ትላንት ምሽት በተከሰተው ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ!
ትላንት ምሽት በተከሰተው ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ዳርፉር ወንዝ አካባቢ ትላንት ምሽት ከ3 ሰዓት ጀምሮ በጣለው ዝናብ በተፈጠረ ጎርፍ ሁለት ሴቶች መወሰዳቸውንና ሕይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ አስከሬናቸው በተደረገው ፍለጋ ዛሬ ጠዋት መገኘቱን አመላክቷል፡፡
የሟቾቹ አስከሬን ዛሬ ጠዋት 2:30 እስከ 4 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጥቁር አባይ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ በእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች ፍለጋ መገኘቱን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ አስታውቀዋል።
በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ባለሙያው አስታውሰዋል፡፡ሕብረተሰቡ በአካባቢው ከባድ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ከጎርፍ አደጋ ራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa

👍9❤5🔥1
በደቡብ አፍሪካ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ፤ የራሳቸውን ዜጋ በማገት ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በደቡብ አፍሪካ በፖሎክዋኔ ግዛት ሊምፖፖ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሌላ አንድ ኢትዮጵያዊን በማገት በከተማዋ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተዘግቧል።
የ 20 አመት ወጣት የሆነዉን ታጋች ለማስለቀቅ ቤተሰቦቹን 80 ሺህ የደቡብ አፍሪካ ራንድ መጠየቃቸዉንም የሊምፖፖ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ማሌስላ ለደዋባ ተናግረዋል። አጋቾቹ የ 20 እና የ 22 እድሜ ያላቸዉ ወጣቶች መሆናቸዉም ተነግሯል።
ታጋቹን ፖሊስ አፈላልጎ ሲያገኝም ከሌሎች ስምንት ሰዎች ጋር ነዉ የተገኘዉ ተብሏል። እገታ የግለሰቦቹ ዋነኛ ስራ ይሆናል ተብሎ የታሰበ ሲሆን ሌላ ከሶስት ወራት በፊት የታገተ ግለሰብ መገኘቱም ተነግሯል።
የተቀሩት ስምንት ሰዎችም ፖሊስ ደርሶ እስኪያስለቅቃቸዉ በትንሹ ከ 10 እስከ 15 ቀናት ታግተዉ ቆይተዋል ነዉ የተባለዉ። ግለሰቦቹ በደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር የተለያዩ 9 ክሶች ይቀርብባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

👍36❤5
በአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች በሚያስከፍሉት ክፍያ ላይ የተማሪ ወላጆች ቅሬታ አቀረቡ!
በአዲስ አበባ የሚገኙ የግል ትምህት ቤቶች ለተማሪዎች የሚያስከፍሉት ክፍያ አሁን ያለውን የኑሮ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ሲሉ የተማሪ ወላጆች ለአዲስ ማለዳ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ለአብነትም በዚሁ ዓመት አንደኛ ክፍል ለመማር ለተመዘገበ ልጃቸው የመመዝገቢያ፣ የጥናት እና የአንድ ተርም ክፍያ 9 ሺሕ 250 ብር መክፈላቸውን የገለጹት አንድ ወላጅ፤ ይኸው ክፍያ ባለፈው ዓመት 6 ሺሕ 500 ብር እንደነበር ተናግረዋል።
“ከከፈልኩት 9 ሺሕ 250 ብር ተጨማሪ ደግሞ ለመጽሐፍ፣ ለሶፍትና ለሳሙና ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ ይጠብቀኛል፡፡” ካሉ በኋላም፤ “ልጄ የተሻለ ትምህት ያገኝ እንደሆን ብዬ እንጂን ዋጋው ለአንደኛ ክፍል ልጅ ፈጽሞ የተጋነነ እና አሁን ያለንበት ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያላገናዘበ ነው፡፡” ብለዋል።
እንዲሁም ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ሌላ የተማሪ ወላጅ፤ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ለሚማር ልጃቸው የመመዝገቢያ እና የአንድ ተርም ክፍያ 7 ሺሕ 150 ብር መክፈላቸውን ገልጸው፤ ባለፈው ዓመት ይኸው ክፍያ 4 ሺሕ 900 ብር እንደነበር ጠቁመዋል።
አንድ ሌላ ወላጅ እንዲሁ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን 10ኛ ክፍል ለተመዘገበ ልጃቸው የአንድ ወር ክፍያ 2 ሺሕ 495 ብር መክፈላቸውን በመጥቀስ፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከአንድ ሺሕ ብር በላይ ጭማሪ ማሳየቱን እና ተጨማሪ የጥናትና የመጸሃፍት ክፍያ እንደሚጠብቃቸው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ባለፈው ዓመት መዋዕለ ሕጻናት ለሚማር አንድ ልጃቸው በተርም 8 ሺሕ ብር ይከፍሉ እንደነበረ የገለጹ አንድ ወላጅ በበኩላቸው፤ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን ይኸው ክፍያ 14 ሺሕ ብር መድረሱን ተናግረዋል።
ያለፈው ዓመት ግማሽ ላይ የሚኖሩበት ቤት በመፍረሱ ልጃቸው ትምህርት ማቋረጧን ያነሱት አንድ ወላጅ ደግሞ፤ ለዘንድሮ የትምህርት ዘመን ልጃቸውን ሌላ ትምህርት ቤት ለማስገባት መሸኛ ሲጠይቁ፣ ውዝፍ ዕዳ የመሸኛ ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
“መክፈል እንደማልችል እና ችግር ዉስጥ መሆኔን ባስረዳቸውም በምንም መልኩ ሊተባበሩ ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡” ሲሉም ተደምጠዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች እየጠየቁት ያለው ክፍያ በጣም የተጋነነ ነው በማለት ቅሬታቸውን ያቀረቡት ወላጆቹ፤ “የግል ትምህርት ቤቶች ዓላማቸው ማስተማር መሆኑን በመዘንጋት እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ነው የሚያስቡት፡፡” የሚል ሀሳብ ሰንዝረዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች በሚያደርጉት የክፍያ ጭማሪ ላይ 51 በመቶ የሚሆኑ የተማሪ ወላጆች በተገኙበት ውይይት የማድረግ እና ተስማምቶ የመወሰን ግዴታ እንዳለባቸው፤ እንዲሁም የመጀመሪያው ውይይት ላይ የሚገኙ ወላጆች ከተጠቀሰው ቁጥር በታች ከሆኑ ስብሰባው መበተን እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአሰራሩ ላይ አስቀምጧል።
ሆኖም ለኹለተኛ በሚጠራው ስብሰባ ላይ ሊደረግ የታሰበው ጭማሪ በሥፍራው በተገኙ ወላጆች መጽደቅ እንደሚችል አሰራሩ ይደነግግጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ የግል ትምህርት ቤቶቹ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ፕሮፖዛል አቅርበው እንደነበር አውስቶ፤ ሆኖም ከወላጅ ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርሱ ጭማሪውን መተግበር እንደማይችሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ዘመናይ ኀይለጊዮርጊስ፤ በክፍያ ጭማሪ ላይ መስማማት ያልቻሉ ትምህርት ቤቶች እና ወላጆች ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ በማወያየት ችግሩ እንዲፈታ ማድረጉን ገልጸዋል።
እንዲሁም አሁን ወቅቱ ትምህርት የሚጀመርበት እና የምዝገባ ጊዜ የተጠናቀቀ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ወቅቱን ያላገናዘበ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን አስመልክቶ ትናንት መስከረም4/2016 ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ተማሪዎች 40 በመቶ የሚሆኑትን እንደሚያስተምሩ የሚገለጸው የግል ትምህርት ቤቶች፤ በተማሪዎች ወርሃዊ ክፍያ ላይ ከ20 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ለማድረግ እቅድ ማቅረባቸውንና “ይህም በወላጆች ዘንድ በቂ ውይይት ያልተደረገበት እና መስማማት ያልተደረሰበት ነው፡፤” የሚል ቅሬታ ማስነሳቱን ገልጿል።
Via Addis Maleda

👍52❤7👎1
ዛሬ የሚደረጉ የአምስቱ ታላላቅ ሊጎች የተመረጡ ጨዋታዎች የቤቲንግ ግምትና መረጃዎች
ሆፈንሃይም፣ ዶርትመንድ፣ ፉልሃም ፣ አስቶንቪላ እና ኒውካስትልን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የአምስቱ-ታላላቅ-ሊጎች-የተ/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett

👍12🔥2
ፀሐይ ባንክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ!
መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ስምምነት ያደረጉት ፀሐይ ባንክ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይ ባንኩ ለካፒታል አስታዉቋል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር የተደረገው ስምምነት በባንኩ በኩል "የክለብ ደጋፊዎች የአባልነት ክፍያቸውን እንዲከፍሉ ፣ ለተጨዋችም እንዲሁም ለሰራተኞቹ የደመወዝ ሂሳብ በባንኩ በኩል ተፈፃሚ እንደሚሆን ፣ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች እና የክለቡ ቲሸርቶች በተቋሙ እንደሚሸጥ ገልጿል።
ፀሐይ ባንክ ለክለቡ በስፖንሰርሺፕ መልኩ በየዓመቱ 10 በመቶ የሚያድግ የ5 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያደርግ ሲሆን እስከ 40 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የረጅም ጊዜ ብድር እንደሚያመቻች ስምምነቱን ባደረገበት ወቅት አስታውቋል።
Via Capital

👍38👎6❤4
የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ!
ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት የ2016 ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደርን ይፋ አድርጎል።
መስከረም 14 2016 ዓ.ም የአንደኛው ወሰነ ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት ይጀምራል፡፡
ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ ይችላሉም ብሏል።
ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለመምህራንና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትውውቅይ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ባወጣው ካላንደር ተመላክቷል።
ከመስከረም 7 እስከ 11/ 2016ዓ፣ም የትምህርት ሳምንት ሆኖ እንደሚከበርም ገልጿል።

👍35👎11❤4
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል አምጡ” በሚል ግድያዎች መፈጸማቸው ተገለጸ!
በመንግሥት የጸጥታ አካላት የታሰሩ ሰዎች “ለታጣቂ ቡድኑ ድጋፍ ታደርጋላችሁ” እንዲሁም “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል” በሚል ምክንያት እንደሆነም ኢሰመኮ ገልጿል። በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ውሏቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ነዋሪዎች ተይዘው የሚቆዩበት ጊዜያዊ ማዕከል እንዳለም ተመልክቷል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፤ ሙሉውን ለማንበብ:
https://bbc.in/3PJten6

👍38❤7👎6
የ2016 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27 ይከበራል!
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 27 በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 27 በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👎89👍21❤8
በሰሜን ሸዋ ሙሉ ወረዳ ከኹለት ዓመት በላይ በዘለቀው የታጣቂዎች እገታ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ገለጹ!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሙሉ ወረዳ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ በመባል በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን፤ ከኹለት ዓመት በላይ እያደረሰ ባለው ተደጋጋሚ ጥቃት የተማረሩ ነዋሪዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ለቀው እስከመውጣት መድረሳቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው ማህብረሰብ ላይ እገታና ጥቃት ማድረስ ከጀመረ ከኹለት ዓመት በላይ እንደሆነው የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርገው የአፈና እና ዝርፊያ ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ዱበር፣ ጫንጮ፣ ሱሉልታ እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ተፈናቅለው እየሄዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ታጣቂ ቡድኑ ለአብነትም ባለፈው ቅዳሜ ጳጉሜ 04/2015 በወረዳው ውስጥ ድሬ ከተባለ አካባቢ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን ነው የገለጹት።
ቡድኑ በተለይም ከኹለት ወራት ወዲህ በነዋሪው ላይ የሚፈፅመውን ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉን በመጥቀስም፤ "ይህ ኹሉ ሲፈጸም የሚያስቆም የመንግሥት አካል የለም።" ሲሉ አክለዋል።
ነዋሪዎች ከዚህ ባለፈው በእጅ ስልካቸው እየተደወለ “ይህን ያህል ብር ካላመጣችሁ እንገላችኀለን፣ ቤታችሁንም እናቃጥላለን” በሚል ዛቻና ማስፈራሪያ መማረራቸውን ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ በሚያደርገው እንቅስቃሴ በተለይም በወረዳው ዋና ከተማ ዕሮብ ገበያ እና በተወሰኑ የገጠር ቀበሌዎች የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አገለግሎት መስጠት እንዳልቻሉ ተመላክቷል።
በተመሳሳይ በዞኑ ወረጃርሶ ወረዳ ጎሃፅዮን ከተማ እና በተለያዩ የወረዳው የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ነዋሪዎችን አፍነው እንደሚወስዱ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚጠይቁ መረዳት ተችሏል።አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ የሙሎ ወረዳ ሠላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት የጠየቀች ሲሆን፤ "በአካል መጥታችሁ ጠይቁን" በማለታቸው ምላሹን ማካተት አልቻለችም።

👍31❤5
የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባሄና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ!
20ኛዉ የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች እና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን ጉባሄና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ
ባለስልጣኑ ይህን አስመልክቶ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በመጪዉ ጥር ወር ላይ የሚካሄደው ጉባሄ የኢትዮጵያ ቡና በአፍሪካ እና በዓለም ገበያ ይበልጥ ለማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጥር ገልጿል።
"Speciality Coffee at Origin" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ጉባሄዉ ላይ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የዓለም አቀፍና የቀጠናዊ የቡና ቆይዎች ነጋዴዎች አምራች ገዥዎች እና የዘርፉ ባለሞያዎች በአንድ ጣሪያ ስር ለማሰባሰብ ታቅዷል።
የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባሄና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን "IACO" ከጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በዚሁ ጊዜ የመጀመሪያዉ የአፍሪካ ቡና ሳምንት የሚካሄድ መሆኑ ካፒታል ሰምቷል።

👍17❤8👎2🔥1
የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ!
በሪያድ በመካሄድ ላይ ባለው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ቅርሶች በተጨማሪ ይሄንኛው አስረኛ ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
በሪያድ በመካሄድ ላይ ባለው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ቅርሶች በተጨማሪ ይሄንኛው አስረኛ ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
👍35❤7
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች!
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ በኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን የተያዘውን ክብረ ወሰን በመስበር የዲያመንድ ሊግ አሸናፊ ሆነች።
አትሌቷ ክብረ ወሰኑን የሰበረችው 14:00.21 በሆነ ሰዓት በመግባት መሆኑን ዎርልድ አትሌቲክስ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ በኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን የተያዘውን ክብረ ወሰን በመስበር የዲያመንድ ሊግ አሸናፊ ሆነች።
አትሌቷ ክብረ ወሰኑን የሰበረችው 14:00.21 በሆነ ሰዓት በመግባት መሆኑን ዎርልድ አትሌቲክስ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤98👍44🔥4
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።
ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።
Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583

❤2👍1
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ የሚያገኙት አገልግሎት
👉 በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ
👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት
👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር
በስልካችን
0965083443
0118536066
በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ
እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ

👍8❤7
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ
የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY
🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525

👍4❤2
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ
የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY
🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)

❤4👍3
በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት አለፈ!
መስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም እለተ ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከጉንዶ መስቀል ከተማ ወደ ኩቲ 53 በሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 ( 75263 ኦሮ ) የሆነ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላሻ ተሽከርካሪ ፤ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ 30 ባጋጠመዉ የመገልበጥ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በአደጋዉ ህይወታቸዉን ያጡት 8 ወንዶች እና 7 ሴቶች ናቸዉ።
ሌሎች 4 ሰዎች በእጅግ ከባድ የተባለ ጉዳት ደርሶባቸው በጳዉሎስ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኢንስፔክተር ባዩሳ ደበላ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ለአደጋዉ መንስኤ የተሽከርካሪዉ የቴክኒክ ብቃት ማነስ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተጨማሪም በ 30 ሰዎች ላይ 18 ሴት እና 12 ወንዶች ከባድ የተባለ ጉዳት እንዲሁም በ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል ነዉ የተባለዉ።
ተሽከርካሪዉ ዳገት በመዉጣት በነበረበት ወቅት ወደ ኋላ በመመለሱ አደጋዉ ማጋጠሙን የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል። በአደጋዉ አሽከርካሪዉ እና ረዳቱ ወዲያዉኑ ህይወታቸዉ ማለፉንም አክለዋል።በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሌሎች 30 ሰዎች በፍቼ እና ጉንዶመስቀል ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ባዩሳ ደበላ ጨምረዉ ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል]

👍28❤5🔥1
በምዕራብ ጎጃም በምትገኘው የደንበጫ ከተማ ትላንት በተካሄደ የድሮን ጥቃት 16 ወጣቶች ተገድለው 3 መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።
የቆሰሉ ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።በደንበጫ ከተማ ከቅዳሜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውግያው እንደቀጠለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ገልጸዋል። ውግያው ቅዳሜ በርትቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን አልፎ አልፎ ከሚሰማ የተኩስ ድምጽ በስተቀር ረገብ ማለቱን ነው እኒህ የአይን እማኝ የተናገሩት።
ትናንት እሁድ በከተማዋ በተካሄደ የድሮን ድብደባ ስለሞቱት ወጣቶች ማንነት የተጠየቁት እኚህ የዓይን እማኝ «የፋኖን ኃይል ለመርዳት የተዘጋጁ መሣሪያ ያልታጠቁ ወጣቶች ናቸው» ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪ በገጠራማ አካባቢዎች የሄሊኮፕተሮች ድብደባ የነበረ ቢሆንም በቤቶች ላይ ከደረሰ ውሱን ጉዳት በስተቀር በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተናግሯል።
Via DW

👍23❤3
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ!
የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ አሳልፏል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርስነት የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።
45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሁለት ታላለቅ የቱሪስት መዳረሻዎችን በአለም ቅርስነት ማስመዝገቧን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

👍28❤7👎2