YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ከትብብር ውጪ ሌላ አማራጭ የለም -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ74 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዚዳንቷ በአማርኛ ባደረጉት ንግግራቸው በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት በበርካታ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።በዚህ መሰረትም የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት በማስከበር፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በሴቶች ተሳትፎና በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር በርካታ ስራዎች እያከናወነች መሆኗንም አክለዋል።

በመንግስት ይዞታ ስር የነበሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር ስራ የሀገር ተጠቃሚነትን ባረጋገጥ መልኩ ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩንም አንስተዋል።
የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር በመቅረፅ አበረታቸ ስራ መስራቷን ነው የተናገሩት።በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ያለውን የፀጥታና የደህንነት ሁኔታ ከማስከበር አንፃርም ኢትዮጵያ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣች የምትገኝ መሆኑን አውስተዋል።የአባይ ወንዝ በተመለከተ ባደረጉት ንግግርም ወንዙ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ሃብት እንጂ የጥርጣሬ እና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም ነው ያሉት።የአባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀምም የተፋሰሱ ሀገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ አፍሪካ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ አንዲኖራት ጠይቀዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሚያመነጩት ሃይል የአለም 10 ታላላቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች:

1.Three Gorges(China) 22500MW

2.Itaipu(Paraguay & Brazil) 14000MW

3.Guru(Venezuela) 10,200MW

4.Tucurui(Brazil) 8,370MW

5.Grand Coulee(USA) 6809MW

6.Sayano-Shushenskaya (Russia) 6400MW

7.Longtan(China) 6300MW

8.Krasnoyarsk (Russia)

9.Robert-Bourassa(Canada) 5616MW

10.Churchill Falls(Canada) 5428MW

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በ74ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በአማረኛ ቋንቋ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአንድ ወር የወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ እጩ ዲፕሎማቶችን አስመረቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሜጀር ጄኔራል ሐየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ለአንድ ወር ስልጠና የወሰዱ የ5ኛ ዙር 70 እጩ ዲፕሎማቶችን ትናንት መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም አስመርቋል።

ምንጭ: የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
AMH-Bahir-Dar-9-25-2019
በባህር ዳር ከተማ አልፎ አልፎ ምሽት ላይ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ምንነት ግራ እንዳጋባቸው ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።

በለቅሶ ላይ የሚተኮስ በማኅበራዊ ትሥሥር አሉታዊ ተፅዕኖ እያስከተለ መሆኑን የእነዚህ ነዋሪዎች ዕምነት ነው። የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ በጉዳዩ ዙሪያ መልስ ከመስጠት ተቆጥቧል።

⬆️⬆️ የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ።

ምንጭ: የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ⬆️
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከተለያዩ እምነት ተከታዮች ጋር በመሆን የመስቀል አደባባይን አፅድተዋል፡፡በፅዳት መርሃ ግብሩ ላይ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ጨምሮ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
ጂግጅጋ ዩንቨርስቲ ነባር ተማሪዎች መስከረም 28-30 እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥቅምት 12 -14 መሆኑን አሳውቋል እንዲሁም ሙሉ ኢንፎርሜሽን በEBC እና በSRTV የሚያስተላልፍ መሆኑን አሳውቋል።

Via:- ጂግጅጋ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ለደመራ በዓል አከባበር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች
ዛሬ በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከረፋዱ 4 ሰአት ጀምሮ ተከታዮቹ መንገዶች ዝግ ይሆናሉ፡፡

📌 ከኦሎፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከብሄራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከአምባሳደር ቲያትር ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ፣ 6727 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚስን አሳስቧል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አባባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን “ውኃ በተሽከርካሪ እናቀርባለን “የሚሉ ግለሰቦችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡

ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንፁህ የመጠጥ ውኃ አምርቶ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት የአገልግሎት ክፍያ እንደሚሰበስብ አስታውቋል፡፡ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ስልጣን ያልተሰጣቸው ግለሰቦች “ውኃ እናቀርባለን” በሚል ጥራቱ ያልተጠበቀ እና ከየት እንደተቀዳ የማይታወቅ የውኃ ሽያጭ እያካሄዱ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡ ህብረተሰቡም ከባለስልጣኑ ዕውቅና ውጭ የሆኑ ግለሰቦች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ውኃ የጥራት ደረጃው ያልተረጋገጠ ከመሆኑም ባለፈ ለጤና ጠንቅ ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ያለፍቃድ ውሃ በመሸጥ ላይ የተሰማሩ አካላትም ከዚህ ተግባር እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን ማሳሰቢያ በቸልታ ያለፈ እና በተግባሩ የቀጠለን ግለሰብ በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
አንጋፋዉ እና ዉጤታማዉ አሰልጣኝ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ በኳታር ታወሱ።

ዶክተር ወልደመስቀል በኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ ስኬታማ የረጅምና መካከለኛ ርቀት አሰልጣኝ ነበሩ፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ሆነ በኦሎምፒክ በየዘመናቱ እንደ ኮከብ ያበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችን ያፈሩ በመሆናቸዉ በህይወት በነበሩበት ጊዜም ሽልማትን አግኝተዉ ነበር፡፡ትናንት ከሰዓት በኳትር ዶሃ አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር/IAAF/ ለዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ በአለም ላይ ከተፈጠሩ 7 ምርጥ አሰልጣኞች ቀዳሚዉ አድርጎ ሰይሟቸዋል፡፡

Via Addis TV
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ለኢትዮጵያ ከገነባችላት 11 መርከቦች መካከል ሁለቱ ነዳጅ እንዲያመላልሱ ቢጠበቁም፤ የኢትዮጵያን ነዳጅ ግን እስካሁን ለማመላለስ አልቻሉም፡፡አስገንቢው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሲሆን መርከቦቹ ለነዳጅ መጫኛነት እንዲያገለግሉ በሚል በቻይና ሃገር ተገንብተው ከተጠናቀቁ በኋላ፤ ድርጅቱ ቢረከባቸውም ለኢትዮጵያ ነዳጅ እያመጡላት ግን አይደለም፤ ይልቅስ ሰርተው እዳቸውን መክፈል ስላለባቸው ለውጪ ባለጠጎች ኪራይ ገብተው እየሰሩ ነው፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ምስራቃዊ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ በኢትዮጰያ በኩል ተጠናቀቀ።

ከኢትዮጵያ ኬንያ ድረስ የሚዘረጋው እና በኢትዮጵያ በኩል 437 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍነው መስራቃዊ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በኩል ያለው ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለፀ። በቻይናው ኩባንያ ቻይና ኤሌክትሪክ ፓወር ቴክኖሎጂ የሚገነባው ፕሮጀክቱ ከወላይ ታ ሶዶ በመነሳት ኬንያ ድረስ የሚዘልቀው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልት የሚሸከም ሲሆን የኹለቱን አገራት የኃይል ማሰራጫዎችን የሚያገናኝ ይሆናል።

በቀጣይ ደግሞ በኬንያ በኩል ያለው ፕጀክት የሚጠበቅ ሲሆን ይህም 622 ኪሊ ሚቴሮችን እንደሚረዝም ለማወቅ ተችሏል። በኬንያ በኩል ያለው መስመር ዝርጋታ በጀርመኑ ሲመንስ ኩባንያ እንደሚከናወንም ታውቋል። ለፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 2 በሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 88 ሚሊዮን ዶላር በኬንያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን 32 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከኢትዮጵያ መንግስት ወጪ ይደረጋል። ቀሪው ደግሞ 684 ሚሊዮን ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር፣ 338 ሚሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ እዲሁም 118 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በሚገኝ ብድር ተግባራዊ ይሆናል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና እና የስም ቅየራ የተሰጣቸው ፓርቲዎችን ለህዝብ ማሳወቅ አለበት በሚለው የህግ ድንጋጌ መሰረት የሚከተሉት ፓርቲዎች የስም ቅየራ እና የእውቅና ሰርተፍኬት እንደተሰጣቸው አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ ለምርጫ ቦርድ መልስ የሰጠበትን መግለጫ አዉጥቷል::

@YeneTube @FikerAssefa