ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ዮናስ አማረ ያሉበትን ሁኔታ መንግስት በግልፅ እንዲያሳውቅ ኢዜማ እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጠየቁ!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር፤ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ “ከሕግ አግባብ ውጪ መሰወራቸውን” በመግለጽ ያሉበትን ሁኔታ መንግስት በግልፅ እንዲያሳውቅ በተናጥል ባወጡት መግለጫ ጠየቁ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበርም በበኩሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ "ጋዜጠኞቹ በወንጀል ተጠርጥረው ቢሆን እንኳን በሕግ አግባብ ተይዘው በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ያሉበት አለመታወቁ በእጅገ ያሳስበናል" ብሏል።
ኢዜማ በበኩሉ፤ "በመንግሥት በኩልም በተደጋጋሚ ያለአግባብ ያሠርኩት ጋዜጠኛም ሆነ ዜጋ የለም የሚል ምላሽ ሲሰጥም ተመልክተናል" ሲል ጠቅሶ፣ “መንግሥት ድርጊቱን እየፈፀመ እየደበቀው ወይም ከመንግሥት እውቅና ውጪ በሌሎች የተደራጁ አካላት እየተፈፀመ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa

❤23👀4👍3
በምዕራብ ትግራይ ወደ ቀያቸው በተመለሱ ተፈናቃዮች ላይ የመንግስት ወታደሮች ተሳታፊ የሆኑበት ግድያ እና አፈና እየተበራከተ ይገኛል ሰል ህወሓት አስታወቀ!
ወደ ቀያቸው በተመለሱ የምዕራብ ትግራይ ጸለምት ወረዳ ተፈናቃዮች ላይ “የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊት ተሳታፊ የሆነበት ግድያ እና እገታ እየተበራከተ ነው” ሲል ህወሓት ከሰሰ።
በምርጫ ቦርድ ምንም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ የተላለፈበት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ነሃሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫው፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ከለላ እሰጣችኋለሁ ብሎ እንዲመለሱ ባደረጋቸው የጸለምት ነዋሪዎችን ሊከላከልላቸው አልቻለም" ሲል ተችቷል፤ “ከሌሎች ታጣቂዎች ሊከላከልላቸው ይቅር እና እራሱ ተሳታፊ ሆኗል” ሲል ገልጿል።
“በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ባሳለፍነው ሳምንት በማይጸብሪ የተፈጸመው ግድያ የቅርብ ማሳያ ነው” ሲል በመግለጫው አመላክቷል።

❤14😭3👀2👎1
Forwarded from Nati Getnet
ናቲ ስፒች ላንጉጅ ቴራፒ ኪሊኒክ
Nati Speech language therapy clinic
ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?
እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ
“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”
👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52
👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19
👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉 የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY
👂👂በነፃ
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ

❤1
በአዲስ አበባ ቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች እየታሸጉ መሆኑ ተነገረ
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታሸጉ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ እነዚህ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ፣ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ይህ መታሸግ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋለ ቢሆንም፣ በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የሚገኙ በርካታ የቢንጎ ቤቶች በዛሬው ዕለት መታሸጋቸው ካፒታል ተመልክቷል።
አንዳንድ የጨዋታ ቤቶቹ ባለቤቶች እንደተናገሩት፣ መታሸጉ የተፈጸመው “አዋኪ ድርጊት” ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ነው። በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እነዚህ አጫዋቾች፣ እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ምንም እንኳ እነዚህ ቤቶች ዋነኛ ተግባራቸው የቢንጎ ጨዋታ ማቅረብ ቢሆንም፣ ከጨዋታው በተጨማሪ የጫት መጠቀሚያ እና ለህገወጥ ወንጀሎች መነሻ ቦታዎች እንደሆኑ እና ይህንንም መንግስት ለማስቆም በሚል እርምጃውን እየወሰደ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
በተለይ በአዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በስፖርት ውድድር ላይ የሚደረጉ የውርርድ (ቤቲንግ) ጨዋታዎችን ከማሸግ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንዲገኝ የሚታወቅ ሲሆን አሁን የቢንጎ ቤቶች መታሸግ ከዚህ ጋር ግንኙነት ያለው ስለመሆኑ ግን እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር የለም።

❤16👍3