቂት ወረዳዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ቢቻልም በተቀሩት ወረዳዎች ያለው ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ ነው ብለዋል።ዶክትር ደረጀ ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት “ወረርሽኙ ከአራት ወራት በፊት በሌሎች ክልሎች ተከስቶ ነበር።
Via DW/Addis Maleda

ኢትዮጵያ ለ1 ሺህ የጎረቤት ሀገራት ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠች።
ኢትዮጲያ በየዓመቱ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ነፃ የትምህርት ዕድል የምትሰጥ ሲሆን ዕድሉን የሚያገኙ ተማሪዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን አውቀናል፡፡በ2012 ዓመት ኢትዮጲያ ለ6 ጎረቤት ሀገራት 1ሺ ተማሪዎች ነፃ የትምርት ዕድል ሰጥታለች ተብሏል፡፡ተማሪዎቹ የትምህርት ዕድሉን በቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ማግኘታቸውን በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም አቀፋዊነት አጋርነት እና ስኮላርሺፕ ዳይሬክተር አቶ ምትኩ በሬቻ ነግረውናል፡፡
ባለፈው 2011 ዓመት ለ600 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል የሰጠች ሲሆን በ2012 ዓመት ደግሞ ለ1 ሺህ ዜጎች የትምህርት እድል ሰጥታለች፡፡የነፃ ትምህርት ዕድል ለጎረቤት ሀገራት መሰጠቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ያጠናክረዋል ኢትዮጲያ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ተሰሚነትንም ያጎላል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ደቡብ ሱዳን፣ ሰማሊያ ፣ ጅቡቲ እና ኤርትራ ዜጎች የነፃ የትህርት ዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ሀገራት ናቸው፡፡