YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
2
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሁለት ኮሚሽነሮች የሥራ ዘመናቸው ሳይጠናቀቅ መልቀቂያ አስገቡ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና የተቋቋሙ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተገለፀ።

የከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ የሥራ መልቀቅ ከአዲሱ ዋና ኮሚሽነር "የአመራር ስልት" ጋር በተያያዘ "ተገፍተው" እንደሆነ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"አሳታፊነትን" ይከተል የተነበረው የተቋሙ አሠራር ባለፉት ወራት ለሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ ውሳኔዎቹን "አለማሳወቅ፣ አለማሳተፍ እና መመካከርን" ወደ ጎን ማለቱ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መልቀቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አሳታፊነት በኮሚሽኑ "አደረጃጀት" ላይ የተመሠረተ እንደነበር ያነሱት የቢቢሲ ምንጮች፤ ተቋሙ ባለፉት ወራት ያለ ምክክር እና እውቅና ሠራተኞቹን ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ መመደብ እንዳለ አመልክተዋል።

ይህን የአመራር ስልት "ለሰብዓዊ መብት የማይሠራ" ያሉት ምንጮቻችን፤ ባለፉት ስድስት ወራት "ያለ ምክንያት" አምስት ዳይሬክተሮች የሥራ መደብ ላይ ሽግሽግ መደረጉን መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ኮሚሽነሮቹ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መልቀቂያ ማስገባታቸውንና የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠታቸውን ተገልጿል።ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ ሰኔ 18/2013 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ልዩ ጉባኤ የተሾሙ ሲሆን፣ ተቋሙ ባካሄደው ለውጥ ስማቸው ይነሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
21
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እነዚህን ውሳኔዎች ወስኗል፦

1ኛ በሁሉም የሊግ እርከን የሚገኙ ክለቦች በ2018 የውድድር አመት ምዝገባ ወቅት የክለብ ስያሜያቸው ከብሔር ስም ጋር የተገናኘ ከሆነ በመቀየር ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ ክለቦች በኦፊሴላዊ መለያ (አርማ) ላይ ፖለቲካዊና የብሔር ይዘት ያላቸው መልዕክቶችና ምስሎችን መጠቀም የተከለከለ ነው ሲል አሳስቧል፡፡

👉በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ስም ሊያስተካክሉ የሚችሉ ክለቦች መካከል፦

መቐለ 70 እንደርታ
ሀድያ ሆሳዕና
ወላይታ ድቻ
ስሁል ሽረ
ሲዳማ ቡና
👉ኦፊሴላዊ መለያ (አርማ) ሊቀይሩ የሚገደዱ ክለቦች መካከል፦

ስሁል ሽረ
ፋሲል ከነማ አርማቸውን ሊቀይሩ ይገደዳሉ፡፡

እናንተስ ምን ትላላችሁ?
37👍21🔥1
አከራካሪ የነበረው ግብር የማይከፈልበት የደመወዝ መጠን ማሻሻያ ሳይደረግበት 2 ሺሕ ብር ሆኖ ጸደቀ

አዋጁ ዓመታዊ ግብር መሰብሰቢያ ጊዜ በየሩብ ዓመቱ እንዲሆን የሚደነግግ አንቀጽ ተካቶበታል

ሐምሌ 600 ብር የነበረው ግብር የማይከፈልበት ከደመወዝ የሚገኝ ገቢ እንዲሻሻል ጥያቄ እየቀረበበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴርም ሥራ ላይ ከዋለ 9 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የገቢ ግብር አዋጅ እንዲሻሻል ረቂቁን አዘጋጅቶ ሊሚኒስቴሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም በረቂቁ ላይ ከተወያየበት በሗላ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኮታል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ከተካተቱ አከራካሪ ጉዳዮች መካከል ከግብር ነጻ የሚደረገው ከደመወዝ የሚገኝ ገቢ 2 ሺሕ ብር እንዲሆን የሚደነግገው አንቀጽ አንዱ ነው፡፡

ድንጋጌው በረቂቅ አዋጁ ላይ በተካሄደ ውይይት ወቅት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከበርካታ ሰዎች ተቃውሞ ቢገጥመውም፤ በዛሬው ዕለት ማሻሻያ ሳይደረግበት 2 ሺሕ ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

በአዋጁ አንዳንድ ድንጋጌዎች እንዲሻሻሉ ሐሳብ ከሰጡ የምክር ቤት አባላት መካከል ደሣለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ይገኙበታል፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ "አዋጁ የሰራተኞችን የኑሮ ጫና ያላገናዘበ ነው" የሚል ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም "ከድህነት ወለል በታች ካለ አንድ ሠራተኛ ግብር መሰብሰብ ሰብዓዊነት እና ርህራሄ የጎደለው አዋጅ ነው" ብለዋል፡፡

የገቢ ግብር ማሻሻያ አንዱ ዓላማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያለባቸውን የግብር ጫና መቀነስ እንደሆነ በረቂቁ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ በክልልና በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ባሉ አስተዳደሮች ከፍተኛ ገቢያቸው ከደመወዝ የሚያገኙት ግብር በመሆኑ መነሻው ከፍ ባለ ቁጥር ገቢያቸው እንደሚያሽቆለቁል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስር ድኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ለኅብረተሰቡ የሚቀርበውን አገልግሎትም አደጋ ውስጥ ይከተዋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም በክልሎች የሚገኘውን ገቢ እንዳያሳጣ ተብሎ መዘጋጀቱን ተገልጿል፡፡

ይህንን በሚመለከት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ የቋሚ ኮሚቲው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ምላሽ ሲሰጡ እንደገለፁት፤ "2 ሺሕ ብር የሚለው መንግሥት ማግኘት የነበረበትን 38 ቢሊዮን ብር እንዲያጣው ተድርጎ ነው" ብለዋል፡፡

ሌላው ጥያቄ የተነሳበት የአዋጁ ክፍል "ዓመታዊ የገቢ ግብር አሰባሰብ በሩብ ዓመት እንዲሆን መቅረቡ መጨናነቅን ከመፍጠርም በላይ በዓመቱ መጨረሻ ሊከስር ይላል" የሚሉት የምክር ቤት አባሉ ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ፤ ይህ መስተካል አለበት የሚል ጥያቄም አንስተዋል፡፡

ይህንን በሚመለከት ከገንዘብ ሚኒስትር እና ከቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡

በሩብ ዓመት መሆኑ ታክስ አስተዳደር ስርዓቱን የሚያስተካልና የነጋዴውንም ጫና የሚያቀል መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"ይህ አዋጅ በጀት ሲጸድቅ የጸደቀ ነው" የተባለ ሲሆን፤ የገቢ ማሰባበቢያውን ማሳካት የሚያስፈልግ በመሆኑ ከሀምሌ ጀምሮ ወደ ስራ እንደገባ ለማስቻል የታሰበ መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ተብሏል።

ይህ አዋጅ ከሰሞኑም ውይይቶች የተደረጉበት ቢሆንም ጥያቄ ያስነሱት ከግብር ነፃ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የመሰሉ ጉዳዮች ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግባቸው አዋጁ በስድስት ተቃውሞ በ12 ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👎6133👍1😭1
"የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ "የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" ሲሉ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንንያሉት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን ትላንት ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ አንድሪው ምቦጊሪን ጋር በነበራቸው ቆይታ “ያለ ደህና መጠለያ እና ምግብ ተጥለው በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለአምስተኛ የክረምት ወራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ህይወታቸውነ እያሳለፉ ማየት በጣም ከባድ ነው” ሲሉ መናገራቸውን ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን በበኩላቸው በክልሉ በተካሄደው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎችን ተቋማቸው ተቀብሎ መጠለያ እና ምግበ እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውሰው በቀጣይ በሚደረገው የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ይሁን በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን መረጃው አካቷል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
34👀3
ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል አዋጅ ማሻሻያ በምክር ቤቱ ፀደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው በ2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው አፀደቀ።

የታገደ የፖለቲካ ፓርቲ እገዳው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜያት ከማንኛውንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ በየትኛውም ደረጃ በሚደረግ ምርጫ ላይ እንዲሁም በጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ መሳተፍ ይከለክላል። ከመንግስት ከሚሰጥ ደጋፍ ተጠቃሚም አይሆንም።

በጸደቀው አዋጅ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡ የወላይታ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አመራሩ ጎበዜ ጎኣ “ምርጫ ቦርድ አሻሻሎ ባስጸደቀው ህግ ገዢው ፓርቲ ብቻውን ቢወዳደር እንጂ ሌላው ሰው የሚወዳደርበት ምንም አይነት ሜዳ የለም” ብለዋል። “ፓርቲዎችን ከምርጫ ሜዳ የሚያስወጣ ነው” ሲሉም ተችተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁2518👎2
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
👍31
ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው፣ "የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያልያዙ ፖሊሶች" ቢሸፍቱ ከተማ ከሚገኘውና ከአገር ከመውጣታቸው በፊት ለ10 ዓመት ከኖሩበት ቤት በ10 ቀናት ውስጥ እቃቸውን እንዲያወጡ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ቤቱ ላይ ለጥፈው እንደሄዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን ባሠራጩት መረጃ አስታውቀዋል።

ደብዳቤው፣ ቤቱ "ለማኅበራዊ ፖሊስ" አገልግሎት እንደሚፈለግ የሚገልጽ መሆኑን ልደቱ ገልጸዋል። ልደቱ፣ በ10 ቀናት ውስጥ ቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ካልወጣ፣ ፖሊስ ርምጃ እንደሚወስድ በደብዳቤው ላይ ማስጠንቀቁንም ጠቅሰዋል።

የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ የያዘውን ደብዳቤ የጻፈው፣ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሆራ አርሰዴ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደኾነም ልደቱ ገልጸዋል።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa
😁3118👎13😭21
በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ ከፈተ።

በተጨማሪም ፓርቲድ የመቐለ እና ደቡባዊ ምስራቕ ዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቷል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ በመክፈት የፓለቲካ ስራውን በግልፅ ጀምሯራ።

ፓርቲው በሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳና ከተሞች ፓለቲካዊ ፅህፈት ቤቶች መክፈት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ከአንድ ወር በፊት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ  የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ ለምስረታ ብቁ የሚያደርጉት አባላት መልምሎ ጨርሷል።

የክልል ፓርቲ ለመመስረት የሚስፈልገው 4 ሺህ በላይ መስራች አባላት መልምሎ ለይፋዊ ምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮቹ ተናግረዋል።

ስምረት ፓርቲ በቀጣዩ የነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ ይፋዊ ምስረታ በማከናወን ከቅድመ እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና እንደሚሸጋገር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@Yenetube
28👍1
ሰበር

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአለልኝ ባለቤት እና የባሌቤቱ እህት ባልን በተጨዋቹ ሞት ጥፋተኛ ናቸው ብሎ ወስኗል::

ፍርድ ውሳኔውን ለመስማት ለከሰዓት ቀጠሮ ታይዟል::

አለልኝ አዘነ ራሱን አጥፍቶ አልሞተም!

ሸገር ስፖርት
44👍16😭61
ጠ/ሚኒስትሩ ከትግራይ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ!

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፤ ምክክሩ በተፈናቃዮች፣ በትግራይ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን መቅረፍ በሚቻልበት መንገድና የትግራይን ማገገምና ወደ መደበኛ ህይወት መመለስ በተመለከት ከተወካዮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1311👎11🔥2
ለተቀጣሪ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲኖር ማድረግ እንደ አንድ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ እየታየ ነው ተባለ።

ከኢትዮጵያ ምርቶችን የሚገዙ የአውሮፓ ሀገራት እና አሜሪካ ጉዳዩን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ እያቀረቡት እንደሆነ ተጠቅሷል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በኢትዮጵያ በህግ እንዲወሰን ካልተደረገ እነዚህ ሀገራት ምርቶችን ከኢትዮጵያ መግዛት ሊያቆሙ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ባዘጋጀው አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ሲነገር ሠምተናል።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ዛሬ ሲኤምሲ በሚገኘው መስሪያ ቤቱ ማካሄድ የጀመረው አለም አቀፍ ጉባኤ እስከ ነገ ይቆያል።

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ የተዘጋጁ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበውም ተሳታፊዎች እየተወያዩባቸው ነው።

ማህበሩ እንዲህ አይነቱን አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለ22ኛ ጊዜ እንደሆነ ሠምተናል።

ከ34 ዓመት በፊት የተመሠረተው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር አሁን ከስድስት ሺህ በላይ አባላት አሉኝ ብሏል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
53👍1
በአፋር ክልል መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሲጎዱ ከ1 ሺህ 800 በላይ ቤቶች ተቃጠሉ!

በአፋር ክልል ዳሎል ወረዳ ትናንት ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት አከባቢ በደረሰ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱንና 1 ሺህ 805 ቤቶች መቃጠላቸውን የዳሎል ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን አሕመድ ገለጹ።

በአደጋው በበዳ-አድሙሩግ ቀበሌ 600 ሱቆች፣ 950 ምግብ ቤቶች እና 255 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ኃላፊው ለኢቢሲ ተናግረዋል።በተጨማሪም ከ20 በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት በእሳት አደጋው መሞታቸውን ገልጸው
ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።

አክለውም በክልበቲ ረሱ ዞን የሚገኘው የአብኣለ እና በራህሌ ሆስፒታል ባለሙያዎች በአከባቢው በመገኘት የሕክምና ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የተነሣውን እሳቱ እስካሁን ድረስ ማጥፋት አለመቻሉ የተገለጸ ሲሆን በአደጋው ቤት ንብረት የወደመባቸው የቀበሌዋ ነዋሪዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
17😭16👍1
Spiritual Gift መንፈሳዊ ስጦታ
YAHO💚 WOMEN'S GIFT PACKAGE
- ነጠላ
- ዉዳሴ ማርያም
- የሚያበራ ምስል 
- ሽቶ
FREE DELIVERY

⨳ዋጋ 3500br

For order @Fikerassefa
10😁5
ማስታወቂያ

በZoje Digital slightly Used ማሽን interlock, Overlock, Single needles machine ያላቹ በዚህ @Fikerassefa ያናግሩን።
6