ሶማሌ ክልል ‼️
የሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር ከክልሉ ተፈናቅለዉ የነበሩ #ከ250ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን ወደየቀያቸዉ መልሶ #ማቋቋሙን የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር #አስታወቁ።
ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የኢትዮጵያ የንግድ ባንክ የሰጠዉን ርዳታ ትናንት ሲቀበሉ እንዳሉት መስተዳድራቸዉ ተጨማሪ ተፈናቃዮችን ወደየቀያቸዉ እየመለሰ ነዉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች መርጃ የለገሰዉን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የባንኩ ፕሬዝደንት ባጫ ጊና ለአቶ ሙስጠፋ አስረክበዋል። የሶማሌ ክልልን ባለፈዉ አንድ ዓመት ባወከዉ ግጭት #ከ6_መቶ 65 ሺሕ በላይ ሕዝብ #ተፈናቅሏል።
አሁን ወደየቀያቸዉ የተመለሱትና ያልተመለሱት ተፈናቃዮች የነበሩበትም ሆነ ያሉበት ሥፍራ በግልፅ አልተነገረም። ንግድ ባንክ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መርጃ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር መለገሱን ፕሬዝደንቱ አስታዉቀዋል።
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa