YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የመስቀል በዓል የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአለም ሕዝብ ያበረከተችው የአለም ቅርስ ነው።

ቤተክርስቲያኒቱ እና ልጆቿ በተለይ በመስቀል አደባባይ በየአመቱ ለአይን በሚያስደምም፣ ለጆሮ በሚጥም፣ መንፈስን በሐሴት በሚያመጥቅ፤ መንፈሳዊ ትርዒት በየአመቱ ደምቀው ያደምቁናል። ችቦዎች በአንድ ላይ ተዳምሮ የደመራ ብርሃን እንደሚፈጥሩ ሁላችንም በአንድነት የበዓሉን ዝግጅት ደማቅ እንዲሆን እንርዳ።

የከተማችን ወጣቶች ሁላችን ሃይማኖት ሳይለየን ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 ጀምሮ መስቀል አደባባይን እንድናፀዳ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

Via:- ኢንጂነር ታከለ ኡማ
@YeneTube @Fikerassefa
ዘንድሮ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ነባርና አዲስ ተማሪዎች የኃላፊነት መውሰጃ ውል መፈጸም እንዳለባቸው ተገለጸ

⚡️በ2012 ዓ.ም ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ነባርና አዲስ ተማሪዎች ከመግባታቸው በፊት ከሚኖሩበት ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ጋር የኃላፊነት መውሰጃ ውል መፈጸም አለባቸው

⚡️ የተማሪዎች ቤተሰቦች በተገኙበት በወረዳቸው ትምህርት ፅህፈት ቤት ተሞልቶና ተፈርሞ ማህተም የሚደረግበት ፎርም ይፋ ተድርጓል።

⚡️ነባርና አዲስ ተማሪዎች ይህን ውል ይዘው እስካልቀረቡ ድረስ መመዝገብ የማይችሉ መሆኑ ተገልጿል።

⚡️ “የተማሪዎችና የግቢ ደህንነት አጠባበቅ ስርአት በተማሪዎች፣ በወላጆችና በዩኒቨርስቲ መካከል የሚገባ የሃላፊነት መውሰጃ ውል” ለውሉ የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡

⚡️የውሉ አላማም የተማሪዎችንና የተቋማቱን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ተማሪዎች ተረጋግተው በመማር የሚጠበቅባቸው ደረጃ ላይ እንዲደርሱ፣ መብታቸው ተጠብቆ ግዴታቸውን እንዲወጡ፣ ዩኒቨርስቲውም ሙሉ ሃላፊነቱንና ተጠያቂነቱን እንዲወስድ ለማድረግና ተማሪዎችም ለሚያጠፉት ጥፋትም ሆነ ለሚያደርሱት ጉዳት እነርሱም ሆነ ወላጆጃቸው ወይም አሳዳጊዎቻቸው ተጠያቂ መሆናቸውን ለማስገንዘብና ሃላፊነት እንዲወስዱ ለማድረግ ነው።

- ብሌ ሆራ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @Fikerassefa
ጋምቤላ ዩንቨርስቲ ነባር እና አዲስ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

⚡️ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ቀን መስከረም 29 - 30

⚡️አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ቀን ጥቅምት 3 - 4 መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀን እንድትገቡ ዩንቨርስቲው ያሳስባል።

@YeneTube @Fikerassefa
ማስታወቂያ⬇️

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ወደዩኒቨርሲቲው ለተመደባቹ ተማሪዎች በሙሉ
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2012 ዓ,ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችቹ እያለ
ለ2012 ዓ.ም ለትምህርት ወደዩኒቨርሲቲያችሁ የመግቢያ ቀን

☞ለነባር ተማሪዎች ከጥቅምት 3-4/2012 ዓ.ም

☞ለአዲስ ገቢ/Fresh man ከጥቅምት 10-11/2012 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን።

-- ብሌ ሆራ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @Fikerassefa
Audio
በሐረሪ ክልል የሚገኝ የማኅበረሰብ የትምህርት ተቋም በይዞታው ውስጥ በሚፈፀም ህገወጥ የመሬት ወረራ የተነሳ የመማር ማስተማር ሥራ መጀመር አልቻልኩም አለ።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንም በህገወጥ መሬት ወረራው እየተቸገርኩ ነው ብላለች። የክልሉ ፀጥታ ምክር ቤት ችግሮቹን ለመፍታት ዝርዝር መርኃ ግብር አውጥቼ እየተንቀሳቀስኩ ነው ብሏል።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትና በምዕራብ ወለጋ አይራ ወረዳ ሰሞኑን አሰቃቂ ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑን ምስሉ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሲታይ የነበረ አንድ ወጣት ወንድማቸው መሆኑን ያመለከቱ ግለሰብ ወጣቱ “በፀጥታ ኃይሎች ነው የተገደለው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።የአይራ ወረዳ ፀጥታና አስተዳደር በበኩሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ ወጣቱ በወንጀል ተጠርጥሮ የሚፈለግ የነበርና በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርግ መገደሉን አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ምሽት በአሶሳ ከተማ መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን (ከመናኸረያ ወረድ ብሎ) ባልታወቁ ሰዎች ቦንብ ተወርዉሮ በሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ፖሊስ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ሰምተናል::

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ሕዝቦች የሰገን ዞን እንዲፈርስ የተወሰደውን ወሳኔ ተከተሎ የዞኑ ሰራተኞች መበተናቸውንና የደመወዝ ክፍያም ተነፈግን ሲሉ አማረሩ።የክልሉ የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በበኩሉ የ610 ሰራተኞችን ምደባ በተመለከተ የማስተባበር ላይ ይዣለሁ፤ የደሞዝ ክፍያው ይፈፀም ግን በቅድሚያ የስራ መደብ ልሰጣቸው ይገባል እያለ ነው። ቅሬታቸው ተገቢ ነው። ወደ ሥራቸው የሚመለሱበትም ጥረት ተጀምሯል ነው የተባለው።

ምንጭ:VOA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ ለማልታው ቢርኪርካራ የእግር ኳስ ክለብ በቋሚነት ፈረመች።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የፊት አጥቂ ሎዛ አበራ ከክለቡ ተጫዋቾች ጋር ለሳምንታት የቆየ አስደናቂ ብቃቷን ያሳየችበት ልምምድ ካደረገች በኋላ በይፋ የቡድኑ አባል ሆናለች ነው ያለው። በክለቡ በሚኖራት ቆይታም መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማት ምኞቱን ገልጿል። የ21 ዓመቷ ሎዛ ለክለቡ ፊርማዋን ባኖረችበት ወቅት “ላለፉት ዓመታት የሊጉ አሸናፊ የሆነውን ክለብ በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ፤ እንደ አንድ የስኬት እርምጃ እወስደዋለሁ” ብላለች።

እንደ ማንኛውም የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ግብ ማስቆጠር ቢኖርብኝም፥ በተለይ ቡድኔ የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን እና በአውሮፓ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር እንዲሳተፍ ውጤታማ ጥረት አደርጋለሁ ነው ያለችው።ሎዛ የቢርኪርካራ ክለብ ተጫዋች መሆኗ በማልታ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እውቅና ያገኘ ሲሆን፥ ተጫዋቿ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት 9 ቀን ከሄበርኒያንስ ክለብ ጋር በሚደረገው ጨዋታ እንደምትሰለፍ ክለቡ በይፋዊ ድረገፁ አስነብቧል።

ምንጭ: ዋልታ
@YeneTube @FikerAssefa
አውስትራሊያ ፅንስ ማስወረድን ከለከለች!!

ከአውስትራሊያ ይሄን ፅንስ ማስወረድን የሚከለክለውን ህግ ያላፀደቀችው ግዛት ኒው ሳውዝ ዌልስ ነበረች፡፡ አሁን ረቂቁ ድምፅ ተሰጥቶበት አፅድቃለች፡፡

ረቂቁ የጸደቀው የ 119 አመት ዕድሜ ያለውን ህግ ገልብጦ ነው፡፡ ይሄ ህግ በተቃዋሚዎች ያረጀ፣ ጊዜ ያለፈበት ተብሎ ይተች ነበር፡፡
ይሄ አዲስ ህግ ለሳምንታት የፈጀ ንትርክ ተደርጎበት ነበር፡፡ በመንግስት መዋቅር ውስጥም ክፍፍል ፈጥሯል፡፡

ከዚህ በፊት ማስወረድ ይቻል የነበረው ዶክተር ለሴቷ ጤና አደጋ ስላለው ፅንሱ መውረድ አለበት ካለ ብቻ ነበር፡፡

አዲሱ ህግ ፤ ፅንስ ለማስወረድ የሚሞክሩ ሴቶችና ዶክተሮች የ 10 አመት እስር ይጠብቃቸዋል ሲል ቢቢሲ የአገሪቱን የጤና ሚኒስቴር ጠቅሶ ዘግቧል።

Via:- EthioFM
@YeneTube @Fikerassefa
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን አስመለክቶ ከ48 ቀናት በኋላ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክቶች ይፋ ሆኑ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።

Via:- Ethio Fm
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ አማራጭ ሃሳቦችና የሚወከሉበት ምልክቶችን ይፋ አደረገ። በዚህም መሰረት፡-

(ጎጆ )“ሲዳማ በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ውስጥ እንዲቆይ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የጎጆ ቤት ምልክት።

(ሻፌታ) ሲዳማ እራሱ ችሎ እንዲያስተዳድር እፈልጋለሁ ለሚለሁ አማራጭ ሻፌታ ምልክት።

Via:- ELU
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ክብረ በዓል ልዩ ትራንስፖርት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

አየር መንገዱ ይህ ልዩ ትራንስፖርት ከዚህ ቀደም ያልነበረኝ ነው ብሏል፡፡ ከአዲስ አበባ ኮምቦልቻ ድረስ በአየር አድርሼ ከኮምቦልቻ ግሸን ማርያም ድረስ ደግሞ ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን በየብስ አጓጉዛለሁ ማለቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አስራት በጋሻው ለሸገር ነግረዋል፡፡ከመስከረም 19 ጀምሮም ለተከታታይ 4 ቀናት በረራዎቹን እጥፍ እንደሚያደረጉ ሰምተናል፡፡ አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ግሸን ማርያም ስፍራው ድረስም 4 ሺ 999 ብር እጠይቃለሁ ብሏል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ያዘጋጀው ውል «የተሳከረ» ከአገሪቱ ሕግጋት የሚጣረስ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሞያ ተናገሩ። በ2012 ዓ.ም. በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚጀምሩ 142 ሺሕ ገደማ ወጣቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች «በግልም ይሁን በቡድን በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥፋቶች ተሳታፊ ወይም ተባባሪ» እንዳይሆኑ ለመጠበቅ በተማሪዎች፣ በወላጆች እና በወረዳ የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች የሚፈረም ውል ተዘጋጅቷል።

በሰነዱ ወላጆች ልጆቻቸው «በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በማንኛውም መነሻ በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥፋቶች በግልም ይሁን በቡድን እንዳይሳተፍ፣ ተባባሪም እንዳይሆን» መምከራቸውን ተስማምተው እንዲፈርሙ ያስገድዳል።

በወላጅ ወይም በአሳዳጊ እንዲሞላ በተዘጋጀው ቅጽ ልጅ በዩኒቨርሲቲ «በጥፋቶች ተሳታፊና ተባባሪ በመሆን ለሚያደርሰው ጥፋትና ጉዳት ለሚወሰድበት ርምጃ በሕግ ተጠያቂ» እንደሚሆን ማስገንዘባቸውን ተስማምተው ወላጆች ይፈርማሉ።

በዚያው ሰነድ የወረዳ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲፈርሙበት በተዘጋጀው ክፍል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለሚያጠፉት ጥፋት ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ ያትታል። በሰነዱ መሰረት ልጅ «በዩኒቨርሲቲ ቆይታው በማንኛውም ምክንያት በግልም ይሁን በቡድን በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥፋቶች ተሳታፊ ወይም ተባባሪ እንዳይሆን ስልጠና የወሰደ ሲሆን ይህንን ተላልፎ ችግር ቢፈጥር ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ እሱም ሆነ ወላጆቹ/አሳዳጊዎቹ ተጠያቂ» ይሆናሉ።

የሕግ ባለሞያው አቶ አብዱረዛቅ ነስሮ ይኸ እርስ በርሱ የሚጋጭ ሆኖ አግኝተውታል። «የወላጆችን ስታየው ወላጆች እንደማይጠየቁ፤ ግዴታቸው ማስገንዘብ እንደሆነ የሚያወራ ይመስላል። ለወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀውን ስታየው ደግሞ ወላጅ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል፤ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን ያወራል። ይኸ አንድም እርስ በርሱ የተጋጨ፤ የተሳከረ ነው» ሲሉ ተችተዋል።

via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
የመተከል ግጭት እየተረጋጋ ባለበት ቢሆንም ማክሰኞ መስከርም 13 ቀን በዳንጉር ወረዳ ሁለት የከብት እረኞች ተገለዋል:: ትናንት ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል። አሁን መከላከያ ሠራዊት አከባቢዉን እንደተቆጣጠረውና እያረጋጋ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀውልናል::

@YeneTube @FikerAssefa
"አዲስ አበባችንን እንደስሟ አዲስና አበባ ለማድረግ ያቀድነው ዕቅድ በእርግጠኝነት ይሳካል።አጠቃላይ ስፋቱ 13.9 ሔክታር በዛሬው ዕለት ሦስት ፓርኮችን እናስመርቃለን።"

-ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536
 
የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ነገ በሚከበረው የደመራ በዓል "ግጭት ቀስቃሽ፣ አንዱን የሚያሞግስ ሌላውን የሚያንቆሽሽ፣ ብዙሀነታችንን የማይገልፁ ፅሁፎች፣ በሕገ መንግስቱ ከተፈቀደው #ሰንደቅ_ዓላማ ውጪና የተለያዩ አርማዎችን" መያዝን ከለከለ።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @Fikerassefa
የ63 ሚሊዮን ዶላር የብድር ግምገማ ተፈረመ

ለአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን የከተማ አውቶቡስ B6 ኮሪደር ፕሮጀክት የሚውል የ63 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ግምገማ ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር አዳራሽ ተፈራርመዋል።

@YeneTube @Fikerassefa