YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሀገር አቀፍ የሥርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ተደረገ።

ጥናቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የሚሰጠው ትምህርት ምን መምሰል አለበት? ተማሪዎችም በየደረጃቸው ሊይዙ የሚገባቸው የእውቀት ደረጃ ምን ይመስላል? የሚለውን ይዘት የሚዳስስ እንደሆነ ተመልክቷል።

በውጭ ሀገር ባለሙያዎች እንደተደረገ የተገለጸው የሥርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናቱ ይፋ የተደረገው ዛሬ ትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ በጠራው ጉባኤ ላይ ነው። ጥናቱን የውጭ ዜጎች እንዲያደርጉ የተፈለገበት ምክንያት «በነጻነት፣ እውነተኛ የጥናት ውጤት እንዲያመላክቱ ለማድረግ በመታሰቡ» መሆኑን በጉባኤ ላይ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ትምህርት ላይ የተካሄደው የሥርዓተ ትምህርት ጥናት ምን አዲስ ነገሮችን እንዳካተተ ለጉባኤው ታዳሚያን አብራርተዋል። የጥናቱን ውጤት ተከትሎ አሁን በተግባር ላይ ያለው ሥርአተ ትምህርት በአንድ ጊዜ ይተካል ማለት እንዳልሆነም ተጠቁሟል። #ከ2013 ዓ. ም #ጀምሮ_ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀመር የተገለጸው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ የሚገባው በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚሆን ተገልጿል።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa