መንግስት በህገወጦች ላይ ተገቢውን እርምጃ በየጊዜው ባለመውሰዱ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ምክንያት እንደሆነ የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የኑሮ ንረትን በተመለከተ ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ባዘጋጀው የንቅናቄ ውይይት መድረክ ላይ እንደተባለው ምንም እንኳን በመንግስት በተለያየ ጊዜ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ሰዎች ቢያዙም ተገቢ እርምጃ ባለመወሰዱ ምክንያት የኑሮ ንረቱ ገደብ አጥቷል፡፡በመድረኩ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው እንዳሉት ህገ ወጦች ላይ መቀጣጫ የሚሆን እርምጃ አለመውሰዱ እንዲሁም ጠንካራ የሆነ የክትትልና ቁጥጥር ስርአት ዝርጋታባለመበጀቱ ህገወጦች እንደልባቸው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡
እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለፃ የደላላ ጣልቃ ገብነት፣ ምርትን በክምችት መያዝ፣ ፍትሀዊ ያልሆነ የዋጋ ውድድር (የዋጋ ወሰን)፣ ያለ ደረሰኝ ግብይት ማካሄድና ፎርጅድ ደረሰኝ እንዲሁም የመግዣ ዋጋ አለማየትና የመሸጫ ዋጋ አለመለጠፍ በሀገራችን ለሚታየው ኑሮ ውድነት እንደ አብይ ምክንያት ናቸው፡፡በሚኒስቴር ዴኤታው የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት በመንግስት በኩል የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳብ ተብለው የቀረቡ ሲሆን ስንዴን ለማሰራጨት መዘጋጀቱን፣ የህብረት ስራ ማህበራት ብድር እንዲያገኙና ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ መደረጉን ለአብነት ጠቅሰዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

የዓባይ ኅትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ በቀጣይ ዓመት በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነ ሚስጥራዊ ኅትመት ሊጀምር ነው፡፡
የዓባይ ኅትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ በአማራ ክልል የነበረውን የኅትመት ችግር እንደቀረፈ ተገልጧል፡፡ዓባይ ኅትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ሀምሌ 2010 ዓ.ም ነበር ተመርቆ ወደ ሥራ የገባው። የተቋቋመውም በአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር እና በአማራ ክልል ደን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት ነው፡ፋብሪካው በ2011 በጀት ዓመት ደግሞ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ በሥራ ላይ በቆየባቸው ጊዜያትም ከ1ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የመማሪያ መጻህፍትን በክልሉ በሚነገሩ በሁሉም ቋንቋዎች አሳትሞ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ እንዳስረከበ የፋብሪካዉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ታደሰ መላሽ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የልቦለድ መፅሐፍት እና የበኩር ጋዜጣ ሳምንታዊ ህትመቶችን፣ የልማት ድርጅቶች ማስታወቂያዎችን፣ የአብቁተ የደበኞች የቁጠባ ደብተሮችን እና ሌሎች ኅትመቶችን በተሻለ ደረጃ ማሳተማቸውንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
Via AMMA

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) አመራሮች መካከል በተከሰተው አለመግባባት፣ ንቅናቄው ለኹለት ተከፍሎ ግጭት ውስጥ መግባቱን አዲስ ማለዳ ከፓርቲው አመራሮች አገኘሁት ያለው መረጃ ያመለክታል።
በሚሊዮን ቱማቶ (ዶ/ር) የሚመራው ወገን “የሲአን ሕጋዊ አመራር እኔ ነኝ” ያለ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ነሐሴ 20/2011 የንቅናቄውን የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ አካሒዷል። የተካሔደው ስብሰባ ዕውቅና የሌለው ነው በማለት ያወገዘው በዱካሌ ላሚሶ የሚመራው ቡድን በበኩሉ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴውን ያካሔዱት አመራሮች በከባድ የሥነ ምግባር ጉድለት ያሰናበትናቸው በመሆናቸው ተቀባይነት የሌለው ሲሉ ስብሰባውን ተቃውመውታል።

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እና በራስ ዳሽን ተራራ ላይ ብቻ የሚገኘው ብርቅዬው የዱር እንስሳ ዋልያ ከመጥፋት ስጋት በመውጣት ወደ ዘጠኝ መቶ ከፍ አለ።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ ከ 15 ዓመት በፊት የዋልያዎቹ ቁጥር ወደ 150 ማሽቆልቆሉን ተከትሎ በአደጋ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ አድርጎ የነበረ ቢሆንም በ2010 ከፍተኛ የሚባል የቁጥር እድገት በመታየቱ በድጋሚ የቋሚ ቅርስ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ይታወሳል።
ፓርኩ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበበት ጊዜ አንስቶ በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ የዋልያዎቹን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ተችሏል ሲሉ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለስልጣን የብሔራዊ ፓርኮች መጠለያና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገብረመስቀል ግዛው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የወንዶች የእግር ኳስ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ነገ ይካሄዳል
የኢትዮጵያ የወንዶች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ለ2020 የኳታር የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የሚያደርገውን ጨዋታ በነገው ዕለት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከቀኑ 10፡00 ላይ ይካሄዳል።
የመልሱ ጨዋታ ጳጉሜ 3/2011 ዓ.ም በሌሴቶ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
በሌላ ዜና፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ከካሜሮን አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ እንዳለበት ተገልጿል።
ቡድኑ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከካሜሮን አቻው ጋር በያውንዴ ያደርጋል።
ጨዋታው 42 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው አህማዱ አሂጆ ስታዲየም ከቀኑ 11፡30 ይካሄዳል።
29 አባላትን የያዘው የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ያውንዴ መግባቱን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ነሐሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም በባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የተደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
በቶኪዮው ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር 12 ብሔራዊ ቡድኖች ይሳተፋሉ።
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነገው እለት እሮብ ነሃሴ 29/2019 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰአት ጀምሮ በማሪዮት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው ለሁሉም ሚዲያ ክፍት ስለሆነ ቦርዱ በመግለጫው ላይ በመገኘት እንዲዘግቡለት ጥሪውን አስተላልፏል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው ማዕከላዊ እስር ቤት ለጉብኝት ክፍት እንደሚደረግ ተገለጸ፡፡
ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረውን የፍትህ ቀን ምክንያት በማድረግ የቀድሞው ማዕከላዊ እስር ቤት ለጉብኝት ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግ የበአሉ የኮሚዩኒኬሽን፣ ሚድያና መድረክ ዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ገለጹ፡፡እስር ቤቱ ከዚህ ቀደም በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት እንደነበር የሚታወስ ሆኖ ለውጡን ምክንያት በማድረግ መንግስት እንዲዘጋና ወደ ሙዚምነት እንዲቀር መወሰኑ ይታወቃል፡፡ በማእከላዊ እስር ቤት በፖለቲካ ነክ የህግ ተጠያቂ እስረኞች ላይ የማይሻር የስነ-ልቦና ቅጣት እስከ አካል ማጉደል የሚያደርስ የስቃይ/ተርቸር/ ዘዴዎች ይፈጸሙ ነበር፡፡
በተጨማሪም በተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ሂደት ሲከናወን በጨለማ ቤቶች ተዘግተው ከፍተኛ የሆነ ጫናና በደል ሲደርስባቸው አንዳንዶችም ህወታቸው ያልፍ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሆኖ የእናቶች እንባ ከታበሰና የለውጡ ምህዳር ከሰፋ ጊዜ ጀምሮ እስር ቤቱ ዝግ ተደርጎ በዚህ ቦታ ላይ ይፈጸም የነበረው የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት ጥሰት ቆሟል፡፡
በመሆኑም የኮሚኒኬሽን ሚዲያና መድረክ ዝግጂት ኮሚቴ እንዳስታወቀው የፍትህ ቀንን ምክኒያት በማድረግ እስርቤቱ ለጉብኝት ከጳጉሜን 1 እስከ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ለሁሉም ሰው ክፍት ሆኖ እንደሚቆይና በህብረተሰቡ ጉብኝት እንደሚደረግ በተጨማሪም በየፍትህ አካላት ማለትም በጠቅላይ ፍርድ ቤት፣በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የተለያዩ የስዕል አውደ ርዕዮች እና በፍትህ ላይ የሚያጠነጥኑ የኤግዚቢሽን መርሃ ግብር እንዲሁም በእስር ቤቱ በፊት በአገልግሎት ላይ እያለ ተጠርጣሪዎች የሚመረመሩባቸውን ጨለማ ቤቶች ከጳጉሜ1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት ለዕይታ ለህዝብ ክፍት ስለሚደረግ ማንኛውም ህብረተሰብ በተገለጹት ቀናቶች በቦታው ላይ በመገኘት የጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ኮሚቴው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
Via Federal General Attorney

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያለበትን 151 ሚሊዮን ብር እዳ ባለመክፈሉ ምክንያት የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት አቋረጠ።
ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የላብራቶሪ መመርመሪያና ሌሎች የህክምና ግብዓት የሚቀርቡለት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ነበር።ኤጀንሲው ከዚህ በፊት ለዚህ ሆስፒታል ያቀረበለትን ገንዘብ ባለመከፈሉ ምክንያት ግብዓት አላቀርብም በማለቱ ሆስፒታሉ ለጊዜው የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎትን እያካሄደ አይደለም።በዚህ ምክንያት ደግሞ ታካሚዎች ህክምና በላብራቶሪ ግብዓት እጥረት ምክንያት ለሳምንታት እየተንገላቱ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።ታካሚዎቹ እንዳሉት ከምንኖርበት አካባቢ ሪፈር ተብለን የተሻለ ህክምና ፍለጋ ብንመጣም ሆስፒታሉ የላብራቶሪ መመርመሪያ ግብዓት እጥረት ገጥሞኛል ብሎ የምርመራ አግልሎቱንም አቋርጧል።
በአንድ ኩላሊት የሚኖር አለ፣ለምግብና ለትራንስፖርት ወጪ ብቻ የሚሆን ገንዘብ ይዘን ነበር ከቤት የወጣነው፣በአንድ ቀን ሁለት ቀን ህክምና እናገኛለን ብለን ብንመጣም ይሄው ሳምንታትን አስቆጠርን መንግስት መፍትሔ የስጠን ሲሉ ታካሚዎቹ ቅሬታቸውን ተናግረዋል። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የዲያግኖስቲክስ ሀላፊ ዶክተር ምህረቱ መሃሪ እንዳሉት ታካሚዎቹ ያነሱትን ቅሬታ እናውቃለን ፣ አገልግሎት የሚጀምርበትን ቀን በእርግጠኝነት መናገር አንችልም ብለዋል።አገልግሎቱ የተቋረጠው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ግብዓት ስላላቀረበልን ነው ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ተስፍአለም አዳራሮ በበኩላቸው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ላለፉት አምስት አመታት የተከማቸ 151 ሚሊየን ብር ዕዳውን ባለመክፈሉ አቅርቦቱን አቋርጠናል ብለዋል።
Via Ethio FM

ገበሬዎች ሰፋፊ እርሻ አልሚ የሚሆኑበት ህግ ሊዘጋጅ ነው።
መንግሥት በትናንሽ መሬት ላይ የሚያርሱ ገበሬዎች ሰፋፊ እርሻዎች ከመንግሥት በሊዝ ወስደው ባለድርሻ የሚሆኑበት አዲስ ሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት መወሰኑን ሃገር በቀል ኢኮኖሚ አጀንዳ ይፋ በሆነበት ወቅት አስታወቀ።ከ 20 ዓመታት ጀምሮ ሲሠራበት በነበረው ግብርና መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት፣ በትንንሽ የእረሻ መሬቶች ላይ የማምረት አሠራር የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አለማስቻሉን ተከትሎ ይፋ የሆነው ማዕቀፉ፣ ገበሬዎች ከመንግሥት ብድር ወስደው ሰፋፊ እርሻዎችን ማስተዳደር የሚችሉበትን መንገድ እንደሚያመቻች ተነግሯል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያሉ ኹሉም ሼዶች በ2012 ወደ ስራ ይገባሉ።
የሐዋሳ ኢንዳሰትሪያል ፓርክ አስተዳደር እና በፓርኩ የሚገኙ ድርጅቶች በቅርቡ ኹሉንም ሼዶች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት እየሰሩ መሆኑን የፓርኩ አስተዳደር ገለጸ።የሐዋሳ ኢንዳሰትሪያል ፓርክ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍጹም ከተማ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት የተገነቡት 52 ሼዶች ለ21 ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ የተከፋፍሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ የቅድመ ዝግጅት ስራ እንደጨረሱ ገልጸዋል፤ ዘገባው የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ነው፡፡

ማስታወቂያ‼️
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ከላይ በምስሉ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ
http://197.156.83.153/admission/ ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ::
#Share #Share

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መደ ወላቡ ወረዳ አዲስ የዋሻ ቅርስ መገኘቱ ተገለፀ።
ዋሻው በመደ ወላቡ ወረዳ ሊቂምሳ ቦኮሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዋጫራ ሀይቅ በመባል በሚጠራ አካባቢ መገኘቱ ነው የተነገረው።አዲስ የተገኘው ዋሻ “መነ ዋቃ (የእግዜር ቤት)” በመባል እንደሚታወቅም ዋሻውን በጥናት ያገኘው የመደ ወላቡ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታውቋል
Via FBC

YeneTube
ማስታወቂያ‼️ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከላይ በምስሉ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ http://197.156.83.153/admission/ ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ:: …
ተጨማሪ ⬆️⬇️
ቅዱስ ፓውሎስ መግቢያ ነጥብ
ለወንዶች 516
ለሴቶች 491
እንዲሁም ትኩረት ለሚሹ ክልሎች
ለወንዶች 466
ለሴቶች 441
ቅዱስ ፓውሎስ ሜዲካል ኮሌጅ አስታውቋል። መወዳደር የምትፈልጉ ሊንኩን በመክፈት ገብታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።
http://197.156.83.153/admission/
@YeneTube @FikerAssefa
ቅዱስ ፓውሎስ መግቢያ ነጥብ
ለወንዶች 516
ለሴቶች 491
እንዲሁም ትኩረት ለሚሹ ክልሎች
ለወንዶች 466
ለሴቶች 441
ቅዱስ ፓውሎስ ሜዲካል ኮሌጅ አስታውቋል። መወዳደር የምትፈልጉ ሊንኩን በመክፈት ገብታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።
http://197.156.83.153/admission/
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው እለት በሽረ እንደስላሴ ከተማ አራት የትዴት(TAND) አባላት በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ታስረዋል ብሏል የአረናው ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ባሰፈረው መረጃ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ካላንደረ⬆️
ሁለተኛ አመት እና ከዛ በላይ የሆናችሁ ተማሪዎች መስከረም 21 እስከ 23 መሆኑ ዩንቨርስቲው ባወጣሁ ካላንደር ላይ አስፍሯል።
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለተኛ አመት እና ከዛ በላይ የሆናችሁ ተማሪዎች መስከረም 21 እስከ 23 መሆኑ ዩንቨርስቲው ባወጣሁ ካላንደር ላይ አስፍሯል።
@YeneTube @FikerAssefa
በካቡል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል በተፈጸመ ጥቃት 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።ጥቃቱ የተፈጸመው በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። ለጥቃቱ የታሊባን ታጣቂ ቡድን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።ታሊባን በቅርብ ቀናት ውስጥ ብቻ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ሃላፊነቱን ሲወስድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የእርዳታ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንደሆነ የተነገረው አካባቢው በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሆኗል፡፡
ምንጭ፦ አልጀዚራ

ቀደምት ከሚባሉ የክልል ሚዲያዎች ተርታ የሚመደበው ድሬ ቲቪ የስርጭት አድማሱን ወደ ሳተላይት በማሳደግ በአገር ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም ለሚገኙ የከተማዋ ተወላጆች ለመድረስ እቅድ ቢኖረውም የበጀት እጥረት እንቅፋት እንደሆነበት ገለፀ።
ከተመሰረተ ከ10 ዓአመት በላይ ያስቆጠረው ድሬ ቲቪ በከተማዋ ውስጥ ብቻ ተወስኖ የ15 ሰዓት የአንቴና የቴሌቪዥን ስርጭት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የድሬደዋ ነዋሪዎች ቴሌቪዥኑ የስርጭት አድማሱን እንዲያሰፋ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
- አዲስ ማለዳ

የተለያዩ ተቋማት በዛሬው ዕለት ከ761 ሺ በላይ ደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በዚህም ፦
1. ወጋገን ባንክ 116 ሺ 615 ደብተር
2. ዳን ኢነርጂ ኢትዮጵያ 100 ሺ ደብተር
3. በጎ ፈቃደኛ ነጋዴዎች 100 ሺ ደብተር
4. ፕረዘንስ ኦፍ ጋድ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን 100 ሺ ደብተር
5. የየካ ክ/ከተማ እና ወረዳ መንግስት ሰራተኞች 133 ሺ 940 ደብተር
6. የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፈደሬሽን 50 ሺ 858 ደብተር
7. የአዲስ አበባ እድሮች ፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን ማህበራት 25 ሺ ደብተር
8. ICMC አጠቃላይ ሆስፒታል 20 ሺ ደብተር
9. የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፈደሬሽን 10 ሺ ደብተር
10. የሾላ ገበያ ነጋዴዎች ማህበር 6060 ደብተር
11. የ Elico ሰራተኛ ማህበር 1200 ደብተር
12. የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች 70 ሺ ብር የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ
13. ኦሮሚያ ደን እና ዱር እንስሳት ሸገር ቅርንጫፍ 600 ደብተር
ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ነው፡፡የከተማውን ተማሪ በመወከል ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ተማሪ ሮቤል ባምላክ ተሰማ እና ተማሪ ሔመን ኪዳኔ ስጦታውን ተቀብለዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተቋሞቹ ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላደረጉት የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
Via OBN

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መንግስት ሆይ ድረስልን የሚል ድምጽ እያሰሙ ነዉ፡፡
ኑሯቸዉን በደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ለደህንነታቸዉ በሚያሰጋ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ እንደሆኑና እያደር ከመረጋጋት ይልቅ እየከፋ መሄዱን ተናግረዋል፡፡አንድ ደቡብ አፍሪካዊ የታክሲ አሽከርካሪ ተገደለ በሚል የተጀመረዉ ጥቃት አሁን ላይ መልኩን ቀይሮ ጥቃቱ በሙሉ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ነግረዉናል፡፡
ይህን ጉዳይም ለሀገሪቱ ባለስልጣናት በደብዳቤና በአካልም ጭምር ብናሳዉቅም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አጋጣሚዉን ለራሳቸዉ የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ እያደረጉት ነዉ፤በሀገሪቱ ለተፈጠሩ የስራ አጥነትና ወንጀል ድርጊቶች ተጠያቂዎቹ ስደተኞች ናቸዉ በሚል እየቀሰቀሱ ጥቃቱ እንዲባባስ እያደረጉ ይገኛል ሲሉ ነዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ቀደም ሲልም ይህን መሰል ድርጊቶች አልፎ አልፎ ያጋጥም የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዋና ዋና ከተሞች በሚባሉት ፕሪቶሪያ፣ጆሃንስበርግ፣ አሌክሳንደሪያና ሌሎችም ታላላቅ ከተሞች ጭምር መከሰቱ ችግሩ የከፋ እንደሆነ ማሳያ ነዉ ይላሉ፡፡
አስተያየት ሰጭዎቹ እንዳሉት መንቀሳቀስ ይቅርና ቤትና ሱቆች ዉስጥም ተቀምጠን ችግሩን ልናመልጥ አልቻልንም፤ለእስር እየተዳረግንና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየተፈጸመብን በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ የምናገኝበትን መንገድ ይፍጠርልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየሰራ ነው ጉዳዩንስ ያውቀዋል ሲል ጠይቋል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸዉ እንደነገሩን ችግሩን እናዉቃለን፤በዚያዉ በሚገኘዉ ኤምባሲያችን በኩል ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነዉ ብለዋል፡፡
ዜጎቻችንም ችግሩ በዋናነት በሚታይባቸዉ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡና እዛዉ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ጋር ቢነጋገሩ መልካም ነዉ የሚል ምላሽን ሰጥተዋል፡፡
አስተያየት ሰጭዎቹ በበኩላቸዉ ኤምባሲዉ የተቻለዉን እያደረገላቸዉ መሆኑን ገልጸዉ፤ነገር ግን ችግሩ የከፋ በመሆኑ መንግስት ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ስራ እንዲሰራላቸዉ ጠይቀዋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ናይጀሪያ የዜጎቿ ደህንነት የማይጠበቅላት ከሆነ ደቡብ አፍሪካዊያንን ከሀገሯ እንደምታስወጣ ጠንካራ አቋም መያዟንም አስተያየት ሰጭዎቹ ነግረዉናል፡፡