YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
1
ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ!

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡ 

በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።

ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።

ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍2925😁8
ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ 541 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈጽሚያለሁ አለ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ አንድ ሺ 140 ለሚሆኑ ደንበኞቹ 541 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈጽሚያለሁ ሲል ገለጸ።

ከሐምሌ 22 እስከ ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአጠቃላይ ለባንኩ አንድ ሺ 140 ደንበኞች 541 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ፈቅጃለሁ ሲል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

በአንድ ቀን ብቻ ማለትም ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞች ማመልከቻዎችን ሁሉንም ማጽደቁን የጠቆመው ባንኩ በዚህም የ420 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች መፍቀዱን አመላክቷል።

ባንኩ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ ከአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ መፈጸሙንም አስታውቋል።

ይህም የተሰጠው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ የተሰጠ መሆኑን ጠቁሟል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
17😁10