Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩
በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg

⬆️⬆️
ለደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ነባርና አዲስ የመደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!!
1.ለነባር የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 21 እና 22 ፣ 2012 ዓም
2.ለአዲስ ገቢ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የቅበላ ጊዜ መስከረም 28 እና 29 ፣ 2012 ዓም
@YeneTube @FikerAssefa

በሶማሌ ክልል በአፍዶር ዞን አንዲት እናት አራት ልጆችን ተገላገለች።
በሶማሌ ክልል በአፍዶር ዞን አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም ተገላገለች፡፡
ይህች እናት አራት ልጆችን በሰላም የተገላገለችው በአፍዶር ዞን በምዕራብ ኢሜይ ጤና ጣቢያ ውስጥ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡እናት ልጆች በአሁን ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የሶማሌ ክልል ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በዘገባው አመልክቷል፡፡
ባለፈው ዓመት በራያ ቆቦ ወረዳ አረቋቴ በተባለ ቦታ አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም መገላገላቸው የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ:ፋና

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ከ18 ዓመት በፊት ለሰሩት ስህተት ይቅርታ ጠየቁ።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እንደ አውሮፓውያኑ በ2001 በአንድ የትምህር ቤት ሁነት ላይ ነጮች ሌላ ዘርን በተለይም ደቡብ ኢሲያንና ላቲኖችን ወክለው ሲተውኑ የሚያረጉትን ቡናማ ገፅ ለብሰው የሚያሳይ ፎቶ ተለቆ ነበር፡፡ላደርገው አይገባም ነበር ከነበረኝ የተሻለ እውቀት ሊኖረኝ ይገባ ነበር፤ ግን አልነበረኝም፡፡ ድርጊቱም ፎቶውም ዘረኛ ነበር፤ ሳደርገው ግን እንደዚያ ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ ለሰራሁት ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡
በወቅቱ መምህር በነበሩበት ትምህርት ቤት የአረቦች ምሽት የተሰኘ ክብረ በአል እየታደሙ በነበረበት ወቅት የተነሱት ፎቶ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡የወደፊቱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነቱን ከጓደኞቻቸውና ከባልደረቦቻቸው ጋር ሲካፈሉ የአላዲንን ገፀባህሪ ለመምሰል እንደለበሱ፤ሙስሊም ሼኮች በጭንቅላታቸው ላይ የሚጠመጥሙትን ተርባን አድርገው እንደነበርም ተነግሯል፡፡በድጋሚ ለመመረጥ ምርጫ ለመወዳደር በዝግጅት ላይ የሚገኙት ትሩዶ ከተቀናቃኛቸው የኮንሰርቫቲቩ አንድሪው ሺር ብርቱ ፉክክር ይጠብቃቸዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
Via Ethio FM

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከፈረንሳዩ የባህል ሚንስትር ፍራንክ ራይስተር ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የፈረንሳይ የባህል ሚንስትር ፍራንክ ራይስተር በነበራቸው ቆይታም በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እየተካሄዱ ያሉት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትና የኢዩቤልዩ ቤተ መንግስት እድሳት ተወያይተዋል። የኢትዮጵያና የፈረንሳይን ጠንካራ ግንኙነትና የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጥልቅ የትብብር ፍቃደኝነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ እድሳቱን ማፋጠን እንዲቻል አበረታትተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በበኩላቸው የዛሬው ጉብኝታቸውፕሬዝዳንት ማክሮን ለሁለቱም ሀገራት የሚበጅ የቅርስ ጥበቃ ላይ ለመተባበር ያላቸውን ፍቃደኝነት ማሳያ ነው ብለዋል።
Via OBN

ሁለት አሳዛኝ ክስተቶች!
የመጀመርያው ክስተት ያጋጠመው ባለፈው ቅዳሜ ፒያሳ አካባቢ ሲሆን ከካናዳ ለበአል የመጣ እና ሚካኤል ገብሩ የተባለ ግለሰብ በዘረፋ መሀል ባጋጠመው ድብደባ ህይወቱ አልፏል። ስለወንጀሉ ዝርዝር መረጃ ከአ/አ ፖሊስ ጠይቄ እስካሁን መልስ አላገኘሁም። ሚካኤል ባለፈው አመት ካናዳ ውስጥ የ10 ሚልዮን ዶላር ሎተሪ አሸንፎ እንደነበር ከሚያውቁት ሰዎች መረጃ ደርሶኛል።
ሁለተኛው ክስተት ደግሞ ባለፈው ማክሰኞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የሆነች እፀገነት የተባለች ግለሰብ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ህይወቷ አልፎ መንገድ ዳር ተገኝታለች። አንድ የቤተሰብ አባል እንደነገረኝ እፅገነት ለስራ በጠዋት ወጥታ በባጃጅ ወደ ሰርቪስ መኪና ስትሄድ መኪናው ጋር ሳትደርስ ኮብልስቶን ዳር ተገኝታለች። እስካሁን አሟሟቷ ምን እንደሆነ እንዳልታወቀ እና አንድ ሰው ግን "በመታነቅ" ህይወቷ ሳያልፍ እንዳልቀረ እንደነገረው ገልፆልኛል። ጨምሮም "የተፈጥሮ ህልፈት ነው እንዳይባል ምንም ህመም የለባትም። ጠቅላላ የህክምና ውጤቱን ግን ከሆስፒታል ጠይቁ ተብለናል። ብቻ ያው እኛ ትናንት ቀብረናታል" ብሏል።
ነብስ ይማር!
Via Elias Meseret

ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ አንደኛ አመት እና ከዛ በላይ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ቀን መስከረም 26 እና 27 መሆኑን አስታውቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት ከሚገነቡት 19 ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ስድስቱ ለ2012 የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንደሆኑ ታውቋል።
ከአራቱ ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ ላይ ቁስቋም ትምህርት ቤት በሚል የተሠራው ፕሮጀክት ግንባታው መጠናቀቁን እና ትምህርት ቤቱ ተቀይሮ ለሕጻናት ማሳደጊያ እንዲሆን ተደርጓል። ሰበታ ላይ የሚታደሰው የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤትም ሥራው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።
ለማስተማር ዝግጁ ከሆኑት መካከል በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ አስተዳደር ላይ የሚገኘው የሎዛ ማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይገኝበታል።
በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙት የሊበን ጭቋላ፣ የጉጂ እና የጃኮ ትምህርት ቤቶችም ለማስተማር ዝግጁ የተደረጉ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በ2012 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው ተጠናቅቆ በ2013 የትምህርት ዘመን ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገልጿል።
Via:- አዲስ ማለዳ

ለደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ነባር እና አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች!
ለደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ። የ2012 የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ነባርና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት በዩኒቨርስቲው አስተዳደር እንደሚከተለው ተወስኗል። የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 19-21/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል። አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 23-25/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል።
የውጭና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ80 ሚሊየን ብር በላይ አልተከፈለኝም ሲል ተናገረ፡፡
ባለስልጣኑ ዛሬ በመስሪያ ቤቱ አዲስ የጀመራቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫውም በአዲስ አበባ የሚገኙ 3 ሺ የሚጠጉ ድርጅቶች 80 ሚሊየን ብር የአገልግሎት ሒሳብ አልከፈሉኝም ብሏል፡፡በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የግል ደንበኞችም ሒሳባቸውን ለመክፈል በመወላወል ላይ ናቸው ብሏል፡፡የባለስልጣኑ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እነዚህ ድርጅቶችና የግል ደንበኞች እስከ መስከረም 18 ቀን 2012 ድረስ የአገልግሎት ውዝፍ ክፍያቸውን የማይፈፅሙ ከሆነ አገልግሎት ከማቋረጥ ጀምሮ በፍርድ ቤት እስከመክሰስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡
ምክትል ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት አዲስ በጀመሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ክፍያ ጋር በተያያዘ አንዳንድ እክሎች እየገጠሟቸው መሆኑንና ይህንንም ለመቅረፍ 350 የሚደርሱ ባለሙያዎችን በሁሉም በአዲስ አበባ በሚገኙ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ባለሙያዎችን በመመደብ የግንዛቤ መስጠት ስራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡560 ሺ ለሚጠጉ ደንበኞች ደግሞ የቤት ለቤት ማስተማር ስራ እየሰጡ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
Via Sheger

Sport !! ጋዜጣዊ መግለጫ ❗️
የቅዲስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር እና የኢትዮጵያ ብና ስፖርት ክለብ በውቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የጋራ መግለጫ ስለሚሰጡ የስፓርት ጋዜጠኖች ቅዳሜ መስከረም 10 ቀን 2012 ከቀኑ 8 ሰዐት ላይ በሸራተን አዲስ እንድትገኙ በአግብሮት ገልፀዋል።
ክለቦቸ!!
@Yenetube @Fikerassefa

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደራሴ የሁሉም 12 ክፍል ተማሪዎች የምረቃ እና የመዝናኛ ዝግጅት እሁድ መስከረም 11 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ!
መግቢያ በነፃ!
የበዓሉ ተሳታፊ ተማሪዎች የመግቢያ ካርዶችን ከየትምህርት ቤታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Via:- Mayor Office
@YeneTube @Fikerassefa
መግቢያ በነፃ!
የበዓሉ ተሳታፊ ተማሪዎች የመግቢያ ካርዶችን ከየትምህርት ቤታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Via:- Mayor Office
@YeneTube @Fikerassefa
የዋጋ ግሽበት እንዲባባስ ባደረጉ 609 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስድብ ተባለ!
በከተማዋ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ግሽበት እንዲባባስ ባደረጉ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በከተማዋ የተለያዩ ህገወጥ አሰራሮችን በመጠቀም የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ እንዲጨምር ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ ፍተሻ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህ መሰረትም በድርጊቱ ተሳትፈው የተገኙ 609 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ ተናግረዋል።ከዚህ ባለፈም ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ የንግድ ተቋማት ማስጠንቀቂያ የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣም፣ የግብይት ሰንሰለቱ በህገ ወጥ ደላሎች መያዝ እና የህገ ወጥ ንግድ መበራከት በከተማዋ ለተከሰተው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል።ቢሮው በቀጣይ በከተማዋ የሚስተዋለውን የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠርም ከጸጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
Via ኤፍ.ቢ.ሲ

በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በቦልቪያናዊዉ ናማኒ ቺንቼ ኢቬሊን የፓስፖርት ቁጥር AE57255 ከብራዚል ሳዖ ፖሎ አዲስ አበባ የገባዉ 8 ኪሎ ግራም የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
ዕፁን ይዞት ይጓዝ በነበረዉ ግለሰብ ላይ ከብራዚል ሳኦ ፖሎ ጀምሮ በጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንስ ቡድን ባደረገዉ የተቀናጀና ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊዉል መቻሉ ተገልጿል፡፡
ይህንን አድካሚና የተቀናጀ ስራ በመስራት እፁን መያዝ ለቻሉ የቦሌ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራር አካላትና ሰራተኞች የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡
ባለፈዉ ሳምንትም 20 ሚሊየን ብር የሚገመት 10.8 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡፡
Via:- Ethio FM

ገንዘቤ ዲባባ በዶሐ ከሚካሔደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጪ ሆነች። ገንዘቤ በቀኝ እግሯ ላይ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት በሚቀጥለው ሳምንት ከሚጀመረው ውድድር ውጪ መሆኗን አትሌቷን የሚወክለው ፔኔዳ ስፖርት አስታውቋል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ብሪታኒያ ዜጎቿ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክሯን አስተላለፈች!!
የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩም ሆነ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩ ዜጎቹ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያያዘ እንዳይዘዋወሩ አስጠንቅቋል። ማስጠንቀቂያውም አምስት ክልሎችን ያካተተ ሲሆን ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሱማሌ እና ጋምቤላ ናቸው።
የውጭ እና ኮመን ዌልዝ (common wealth) ቢሮ ይፋ እንዳደረገው በጋምቤላ ክልል አራት ወረዳዎች እና ከደቡብ ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ዐስር ኪሎሜትር ድረስ መቅረብ እንደሌለባቸው አስጠንቅቋል። በሱማሌ ክልል ጃር ጃር፣ ቆራሔ እና ደሎ የተባሉ አካባቢዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት የሱማሌ ክልል 100 ኪሎ ሜትር መራቅ እንደሚኖርባቸውም አሳስቧል። በትግራይ ክልልም ከኢትዮ- ኤርትራ ድንበር ዐስር ኪሎ ሜትር እንዲሁም ደብረ ዳሞ እና የሓ የጎብኝዎች መዳረሻዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ ሲል አስጠንቅቆ፥ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ፀገዴ፣ ምዕራብ አርማጭሆ እና ታች አርማጭሆ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ዜጎቹን አሰጠንቅቋል።
ቢሮው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞን ከአዲስ አበባ ጋምቤላ ከሚወስደው ዋና መንገድ ውጪ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት እንዳለ ይፋ አድርጓል።
መግለጫው በየዓመቱ ከአገረ እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ እስከ 20ሽሕ የሚደርሱ ጎብኝዎች እንደሚመጡ ገልፆ ኹሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ጉብኝቶች ከችግር እና ከደኅንንት ስጋት የፀዱ እንደነበሩና አሁንም ዜጎች ችግር እንዳይገጥማቸው ቅድመ ጥንቃቄ መውሰድ ጠቃሚ እንደሆነ አስታውቋል።
Via:- addis maleda

ቶታል ኢትዮጵያ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ የሞተር ዘይት መለወጫ ጣቢያዎች እንደገነባ አስታወቀ።
ላለፉት 69 ዓመታት በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ ተሰማርቶ የቆየው ቶታል ኢትዮጵያ፣ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ 52 የተሽከርካሪዎች የሞተር ዘይትና የቅባት መለዋወጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች መገንባቱን አስታወቀ፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ 32፣ በክልል ከተሞች 20 የሞተር ዘይትና የቅባት መለወጫ ጣቢያዎችን ከሽያጭ ወኪሎች ጋር በመተባበር በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን ኩባንያው አስታውቋል፡፡ እያንዳንዱ ጣቢያ በአማካይ ለአሥር ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
ምንጭ: ሪፖርተር

ሜቴክ የኢምፔሪያል ሆቴል ቢሮውን እንዲለቅ ሊደረግ ነው።
ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከዓመታት በፊት በ108 ሚሊዮን ብር የገዛውን እና ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምበት የነበረውን የኢምፔሪያል ሆቴልን እንደሚለቅ ፋና ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከዓመታት በፊት በ108 ሚሊዮን ብር የገዛውን እና ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምበት የነበረውን የኢምፔሪያል ሆቴልን እንደሚለቅ ፋና ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
ለዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ300 በላይ ድርጅቶች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸውን አቀረቡ።
መስከረም 7/2012 ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ300 በላይ ድርጅቶች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸውን በመላክ የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄ አቀረቡ።ፕሮጀክቶቹን ያቀረቡት ህጋዊ እውቅና ያላችው መንግስታዊ ያልሆኑ እና ሀገር በቀል የልማት ድርጅቶች ናቸው። የህዝብና የሞያ ማህበራት፣ የፌደራል፣ የክልል እና የአካባቢያዊ የመንግስት ተቋሞች እንዲሁም ሰፊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን የሚተገብሩ የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች ናቸው።
ድርጅቶቹ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጋር አብረው ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።ለትረስት ፈንዱ የቀረቡት የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ቁጥር ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ መሆኑንም አመልክቷል።
ምንጭ: በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ