YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Official!
⬆️⬆️
በዘንድሮው ዓመት አዲስ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡም ሆነ ነባር ተማሪዎች የሚከተለውን ፎርም ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በወረዳቸው በሚገኝ ትምህርት ፅ/ቤት ተሞልቶና ተፈርሞ እንዲሁም ማህተም ተደርገበት በዩኒቨርስቲ የምዝግባ ወቅቶች ይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ይሄንን ካላቀረቡ እንደማይመዘገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536
 
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 68.3 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያለበትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በግድቡ የውሃ አሞላል እና በሚለቀቀው የውሃ መጠን ዙሪያ ግብጽ ያቀረበችው የተለዬ አቋም የግንባታ ሥራውን ወደ ኋላ እንደማያስቀረውም ነው ተናግረዋል።እስካሁን ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ግድቡ በፈረንጆቹ 2024 እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ግንባታዉ በታሰበዉ ጊዜ ለማጠናቀቅ የእስካሁኑን ጨምሮ ከ130 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስወጣ ይጠበቃል።

የሁለቱ ቅድመ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች የብረታ ብረት ገጠማና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራም በግማሽ የተጠናቀቀ ሲሆን ግድቡ ሲጠናቀቅም በዓመት በአማካይ 15 ሺሕ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት ሀይል እንደሚያመነጭ አብርሃም በላይ ተናግረዋል።በተጨማሪ የኮርቻ ግድብ ስራው 96 በመቶ፣ የጎርፍ ማስተንፈሻ ስራው 96 በመቶ፣ የሀይል ማመንጫ ክፍል ስራው 70 በመቶ፣ የዋና ግድብ ስራው 80 በመቶ ተጠናቆ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 68.3 በመቶ መድረሱን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
100 ተጨማሪ አዳዲስ አውቶቢሶች ወደ ስራ ሊገቡ ነው፡፡

አውቶቢሶቹ በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል አስተዋፆኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ አውቶቢሶቹ ከነገ ማለትም መስከረም 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ መግባት ይጀምራሉ፡፡በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የብዙሃን ትራንስፖርት አንበሳ እና ሸገር ባስ አገልግሎትን ለማሻሻል በጥናት ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ከዚህ ተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ አውቶቢሶች ከውጪ ለማስገባት እና የትራንስፖርት ስምሪቱን ዘመናዊ የሚያደርግ አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ ነው፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል መንግስት የመስቀል በአልን አስመልክቶ ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ላሉ አመራሮች የእራት ግብዣ አደረገ።

እንደሚታወቀው የደቡብ ክልል የማዳበሪያ ብድር 4.5 ቢሊየን ብር አለበት።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራት ዛሬ ባወጡት መግለጫ ከመንግሥት አካላት ጋር የተነጋገሩባቸውንና የተስማሙባቸውን ነጥቦች ገልጠዋል፡፡ ሕይወታቸውን ላጡ ካህናት፣ ለተዘረፉና ለተቃጠሉ መንግሥት ካሳ እንዲከፍል የሚለው ነጥብ አንዱ መወያያ እንደነበር ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገጹ አስታውቋል፡፡ መግባባት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ለመፍታትም ጊዜ ገደብ ተቆርጧል፡፡ በክልሎች የጋራ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ እና መደበኛ ነባር ቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እንደሚከተለው አሳውቋል። ⬆️

@YeneTube @Fikerassefa
ትናንትና በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ወረዳ በደረሰው የመኪና አደጋ የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን የአማራ ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊው ብስክሌተኛ ሙሉ ክንፈ በሶስት ዓመት ውል የፈረንሳዩ ብስክሌት ክለብ ዴልኮ ተቀላቀለ፡፡ ከዓዲግራት የተነሳው ብስክሌተኛው ሙሉ በትግራይ ለጉናና ትራንስ ተጫውቷል፡፡

Via ሚልዮን ኃ/ስላሴ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች የማይስ አሸናፊዎች (MICE Champion Award) ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

ኢ/ር ታከለ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ ዲያስፖራ ቱሪዝም ኮንፍረንስ ላይ ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል–ሲሲ ኢትዮጵያ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ለመገንባት ስትነሳ አመርቂ ጥናት አልሰራችም ሲሉ ከሰዋል። በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር ፈቅ ሳይል መቀጠሉ በቀጠናው መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ኢንስቲትዩት ቴክኖሎጂ ፋክልቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች መታወቂያ እድሳት ከዛሬ ማክሰኞ 13/01/2012 እስከ አርብ 16/01/2012 መሆኑን ብቻ በጥብቅ ያሳስባል።

#ሬጅስትራር
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536
 
7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ወርቅና በርካታ የዉጪ አገር ገንዘቦች ተያዙ!

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት የቶጎ ጫሌ መቅርጫ ጣቢያ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 5ከ.ግ ወርቅና የዉጪ አገር ገኝዘቦችን ያዘ።በቀን 13/01/12 ከለሊቱ 9 ሰአት አካባቢ ከሰ/ቁጥር ኮድ3-05861 ድሬ አይሱዚ ኤክስፖርት የሚደረግ ጫት የጫነ ተሽከርካሪ የቶጎጫሌ ፈታሾች ባደረጉት ጥረትና ጠንካራ ፍተሻ 5 ኪ.ግ ጥፍጥፍ ወርቅ ፤ 175,584 የሳውዲ ሪያል እንዲሁም 7,155 ድርሀም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽንየ ጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት የቶጎ ጫሌ መቅረጫ ጣቢያ ፈታሾች ቀን ከሌሊት ህገ ወጥ የገንዘብ ዝዉዉርና ኮንትሮባንድን ለመከላከል እያደረጉት ላለዉ ጠንካራ ስራ የገቢዎች ሚኒስቴር ያለዉን አድናቆት ያቀርባል፡፡ የተያዘዉ ወርቅና ገንዘብ እንደተለመደዉ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ይሆናል፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡

ምርመራው ዘግይቷል የሚባለው ነገርም ትክክል አይደለም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡ የተወሰ ጊዜም እንደሚወስድ ይታወቅ እንደነበርም አብራርተዋል፡ፖሊስ በጅምር ላይ የነበረውን ምርመራ አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱን ያስታወሱት ኮሚሺነሩ፣ ሲጠናቀቅም ለሚመለከተው አካልና ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ኮሚሺነሩ አክለው እንዳሉትም ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ ከታሰሩ ተጠርጣሪዎች አብዛኛዎቹ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ቁጥርም ከመቶ እንደማይበልጥ አስረድተዋል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚሁ ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር፣ በመንግሥት ከሚገልፀው የበለጠ መሆኑን እንደሚናገሩ ይታወቃል፡፡

ምንጭ:VOA
@YeneTube @FikerAssefa
የባህር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ተባለ።

አዳዲስ የላቦራቶሪ መሣሪያዎችም መጥፋታቸው ተነግሯል።የባህርዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ታካሚዎች ለተጨማሪ ወጪ እንዲዳረጉ በማድረግና በቂ የመድኀኒት አቅርቦት ባለማቅረብ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም የሚል አቤቱታ ከሠራተኞቹ ቀረበበት።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት፣ በሆስፒታሉ ያሉ ላቦራቶሪዎች ግማሾቹ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል፣ ግማሾቹ ደግሞ የት እንደገቡ እንደማይታወቅና ታካሚዎች በዚህ ሳቢያ ለምርመራ ወደ ግል ህክምና ተቋማት እየተላኩ ለለከፍተኛ ወጪ መዳረጋቸውን አስታውቀዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራሱ" የተሰኘ የጥቅል እቃ መቀበልና ማድረስ አገልግሎት ስራ ጀመረ።

በሆራይዘን ኤክስፕረስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ይፋ የተደረገው ይህ አዲስ አገልግሎት የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።ባልደራሱ የተሰኘው ይህ አዲስ ፕሮግራም በዋናነት በቴክኖሎጂ የታገዘ የጥቅል እቃ መቀበልና ማድረስ አገልግሎት ላይ ያተኩራል ተብሏል።ይህ አገልግሎት ከዚህ በፊት በተለያዩ ተቊማት ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ መረጋገጡ ተገልጿል።

ይህ አገልግሎት በዋና ማሰራጫ ማዕከል በመደራጀት በሞባይል መተግበሪያዎችና በድረገጽ ተቀናጅቶ እንደሚሰጥ በፕሮግራሙ ማስተዋወቂያ ላይ ተጠቅሷል።በዚህ ድርጅት ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከልም ቀላልና ከባድ እቃወችን በሞተርና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ይሰጣል ተብሏል።አገልግሎቱ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባለፈ በተለይም እያደገ ለመጣው የሎጅስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ጊዜንና ወጭን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በእስራኤል አገር የሚገኝ አንድ መዋዕለ ሕፃናት ኢትዮጵያዊያን ዝርያ ያላቸውን ሕፃናት ተማሪዎች ላይ ማግለል በመፈፀሙ መዘጋቱን ሰምተናል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ወርቅና በርካታ የዉጪ አገር ገንዘቦች ተያዙ! በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት የቶጎ ጫሌ መቅርጫ ጣቢያ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 5ከ.ግ ወርቅና የዉጪ አገር ገኝዘቦችን ያዘ።በቀን 13/01/12 ከለሊቱ 9 ሰአት አካባቢ ከሰ/ቁጥር ኮድ3-05861 ድሬ አይሱዚ ኤክስፖርት የሚደረግ ጫት የጫነ ተሽከርካሪ የቶጎጫሌ ፈታሾች ባደረጉት ጥረትና ጠንካራ ፍተሻ 5 ኪ.ግ ጥፍጥፍ ወርቅ…
ተጨማሪ መረጃ!

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጂጋ ቅርንጫፍ የቶጎ ጫሌ መቅረጫ ጣቢያ ዛሬ ጠዋት ከተያዘዉ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 5ኪ.ግ ወርቅና የዉጪ አገራት ገንዘብ በተጨማሪ የተሽከርካሪውን አካል ጠዋት በጥንቃቄ በዝርዝር ሲፈተሽ 63,035 የአሜሪካን ዶላር እና 146,500 የሳውዲ ሪያል ተገኝቷል፡፡የገቢዎች ሚኒስቴር ቀንና ሌሊት ከኮንትሮባንዲስት ጋር ተጋፍጠዉ ህገ ወጥነትን ለመከለከል የሚሰሩ የመቅረጫ ጣቢያዉን ፈታሾችና ሰራተኞች ያለዉን አድናቆት ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa