YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሯቸው ተወያይተዋል።የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል።በለውጡ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በውይይቱ የተነሡ ሲሆን፥ በአንዳንድ አካላት እየተፈጸሙ ያሉ ጥፋቶችን በማንሣት ጳጳሳቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም የእርሳቸውም ሆነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ሁሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መሆኑን ገልፀዋል።የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት መጠናከርና አንድ መሆን ጥቅሙ ለእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሡ ሲሆን፥ ዓይነታቸው ቢለያይም የተለያዩ የእምነት ተቋማት በለውጡ ሂደት ፈተና አጋጥመዋቸዋል፤ በመሆኑም ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው ብለዋል።

የቀረቡትን ችግሮች በዝርዝር በማጥናትና በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በመነጋገር በጋራ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል። በሀገር ላይ የሚደርሱ ጥፋቶች በሁሉም ላይ የሚደርሱ በመሆናቸው መንግሥትና የእምነት ተቋማት በጋራ በመሥራት መፍታት እንዳለባቸው ገልፀዋል። በመጨረሻም የተፈጠሩትን ችግሮች የጋራ በማድረግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነትና ክብር በጠበቀ መልኩ በጋራ ለመፍታት ከስምምነት ላይ መደረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via:-FBC
@Yenetube @FikerAssefa
የለኩ የእኔም ለወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር ጷግሜን በመልካምነት በማለት ዛሬ እና ነገን ማለትም ጷግሜ አንድ ና ሁለት ከስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ የደም ስጦታነው በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ በማረግ ላይ ይገኛል።

Via:-Abex
@YeneTube @Fikerassefa
#አስቸኳይ_መልእክት

ቀብር - ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ9፡ 00 ሰዓት ይፈጸማል

ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ ለአገር እና ለሕዝብ አድርሱ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል፣ ከትናንት ጀምሮ ስብሰባ ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን መግለጫውም የስብሰባውን ይዘትና አቋም ይገልፃል ተብሎ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምስሉ የምትመለከቱ ዛኪር ኢብራሂም በቀን 24/12/2011 ልዩ ቦታው ደብረ አባይ አግማስ ዉሀ አካባቢ ከቀኑ በ4:00 ቀይ ሱሪ እርሳስ ከለር ሹራብ ለብሶ እንደወጣ አልተመለሰም ይህንን ልጅ ያየ ወይም ያለበትን ቦታ የሚያቅ ካለ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወረታ ከፋይ ነን ይላሉ ቤተሰቦቹ።
09-20-59-43-00
09-12-05-86-60
የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ የአመራር ሽግሽግ አደረገ።

በትናንትናው እለት በተደረገው በዚህ ሹመትና የአመራር ሽግሽግ፦

1. አቶ መልካሙ ወርቁ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ ቦንቴ ቦቼ የከተማዋ የደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣

3. ኮሌኔል ሮዳሞ ኪአ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣

4. ምክትል ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና

5. አቶ ሀይለዮሐንስ ነጌሶ የቤቶች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ መስጠቱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

Via:- Hawassa City Administration
@YeneTube @FikerAssefa
#Reminder - AAU

Regular undergraduate students registration for 2019/20 academic year is on September 16&17,2019(መስከረም 5 እና 6,2012)
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ያረፉትን የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለማሰብ የሀገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበልብ ትዕዛዝ ሰጡ። ሙጋቤ 95 ዓመታቸው ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
የድሬዳዋ ፖሊስ 146 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ አቃጠለ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የ2011 ዓ. ም. በከተማዋ የያዘውን 146.53 ኪሎ ግራም የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ ክምችት በዛሬው ዕለት አቃጠለ። የከተማይቱ ፖሊስ እርምጃውን የወሰደው በፍርድ ቤት በተላለፉ ውሳኔያዎች መሠረት ነው ተብሏል። ዛሬ የተቃጠለው አደንዛዥ ዕፅ «በአብዛኛው ወደ ጎረቤት ሃገራት ሊሄድ የተዘጋጀ ነበር» ሲል የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል። «በኅብረተሰብ ጥቆማና ትብብር» እንደተያዘ የተነገረለት አደንዛዥ ዕፅ ክምችት የተቃጠለው ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የዓይን እማኞች በተገኙበት ነው።

በድሬዳዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተበራከተ ለመጣው የወንጀል ድርጊት «ከተማዋን መናኸርያ ያደረገው የአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ድርሻ ከፍተኛ ነው» የሚሉ ነዋሪዎች አሉ። የአደንዛዥ ዕፅ ንግዱ በተለይ በከተማዋ የሚገኘውን ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ቤቶች ተገን ባደረጉት አካባቢዎች በስፋት እንደሚስተዋል ነዋሪዎቹ ይጠቁማሉ። በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ዘርፍ ምክትል ኮምሽነር ማሆ ተሾመ «በአስተዳደሩ እየተበራከተ ያለውን የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ለመግታት ሰፊ ጥረት እየተደረገ» መሆኑን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የቀድሞ የካሜሩን አምባሳደር አስከሬን በክብር ተሸኘ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ. ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና አዳራሽ በተደረገው የቀድሞው በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደር ጃኩዌስ አልፍረድ አስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተገኝተዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር አምባሳደር ጃኩዌስ አልፍረድ ሰዉ-አክባሪ ከመሆናቸው ባሻገር የኢትየጵያና የካሜሩን ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰዉ እንደነበሩ ገልጸዋል። በጃኩዌስ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለመላዉ የካሜሩን ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa