YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መከላከያ~ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️

ወታደራዊ መለዮ እየለበሱ ዝርፊያ እና ውንብድና በሚፈጽሙ አካላት ላይ #እርምጃ እንደሚወስድ 33ኛ አባይ ክፍለ ጦር አስጠነቀቀ።

ክፍለ ጦሩ በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስተካከል ከሕዝቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

የ33ኛ አባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #ዓለሙ_አየነ ሠላምን ለማስፈን በሁለቱም ዞኖች ከ37 ሺህ በላይ ሠዎችን ማወያየታቸውን ተናግረዋል። እርቅና መግባባት ላይም ተደርሷል ነው ያሉት።

በቤት ዝርፊያ እና በሌሎች የውንብድና ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሰላምን ሲያሳጡ የነበሩ 76 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ታውቋል።

እስካሁንም በቡድንና በግል ሆነው በቤት ዝርፊያ እና በሌሎች የውንብድና ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሰላምን ሲያሳጡ የነበሩ 76 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጀነራል ዓለሙ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa