#የሃሳብ_ልዩነት መጨረሻ #የሰከነ_ውይይት ሊሆን ይገባል‼️
ዛሬ ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር ፍሬያማ የሆነ ውይይት አድርገናል። ባለፈው ካወጣሁት ፅሁፍ ጋር በተያያዘ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ግልፅ የሆነ ውይይት አድርገናል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየቴን በነፃነት መግለፄን በማድነቅ አበረታተውኛል።
በቀጣይም በከተማ መስተዳደሩ ሆነ በሌሎች የመንግስት አካላት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመንቀስና በመተቸት ትኩረት እንዲያገኙና ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የጀመርኩትን ጥረት አጠናክሬ እንድቀጥል መክረውኛል። እኔ በበኩሌ የከንቲባው የመኖሪያ ቤት ኪራይን ጨምሮ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በማንሳት ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ለወደፊት ማንኛውም ዓይነት ጥያቄና አስተያየት ሲኖረኝ በስልክ ሆነ በአካል ተገኝቼ መረጃና ማብራሪያ መጠየቅ እንደምችል አረጋግጠውልኛል።
የሃሳብና አመለካከት ነፃነትን አክብሮ በቀናነት የመወያየት ልማድ በሁሉም ዘንድ ሊዘወተር የሚገባ ነገር ነው። የተለየ ሃሳብና አስተያየት በሰጠሁ ቁጥር በሰከነ መንገድ ከመወያየትና ሃሳብ ከመለዋወጥ ይልቅ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያዘንቡ ለሚውሉ ጭፍን ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ይሄ ጥሩ ማሳያ ነው። የሃሳብ ልዩነት መጨረሻ የሰከነ ውይይት እንጂ ዛቻና ማስፈራራት መሆን የለበትም።
ምንጭ:- ስዩም ተሾመ
@YeneTube @FikerAssefa