YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
<< መንግስት ከግምት ውጪ በሆኑ ፖለቲካዊ ስራዎች የህዝቡን ልብ ይመልስ >> - አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) "መንግስት ከሚገመተው ውጪ በመሆን የህዝብን ልብ የሚመልሱ ፖለቲካዊ ስራዎች ላይ እንዲያተኩር" ጠይቋል።

አብን፣ ይህን ጥያቄ ለመንግስት ያቀረበው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ላይ አተኩሮ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

ንቅናቄው በዚሁ መግለጫው "መንግስት ጎራ ከፍለው የህዝብ ለህዝብ ግጭት እንዲፈጠር ለሚቀሰቅሱ ሀይሎች የተመቸና የልብ ልብ የሚሰጥ ስህተትን በስህተት ላይ እየሰራ ይገኛል" ሲል ወቅሷል።

አብን በስም ያልጠቀሳቸውና "ግጭት እንዲፈጠር" ለሚቀሰቅሱ ሀይሎች የልብ ልብ ከሚሰጠው ስህተት ይልቅ ከግምት ውጪ በመሆን[መንግስት] ፖለቲካዊ ስራዎችን እንዲሰራ መክሯል።

ንቅናቄው "ከግምት ውጪ የሆኑ ፖለቲካዊ" ስራዎችን መንግስት እንዲሰራና የህዝቡን ልብ እንዲመልስ ይጠይቅ እንጂ በተጨባጭ እነዚህ ፖለቲካ ተግባራት ምን እንደሆኑ በዝርዝር አላስቀመጠም።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንደተፈፀሙ በመግለጫው የዘረዘረው አብን ይህን የፈፀሙት በህግ እንዲጠየቁም አሳስቧል።

"የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በተለይ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል ዜጎች እንደ ግለሰብ ባልፈፀሙት እና ተጠያቂ በማይሆኑበት ወንጀል መታሰራቸውን ከጥቆማ እና ከመረጃ ትንተናዎች ማረጋገጥ" ችያለሁ ባይ ነው - አብን።

ምንም እንኳን አብን ስለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ ባልፈፀሙት ወንጀል የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን ያትት እንጂ ስለ ፓርቲው ከፍተኛ አመራርና የእንደራሴዎች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለ፣ ስለሚገኙበት ሁኔታ ያለው ነገር የለም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ባወጣው መግለጫ የምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለ " አዋሽ አርባ " እንደሚገኙ መግለፁ አይዘነጋም።

አብን ሊቀመንበሩን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮቹ፣ የ2013 ምርጫን ተከትሎ በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተመሠረተው መንግስት በፌደራል፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በአማራ ክልል የተለያዩ መንግስታዊ ሃላፊነቶች ተቀብለው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍50👎243
በኢትዮጵያ ለአራት ወራት ዕርዳታ ያልቀረበላቸው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ሕይወት አደጋ ላይ መሆኑ ተነገረ!

ኢትዮጵያ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች አስጠልላቸው የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች የዕርዳታ እህል በመቋረጡ፣ ሕይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑንና ለአገርም የደኅንነት ሥጋት መደቀኑ ተነገረ፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት የዓለም የምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በኢትዮጵያ ተፈጸመ ባሉት የዕርዳታ እህል ዝርፊያ ምክንያት፣ ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ዕርዳታ ማቆማቸው ይታወሳል፡፡

የምግብ አቅርቦቱ እንደገና እንዲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥት እየተነጋገርኩበት ነው ቢልም፣ ዕርዳታው እየቀረበ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ የተጠለሉ የውጭ አገሮች ስደተኞች በምግብ ዕጦት እየሞቱና ሕመም ላይ መውደቃቸውን፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተመሳሳይ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለተረጂዎች እየቀረበ ባለመሆኑ ወደ 400,000 የሚጠጉ በጋምቤላ ክልል ውስጥ በካምፕ የሚገኙ ስደተኞች ሕይወት አደጋ ውስጥ መውደቁን ገልጾ አፋጣኝ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 2015 ዓ.ም. ወር ጀምሮ ዕርዳታ ያላገኙ ስደተኞች በምግብ እጥረት የተነሳ በሚመጣ ረሃብ ለሞትና ለከፋ ሕመም እየተጋለጡ መሆናቸውን፣ አካሄድኩት ባለው ክትትል አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ተቋም አገኘሁት ባለው መረጃ በምግብ እጥረት ምክንያት በጋምቤላ ብቻ 30 ሰዎች መሞታቸውን፣ አምስት ዓመት ያልሞላቸው ሕፃናት ለከፋ ሕመም መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡

በተከሰተው የምግብ እጥረት የተነሳ ከስደተኞች መጠለያ ካምፕ ወጥተው ወደ ማኅበረሰቡ በሚገቡበት ወቅት ለሰላም ችግር መንስዔ መሆናቸው በኮሚሽኑ ሪፖርት የተገለጸ ሲሆን፣ ከመጠለያ ወጥተው በምግብ ስርቆት በመሰማራታቸውና ከቆሻሻ ላይ ምግብ ለማንሳት ሲጥሩ ሕይወታቸው ያለፉ መኖራቸውንም አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላ ክልል ቢሮ ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በጋምቤላ የሚኖሩ ስደተኞች በአብዛኛው ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን የተሰደዱ ናቸው፡፡ በምግብ እጥረት የሞቱትም በአብዛኛው እነዚሁ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች ናቸው ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በጋምቤላ ከሚገኙ በሦስት መጠለያ ካምፖች ክትትል ያደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ አቤል፣ በርካታ ስደተኞች አደጋ ላይ በመሆናቸው የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆኑ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
👍111
የእርዳታ ጥሪ
ከላይ በምስሉ ምትመለከቷት እናት ረውዳ ሙደሲር ትባላለች ኑሮዋን በ ጨርቆስ ክ/ከ ትኖር የነበረች ሲሆን የሁለት ልጆች እናትም ናት ። በቅርቡ ድንገት ባጋጠማት ህመም በዘውዲቱ አጠቃላይ ሆስፒታል   ሰትታከም የቆየች ቢሆንም ነገር ግን ያጋጠማት ህመም በጣም ከፍተኛ በመሆኑም ልቧን,፣የአተነፋፈስ ሁኔታዋን ሁሉ ሳይቀር  ለከፍተኛ ህመም በመዳረግ ህይወቱዋን ስጋት ላይ ጥሏል።ባለቤቷም የመንግስት ሰራተኛ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ጡረታ ወቷል እና ኑሮን እንጂ ለዚ ከባድ ሁኔታ ሚሆን የኑሮ ደረጃ  አለመኖሩም ሁኔታውን ከባድ አድርጎታል ለአመታት አትክልት በመሸጥ ቤተሰቧን ስታስተዳድር ቆይታለች:: አሁን ላይ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ስራ አቁመው በዘውዲቱ ሆስፒታል ህክምና አየተከታተለች ትገኛለች
ቤተሰቧ ለህክምና ከፍተኛ ወጪ ሲያወጣ ቆይቶ አሁን ላይ ከአቅም በላይ ስለሆነ ሁላቹም ከታች ባለው የባንክ አካውንት ያላችሁን በመላክ
ለአላህ ብላቹ እንድትተባበሩና ህይወቷን ሰታ ያሳደገችን እናታችን አይናችን እያየ እንዳናጣት አግዙን እያልን እንጠይቃቹኋለን


1000418236691

Amira shamil sherif


ንግድ ባንክ


ስልክ ቁጥር

0989160839
0947211611  አሚራ ሻሚል

0922351658 ሰሚራ ሻሚል

0921401555 ሀውድ ሻሚል
👍2410
አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች!

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረችው።

ኬኒያዊቷ አትሌት ብሪግድ ኮስጌይ በፈረንጆቹ 2019 በ2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት ይዛው የነበረውን ሪከርድ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ሰብራለች፡፡ባለፈው ዓመት በተካሄደው የበርሊን ማራቶንም 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በመግባት የዓለምን ሦስተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡

ከዚያ በፊት በጉዳት ላይ እያለች ባካሄደችው የማራቶን ውድድር የገባችበት ሰዓት 2 ሰዓት ከ34 ደቂቃ ከ1 ሰከንድ ነበር፡፡ዛሬ ያደረገችው ውድድር የአትሌቷ ሦስተኛ የማራቶን ተሳትፎዋ ነው ሲል ኤን ቢ ሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍7513🔥8
ኢሰመጉ ፤ በአዲስ አበባ በህገወጥ የሚታሰሩ ሰዎችን የመንግሥት ትምህርት ቤቶች በማቆያነት ያገለግላሉ መባሉን ለማረጋገጥ የሚመለከታቸውን አካላት ብጠይቅም ምላሽ አልሰጡኝም አለ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአዲስ አበባ ከተማ እና በአማራ ክልል በንጹሀን ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰዋል ሲል በትናንትናዉ እለት ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።

ኢሰመጉ በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ እና አንዳንዶቹም አስገድዶ የመሰወር ባህርይ ያላቸው የጅምላ እስሮች መፈፀም መቀጠላቸውንም ተናግሯል። የሚታሰሩ ሰዎችም በተገቢው ጊዜ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ ፣ የታሰሩ ሰዎች የት እንዳሉ በቤተሰቦቻቸው እንደማይታወቅ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ለእነዚህ እስሮች በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንደማቆያነት እንደሚያገለግሉ የደረሳቸውን መረጃ ለማረጋገጥም አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮን ፣ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በደብዳቤ ቢጠይቅም ሪፖርቱን እስካወጣበት መስከረም 12/ 2016 ዓ.ም. ድረስ ምላሽ አለማግኘቱን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።

በተጨማሪም አንዳንድ የእስረኞች ማቆያዎች ለዚህ ተግባር ያልተቋቋሙ እና በንጽሕና ያልተያዙ በመሆናቸው ታሳሪዎች ለከፍተኛ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውንም ኢሰመጉ በሪፖርቱ ገልጿል።

በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላም ጋዜጠኞችንና ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የምክር ቤት አባላት ጨምሮ መጠነ ሰፊ የጅምላ እስሮች መፈፀማቸውን አስታውሶ፣ የሚመለከታቸው አካላት እነዚህን ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈፀሙ እስሮች ለማስቆም እርምጃ ባለመውሰዳቸው አሁንም የጅምላ እስሮች ቀጥለዋል ሲል በመግለጫው ጠቅሷል። ከታሳሪ ቤተሰቦች አገኘኋቸው ባላቸው መረጃዎች በመዲናዋ በርካታ ሰዎች ያለአግባብ እንደታሰሩም አሳዉቋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
👍47👎83
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍41
ፈረንሳይ ወታደሮቿንና አምባሳደሯን ከኒጀር ልታስወጣ መሆኑን ፕሬዚደንት ማክሮን ተናገሩ!

በኒጀር የተከሰተውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ፈረንሳይ አምባሳደሯን እንደምታስወጣ እና ከአገሪቷ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር እንደምታቆም ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናገሩ።ማክሮን “ ፈረንሳይ ከኒጀር አምባሳደሯን ለማስወጣት ወስናለች። በሚቀጥሉት ሰዓታት አምባሳደራችን እና በርካታ ዲፕሎማቶች ወደ ፈረንሳይ ይመለሳሉ “ ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ ጨምረውም ከአገሪቷ ጋር የሚኖረው ወታደራዊ ትብብር ማብቃቱንና የፈረንሳይ ወታደሮች በሚቀጥሉት ወራት ከአገሪቷ እንደሚወጡ ተናግረዋል።ሐምሌ ወር ላይ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረው የኒጀር ወታደራዊ ኃይል ውሳኔው ተቀብሎታል።

የወታደራዊ ኃይሉ መሪ በሰጡት መግለጫም “ በአሁኑ እሑድ ኒጀር ወደ ሉዓላዊነቷ እያመራች ያለችበትን አዲስ እርምጃ እናከብራለን” ማለታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የባህር በር በሌላት የምዕራብ አፍሪካዋ አገር ከ1 ሺህ 500 በላይ የፈረንሳይ ወታደሮች ይገኛሉ።ይህ የፓሪስ ውሳኔ የተሰማው በአገሪቷ የፈረንሳይ መገኘትን በመቃወም ለወራት በዋና መዲናዋ ኒያሚ በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎች ከተካሄዱ፣ ግጭትና ተቃውሞ ከተከሰተ በኋላ ነው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
👍322
ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ

መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ ኮማንድ ፖስቱ እየሠራ ነው።

የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መከልከላቸው ይታወቃል። ይሄም ጽንፈኛና ዘራፊ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ሊያደርሱት የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ ነው። መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀድ አስፈልጓል።

በመሆኑም የሚከተሉት ትእዛዛት እንዲፈጸሙ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ ያስታውቃል፦

1. እነዚህ መሰባሰቦች ለሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ብቻ የሚውሉ ናቸው።

2. የአደባባይ መሰባሰቦች የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ የሚከናወኑ ናቸው።

3. በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር ግዴታ ነው።

መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ

@YeneTube @FikerAssefa
👍28👎73
የመውሊድ በዓል ረቡዕ ይከበራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1498ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የመውሊድ በዓል የፊታችን ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር አሳውቋል።ለበዓሉ አከባበር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከታላቁ አንዋር መስጂድ ጋር በቅንጅት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።በዓሉ ረቡዕ ከጠዋት አንስቶ እስከ ቀን 7:00 ሰዓት ድረስ በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር ተመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍29👎63
በአዲስ አበባ ሞተር ብስክሌቶች፣ የባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጆችን ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ማሽከርከር አይቻልም ተባለ!

በአዲስ አበባ ከዛሬ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌትን ፣ የባለ አራት እግርና የባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮው አሳዉቋል፡፡

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን ፤ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው ገልጿል። ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው አሳስቧል፡፡ የአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ በተሽከርካሪዎቹ ላይ ለምን እግዱን እንደጣለ አልገለጸም።

@YeneTube @FikerAssefa
👎50👍20
"የፓርቲው ሊቀመንበር ታርጋ በሌለው መኪና ተወስደዋል" - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ሊቀመንበር "ጫኔ ከበደ እሁድ መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን" ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ኢዜማ "ቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ ነው" ብሏል።

"በምን ምክንያት እንደተያዙም እስከዚህ ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም" ያለው ፓርቲው "ይህን መሰል ህግ እና ሥርዓት ያልተከተለ እርምጃም በፅኑ አወግዛለሁ" ሲል ኮንኗል።

ፓርቲው በመግለጫው "ጉዳዩን በጥንቃቄ እና በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ ለአባላት እና ደጋፊዎች እያሳወቀ መሆኑን" ጠቅሶ "የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መስከረም 14 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ኮሚቴ ማቋቋሙን" ይፋ አድርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍5110👎6
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍121
እየተገነባ ባለ አፓርታማ ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

ትላንት መስከረም 14 2016 ዓ.ም ምሽት 1:05 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሀጫሉ ሁንዴሳ መንገድ ትራኮን ሪል እስቴት እየገነባ ባለዉ አፓርታማ 5ኛና 6ኛ ፎቅ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ሲያደርስ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

አደጋዉ የደረሰባቸዉ ሁለቱም የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሲሆኑ አንደኛዉ ሰራተኛ እሳቱን በማጥፋት ሂደት ከህንጻዉ ላይ ወድቆ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁን ሰዓት በአለርት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል ተብሏል።

የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 9 ሰዓት ፈጅቷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የዉሀ ቦቴዎችን ጨምሮ 18 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ከ94 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል።የአዲስ አበባ መንገዶችና የአዲስ አበባ ዉሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ዉሀ የጫኑ ቦቴዎችን በማቅረብ ድጋፍ አድርገዋል።መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍335
ለደመራ በዓል ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ ሆኑ!

በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የደመራ በዓል ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት ነገ ከረፋዱ 5:00 ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍፃሜ ድረስ፡-

• ከኡራዐል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ

• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ

• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ

• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም

• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

አሽከርካሪዎች ይህን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳዩአቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

@YeneTube @FikeAssefa
👍365👎5
ልማት ባንክ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።የባንኩ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የአብሥራ ከበደ÷ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ ባንኩ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በእውቀትና ክህሎት የሚመሩ ጠንካራ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ ተከታታይ ሥልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ገልጸው፤ ባለፉት አራት ዙር ሥልጠናዎችም 133 ሺህ ዜጎች መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል።ሥልጠናውን ለመውሰድ ተመዝግበው ከሚጠባበቁ 320 ሺህ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች መካከል በበጀት ዓመቱ እስከ 75 በመቶ ያህሉን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል።

ሥልጠና የወሰዱ የብድር አገልግሎት ፈላጊ ዜጎችም የገበያ አዋጭነት ሃሳባቸውን ለባንኩ ማቅረብ እንዳለባቸው የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ባንኩ ብድር በመስጠት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አንቀሳቃሾች 20 ከመቶ የስራ ማሟላት ያለባቸው ሲሆን÷ ባንኩ የቴክኒክና የምክር አገልግሎትን ጨምሮ 80 ከመቶ ብድር እንደሚያቀርብ አረጋግጠዋል።እስካሁን ስልጠናውን ተከታትለው የንግድ እቅዳቸውን ላቀረቡ ዜጎች 20 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ብድር ባንኩ መስጠቱንም ጠቅሰዋል።

በ2016 በጀት ዓመትም የባንኩን ስልጥና በአግባቡ ለተከታተሉና ዝርዝር የንግድ ስራ እቅድ ለሚያቀርቡ ኢንተርፕራይዞች 20 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር ለመስጠት መታቀዱን ይፋ አድርገዋል።የባንኩ የፋይናነስ አካታችነትን ለማረጋገጥ አማራጮችን እያሰፋ መሆኑን ገልጸው፤ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ዜጎች የብድር አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመርም ጠቁመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍3013👎9🔥3👏1
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ1ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!!
👍28👎106
የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው!

የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብጹዓን አባቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ዲፕሎማቶች እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች በተገኙበት ነው የደመራ በዓል እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መሪነት የደመራ በዓል እየተከበረ ያለው።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
👍3513👎3