YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል አዋጅ ማሻሻያ በምክር ቤቱ ፀደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው በ2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው አፀደቀ።

የታገደ የፖለቲካ ፓርቲ እገዳው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜያት ከማንኛውንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ በየትኛውም ደረጃ በሚደረግ ምርጫ ላይ እንዲሁም በጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ መሳተፍ ይከለክላል። ከመንግስት ከሚሰጥ ደጋፍ ተጠቃሚም አይሆንም።

በጸደቀው አዋጅ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡ የወላይታ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አመራሩ ጎበዜ ጎኣ “ምርጫ ቦርድ አሻሻሎ ባስጸደቀው ህግ ገዢው ፓርቲ ብቻውን ቢወዳደር እንጂ ሌላው ሰው የሚወዳደርበት ምንም አይነት ሜዳ የለም” ብለዋል። “ፓርቲዎችን ከምርጫ ሜዳ የሚያስወጣ ነው” ሲሉም ተችተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁208👎1