YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ካላንደረ⬆️

ሁለተኛ አመት እና ከዛ በላይ የሆናችሁ ተማሪዎች መስከረም 21 እስከ 23 መሆኑ ዩንቨርስቲው ባወጣሁ ካላንደር ላይ አስፍሯል።
@YeneTube @FikerAssefa
በካቡል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል በተፈጸመ ጥቃት 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።ጥቃቱ የተፈጸመው በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። ለጥቃቱ የታሊባን ታጣቂ ቡድን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።ታሊባን በቅርብ ቀናት ውስጥ ብቻ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ሃላፊነቱን ሲወስድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የእርዳታ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንደሆነ የተነገረው አካባቢው በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሆኗል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ
@YeneTube @FikerAssefa
ቀደምት ከሚባሉ የክልል ሚዲያዎች ተርታ የሚመደበው ድሬ ቲቪ የስርጭት አድማሱን ወደ ሳተላይት በማሳደግ በአገር ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም ለሚገኙ የከተማዋ ተወላጆች ለመድረስ እቅድ ቢኖረውም የበጀት እጥረት እንቅፋት እንደሆነበት ገለፀ።

ከተመሰረተ ከ10 ዓአመት በላይ ያስቆጠረው ድሬ ቲቪ በከተማዋ ውስጥ ብቻ ተወስኖ የ15 ሰዓት የአንቴና የቴሌቪዥን ስርጭት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የድሬደዋ ነዋሪዎች ቴሌቪዥኑ የስርጭት አድማሱን እንዲያሰፋ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የተለያዩ ተቋማት በዛሬው ዕለት ከ761 ሺ በላይ ደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በዚህም ፦

1. ወጋገን ባንክ 116 ሺ 615 ደብተር
2. ዳን ኢነርጂ ኢትዮጵያ 100 ሺ ደብተር
3. በጎ ፈቃደኛ ነጋዴዎች 100 ሺ ደብተር
4. ፕረዘንስ ኦፍ ጋድ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን 100 ሺ ደብተር
5. የየካ ክ/ከተማ እና ወረዳ መንግስት ሰራተኞች 133 ሺ 940 ደብተር
6. የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፈደሬሽን 50 ሺ 858 ደብተር
7. የአዲስ አበባ እድሮች ፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን ማህበራት 25 ሺ ደብተር
8. ICMC አጠቃላይ ሆስፒታል 20 ሺ ደብተር
9. የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፈደሬሽን 10 ሺ ደብተር
10. የሾላ ገበያ ነጋዴዎች ማህበር 6060 ደብተር
11. የ Elico ሰራተኛ ማህበር 1200 ደብተር
12. የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች 70 ሺ ብር የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ
13. ኦሮሚያ ደን እና ዱር እንስሳት ሸገር ቅርንጫፍ 600 ደብተር

ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ነው፡፡የከተማውን ተማሪ በመወከል ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ተማሪ ሮቤል ባምላክ ተሰማ እና ተማሪ ሔመን ኪዳኔ ስጦታውን ተቀብለዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተቋሞቹ ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላደረጉት የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መንግስት ሆይ ድረስልን የሚል ድምጽ እያሰሙ ነዉ፡፡

ኑሯቸዉን በደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ለደህንነታቸዉ በሚያሰጋ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ እንደሆኑና እያደር ከመረጋጋት ይልቅ እየከፋ መሄዱን ተናግረዋል፡፡አንድ ደቡብ አፍሪካዊ የታክሲ አሽከርካሪ ተገደለ በሚል የተጀመረዉ ጥቃት አሁን ላይ መልኩን ቀይሮ ጥቃቱ በሙሉ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ነግረዉናል፡፡

ይህን ጉዳይም ለሀገሪቱ ባለስልጣናት በደብዳቤና በአካልም ጭምር ብናሳዉቅም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አጋጣሚዉን ለራሳቸዉ የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ እያደረጉት ነዉ፤በሀገሪቱ ለተፈጠሩ የስራ አጥነትና ወንጀል ድርጊቶች ተጠያቂዎቹ ስደተኞች ናቸዉ በሚል እየቀሰቀሱ ጥቃቱ እንዲባባስ እያደረጉ ይገኛል ሲሉ ነዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ቀደም ሲልም ይህን መሰል ድርጊቶች አልፎ አልፎ ያጋጥም የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዋና ዋና ከተሞች በሚባሉት ፕሪቶሪያ፣ጆሃንስበርግ፣ አሌክሳንደሪያና ሌሎችም ታላላቅ ከተሞች ጭምር መከሰቱ ችግሩ የከፋ እንደሆነ ማሳያ ነዉ ይላሉ፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ እንዳሉት መንቀሳቀስ ይቅርና ቤትና ሱቆች ዉስጥም ተቀምጠን ችግሩን ልናመልጥ አልቻልንም፤ለእስር እየተዳረግንና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየተፈጸመብን በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ የምናገኝበትን መንገድ ይፍጠርልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየሰራ ነው ጉዳዩንስ ያውቀዋል ሲል ጠይቋል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸዉ እንደነገሩን ችግሩን እናዉቃለን፤በዚያዉ በሚገኘዉ ኤምባሲያችን በኩል ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነዉ ብለዋል፡፡

ዜጎቻችንም ችግሩ በዋናነት በሚታይባቸዉ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡና እዛዉ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ጋር ቢነጋገሩ መልካም ነዉ የሚል ምላሽን ሰጥተዋል፡፡
አስተያየት ሰጭዎቹ በበኩላቸዉ ኤምባሲዉ የተቻለዉን እያደረገላቸዉ መሆኑን ገልጸዉ፤ነገር ግን ችግሩ የከፋ በመሆኑ መንግስት ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ስራ እንዲሰራላቸዉ ጠይቀዋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ናይጀሪያ የዜጎቿ ደህንነት የማይጠበቅላት ከሆነ ደቡብ አፍሪካዊያንን ከሀገሯ እንደምታስወጣ ጠንካራ አቋም መያዟንም አስተያየት ሰጭዎቹ ነግረዉናል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅን እንደሚቃወም አስታውቋል። አዋጁ "ሥጋቶችን የማይቀርፍ፣ የጋራ ምክር ቤቱን ዓላማዎች የማያስፈፅም ፣ ከቃል-ኪዳናችን በተፃራሪ የተለመደውን አሰራር የሚያስቀጥል" ነው ብሏል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ በስልክ እንደነገሩኝ አንድ የግል ጠባቂያቸው ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ደብዛው እንደጠፋ እና ታፍኖ ተወስዷል የሚል ግምት እንዳላቸው ነግረውኛል ብሏል ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት።

@YeneTube @FikerAssefa
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የ2019/2020 ካላንደር የመጀመሪያ መንፈቅ አመት ምዝገባ October 21-22 መሆኑን ዩንቨርስቲ ያወጣው ካላንደር ያሳያል።

የተማሪዎች ተወካይ የተረጋገጠ መረጃ በማድረስ ተባበሩን መረጃዎችን በ @FikerAssefa ላይ ይላኩ።

@YeneTube @FikerAssefa
Audio
አሳዛኝ ዜና!! ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ንብረታቸውን ከዘራፊዎች ለማትረፍ በመሸሽ ላይ እያሉ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ መሞታቸው ተነግሯል።

ኢትዮጵያዊያኑ የመኪና አደጋው የገጠማቸው ደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ አቅራብያ በሚትገኝ ጁሊየስ የምትባል መንደር ውስጥ ወደሚገኝ ንብረታቸው እየነዱ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሱቆቻቸው ለመሄድ የተነሱት የአካባቢው ነዋሪዎች የስደተኞች ሱቆችን እየዘረፉ ነበር በተባለበት ወቅት እንደነበረ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ ምክትል ሰብሳቢ ናህሊ ሙሳ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
President Sahle-Work Zewde has arrived at South Africa to participate on 2019 World Economic Forum for Africa.
@YeneTube @FikerAssefa
#መቐለ_ዩንቨርሲቲ

የመቐለ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን ከመስከረም 7 እስከ 10 እንዲሁም የማታ ተማሪዎች ከመስከረም 13 እስከ 16 መሆኑን በETV አስተዋውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ካሜሩን ከኢትዮጵያ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች እግርኳስ ቡድን ለ2020 የቶኪዮ የኦሎምፒክ ለማለፍ የቅድመ ማጣሪያ የመልሱን ጨዋታ ለማድረግ ያዉንዴ ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በካሜሮን አቆጣጠር 9፡30 ወይም በኢትዮጵያ የሰአት አቆጣጠር 11፡30 ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ ። ሁለቱም ቡድኖቹ በአሄሙዱ አህዲዮ ስታዲየም እያምሟቁ ይገኛሉ ።

Via Ethio-Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ 14ኛውን የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ አሰፋፈር ጉባኤን ታስተናግዳለች። ጉባኤው ነገ ሐሙስ እና ዓርብ ነሐሴ 29 እና 30/2011 አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሔዳል። ጉባኤው በአፍሪካ ሲካሔድ ይሄ የመጀመሪያው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን እንዲመለመሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
“በኢትዮጵያ የጨለማ እስር ቤቶች የሉም ”- የጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት «የጨለማ እስር ቤቶች» እንደሌሉ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ገለጸ። መስሪያ ቤቱ በጨለማ ክፍሎች ሰዎችን ማሰር ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸሙበት የነበረውን በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚጠራውን እስር ቤት ከጳጉሜ 1 ጀምሮ ባሉት አራት ተከታታይ ቀናት ለጉብኝት ክፍት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የጠቅላይ አቃቤ ሕግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደተናገሩት በማዕከላዊ ጉብኝት ወቅት ለዕይታ ከሚቀርቡ ነገሮች መካከል በእስር ቤቱ «ምርመራ እንዴት ይደረግ እንደነበር» የሚያሳየው ይገኝበታል።

«ሳይቤሪያ» እና «ሸራተን» ተብለው የሚታወቁትን የእስር ቤቱን የተለያዩ ክፍሎች ጨምሮ የእስረኞች ማደሪያ እና ፀሀይ መሞቂያ ቦታዎች የጉብኝቱ አካል እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከላዳ ታክሲ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡በቆይታቸውም በከተማዋ ውስጥ ያለው የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት በሚቀረፍበት መንገዶች ዙሪያ ከታክሲ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡የላዳ ታክሲ ባለንብረቶቹም ያለባቸውን የስራ ላይ ችግር እና የህግ ክፍተቶች ለኢ/ር ታከለ ኡማ አቅርበዋል፡፡
ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም በሚተገበሩ አዳዲስ አሰራሮች ላይ ግብዓት በመስጠት እና በከተማዋ ያለው የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ እንደሚሰሩም የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች ተናግረዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶችን ህይወት ለማሻሻል እና ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ እንደሚሰራ እና የተመቻቸ የስራ ቦታን እንደሚፈጥርላቸውም ተናግረዋል፡፡

-የከንቲባው ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
Academic Calender for 2019-20 AY Final.pdf
175 KB
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019/20 የት/ት ዘመን አካዳሚክ ካላንደር።

@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 5 እና 6 መሆኑ ታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለነሐሴ 30 አስቸኳይ ምልዓተ ጉባዔ መጥራቱ ተሰምቷል፡፡

ጉባዔው በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ሲፈጸሙ ለቆዩ ጥቃቶች እና ጥያቄዎች እየሰጠ ባለው ምላሽ እና በቅርቡ ራሱን “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ” ሲል የሰየመው ቡድን ባወጣው መግለጫ ላይ ይነጋገራል፡፡ ሲኖዶሱ ምን ያድርግ በሚለው ላይ የተለያዩ አቋሞች እንዳሉ ትተሰምቷል፡፡ በየደረጃው ጠንካራ አቋም እንዲወሰድ የሚጠይቁ ድምጾች እየበዙ መምጣታቸው፣ በሌላ በኩል ደሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለቤተ ክርስቲያኗ ሲኖዶስ አንድነት ያደረጉት አስተዋጽዖ የጉባዔውን አቅጣጫ የሚወስኑ እንደሚሆኑ የዋዜማ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa