YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
NEWS ALERT!!

የአቃቂ ገበያ ከፍተኛ በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደረሰበት።


በግዝፈቱ ከመርካቶ ቀጥሎ የሚታወቀው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ እሁድ ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት እንደረደሰበት ተረጋግጧል ። መነሻው ቅመም ተራ እንደሆነ የተነገረው አደጋው በፍጥነት ተዳርሶ በርካታ ቁጥር ያላቸው ልብስቤቶች እና ጫማ ቤቶችን አውድሟል።

እሳቱ ከምሽቱ 4 ሰአት በሁዋላ መነሳቱን(እኛም በተቻለን አቅም መረጃ ስንሰጣችሁ ነበር) በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች የተናገሩ ቢሆንም እስከ ሊሊቱ 9 ሰአት ድረስ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቢረባረቡም ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተስኗቸው ቆይቷል። በአደጋው አትክልት ተራ የሚባለውና እንደ ጌሾ እና በርበሬ እንዲሁም ሌሎች ቅመማ ቀመም የሚሸጥባቸው ቦታዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመዋል።የእሳት አደጋ ሰራተኞች ዘግይተው ቢደርሱም ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የዴሞክራሲ ቀን እየተከበረ ነው!

የዴሞክራሲ ቀን በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው።ቀኑ በተለይም በሸራተን አዲስ ሆቴል “በመደመር እሳቤ ጠንካራ እና ዘላቂ ዴሞክራሲን ለመገንባት እንነሳ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
የምስራቅ ዕዝ ያዘጋጀው የ2012 ዘመን መለወጫ በዓል ዛሬ በሃረር ከተማ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በሀረር ኢማም አህመድ ስታዲየም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላትና አመራሮች፣ የክልል ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ የሀረሪ ነዋሪዎች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።ከበዓሉ ቀደም ብሎ አጠቃላይ የበዓል ዝግጅት ስራዎችን በተመለከተ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ዘውዱ በላይ በተገኙበት የጋራ መድረክ ተካሂዷል።

Via የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
NEWS ALERT!! የአቃቂ ገበያ ከፍተኛ በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደረሰበት። በግዝፈቱ ከመርካቶ ቀጥሎ የሚታወቀው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ እሁድ ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት እንደረደሰበት ተረጋግጧል ። መነሻው ቅመም ተራ እንደሆነ የተነገረው አደጋው በፍጥነት ተዳርሶ በርካታ ቁጥር ያላቸው ልብስቤቶች እና ጫማ ቤቶችን አውድሟል። እሳቱ ከምሽቱ 4 ሰአት በሁዋላ…
በአደጋው ወደ 60 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት የወደመ ሲሆን 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ማዳን ተችሏል።

በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል።የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጠጣጠር 15 የአደጋ ተሽከሪካሪዎች ተሰማርተዋል፤ አምስት ቦቲ ተሽከርካሪ፣ አምስት ቀላል ተሽከርካሪ፣ ሁለት አምቡላንስ፣ 552 ሺህ ሊትር ውሃ ፣ ወደ 2 ሺህ ሊትር ፎም እንዲሁም 136 ሰራተኞች እና አመራሮች ተሳትፈዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዳሽን ባንክ በታዋቂው ኢትዮ-ሳውዲ ቢሊዮነር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ሥም የተሰየመ ልዩ ቅርንጫፍ ነሐሴ 30/2011 በዋና መስሪያ ቤቱ በይፋ አስመረቀ፡፡ ቅርንጫፉ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለውጪ ኢንቨስተሮች፣ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ ለኮርፖሬት አገልግሎት እና ለጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎት እንዲሰጡ የተዘጋጁ መስኮቶችን አካቷል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ እና ጂፒኤስ ሳይገጠምላቸው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መሆን ጀመረ።

ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ እና ጂፒኤስ ሳይገጠምላቸው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ያዘጋጀውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ መመሪያው ታህሳስ /2011 ዓ.ም አጋማሽ የፀደቀ ቢሆንም ተግባራዊ መሆን የጀመረው ግን ከሀምሌ 2011 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ለመሰማራት በመንቀሳቀስ ላይ ካሉ ባለሀብቶች ጋር በትላንትናው እለት ተወያይተዋል፡፡

በውይይት መድረኩም የጅማ ዞን አስተዳዳሪና የጅማ ከተማ ከንቲባ ተሳትፈዋል፡፡የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ በ1.5 ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት ላይ በ61 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተገንብቶ ህዳር 29፣2011 መመረቁ የሚታወስ ነው፡፡በፓርኩ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በፓርኩ በአብዛኛው ጨርቃ ጨርቅ ና የግብርና ምርቶችን የማቀነባበር ስራ ይከናወናል፡፡

Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa
MasterCard Foundation አዲስ አበባ ላይ ቢሮውን ሊከፍት እንደሆነ ተሰምቷል ።ለዚህም የሚረዳውን ስምምነት ባለፈው አርብ እንደተፈረመ ከስራ ፈጠራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፍትህ ቀን ማጠቃለያ ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል።

“የህግ ተገዢ ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የቆየውን የፍትህ ወር ማጠናቀቂያ እና ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረውን “የፍትህ ቀን” ምክንያት በማድረግ የፌዴራል የፍትህ አካላት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡በመሆኑም ከዝግጅቶቹ መካከል አንዱ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚኖረው ማጠቃለያ ፕሮግራም ከ15ሺህ ተሳታፊ በላይ የሚሳተፉበት ዝግጅት ከሰዓት ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚከናዉን ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በቡሪኪናፋሶ በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች በትንሹ የ29 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በቡሪኪናፋሶ ሰሜን ሳንማተንኛ ግዛት ተሳፋሪዎችን እና እቃ ጭኖ ሲጎዝ የነበረ ተሸካርካሪ ላይ በትናንትናው ዕለት በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በትንሹ 15 ንጹሃን ዜጎች ሕይወት ሲያለፍ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡በተመሳሳይ ሰዓት በዚሁ አካባቢ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሌሎች 14 ሰዎች በታጠቁ ሃይሎች መገዳለቸው ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፡- ሲጂ ቲ ኤን አፍሪካ/FANA
@YeneTube @FikerAssefa
ሪክ ማቻር ወደ ጁባ አቀኑ!

የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ሊወያዩ ነው።ማቻር ከሳልቫ ኪር ጋር ለሚያደርጉት ውይይትም ዛሬ ወደ ጁባ አቅንተዋል ነው የተባለው።ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታም ሳልቫ ኪርን ጨምሮ ከሌሎች ተቀናቃኝ ሃይሎች ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።

ምንጭ:Fana
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️⬆️

በ17ኛው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክለው የመጨረሻ አትሌቲክስ ቡድን ዝርዝር።

@YeneTube @FikerAssefa
የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጪው መስከረም መጨረሻ ወደ ስራ ይገባል።በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በባህር ዳር ከተማ የሚገኘው የባህር ዳር ቁጥር አንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጪው መስከረም መጨረሻ 2012 ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለፀ።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በወለጋ ዞን የአግሮ ኢንዱስተሪያል ፓርክ ሊገነባ ነው፡፡

አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርኩን ለማስገንባት የቦታ መረጣ እና የአዋጭነት ጥናት ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የግብርናውን ዘርፍ ግብዓቶችን በማቅረብ የሚያግዝ ሲሆን በግብርና ምርቶች ላይ ዕሴት በመጨመር በምግብ ራስን ለመቻል እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ ሚና እንደሚኖራችው ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል ሲል አስታውቋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ የመደበኛ ተማሪዎች በሙሉ⬇️

1⃣የነባር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምዝገባ ጊዜ መስከረም 5 እና 6 ሲሆን

2⃣የሌሎች ነባር ተማሪዎች መስከረም 21 እስከ 22

3⃣እንዲሁም አዲስ ወደ ዋቻሞ የተመደባችሁ ጥቅምት 28 እና 29 መሆኑን እንገልፃለል።

#ሬጅስተራር
@YeneTube @Fikerassefa
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች መግቢያ #መስከረም 20 - 21 መሆኑ አውቃችሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህብረት
@YeneTube @Fikerassefa
የእውቅና ፈቃድ (እድሳት) ሪፖርት ባልወጣለት ተቋም መመዝገብ ክልክል መሆኑን ኤጀንሲው አስታወቀ


የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የ201 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የእውቅና ፈቃድ ሙሉ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

መረጃው በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመዝግበው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚያገለግል ነው፡፡

ይህ ወቅታዊ መረጃ እስከ 2011 ዓ.ም መጨረሻ ያለውን የሚያካትት ሲሆን በሂደት ላይ ያሉትን ተከታትሎ እንደሚያሳውቅ ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ይደርሳል በሚል የእውቅና ፈቃድ ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ሪፖርት ባልወጣለት የትምህርት ተቋም ቀድሞ መመዝገብ ክልክል መሆኑንም ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡


የተቋማቱን የእውቅና ፈቃድ ሙሉ መረጃ ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ

https://bit.ly/2kCBtWb
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ አትክልት ተራ አካባቢ አንድ የ20 ዓመት ወጣት ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መሞቱ ተገለጸ።

የ20 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት ጅብሪል አህመድ በአትክልት ተራ አካባቢ የተለያዩ አትክሎትችን በመቸርቸር ስራ ህይወቱን ይመራ እንደነበር ኢትዮ ኤፍ ኤም በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አረጋግጧል።እናቱን በቅርቡ በሞት በማጣቱ ምክንያት ታናናሾቹን አንድ ወንድምና እህቱን ከዚሁ ስራ በሚያገኘው ገቢም ያስተዳደር ነበር።

ይሁንና በትናንትናው ዕለት ጧት ላይ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ይገባሉ። በሁለቱ ግገለሰቦች ምክንያት በአካባቢው የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች እንደመጡ በወጣት ጅብሪል አህመድ ላይ ሶስት ጥይት ተኩሰው እንደገደሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ወጣት ጅብሪል ወዲያውኑ ወደ አቤት ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።የሟች አስከሬንም ዛሬ ለአካባቢው ነዋሪዎች በመሰጠቱ ስርዓተ ቀብሩ በኮልፌ ሙስሊም መቃብር አካባቢ ተፈጽሟል።ፖሊስ ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ ጥይት መተኮሱም በተለይም በስፍራው የነበሩ ሰዎችን አስቆጥቷል።

ነዋሪዎቹ እንዳሉት ፖሊስ ጉዳዩን ሳያጣራ ነው ልጁ ላይ የተኮሰበት፣ መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በጉዳዩ ዙሪያ መልስ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም።

Via :- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
Wollega University Corporate Communications

#OFFICIAL_Announcement .
Simannaan barattoota yuunivarsiitii Wallaggaa ifoomeera.
Barattoota buleeyyii fulbaana 19-20/2012
Barattoota haaraa Ful.26-27/2012 ta'uusaa akka bartan isin beeksifna.


Dates of Registration for senior and newly assigned Students has been decided the University's Senate ,accordingly :-

Registration Date for Senior Students will be from Septemeber 19 upto 20/2012 E.C .

Regsitration Date for Newly Assigned students Will be from September 26 up to 27/2012 E.C.

Further annocement will be made in the future by using different Media Outlets . Corporate Communications Directorate .

ማስታወቂያ ለወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ።

የ2012 የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንደሚከተለው ተወስኗል።
በዚሁ መሠረት :-

የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም
19-20/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 26-27/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል።
@YeneTube @Fikerassefa
የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ የእርቅ ሳምንት አወጀ።

የእርቅ ሳምንቱ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 22 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa