YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቅርቡ በቻይና መንግስት የተሰጠው የአንድ አመት የእዳ ክፍያ ማቋረጥ ውሳኔ ቢያንስ ከጠቅላላ የውጭ እዳ ክፍያ እሩብ ያህሉን የሚሸፍን ሊሆን እደሚችል ይጠበቃል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በነበረው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በንግግራቸው ጋገኙት ውጤት መካከል የእዳ ሽግሽግ እስኪደረግ ለቻይና በዚህ አመት የሚከፈል እዳ ለአንድ አመት እፎይታ እንዲያገኝ መደረጉ ነው፡፡ይህም ትልቅ ውሳኔ ነው ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡በውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያ ከጠቃላላ የውጭ እዳ ክፍያዋ ቢያንስ አንድ አራተኛ የሚሆነውን ማዳን እንደሚትችል ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡

ለምሳሌ በተጠናቀቀው የ2015 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ከተከፈለ ጠቅላላ የውጭ እዳ 1.24 ቢሊየን ዶላር ውስጥ በመንግስት ዋስትና ከግል አበዳሪዎች እንዲሁም ያለ መንግስት ዋስትና ለተወሰዱ ብድሮች የተከፈለውን ሳይጨምር የቻይና ድርሻ 24 በመቶ ወይም ወደ 300 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ነው፡፡በዚህ መሰረት መንግስት ለአንድ አመት ያገኘው የእዳ ክፍያ እፎይታ ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው ባለሞያዎች እየገለጹ ነው፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍272👎2
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ!

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሠረት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ነፃነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ቦረዱም ዩኒቨርሲቲውን በኃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍49👎447🔥2
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ530 በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ህይወታቸው ያልፋል!

በዓለም ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ስርጭት ያለው የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቂ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስቴር የማህፀን በር ካንሰር አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቦጋለ ለብስራት ሬድዮና ቲቪ እንደተናገሩት ከካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ በሚያደርሰው ጉዳይ 30 በመቶ ሽፍን በመያዝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲቀመጠ የማህፀን በር ካንሰር ከ13 በመቶ በላይ በመሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ያለ የካንሰር ዓይነት መሆኑን ተናግረዋል።

በየዓመቱ 7ሺ 445 አዲስ የማህፀን በር ካንሰር ተጠቂ ሴቶች የሚመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 533 የሚሆኑት ህይወታቸው ያልፋል።የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከሌሎች የካንሰር አይነቶች የሚለየው መነሻው ይታወቃል ያሉን አቶ መንግስቱ መነሻውም HPV በሚባል ቫይረስ ነው።

መነሻው መታወቁ አስቀድሞ ክትባት ለመስጠት የሚስችል እና በሽታው አስቀድሞ በመመርመር ህክምና ማድረግ ይቻላል።ሆኖም የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ህመም የሌለው በመሆኑ ሰዎች ቫይረሱ ተስፋፍቶ ህመም ሲጀምራቸው እና ወደ ካንሰር ከተቀየረ በኃላ ወደ ጤና ተቋም መምጣታቸው ህክምናውን አስቸገሪ አድርጎቷል።

በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆኑት የማህፀን በር ካንሰር ህመምተኞች የሚመጡት የማይድን ደረጃ ላይ ከደረሰ በኃላ ነው ።የማህፀን በር ካንሰር ያለእድሜ በሚደረግ የፆታ ግንኙነት፤ ወንዶችም ሆነ ሴቶች በፆታዊ ግንኙነት ከአንድ ሰው ጋር አለመወስን ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው።የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ለመከላከል ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍156👎2
ፍሬሕይወት ታምሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቦርድ ሊቀመንር ሆነው ተሾሙ!

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ለተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ ቴሌኮም ወና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን ፍሬህይወት ታምሩ የየኒቨርስቲው የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 ዓም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም ፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ከተዘጋጁ በኋላ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
👍43👎213
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍6🔥1
YeneTube
Photo
በጅግጅጋ በአራት ወንዶች ተደፍራ በገመድ ታንቃ የተገደለችው የ11 ዓመቷ ፋጡማ ኡጋሳ!

በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነዋሪ የነበረችው የ11 ዓመቷ ታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ፣ በደቦ ከተደፈረች በኋላ በገመድ ታንቃ የተገደለችው ባለፈው እሁድ ነሐሴ 21/ 2015 ዓ.ም. ነው።

በልጃቸው ግድያ ከባድ ሐዘን የገጠማቸው አባት ኡጋስ አረብ፣ ፍትሕን አጥብቀው እንደሚሹም ለቢቢሲ ሶማሊ ተናግረዋል።“እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ። ለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፋ ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።

ታዳጊዋ በቤቷ ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ በከተማዋ በሚገኘው ካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል ለምርመራ በተወሰደችበት ወቅት በገመድ ታንቃ ከመገደሏ በፊት መደፈሯንም ተገልጿል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ በፋጡሞ ኡጋስ አረብ ግድያ እና መደፈር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አረጋግጧል።ታዳጊዋ ተደፍራ የተገደለችው በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ሲሆን፣ አባቷ ለቢቢሲ ሶማሊ ጥቃቱ ሲፈጸም ጩኸት ሰምተው ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ተናግረዋል።

“በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከእኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም። ልጄ ጋር ሄጄ ሳያት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ። አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጬ ወደ ሐኪም ወሰድኳት” ሲሉም አባቷ ኡጋስ አረብ ለቢቢሲ ሶማሊ ተናግረዋል።ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰው ቢወስዷትም ታዳጊዋ ሕይወቷ ማለፉ በሕክምና ባለሙያዎች ተረጋግጧል።የታዳጊዋ አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸውን ደፍረው የገደሏት “ሠራተኞቻቸው” እንደሆኑ ነው።

በጅግጅጋ በሚገኘው ሞባይል ጥገና ሱቃቸው ተቀጥረው የሚሠሩ “አራቱ ሠራተኞቼ በድርጊቱ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል” ብለዋል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ታዳጊዋን በቡድን ደፍረው ግድያ ፈጽመዋል በሚል አራት ተጠርጣሪዎች በሕግ ጥላ ሥር እንደሚገኙ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለልጅቷ ቤተሰብም ፍትሕን እንደሚያስገኝ ነው የገለጸው።

የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል አብዲ አሊ ሲያድ ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎች በሕግ እንደሚጠየቁ ገልጸው፣ ቤተሰቡም ፍትሕ እንደሚያገኝ ነው ለቢቢሲ ተናግረዋል።ግድያውንም ተከትሎ ባለንበት ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሰኞ ነሐሴ 22/ 2015 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሶ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
👍443🔥2
በግብዓት እጥረት ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ስራ ጀመረ!

በግብዓት እጥረት ምክንያት ላለፉት ሶስት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ማዕከሉ በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ፣ በዳግማዊ ሚኒልክ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በየአብ ሜዲካል ሴንተር ኤንድ ሪሃብሊቴሽን በሦስትዮሽ ስምምነት ውል እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ቦሶስቱ ተቋማት ድጋፍና በሌሎች አጋር ድርጅት ያላሰለሰ ጥረት በዛሬው ዕለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍124
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለጸጥታ አመራሮች ሹመት ሰጠ!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ ጸጥታ አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

1. ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ወልዴ - የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

2. ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ ገ/መስቀል- የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

3. ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ ገዳሙ- የአብክመ ማረሚያ ቤቶች አገ/ኮሚሽን ኮሚሽነር

4. ዶ.ር እሸቱ የሱፍ አየለ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

5. ደጀኔ ልመንህ በዛብህ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

6. በሪሁን መንግሥቱ ከበደ - የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

7. ዳኛው በለጠ ጎኔ - የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ

8. ገደቤ ኃይሉ በላይ - የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ

9. ኮሚሽነር ውበቱ አለነ - የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ

10. ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ - የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሰው ኃይል አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ

11. ም/ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ - የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሎጀስቲክስ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👎47👍365
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት በመጪው ሰኞ በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በተሰናባቹ አቶ ጸጋዬ ቱኬ ምትክ አዲስ ከንቲባ ሊሾም ነው!

የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት በመጪው ሰኞ ነሐሴ 29፤ 2015 በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የከተማዋን ከንቲባ ጨምሮ የካቢኔ አባላትን ሹመት ሊሰጥ ነው። የከተማዋ ምክር ቤት ሹመቶችን የሚሰጠው፤ የሲዳማ ክልል ካደረገው ግምገማ በኋላ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም እንዲነሱ መወሰኑን ተከትሎ ነው።

የሲዳማ ክልል ከአንድ ሳምንት በፊት ካካሄደው የፓርቲ እና የመንግስት አፈጻጸም ግምገማ በኋላ፤ “ብልሹ አሰራር ፈጽመዋል” ያላቸውን 10 ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቆ ነበር።በዚህ ግምገማ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ባለስልጣናት መካከል ሰባቱ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ተመድበው የሚሰሩ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያገኘችው ዝርዝር ያመለክታል።

ከእነዚህ የከተማይቱ አስተዳደር አመራሮች ውስጥ በስልጣን ከፍተኛውን ቦታ የያዙት፤ ለሶስት ዓመታት ገደማ ሀዋሳን በከንቲባነት የመሩት አቶ ጸጋዬ ቱኬ ናቸው።አቶ ጸጋዬ እና ሌሎች ስድስት የካቢኔያቸው አባላት ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ባሉት ሳምንታት፤ የከተማዋን የስራ እንቅስቃሴ ሲመሩ የቆዩት የሀዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ ናቸው ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍3210👎2
የአይደር ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ17 ወራት ዉዝፍ የሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ እዳ እንዳለበት ተነገረ!

በመቐለ ከተማ የሚገኘዉ አይደር ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆፒራል ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳለበት የሆስፒታሉ ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገብረእግዚአብሔር ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። አይደር ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጦርነቱ በነበረባቸዉ ጊዚያት ለሰራተኞቹ ያልከፈለዉ ዉዝፍ የ 17ወራት የደሞዝ ክፍያ እዳ እንዳለበትም ዶ/ር አብርሃ ገልጸዋል።

ለ 2016 በጀት አመት ለሆስፒታሉ የመደበዉ የገንዘብ መጠንም እስከ ቀጣዩ አመት የሚያዚያ ወር ብቻ የሚበቃዉ ነዉ ብለዋል። ሆስፒታሉ ባለበት እዳ ላይ በቀጣይ አመት የበጀት እጥረት ስጋት ተደቅኖበታልም ሲሉ ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ በጦርነት ወቅት የሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ በማቋረጡ ባለሙያዎች ካለ ክፍያ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን አስታዉሰዋል። ከሰላም ስምምነቱ በኋላም ቢሆን ይህን የሚያካክስ ሁኔታ አልተፈጠልንም ሲሉ ክሊኒካል ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ገልጸዋል። ለአብነትም ሲሉ ለሰራተኞቹ ደሞዝ እና የስራ ማስኬጃ ወጪዎች ከ 2012 በጀት አመት ከተላለፈዉ 50 በመቶ የቀነሰ በጀት ለቀጣዩ አመት ተለቋል ነዉ ያሉት።

የደሞዝ ክፍያዎችን በሚመለከትም በየጊዜው ከሰራተኞቹ የፍርድቤት መጥሪያ ለሆስፒታሉ እንደሚደርሰዉ ዶ/ር አብርሃ ጠቁመዋል። ሆስፒታሉ በዚህ ልክ አጋጥሞታል የተባለዉን የበጀት እጥረት በሚመለከት ለፌደራል መንግስት ጥያቄ አቅርበዉ እንደሆነ ጣቢያችን ጠይቋል።

ክሊኒካል ዳይሬክተሩ በምላሻቸዉ ለጤና ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዉ ፤ "እናግዛችኋለን ከሚል ምላሽ ዉጪ ተጨባጭ እርዳታ አላገኘንም" ብለዋል። ሆስፒታሉ ከፌዴራል መንግስት ፣ የትምህርት ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር አስተዳደራዊ ፣ የገንዘብ እና የህክምና አገልግሎት መስጫ ግብዓቶች ድጋፍ ይሻል ሲሉ የአይደር ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገብረእግዚአብሔር ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍356🔥2
የዛሬ ጨዋታዎች:-

ላይፕዢግ፣ሌጂያ ዋርሶ፣ ግሪሚዮንና ዲፌንሳ ጀስቲሳ የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት

ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇

http://www.betsket.com/ላይፕዢግ፣ሌጂያ-ዋርሶ፣-ግሪሚዮንና-ዲፌ/

ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett
👍71🔥1
"በፀጥታና በሌሎች ችግሮች ፈተና ያልወሰዱ ከ18 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመፈተን ዝግጅት ተደርጓል"- የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት

በፀጥታና በሌሎች ችግሮች ፈተና ያልወሰዱ ከ18 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።በጎንደር፣ በጋምቤላ፣ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች 17 ሺህ 753 ተማሪዎችና በውጭ ሀገራት 300 ተማሪዎች ይፈተናሉ።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙሮች መሰጠቱ ይታወቃል።ሆኖም በአማራ ክልል እና በጋምቤላ ክልል ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሙሉ ለሙሉና በከፊል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች መኖራቸውን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በተለይ ለኢዜአ ገልፀዋል።

በተለይም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሦስት መፈተኛ ጣቢያዎች ሲፈተኑ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል ከ16 ሺህ 580 በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሁለት እስከ ሦስት የትምህርት ዓይነቶችን ሳይፈተኑ መቅረታቸውን ገልፀዋል።በጋምቤላ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት ደግሞ ከ100 በላይ የማኅበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በከፊልና ሙሉ ለሙሉ አልወሰዱም ብለዋል።

በሕግ ጥላ ሥር በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 982 ተማሪዎችና በኢትዮጵያ ሥርዓተ-ትምህርት በውጭ ሀገራት የሚማሩ 300 ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ከ18 ሺህ በላይ በከፊልና ሙሉ በሙሉ ፈተና ያልወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል።በመሆኑም በፀጥታ ችግር ያቋረጡትን፣ በማረሚያ ቤት የሚገኙና በውጭ ሀገራት የሚማሩ ተማሪዎች ፈተናውን እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለዚህም የፈተና ህትመት፣ የሰው ኃይልና የበጀት ዝግጅት እየደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከየአካባቢው አስተዳደሮች፣ የትምህርት ቢሮዎች፣ ከወላጆችና ከተማሪዎች ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል።ተማሪዎች ስነ-ልቦናቸው ለፈተና ዝግጁ ሲሆን እንዲሁም አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጫ ሲገኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈተኑ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።

በውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ ሥርዓተ-ትምህርት የሚማሩ 300 ተማሪዎችም ከዛሬ ነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የሚፈተኑ ይሆናል።ለዚህም የፈተና ጣቢያ አስተባባሪዎች ከኢትዮጵያ ፈተናው ወደሚሰጥባቸው ሀገራት መጓዛቸውን ነው ያነሱት።በፀጥታና ሌሎች ችግሮች ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በአፋጣኝ የሚፈተኑበትና ውጤታቸው ሐምሌ ላይ ከተፈተኑ ሁሉም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር ውጤታቸውን ይፋ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
👍431
የባሕር ዳር ከተማ ሰላም በመሻሻሉ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ መሻሻሉ ተገለጸ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በከተማው ላይ የነበረውን የመንቀሳቀስ የሰዓት ገደብ ከዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2:00 ድረስ እንዲሆን ማሻሻሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍19👎74
አቶ መኩሪያ መርሻዬ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆኑ!

2ኛ ዙር 8 ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ያለው የሐዋሳ ከተማ ምክር ቤት ለከንቲባነት በእጩነት የቀረቡትን አቶ መኩሪያ መርሻዬን ሹመት አፅድቋል።

የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ካንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩት አቶ መኩሪያ መርሻዬ ቃለ መሐላ የፈፀሙ ሲሆን የካቢኔ አባላቶቻቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ላለፉት ሦሥት ዓመታት የሐዋሳ ከተማን ሲያስተዳድሩ የቆዩት እና በቅርቡ በሲዳማ ክልል ምክር ቤት የአፈፃፀም ግምገማ ወቅት ሲተቹ የቆዩት አቶ ፀጋዬ ቱኬ "ከተማ የሚለማው በቅብብሎሽ እንደመሆኑ በቀጣይ ለሚሰየሙ አካላት መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ከወዲሁ እመኛለሁ" ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረው ነበር።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
👍201
በዩናይትድ ኪንግደም የሰውነት ክብደት ለመቀነስ የሚያስችል ዌጎቪ (Wegovy) የተባለ መድኃኒት ሊሰጥ ነው።

የአገሪቱ ብሔራዊ የጤና ተቋም ይህን መድኃኒት በተወሰነ መጠን ማስገባቱን ተከትሎ ለሕሙማን ሊታዘዝ እንደሚችል ተገልጿል።በመርፌ የሚሰጠው መድኃኒቱ በአገር አቀፍ ተቋሙ በኩል ወይም በግል ሕክምና መስጫዎችም ሊሰጥ ይችላል።በአገሪቱ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን እንደሚረዳ ተገልጿል።

በዓለም የዚህ መድኃኒት እጥረት ስላለ ዋጋው መወደዱ ተዘግቧል።ጥናቶች እንደሚያሳዩት መርፌው ከ10% በላይ ክብደት ለመቀነስ ያስችላል። ይህ የሚሆነውም ሰዎች ምግብ በልተው እንደጠገቡ እንዲሰማቸው አድርጎ ምግብ እንዳይበሉ በማስቻል ነው።በአሜሪካና በሌሎች አገራት ታዋቂ ሰዎች ይህንን መርፌ ይወስዳሉ። ባለሙያዎች እንደሚሉት መድኃኒቱ ጤናማ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አይተካም።

ሙከራ ሲደረግ መድኃኒቱን የወሰዱ ሰዎች መድኃኒቱን ሲያቆሙ ተመልሰው ክብደት ይጨምራሉ።በዩኬ በምን ያህል ዋጋ እንደሚሸጥ እስካሁን ባይታወቅም በመደበኛነት አራት መርፌ በ73.25 ዩሮ ሲሸጥ ቆይቷል።ተጠቃሚዎች በሳምንት አንዴ መርፌውን ይወስዳሉ።ይህንን መርፌ የሠራው የዴንማርክ ድርጅት ኖቮ ኖርዲስክ ሲሆን፣ ምርቱን በስፋት እስኪያጠናቅቅ ድረስ ዓለም አቀፍ ማከፋፈል ላይ ገደቦች እንደሚኖሩ አሳውቋል።

“ለተወሰነ ጊዜ ምርቱ እንደሚቀንስ እንጠብቃለን። የተወሰነ ምርት ግን በዩኬ ገበያ ይቀርባል” ሲል መግለጫ አውጥቷል።መርፌውን በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈልጉ ሕሙማን ቅድሚያ እንዲያገኙ ለማድረግ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በቅርበት እንደሚሠራም ገልጿል።ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ሕክምናውን እንዲያገኙም እንደሚሠራ አክሏል።በዩኬ መድኃኒቱን መውሰድ የሚችሉት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸውና በሰውነት ክብደታቸው ምክንያት ለሕመም የተጋለጡ ሰዎች ናቸው።

ከተመጣጠነ ምግብና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር ተደምሮ መድኃኒቱ ለሁለት ዓመታት ይሰጣል።አሁን በዩኬ ሆስፒታሎች በኩል መርፌውን ማግኘት የሚችሉት ወደ 35,000 ሰዎች ሲሆኑ በቀጣይ ተጨማሪ ቁጥር ላላቸው ዜጎች እንደሚዳረስ ተገልጿል።የተቋሙ ቃል አቀባይ እንዳሉት የመድኃኒቱን ዓለም አቀፍ እጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።ወደ 50,000 ሕሙማን መድኃኒቱን ማግኘት እንደሚችሉም ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍21👎2🔥2
በእስራኤል መዲና ቴልአቪቭ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በጎራ ተከፋፍለው ያስነሱት ሁከት “ቀይ መስመሩን” ያለፈ እንደሆነ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።

በርካቶች ተጎድተውበታል እንዲሁም ከፍተኛ የንብረት መውደም ተከስቶበታል በተባለውም የቅዳሜ ነሐሴ 27/ 2015 ዓ.ም ግርግር ተሳትፈዋል የተባሉ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን በአስቸኳይ ከአገር ማባረርን ጨምሮ ጠንከር ያለ እርምጃም ይወሰድባቸዋል ተብሏል።በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በተነሳው ግርግር እና ከፖሊስ ጋርም በተፈጠረው ግጭት ከ170 ሰዎች በላይ ቆስለዋል።

ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ዱላ፣ ድንጋይ እና ሌሎችም መሣሪያዎችን በመጠቀም እርስ በርስ የተወራወሩ ሲሆን ይህንንም ሁከት ኔታንያሁ “ቀይ መስመሩን ያለፈ” እና “ደም መቃባት የታየበት” ሲሉ ነው የገለጹት።ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሕገ ወጥ ሰርጎ ገቦች” ሲሉ የገለጿቸውን አፍሪካውያን ስደተኞችን ከአገር የማስወጣት አዲስ ዕቅድም እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

በሌሎች አገሮች የታየው በኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች እና ደጋፊዎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች ከሰሞኑ በእስራኤል፣ ቴልአቪቭ ተከስቷል።ለዚህም መነሻ የሆነው ተቃዋሚዎች በኤርትራ ኤምባሲ አዘጋጅነት የሚካሄደው ፌስቲቫል እንዲሰረዝ የእስራኤል ባለሥልጣናትን መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው።

ፌስቲቫሉ በተዘጋጀበት ስፍራ ዙሪያ የነበረውን የፖሊስ አጥር ሰባብረው በመግባት ከፍተኛ የሆነ ንብረት መውደሙ ተገልጿል።በቴልአቪቭ የተከሰተውን አመጽ ለመቆጣጠር የእስራኤል ፖሊሶች ጥይት፣ አስለቃሽ ጭስ እና የፕላስቲክ ጥይቶችን የተኮሱ ሲሆን በፈረስ ላይ የተቀመጡ ፖሊሶችም ኤርትራውያኑን በመግፋት ለመበተን ሲሞክሩም ታይተዋል።

ፖሊስ በኤርትራውያን ላይ ጥይት መተኮሱን ተከትሎ ሕጋዊ አሰራር የተከተለ ስለመሆኑ ምርመራ ተከፍቷል ተብሏል።በርካታ አባላቱ እንደቆሰሉበት ያስታወቀው የእስራኤል ፖሊስ በበኩሉ ሕይወታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ ተሰምቷቸዋል ብሏል።ቅዳሜ የእስራኤል ጎዳናዎች የውጊያ ግንባር የመሰሉ ሲሆን በርካቶች እንጨት፣ ዱላ፣ ፌሮ ይዘው እርስ በርስ ሲደባደቡ ታይተዋል።እርስ በርስ ከነበረው ድብድብም በተጨማሪ የሱቆች መስታዎችን እንዲሁም መኪናዎችን መሰባበራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube@FikerAssefa
👍412
የመንገድ ትራፊክ አደጋ ትምህርት በአዲሱ የስርዓተ ትምህርት ላይ እንደተካተተ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በእግረኞች ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በተለያዩ በሀይማኖት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች እንዲሁም ለማህበረሰቡ የሚሆኑ መድረኮችን በማዘጋጅት እየተሰራ እንደሆነ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልገሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፈቲያ ደድገባ ተናግረዋል፡፡ከዚኅም በተጨማሪ በሀገር ደረጃ ዜጎች የመንገድ ደህንነት ጉዳዮችን እንዲያውቁ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር አብሮ በመስራት የትራፊክ ትምህርትን በተለያዩ የትምህርት አይነቶች ውስጥ እንዱተካተተ ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👍183
‹‹ በቅፅል ስሙ ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ያሬድ ዘላለም ላይ የማድረገውን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ›› - ፌደራል ፖሊስ

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄይላን አብዲ ‹‹ በመታወቂያ ስሙ ያሬድ ዘላለም በቅፅል ስሙ ደግሞ ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ግለሰብ ላይ የማድረገውን ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡ከሰሞኑ ‹‹ ልጅ ያሬድ ›› በሚል ቅፅል ስም የሚጠራዉ የቀድሞ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በተረጋገጥ የፌስቡክ ገፁ ‹‹ የአንድ ትልቅ የእምነት ተቋምን ክብር በሚያጎድፍ መልኩ ባስተላለፈዉ ጸያፍና ማንንም ብሄር በማይወክል መልዕክት ምክንያት የፌደራል ፖሊስ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ›› የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ ተሰውሯራል፣ጠፍቷል እያሉ ያልተጣራና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ የሚነዙና ኅብረተሰቡ ላይ ዉዥንብር የሚነዙ ›› ያሏቸው ‹‹ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡም ›› አሳስበዋል፡፡

ጄይላን ሲቀጥሉ ‹‹ ይህን ከኢትጵያዊነት ያፈነገጠ ተግባር የፈጸመዉ ልጅ ያሬድ( ያሬድ ዘላለም) የተባለ ግለሰብ ከ3ቀናት በፊት የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥሩ ስር አውሎት እንደሚገኝ ›› ጠቅሰው ‹‹ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው እንወዳለን ›› ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ወጥቶ የአንድ ብሄር ተወካይ በሚመስል መልኩ ያስተላለፈው ግብረገብነት የጎደለው፣ የተወደደና የተከበረ የእምነት ተቋም ላይ ያስተላለፈው ጸያፍ ቃላቶች ታላቁን የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የአማራን ህዝብ የሚወክል አይደልም ›› ሲሉም ነቅፈዋል፡፡

‹‹ ማንም ደግሞ ለዚህ ግለሰብ የሠጠዉ የእምነትም ሆነ የብሔር ውክልና የለም ›› በማለት ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቁዋል፡፡

‹‹ ሌሎችም ከእንዲህ ዓይነት ከኢትጵያዊነት ከወረደና የእምነት ተቋማትን በመሳደብ ህዝብን ለቁጣ የምታነሳሱና፣ አንድን ብሄረሰብ ከሌላዉ ለማጋጨት በተለያየ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የምትቀሳቀሱ ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ›› አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ‹‹ ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ›› ጠይቃለች፡፡

‹‹ በግለሰቡ እና ተባባሪዎቹ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት በርካታ ኦርቶዶክሳዊያንም ኢትዮጵያውያንም ላይ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀሱን እና ከፍትህ አደባባይ ፍርድን ስለሚጠብቁ ፖሊስን ለማገዝ ይሔን አቤቱታ አቅርቤያለሁ ›› ብላለች።

ቤተ ክርስቲያኗ አክላም ‹‹ የተከሳሹ ድርጊት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን መልካም ስም የሚያጎድፍ ድርጊት፤ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥላቻ በመግለጽ ሰዎችን ለአመጽ እና ብጥብጥ የሚያነሳሳ፤ የቤተክርስቲያንን የአምልኮ ቦታ ያራከሰ ፤ የምዕመናኑን ስሜት የሚነካ በመሆኑ ፣ በሚያዋርድ እና ቤተክርስቲያንን በሚያናንቅ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑ በግለሰቡ እና በተባባሪዎቹም ላይ ጭምር ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ክስ እንዲመሠርት ለአቃቤ ሕግም እንዲልክ ›› ጠይቃለች።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
👍18623👎11🔥1