ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ከግዢ ዋጋ በላይ የሚሸጡባቸው ሀገራት ኢትዮጵያ እና ስሪላንካ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ!
የተሽከርካሪዎች ዋጋ በዓለም ዙሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሲሄድ፣ በኢትዮጵያ እና ስሪላንካ ግን በተቃራኒው ያገለገሉ መኪናዎች ከገዙበት ዋጋ በላይ ይሸጣሉ።እንደ መረጃዎች ከሆነ ሁለቱ ሀገራት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለዓመታት ከተጠቀሙባቸው በኋላም እንኳ ከገዙበት ዋጋ በላይ የሚሸጡባቸው ብቸኛ ሀገራት ናቸው።
የግሎባል ፌዴሬሽን ኦፍ ስሪላንካ ቢዝነስ ካውንስልስ ዋና ጸሐፊ ሳጂቭ ክሻትሪያ ራጃፑትራ እንደተናገሩት ፣ ይህ ሁኔታ ሰዎች በመጨረሻ ጥቅም ላይ የማይውሉ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ብዙ ገንዘብ እንዲያወጡ እንደሚያደርግ እና በመጨረሻም ብረት ክምር ብቻ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ይህን ችግር ለመፍታት ስሪላንካ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ውጭ በመላክ፣ ከሽያጩ የሚያገኘውን ትርፍ ደግሞ የአዲስ ተሽከርካሪዎችን የማስመጣት ግብር ለመቀነስ ልትጠቀምበት እንደምትችል ጠቁመዋል።
በአሁኑ ጊዜ ስሪላንካ ተሽከርካሪዎች ላይ እስከ 300 በመቶ ግብር ትጥላለች፣ በአገር ውስጥ ደግሞ ያገለገሉ መኪናዎች ዋጋ ከመጀመሪያው የግዢ ዋጋ እስከ ሦስት እጥፍ ከፍ ሊል እንደሚችል ተጠቁሟል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

❤33😁25
ናቲ ስፒች ላንጉጅ ቴራፒ ኪሊኒክ
Nati Speech language therapy clinic
ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?
እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ
“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”
👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52
👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19
👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉 የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY
👂👂በነፃ
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ

❤10
YeneTube
Photo
ሶማሊያ ከአልሸባብ ጋር ሠርተዋል ያለቻቸውን ሁለት ወታደሮች በሞት ቀጣች!
የሶማሊያ የመከላከያ ሠራዊት ፍርድ ቤት ለሁለት አስርት ዓመታት የቀጠናው የደኅንነት ስጋት ሆኖ ከቆየው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ሁለት የሀገሪቱ ብሄራዊ ጦር ሠራዊት አባላት ላይ የሞት ቅጣት ውሳኔን አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ "የጦር ሠራዊት አባላቱ ለአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን መግደል፤ ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር በቅርበት ሰርተዋል" ሲል ነው በትናንትናው ዕለት ውሳኔውን ያስተላለፈው።
የሞት ፍርድ ውሳኔው ግድያው በተፈፀመበት ቦታ ላይ የተላለፈም ሲሆን፤ ይህም ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ለሚሰሩ መሰል ወታደሮች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የተደረገ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
'የኦክቶበር 14ኛ ሻለቃ ጦር' አባላት የሆኑት ሞሃመድ ሁሴን ቡሌ እና አዳን ኢሳቅ ያሮው የተባሉት ተከሳሾች፤ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በጋራ በመስራት የ83ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆኑት ሴይዲ መሀመድ አሊ ለተገደሉበት ጥቃት ተጠያቂ ተደርገዋል።
ጦር አዛዡ በሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ውስጥ ከፍተኛ መኮንን የነበሩ ሲሆን፤ የተገደሉት በአልጋቸው ሥር በተጠመደ ፈንጂ መሆኑን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
የወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ከአልሸባብ ጋር ሲሰሩ መገኘታቸውን የገለጸ ሲሆን፤ ስለ ኦክቶበር 14 ብርጌድ ጠቃሚ መረጃ ለአልሸባብ በመስጠት ጦሩን አደጋ ውስጥ መክተታቸውንም ገልጿል፡፡
"ይህ ከወታደራዊ ፕሮቶኮሎች ጋር የሚጋጭ ነው" ሲል ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ያስታወቀ ሲሆን፤ በሶማሊያ ወታደራዊ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት በወታደሮቹ ላይ የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸም ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተዳከመበት ተነቃቅቶ በሶማሊያ ከባባድ ጥቃቶችን በመፈጸም ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተነጥቆ የነበረባቸውን ቦታዎችም መልሶ በመቆጣጠር ለሀገሪቱ እና ለቀጣናው እንደ አዲስ ስጋት እየሆነ መምጣቱ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

❤19
YeneTube
Photo
ኢትዮጵያና አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ለመቆጣጠር መምከራቸው ተገለጸ!
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ህገወጥ ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ማስተላለፊያ ግብይቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናከርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል ተብሏል።በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ባንኩ አስታውቋል፡፡
ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም አራት ተቀማጭነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚሰበስቡት ገንዘብ አማካኝነት በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ የማስመሰል እና ሕገወጥ ተግባራትን በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል ሲል በይፋ ከከሰሰ በኋላ ነው።
እነዚህ ኩባንያዎች ሸገይ ገንዘብ አስተላላፊ፣ አዱሊስ ገንዘብ አስተላላፊ፣ ራማዳ ፔይ እና ታጅ ገንዘብ አስተላላፊ ሲሆኑ የሚገኙትም በቨርጂኒያ እና ሚኒሶታ ግዛቶች ነው። ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል ታጅ ገንዘብ አስተላላፊ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 የ'ዩ.ኤስ. ባንክ ሴክሬሲ አክት' ን በመጣስ ጥፋተኛ እንደሆነ ማመኑን በዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ ካሊፎርኒያ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት መግለጫ ያመላክታል።
ይሄን ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢ-መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸው ይታወሳል።
አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ታማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል።
በዚህም የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት "ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች" የባንክ ሒሳብ ማገዱን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

❤13😁6👎2👍1