YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ወረዳ በአራት ቀበሌዎች በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በ200 ሔክታር መሬት ላይ የተዘራ አዝዕርት ሙሉ በሙሉ በማውደሙ 450 አርሶ አደሮች ለችግር መጋለጣቸው ተገለፀ፡፡

የወረዳው የአደጋ ስጋት ፅ/ቤት አርሶ አደሮቹን ለማቋቋም እየሰራ መሆንን አስታቋል፡፡የፅ/ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ግርማ ሙሉጌታ በወረዳ የአሌ ኮያ፣ደሴ ጀቦ፣በሮ በበሊና ሰንቀሌ አሌ ማሪያም ቀበሌዎች በረዶና ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ የአርሶ አደሮችን ሰብል ሙሉ በሙሉ በማውደሙ አፋጣን ድጋፍ እንደሚያስፈለጋቸው ተናግረዋል፡፡ከአደጋ ስጋት ኮሚሽን ጋር በመተባበር አርሶ አደሮቹን በአፋጣን እንደሚዶጉሙ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደጋ ስጋት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ ሽፈራ መገናገራቸውን OBN ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ለአቅመ ደካሞችና የህክምና ወጪ መሸፈን ለማትችሉ የሀዋሳና በአከባቢዋ የምትገኙ የነፃ ህክምናና የምክር አገልግሎት!

#Share

የሀዋሳ የኒቨርሲቲ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሀዋሳና አካባቢው ለሚገኙ አቅመ ደካማ ሰዎችና የህክምና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ ህክምናና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በመሆኑም ጳጉሜ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00 ሰዓት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዩኒቨርሲቲያችን ጥሪ ሲያደርግላችሁ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል፡፡

(Office of External Relations and Communication, OERC)
@YeneTube @FikerAssefa
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጪው አመት አዲሱን የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርትን ተግባራዊ ያደርጋሉ ተባለ፡፡

ተቋማቱ ይህንኑ አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡ይህንን የሰማነው ሚኒስቴሩ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከግል ተቋማት ባለሀብቶችና ተወካዮች ጋር ሲመካከር ነው።በመድረኩ የተገኙት ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ተቋማቱ ወቅታዊነቱንና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት መስጠት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡የሰለጠነና ብቃት ያለው የሰው ሀይል እንዲኖር ጥራትና አግባብነቱን የጠበቀ ትምህርት ማዳረስ አማራጭ የሌለውና ለነገ የማይባል እንደሆነም ተነግሯል፡፡ከአሁን በኋላ ባለሀብቶች የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንዲኖራቸው ይደረጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡ይሁን እንጂ አሁን ያለው የግል ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በርካታ እንከኖች ያሉበት ነው ተብሏል፡፡

ያለ በቂ ቤተ ሙከራ ተቋማትን መክፈት፣ ለተማሪ ተኮር ትምህርት ትኩረት አለመስጠት፣ ለተማሪዎች ያልተገባ ውጤት መስጠትና የሚሰጡ ትምህርቶችን በተግባር አለመደገፍ ከተለዩት እንከኖች መካከል ይገኙበታል፡፡
በሌሎች አገራት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት ይልቅ ተመራጭና ውጤታማ ናቸው ተብሏል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርትተው ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሯቸው ተወያይተዋል።የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል።በለውጡ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በውይይቱ የተነሡ ሲሆን፥ በአንዳንድ አካላት እየተፈጸሙ ያሉ ጥፋቶችን በማንሣት ጳጳሳቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም የእርሳቸውም ሆነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ሁሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መሆኑን ገልፀዋል።የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት መጠናከርና አንድ መሆን ጥቅሙ ለእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሡ ሲሆን፥ ዓይነታቸው ቢለያይም የተለያዩ የእምነት ተቋማት በለውጡ ሂደት ፈተና አጋጥመዋቸዋል፤ በመሆኑም ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው ብለዋል።

የቀረቡትን ችግሮች በዝርዝር በማጥናትና በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በመነጋገር በጋራ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል። በሀገር ላይ የሚደርሱ ጥፋቶች በሁሉም ላይ የሚደርሱ በመሆናቸው መንግሥትና የእምነት ተቋማት በጋራ በመሥራት መፍታት እንዳለባቸው ገልፀዋል። በመጨረሻም የተፈጠሩትን ችግሮች የጋራ በማድረግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነትና ክብር በጠበቀ መልኩ በጋራ ለመፍታት ከስምምነት ላይ መደረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via:-FBC
@Yenetube @FikerAssefa
የለኩ የእኔም ለወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር ጷግሜን በመልካምነት በማለት ዛሬ እና ነገን ማለትም ጷግሜ አንድ ና ሁለት ከስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ የደም ስጦታነው በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ በማረግ ላይ ይገኛል።

Via:-Abex
@YeneTube @Fikerassefa
#አስቸኳይ_መልእክት

ቀብር - ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ9፡ 00 ሰዓት ይፈጸማል

ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ ለአገር እና ለሕዝብ አድርሱ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል፣ ከትናንት ጀምሮ ስብሰባ ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን መግለጫውም የስብሰባውን ይዘትና አቋም ይገልፃል ተብሎ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምስሉ የምትመለከቱ ዛኪር ኢብራሂም በቀን 24/12/2011 ልዩ ቦታው ደብረ አባይ አግማስ ዉሀ አካባቢ ከቀኑ በ4:00 ቀይ ሱሪ እርሳስ ከለር ሹራብ ለብሶ እንደወጣ አልተመለሰም ይህንን ልጅ ያየ ወይም ያለበትን ቦታ የሚያቅ ካለ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወረታ ከፋይ ነን ይላሉ ቤተሰቦቹ።
09-20-59-43-00
09-12-05-86-60
የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ የአመራር ሽግሽግ አደረገ።

በትናንትናው እለት በተደረገው በዚህ ሹመትና የአመራር ሽግሽግ፦

1. አቶ መልካሙ ወርቁ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ ቦንቴ ቦቼ የከተማዋ የደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣

3. ኮሌኔል ሮዳሞ ኪአ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣

4. ምክትል ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና

5. አቶ ሀይለዮሐንስ ነጌሶ የቤቶች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ መስጠቱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

Via:- Hawassa City Administration
@YeneTube @FikerAssefa
#Reminder - AAU

Regular undergraduate students registration for 2019/20 academic year is on September 16&17,2019(መስከረም 5 እና 6,2012)
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ያረፉትን የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለማሰብ የሀገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበልብ ትዕዛዝ ሰጡ። ሙጋቤ 95 ዓመታቸው ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g