YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሳምሰንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ እንዲሰማራ ጠየቁ።

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በደቡብ ኮሪያ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአገሪቱ ፕሬዘዳንት ሙንጃኒን ጋር በአራት ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት በአካባቢ ጥበቃ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጅ፣ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም እና በቪዛ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳምሰንግ ምክትል ፕሬዚዳንት ዎን ኪዮንግ ጋርም ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱም ኩባንያቸው ኢትዮጵያን አንደኛው መዳረሻው ባደረገ መልኩ ለመስራት እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ወደ ደቡብ ኮሪያ እንዲሁም የደቡብ ኮሪያን ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ ደቡብ ኮሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ ቪዛ ሳይጠየቁ መግባት እንዲችሉ አገራቱ ተስማምተዋል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲን የአቅም ግንባታ ስራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ፈጽመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአስካሁኑ የደቡብ ኮሪያ ቆይታቸውም በደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር የተወያዩ ሲሆን በኮሪያ ጦርነት ወቅት ለተሰው መታሰቢያ በሆነው መቃብር ስፍራ ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

Via:- #የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ነው
@YeneTube @FikerAssefa