የኒፕሲ ሐስል ገዳይ ተያዘ!
በአባቱ #ኤርትራዊ እንደሆነ የተነገረው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ #ኒፕሲ_ሐስልን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብን ፖሊስ #መያዙን አስታወቀ።
ባለስልጣናት እንዳሉት ኤሪክ ሆልደር የተባለው ግለሰብ ከእሁድ ዕለቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ በፖሊስ ሲፈለግ ነበር። ኒፕሲ ሐስል በተሰነዘረበት ጥቃት የተገደለው የእራሱ በሆነው የልብስ መደብር አቅራቢያ ነበር።በጥቃቱ ሌሎች ሁለት ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እሁድ ዕለት በተከፈተበት ተኩስ የተገደለው የራፕ ሙዚቀኛው ኒፕሲ ሐስልን ለማሰብ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ አድናቂዎቹ የተገኙ ሲሆን በስፍራው በተፈጠረ መጨናነቅ ቢያንስ 19 ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።
ትክክለኛ መጠሪያው ኤርሚያስ ዳቪድሰን አስገዶም የሆነው ኒፕሲ ሐስል በደቡባዊ ሎስአንጀለስ ውስጥ ያደገ ሲሆን በታዳጊነት እድሜው የአንድ የጎዳና ላይ የወሮበሎች ቡድን አባል ነበረ።
በኋላ ላይ ግን ከቡድኑ በመውጣት በዙሪያው ያለን ማህበረሰብን ማስተባበርና መርዳት ጀምሮ በጥበብ ሥራዎች ውስጥም አስተዋጽኦን ሲያበረክት ቆይቷል።ከመገደሉ ቀደም ብሎ በትዊተር ገጹ ላይ “ጠንካራ ጠላት ካለህ መባረክ ነው” ሲል አስፍሮ ነበር።
ምንጭ፡BBC
@YeneTube @FikerAssefa