Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

👍5❤2🔥1
በደብረማረቆስ ከተማ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!
በምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረማረቆስ ከአርብ ነሐሴ 19/2015 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ በመከላከያ ሠራዊትና እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከመቶ በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አዲስ ማለዳ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከጤና ባለሙያዎች ሰምታለች።
ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የደብረማርቆስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታል ሐኪም በከተማዋ ቦሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከመቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሰው፤ የሟቾቹ አስክሬን ከኹለት ቀን በላይ ሳይነሳ መንገድ ላይ ወድቆ መታየቱን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
"በቦታው የወደቁትን አስከሬኖች፤ አንዳንድ ሰዎች ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኹሉንም እያነሱ ማሪያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እና በአካባቢ ቀብረዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ሰኞ ድረስ ያልተቀበሩም ነበሩ።" ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
በከተማው ለሦስት ቀናት በተደረገው ውጊያ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የሄዱ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩም፤ የትራንሰፖርት እና የሰው እንቅስቃሴ ባለመኖሩ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚወስዳቸው ጠፍቶ ሕይወታቸው ያለፉ ብዙዎች መሆናቸውንም ሐኪሟ ገልጸዋል።
የደብረማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አንዷለም ገረመው፤ ከአርብ ነሐሴ 19 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ 25 ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን በመጥቀስ፤ "ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ "በተኩስ ልውውጡ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የገቡትና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች እድሜያቸው ከ17 እስከ 50 ዓመት የሆናቸውና ሰዎች ናቸው።" ካሉ በኋላ፤ በሆስፒታሉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ወጊያ "ባለሙያዎቻችን ሥራቸውን እንደፈለጉ ተንቀሳቅሰው መስራት አልቻሉም፤ ታካሚዎችም ወደ ሆስፒታል ገብተው እየታከሙ አይደለም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህን ተከትሎም በተለይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ታካሚ የሆኑ ሰዎች ወደ ተቋሙ መጥተው እየታከሙ አይደለም ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ "የመድኃኒት እጥረት እያጋጠመን በመሆኑ፣ የጸጥታ ችግሩ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሆስፒታሉ ትልቅ ችግር ውስጥ ይገባል።" ሲሉ አክለዋል።
ከደብረማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተጨማሪ አጎራባች የሆኑ ስምንት የመጀመሪያ ደረጃ ሆሰፒታሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የሪፈር ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩና ወደ እኛ ሆስፒታል መምጣት ባለመቻላቸው ችግር ላይ ወደቀዋል ነው ያሉት።በደብረማርቆስ ባለፉት አራት ቀናት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በከተማዋ የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አለመኖሩም ተጠቁሟል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa

👍28❤3👎1🔥1
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ቢሮ በምዕራብ ትግራይ የአማራ ክልል ፖሊስ፣ የካባቢው ባለሥልጣናት፣ የአካባቢው ሚሊሺያና የታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች 250 የትግራይ ተወላጆች እንዳሠሩ መስማቱን ገልጧል።
የታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች በቁጥጥር ስር የዋሉትን ግለሰቦች የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደሚቆጣጠረው ቦታ ሲወስዷቸው፣ መከላከያ ሠራዊት መንገድ ላይ እንዳገኛቸው ቢሮው ጠቅሷል። ቢሮው፣ ሠራዊቱ ለግለሰቦቹ ወደ ምዕራብ ትግራይ የመመለስ ወይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር በሚገኙ አካባቢዎች የመቆየት ምርጫ እንደሰጣቸው መስማቱንም ገልጧል።
[Wazema]

👍26❤3🔥3👎1
የሶማሌ ክልል ካቢኔ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ!
የሶማሌ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 114 አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 23፤ 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የጉባኤውን ስልጣን እና ኃላፊነት የሚዘረዝረውን አዋጅ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።
የጉባኤው አባላት የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ዋነኛ ስራቸው “የማማከር ስራ” መሆኑን የሶማሌ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲቃድር ረሺድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። “በአንዳንድ አዳዲስ የሰፈራ ፕሮግራሞች ግጭት ስለሚከሰቱ፤ በግጭት ዙሪያ፣ በጎሳ ግጭት ዙሪያ፣ በልማት ዙሪያ የሚያማክሩን ይሆናል” ሲሉ የቢሮው ኃላፊው አስረድተዋል።
የጉባኤው አባላት በመሆን የሚመረጡት የሀገር ሽማግሌዎች የተለያዩ የጎሳ ማህበረሰብ ቅንርጫፎችን የሚወክሉ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አብዲቃድር፤ “ከአዋጁ መጽደቅ በኋላ በሚወጣ መመሪያ የአባላት ምርጫ በግልጽ የሚቀመጥ ይሆናል” ብለዋል። በዚህ መመሪያ መሰረት የሚመረጡት የጉባኤው አባላት በሚያደርጉት ስብሰባ፤ የጉባኤውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመርጡም አመልክተዋል። የጉባኤው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር በበኩላቸው፤ በአዋጁ በተቀመጠላቸው ስልጣን መሰረት “አስፈላጊ የሆኑ ሹመቶችን” እንደሚሰጡ የቢሮ ኃላፊው አክለዋል።
Via Ethiopia Insider

👍23❤4🔥1
የጋቦን ጦር ሠራዊት የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ከሥልጣን አስወገደ!
ጋቦን አጨቃጫቂ የምክር ቤት እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦር ኃይሉ በመፈንቅለ መንግስት ፕሬዚዳንት ዓሊ ቦንጎ ኦንዲምባን ከሥልጣን አባረረ።ምርጫው ተጭበርብሯል ያሉ የጦር ሠራዊቱ ባለ ከፍተኛ ማእረጎች ሥልጣኑን መቆጣጠራቸውን ይፋ አድርገዋል።የቀድሞው ፕሬዚደንት ይመሩት የነበረው መንግሥት፦ «ኃላፊነት የጎደለው፤ እንዲህ ተብሎ የሚጨበጥ ነገር የሌለው ነበር» ሲሉም ኮንነዋል ። ዓሊ ቦንጎ ሀገሪቱን «ወደ ቀውስ መርተዋታል» ሲሉም ከሰዋል ።
በዋና ከተማዪቱ ሊብሬቪል የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም የዐይን እማኞች ተናግረዋል።ከአንድ ወር ግድም በፊትም በሌላኛዋ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገር ኒጀር ወታደራዊ ኹንታ ሥልጣኑን በኃይል መቆጣጠሩ ይታወሳል።የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ECOWAS) መፈንቅለ መንግሥት ከፈጸሙት ወታደራዊ ኹንታዎች ጋር ለመደራደር እንደሚሞክር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ካልተመለሰም ጦር እንደሚልክ አስጠንቅቆ ነበር።እስካሁን ከጋቦን ውጪ፤ ኒዤር፤ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ-ኮናክሪ፣ ቻድ፣ ሱዳንና ማሊ ውስጥ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሲፈጸም ኤኮዋስም ሆነ የአፍሪቃ ኅብረት ጥርስ አልባ አንበሳ ሆኖ ከማስጠንቀቁ ውጪ የፈጠሩት ነገር የለም።
[DW]

👍58❤3👎2🔥2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር ዛሬ ከሰዓት መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
👎88👍32❤7
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል
@YeneTube @FikerAssefa
👍16👎14❤5
በቅርቡ በቻይና መንግስት የተሰጠው የአንድ አመት የእዳ ክፍያ ማቋረጥ ውሳኔ ቢያንስ ከጠቅላላ የውጭ እዳ ክፍያ እሩብ ያህሉን የሚሸፍን ሊሆን እደሚችል ይጠበቃል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በነበረው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በንግግራቸው ጋገኙት ውጤት መካከል የእዳ ሽግሽግ እስኪደረግ ለቻይና በዚህ አመት የሚከፈል እዳ ለአንድ አመት እፎይታ እንዲያገኝ መደረጉ ነው፡፡ይህም ትልቅ ውሳኔ ነው ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡በውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያ ከጠቃላላ የውጭ እዳ ክፍያዋ ቢያንስ አንድ አራተኛ የሚሆነውን ማዳን እንደሚትችል ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡
ለምሳሌ በተጠናቀቀው የ2015 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ከተከፈለ ጠቅላላ የውጭ እዳ 1.24 ቢሊየን ዶላር ውስጥ በመንግስት ዋስትና ከግል አበዳሪዎች እንዲሁም ያለ መንግስት ዋስትና ለተወሰዱ ብድሮች የተከፈለውን ሳይጨምር የቻይና ድርሻ 24 በመቶ ወይም ወደ 300 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ነው፡፡በዚህ መሰረት መንግስት ለአንድ አመት ያገኘው የእዳ ክፍያ እፎይታ ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው ባለሞያዎች እየገለጹ ነው፡፡
Via Capital

👍27❤2👎2
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ!
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሠረት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ነፃነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ቦረዱም ዩኒቨርሲቲውን በኃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

👍49👎44❤7🔥2
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ530 በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ህይወታቸው ያልፋል!
በዓለም ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ስርጭት ያለው የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቂ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስቴር የማህፀን በር ካንሰር አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቦጋለ ለብስራት ሬድዮና ቲቪ እንደተናገሩት ከካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ በሚያደርሰው ጉዳይ 30 በመቶ ሽፍን በመያዝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲቀመጠ የማህፀን በር ካንሰር ከ13 በመቶ በላይ በመሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ያለ የካንሰር ዓይነት መሆኑን ተናግረዋል።
በየዓመቱ 7ሺ 445 አዲስ የማህፀን በር ካንሰር ተጠቂ ሴቶች የሚመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 533 የሚሆኑት ህይወታቸው ያልፋል።የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከሌሎች የካንሰር አይነቶች የሚለየው መነሻው ይታወቃል ያሉን አቶ መንግስቱ መነሻውም HPV በሚባል ቫይረስ ነው።
መነሻው መታወቁ አስቀድሞ ክትባት ለመስጠት የሚስችል እና በሽታው አስቀድሞ በመመርመር ህክምና ማድረግ ይቻላል።ሆኖም የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ህመም የሌለው በመሆኑ ሰዎች ቫይረሱ ተስፋፍቶ ህመም ሲጀምራቸው እና ወደ ካንሰር ከተቀየረ በኃላ ወደ ጤና ተቋም መምጣታቸው ህክምናውን አስቸገሪ አድርጎቷል።
በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆኑት የማህፀን በር ካንሰር ህመምተኞች የሚመጡት የማይድን ደረጃ ላይ ከደረሰ በኃላ ነው ።የማህፀን በር ካንሰር ያለእድሜ በሚደረግ የፆታ ግንኙነት፤ ወንዶችም ሆነ ሴቶች በፆታዊ ግንኙነት ከአንድ ሰው ጋር አለመወስን ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው።የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ለመከላከል ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።
Via Bisrat FM

👍15❤6👎2
ፍሬሕይወት ታምሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቦርድ ሊቀመንር ሆነው ተሾሙ!
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ለተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ ቴሌኮም ወና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን ፍሬህይወት ታምሩ የየኒቨርስቲው የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 ዓም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም ፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ከተዘጋጁ በኋላ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
Via Reporter

👍43👎21❤3
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍6🔥1
YeneTube
Photo
በጅግጅጋ በአራት ወንዶች ተደፍራ በገመድ ታንቃ የተገደለችው የ11 ዓመቷ ፋጡማ ኡጋሳ!
በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነዋሪ የነበረችው የ11 ዓመቷ ታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ፣ በደቦ ከተደፈረች በኋላ በገመድ ታንቃ የተገደለችው ባለፈው እሁድ ነሐሴ 21/ 2015 ዓ.ም. ነው።
በልጃቸው ግድያ ከባድ ሐዘን የገጠማቸው አባት ኡጋስ አረብ፣ ፍትሕን አጥብቀው እንደሚሹም ለቢቢሲ ሶማሊ ተናግረዋል።“እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ። ለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፋ ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።
ታዳጊዋ በቤቷ ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ በከተማዋ በሚገኘው ካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል ለምርመራ በተወሰደችበት ወቅት በገመድ ታንቃ ከመገደሏ በፊት መደፈሯንም ተገልጿል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ በፋጡሞ ኡጋስ አረብ ግድያ እና መደፈር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አረጋግጧል።ታዳጊዋ ተደፍራ የተገደለችው በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ሲሆን፣ አባቷ ለቢቢሲ ሶማሊ ጥቃቱ ሲፈጸም ጩኸት ሰምተው ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ተናግረዋል።
“በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከእኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም። ልጄ ጋር ሄጄ ሳያት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ። አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጬ ወደ ሐኪም ወሰድኳት” ሲሉም አባቷ ኡጋስ አረብ ለቢቢሲ ሶማሊ ተናግረዋል።ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰው ቢወስዷትም ታዳጊዋ ሕይወቷ ማለፉ በሕክምና ባለሙያዎች ተረጋግጧል።የታዳጊዋ አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸውን ደፍረው የገደሏት “ሠራተኞቻቸው” እንደሆኑ ነው።
በጅግጅጋ በሚገኘው ሞባይል ጥገና ሱቃቸው ተቀጥረው የሚሠሩ “አራቱ ሠራተኞቼ በድርጊቱ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል” ብለዋል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ታዳጊዋን በቡድን ደፍረው ግድያ ፈጽመዋል በሚል አራት ተጠርጣሪዎች በሕግ ጥላ ሥር እንደሚገኙ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለልጅቷ ቤተሰብም ፍትሕን እንደሚያስገኝ ነው የገለጸው።
የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል አብዲ አሊ ሲያድ ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎች በሕግ እንደሚጠየቁ ገልጸው፣ ቤተሰቡም ፍትሕ እንደሚያገኝ ነው ለቢቢሲ ተናግረዋል።ግድያውንም ተከትሎ ባለንበት ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሰኞ ነሐሴ 22/ 2015 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሶ ነበር።

👍44❤3🔥2
በግብዓት እጥረት ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ስራ ጀመረ!
በግብዓት እጥረት ምክንያት ላለፉት ሶስት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ማዕከሉ በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ፣ በዳግማዊ ሚኒልክ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በየአብ ሜዲካል ሴንተር ኤንድ ሪሃብሊቴሽን በሦስትዮሽ ስምምነት ውል እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ቦሶስቱ ተቋማት ድጋፍና በሌሎች አጋር ድርጅት ያላሰለሰ ጥረት በዛሬው ዕለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

👍12❤4
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለጸጥታ አመራሮች ሹመት ሰጠ!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ ጸጥታ አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ፡-
1. ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ወልዴ - የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
2. ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ ገ/መስቀል- የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
3. ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ ገዳሙ- የአብክመ ማረሚያ ቤቶች አገ/ኮሚሽን ኮሚሽነር
4. ዶ.ር እሸቱ የሱፍ አየለ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
5. ደጀኔ ልመንህ በዛብህ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
6. በሪሁን መንግሥቱ ከበደ - የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
7. ዳኛው በለጠ ጎኔ - የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ
8. ገደቤ ኃይሉ በላይ - የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ
9. ኮሚሽነር ውበቱ አለነ - የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ
10. ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ - የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሰው ኃይል አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
11. ም/ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ - የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሎጀስቲክስ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

👎47👍36❤5
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት በመጪው ሰኞ በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በተሰናባቹ አቶ ጸጋዬ ቱኬ ምትክ አዲስ ከንቲባ ሊሾም ነው!
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት በመጪው ሰኞ ነሐሴ 29፤ 2015 በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የከተማዋን ከንቲባ ጨምሮ የካቢኔ አባላትን ሹመት ሊሰጥ ነው። የከተማዋ ምክር ቤት ሹመቶችን የሚሰጠው፤ የሲዳማ ክልል ካደረገው ግምገማ በኋላ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም እንዲነሱ መወሰኑን ተከትሎ ነው።
የሲዳማ ክልል ከአንድ ሳምንት በፊት ካካሄደው የፓርቲ እና የመንግስት አፈጻጸም ግምገማ በኋላ፤ “ብልሹ አሰራር ፈጽመዋል” ያላቸውን 10 ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቆ ነበር።በዚህ ግምገማ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ባለስልጣናት መካከል ሰባቱ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ተመድበው የሚሰሩ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያገኘችው ዝርዝር ያመለክታል።
ከእነዚህ የከተማይቱ አስተዳደር አመራሮች ውስጥ በስልጣን ከፍተኛውን ቦታ የያዙት፤ ለሶስት ዓመታት ገደማ ሀዋሳን በከንቲባነት የመሩት አቶ ጸጋዬ ቱኬ ናቸው።አቶ ጸጋዬ እና ሌሎች ስድስት የካቢኔያቸው አባላት ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ባሉት ሳምንታት፤ የከተማዋን የስራ እንቅስቃሴ ሲመሩ የቆዩት የሀዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ ናቸው ተብሏል።

👍32❤10👎2