YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሞስኮን ከምድረ ገጽ የሚያጠፋ መሳሪያ ልንልክ ነዉ ! /ትራምፕ /

የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን ከዩክሬን ጋር ካልተደራደሩ ሩሲያ በታሪኳ አይታዉ የማታዉቀዉ መአት እንደሚወርድባትና ከባድ መዘዞችን እንደሚገጥማት ማስጠንቀቃቸው ተነገረ ።

ዶናልድ ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲንን የሰላም ስምምነቱን ካልተቀበሉ ለዩክሬን ሞስኮን ማጥፋት የሚችሉ ኃይለኛ የመርከብ ሚሳኤሎችን እንደሚያስታጥቋት ዝተዋል።

ፑቲን በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ድብደባ ማድረጋቸውን በመቀጠላቸዉ የተናደዱት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ የሚጠቀሙባቸውን “የላይኛው መስመር ጦር” ወደ ኪየቭ ለማሰማራት ለመላክ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

ለሳምንታት በዩክሬን ላይ የቦምብ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ፑቲንን ወደ ድርድር ለመመለስ ትራምፕ በጦር መሣሪያ ቤታቸው ውስጥ ያለውን “ሁሉንም ነገር” የሚያበላሽ የጦር መሣሪያ ለመላክ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩክሬንን ለመርዳት እምብዛም ጥቅም ላይ ያልዋሉትን ሎክሂድ ማርቲን መሳሪያዎችን ለማቅረብ እያሰቡ ነው ተብሏል።

ወደ ዩክሬን ለመላክ ከታቀዱት የጦር መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ የአሜሪካ የጋራ ከአየር ወደ ላይ የሚቆም ክሩዝ ሚሳኤሎች መታጠቅ የሚችለዉ ከ155 ማይል - 75 ማይል ርዝመት ያለው (JASSM) የዉጊያ ጀት ሲሆን ይህ አሜሪካ በተለያዩ አዉደ ዉጊያዎች በማሰማራት ከምትታወቅበት ጀቶች መካከል ቀዳሚዉ መመኪያዋ የሆነ ጀት እስከ 230 ማይል የሚደርስ ክልል የማጥፋት አቅም ያለው እና 450 ኪሎ ግራም የጦር ጭንቅላት የታጠቀ ነው።

ጀምስ ጀቶች በዝቅተኛ ከፍታ ላይ መብረር ስለሚችሉ እጅግ በጣም ጥሩ ራዳር-ማምለጥ ችሎታቸውም የተመሰከረላቸው ናቸዉ ።

በጥቅሉ አሜሪካ ለዩክሬን ለማድረግ ያሰበችዉ $74 billion ወታደራዊ ድጋፍ መካከል ከዩክሬን ድንበር ቢወንጨፉ ቢያንስ 30 የሩሲያ አየር ማረፊያዎችን የማጥፋት አቅም እንዳላቸዉ የሚነገርላቸዉ ከአየር ላይ ወደ አየር የሚተላለፉ የአርበኞች ሚሳኤል ሲስተሞች እና ባትሪዎች ጀቶችንና ሌሎች መሳሪያዎች ይገኙበታል ተብሏል።

ዩክሬንን እያሳየችዉ ያለዉን 'ታላቅ ድፍረት' ያወደሱት
ትራምፕ ቮልዲሚር ዜለንስኪ ኪየቭ የሩስያን ሁለቱን ታላላቅ ከተሞች በአሜሪካ ፋየር ልትመታ ትችል እንደሆነ ጠይቀው እንደነበርም ተነግሯል። ሲል የዘገበው ሲቢሲ የዜና ወኪል ነዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ
@Yenetube @Fikerassefa
52😁34👎7👀2👍1
Forwarded from YeneTube
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት እሽቅድድም የማይደረግባቸው ዘርፎች አልነበረም ማለት ይቻላል። ከፉክክሮቹ አንዱ የሆነው ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። የጠፈር እሽቅድድም ደግሞ ከነዚህ ሁሉ ታዋቂው ነው። ይሁን እንጂ ብዙ የማትሰሙትና ከጠፈር በተቃራኒ የተጀመረ ፕሮጀክት ነበረ። አላማው በተቻለ መጠን በጥልቀት መቆፈር። ይህ ፕሮጀክት ሁለት አስርት አመታትን የፈጀ ሲሆን ምን ምን ተገኙበት? ምን ያህል መቆፈር ተቻለ እና ለምን ቁፋሮው ቆመ የሚለውን እናያለን።

ፕሮግራሙን ከመጀመሮ በፊት ቪዲዮውን ላይክ እና ሼር ቻናሉንም ሰብስክራይብ ያድርጉ

https://youtu.be/4N3QkwkO7Ms
20👎1
Forwarded from YeneTube
ፒያሳ የመጨረሻው ሱቅ እና ቤት ሽያጭ ❗️

ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች

* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው

* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው

* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

ቴምር ሪልስቴት.......
  
ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ +251976195835

በዋትሳፕ ያገኙናል -

https://wa.me/251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

https://www.facebook.com/share/1ABkH3oH9x/
6
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
1
የሽሮ ምርት ጥራቱን ጠብቆ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ የተዘጋጀው ደረጃ መጽደቁ ተገለጸ!

የሽሮ ምርት ለውጭ ሀገር እና ለሀገር ውስጥ ገበያ ሲቀርብ ሊከተል የሚገባውን የአመራረት ሂደት፣ የማሸጊያ ደህንነት፣ ምርቱ በሚጓጓዝበት ጊዜ ሊኖር የሚገባውን አያያዝ የሚሉና እና ሌሎች ተያያዥ የጥራት መመዘኛ ደረጃዎች ዝግጅት ተጠናቆ መጽደቁን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የጸደቀው ደረጃ የሽሮ ዱቄት ብቻ ሳይሆን፤ የተዘጋጀ የሽሮ ወጥ ላይም ነው ተብሏል።የተቋሙ ደረጃ ዝግጅት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግስቱ፤ "በሽሮ ላይ ተጨማሪ ግብዓት በመጨመር የተቀመመ የሽሮ ምርት በማሳደግ ለገበያ ለሚቀርቡ በኢንስቲትዩቱ የተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ደረጃ ጸድቋል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲሁም ለውጭ ሀገር ገበያ በሚቀርቡ በተለያዩ ምርቶች ላይ አስገዳጅ እና አስገዳጅ ያልሆኑ ደረጃዎችን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል። ከኑሮ ዘይቤ መቀየር እና ከዜጎች ፍላጎት በመነሳት የሽሮ እና መሰል መሠረታዊ ሸቀጦች በሱፐር ማርኬቶች ለገበያ እየቀረቡ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ይልማ፤ በመሸጫ መደብሮቹ ላይ የሚገኙ የሽሮ ዱቄት ምርቶች ደህንነታቸው የጠረጋጋጠ መሆኑን ለመለካት የሚያስችል መቆጣጠሪያ ደረጃ ማውጣት በማስፈለጉ፣ ደረጃው መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

"በሱፐር ማርኬቶች አማካኝነት ለገበያ የሚቀርቡ የባልትና ውጤቶች ጥራታቸውን እንዲጠብቁ ደረጃዎች አስፈላጊ ናቸው" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ "የጥራት ደረጃ ፍሻተ ተከናውኖ፣ የማሸጊያ ደህንነት ተጠብቆ፣ እንዲሁም ምርቱ በሚጓጓዝበት ሂደት ደህንንቱ ተረጋጋጦ ለገበያ መቅረብ ይገባዋል" ብለዋል። ምርቱ ለእርጥበታማ ሁኔታዎች ያለው ተጋላጭነት ጭምር ክትትል ሊደረግበት እንደሚገባ አስታውሰው፤ "የወጣለት ደረጃ በእርጥብት ምክንያት የሚከሰተውን ብልሽት እና የጥራት ጉድለት ይከላከላል" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ደረጃው ከመዘጋጀቱ አስቀድሞ ከግብርና ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መሰል የደረጃ ዝግጅት ጥያቄ ስለመቅረቡ ከተረጋጋጠ በኋላ መስፈርቶቹ ሊያካትታቸው የሚገቡ ዝርዝር መረጃዎች ተሰናድተው ይዘጋጃሉ ተብሏል።ሸማቾች ግብይት በሚፈጽሙበት ወቅት ምርቱ የደረጃ ዝግጅት ስለማሟላቱ ሊያረጋግጡ እንደሚገባም፤ መሪ ሥራ አስፈጻሚው አጽንኦት ሰጥተውበታል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
17😁9😭1
በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 82 የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ!

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 82 የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በፑንትላንድ የሚንቀሳቀሰው የአይ ኤስ የሶማሊያ ክንፍ በተለያዩ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ለመስፋፋትና የሽብር ቡድኑን ሴሎች ለመመስረት የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ የመረጃ ስምሪትና ጥናት ሲደረግ ቆይቷል።

በዚህም የሽብር ቡድኑ በፑንትላንድ አሰልጥኖ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሰማራቸው 82 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከፌዴራል ፖሊስና ከክልል የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመላክቷል።ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ፣ አዳማ፣ ሃሮማያ፣ ሻሸመኔ፣ ባሌ፣ ጅማና ሻኪሶ ከተማ ዙሪያ፤ በአማራ ክልል ከሚሴ አካባቢ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞንና ሃላባ ቁሊቶ ከተማ፤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማና በሐረሪ ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል።

የሽብር ቡድኑ የጥፋት ተልዕኮውን ለማስፋፋትና ምልመላ ለማከናወን የሃይማኖት ተቋማትንና ሃይማኖትን እንደ ሽፋን ይጠቀማል ያለው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፤ የሕዝብን አንድነትና ተከባብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ብሎም ለአመጽና ሁከት የሚያነሳሱ አስተምህሮዎችን ለማስፋፋት ሙከራ ሲደረግ እንደነበር በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
😁3320👀5👍3🔥2
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሚመራ ልዑክ ከትግራይ ክልል መሪዎች ጋር ለመወያየት ወደ መቀለ አመሩ።

የሃይማኖት አባቶቹ በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከፌደራል እና ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮች ጋር እየመከሩ ይገኛሉ።

ልዑኩ ወደ ትግራይ ያመራው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ “ትግራይ ወደ ግጭት፤ ወደ ጦርነት እንዳይገባ በሀገሪቱ የሚገኙ የሐይማኖት አባቶች በአቸኳይ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፤ ከተጀመረ በኋላ ብትናገሩ ዋጋ የለውም” ሱሊ ካስጠነቀቁ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
16😁13
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ልታካሂድ ነው!

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መላ አገሪቱን የሚያዳርስ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገች ነው። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም. ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

ይህ ቆጠራ ከመስከረም ወር ጀምሮ በመላው አገሪቱ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ የምርትና የንግድ ድርጅቶች ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በየደረጃው ያለው የመንግሥት አደረጃጀት፣ የኢኮኖሚ ድርጅት ባለቤቶች እንዲዘጋጁ ተጠይቋል።

የቅድመ ዝግጅት ተግባራት የቆጠራውን ስነ ዘዴ ማዘጋጀት፣ የሰው ኃይል ማሰልጠን፣ ለመስክ ሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላትና የቴክኖሎጂ ዝግጅትን ማካተት እንደሚያጠቃልል ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
11👎9😁5👍4👀2😭1
ሰርኩላር ቁጥር 2/2018

ክለቦች ለአዲሱ የውድድር ዘመን ምዝገባ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች።

1:- ሁሉም የሊግ እርከን የሚገኙ ክለቦች በ2018 የውድድር አመት ከብሄር ጋር የተገናኘ ስያሜ ካላቸው እንዲቀይሩ

2:- ክለቦች በማላያቸው ላይ ፒለቲካዊ ይዘት ያለው ፅሁፍ ወይንም ምስል መጠቀም የተከለከለ ነው።

@የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን
41😁9🔥5👍4
Forwarded from YeneTube
ፒያሳ የመጨረሻው ሱቅ እና ቤት ሽያጭ ❗️

ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች

* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው

* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው

* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

ቴምር ሪልስቴት.......
  
ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ +251976195835

በዋትሳፕ ያገኙናል -

https://wa.me/251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

https://www.facebook.com/share/1ABkH3oH9x/
5
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
1
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሁለት ኮሚሽነሮች የሥራ ዘመናቸው ሳይጠናቀቅ መልቀቂያ አስገቡ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና የተቋቋሙ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተገለፀ።

የከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ የሥራ መልቀቅ ከአዲሱ ዋና ኮሚሽነር "የአመራር ስልት" ጋር በተያያዘ "ተገፍተው" እንደሆነ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"አሳታፊነትን" ይከተል የተነበረው የተቋሙ አሠራር ባለፉት ወራት ለሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ ውሳኔዎቹን "አለማሳወቅ፣ አለማሳተፍ እና መመካከርን" ወደ ጎን ማለቱ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መልቀቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አሳታፊነት በኮሚሽኑ "አደረጃጀት" ላይ የተመሠረተ እንደነበር ያነሱት የቢቢሲ ምንጮች፤ ተቋሙ ባለፉት ወራት ያለ ምክክር እና እውቅና ሠራተኞቹን ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ መመደብ እንዳለ አመልክተዋል።

ይህን የአመራር ስልት "ለሰብዓዊ መብት የማይሠራ" ያሉት ምንጮቻችን፤ ባለፉት ስድስት ወራት "ያለ ምክንያት" አምስት ዳይሬክተሮች የሥራ መደብ ላይ ሽግሽግ መደረጉን መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ኮሚሽነሮቹ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መልቀቂያ ማስገባታቸውንና የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠታቸውን ተገልጿል።ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ ሰኔ 18/2013 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ልዩ ጉባኤ የተሾሙ ሲሆን፣ ተቋሙ ባካሄደው ለውጥ ስማቸው ይነሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
11
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እነዚህን ውሳኔዎች ወስኗል፦

1ኛ በሁሉም የሊግ እርከን የሚገኙ ክለቦች በ2018 የውድድር አመት ምዝገባ ወቅት የክለብ ስያሜያቸው ከብሔር ስም ጋር የተገናኘ ከሆነ በመቀየር ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ ክለቦች በኦፊሴላዊ መለያ (አርማ) ላይ ፖለቲካዊና የብሔር ይዘት ያላቸው መልዕክቶችና ምስሎችን መጠቀም የተከለከለ ነው ሲል አሳስቧል፡፡

👉በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ስም ሊያስተካክሉ የሚችሉ ክለቦች መካከል፦

መቐለ 70 እንደርታ
ሀድያ ሆሳዕና
ወላይታ ድቻ
ስሁል ሽረ
ሲዳማ ቡና
👉ኦፊሴላዊ መለያ (አርማ) ሊቀይሩ የሚገደዱ ክለቦች መካከል፦

ስሁል ሽረ
ፋሲል ከነማ አርማቸውን ሊቀይሩ ይገደዳሉ፡፡

እናንተስ ምን ትላላችሁ?
29👍17
አከራካሪ የነበረው ግብር የማይከፈልበት የደመወዝ መጠን ማሻሻያ ሳይደረግበት 2 ሺሕ ብር ሆኖ ጸደቀ

አዋጁ ዓመታዊ ግብር መሰብሰቢያ ጊዜ በየሩብ ዓመቱ እንዲሆን የሚደነግግ አንቀጽ ተካቶበታል

ሐምሌ 600 ብር የነበረው ግብር የማይከፈልበት ከደመወዝ የሚገኝ ገቢ እንዲሻሻል ጥያቄ እየቀረበበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴርም ሥራ ላይ ከዋለ 9 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የገቢ ግብር አዋጅ እንዲሻሻል ረቂቁን አዘጋጅቶ ሊሚኒስቴሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም በረቂቁ ላይ ከተወያየበት በሗላ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኮታል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ከተካተቱ አከራካሪ ጉዳዮች መካከል ከግብር ነጻ የሚደረገው ከደመወዝ የሚገኝ ገቢ 2 ሺሕ ብር እንዲሆን የሚደነግገው አንቀጽ አንዱ ነው፡፡

ድንጋጌው በረቂቅ አዋጁ ላይ በተካሄደ ውይይት ወቅት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከበርካታ ሰዎች ተቃውሞ ቢገጥመውም፤ በዛሬው ዕለት ማሻሻያ ሳይደረግበት 2 ሺሕ ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

በአዋጁ አንዳንድ ድንጋጌዎች እንዲሻሻሉ ሐሳብ ከሰጡ የምክር ቤት አባላት መካከል ደሣለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ይገኙበታል፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ "አዋጁ የሰራተኞችን የኑሮ ጫና ያላገናዘበ ነው" የሚል ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም "ከድህነት ወለል በታች ካለ አንድ ሠራተኛ ግብር መሰብሰብ ሰብዓዊነት እና ርህራሄ የጎደለው አዋጅ ነው" ብለዋል፡፡

የገቢ ግብር ማሻሻያ አንዱ ዓላማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያለባቸውን የግብር ጫና መቀነስ እንደሆነ በረቂቁ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ በክልልና በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ባሉ አስተዳደሮች ከፍተኛ ገቢያቸው ከደመወዝ የሚያገኙት ግብር በመሆኑ መነሻው ከፍ ባለ ቁጥር ገቢያቸው እንደሚያሽቆለቁል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስር ድኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ለኅብረተሰቡ የሚቀርበውን አገልግሎትም አደጋ ውስጥ ይከተዋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም በክልሎች የሚገኘውን ገቢ እንዳያሳጣ ተብሎ መዘጋጀቱን ተገልጿል፡፡

ይህንን በሚመለከት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ የቋሚ ኮሚቲው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ምላሽ ሲሰጡ እንደገለፁት፤ "2 ሺሕ ብር የሚለው መንግሥት ማግኘት የነበረበትን 38 ቢሊዮን ብር እንዲያጣው ተድርጎ ነው" ብለዋል፡፡

ሌላው ጥያቄ የተነሳበት የአዋጁ ክፍል "ዓመታዊ የገቢ ግብር አሰባሰብ በሩብ ዓመት እንዲሆን መቅረቡ መጨናነቅን ከመፍጠርም በላይ በዓመቱ መጨረሻ ሊከስር ይላል" የሚሉት የምክር ቤት አባሉ ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ፤ ይህ መስተካል አለበት የሚል ጥያቄም አንስተዋል፡፡

ይህንን በሚመለከት ከገንዘብ ሚኒስትር እና ከቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡

በሩብ ዓመት መሆኑ ታክስ አስተዳደር ስርዓቱን የሚያስተካልና የነጋዴውንም ጫና የሚያቀል መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"ይህ አዋጅ በጀት ሲጸድቅ የጸደቀ ነው" የተባለ ሲሆን፤ የገቢ ማሰባበቢያውን ማሳካት የሚያስፈልግ በመሆኑ ከሀምሌ ጀምሮ ወደ ስራ እንደገባ ለማስቻል የታሰበ መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ተብሏል።

ይህ አዋጅ ከሰሞኑም ውይይቶች የተደረጉበት ቢሆንም ጥያቄ ያስነሱት ከግብር ነፃ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የመሰሉ ጉዳዮች ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግባቸው አዋጁ በስድስት ተቃውሞ በ12 ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👎4721👍1😭1
"የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ "የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" ሲሉ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንንያሉት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን ትላንት ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ አንድሪው ምቦጊሪን ጋር በነበራቸው ቆይታ “ያለ ደህና መጠለያ እና ምግብ ተጥለው በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለአምስተኛ የክረምት ወራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ህይወታቸውነ እያሳለፉ ማየት በጣም ከባድ ነው” ሲሉ መናገራቸውን ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን በበኩላቸው በክልሉ በተካሄደው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎችን ተቋማቸው ተቀብሎ መጠለያ እና ምግበ እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውሰው በቀጣይ በሚደረገው የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ይሁን በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን መረጃው አካቷል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
18