ነገ ለአትሌቶች አቀባበል ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል ሲባል ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚሁ መሠረት ከጠዋቱ 1፡ 00 ጀምሮ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከሚያርፉበት ሒልተን ሆቴል ድረስ ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓት እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቅዱስ እስጢፋኖስ ወደ አራት ኪሎ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ በደጎል አደባባይ ወደ ቸርችል ጎዳና፣ ከድላችን ሀውልት በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ከዚያም በሚያርፉበት ሒልተን ሆቴል አካባቢ ለተወሰነ ሰዓት መንገዱ ለትራፊክ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
አሽከርካሪዎችም ይህንን በመገንዘብ በቦታው ላይ የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላትን መረጃ በመጠየቅና ተባባሪ በመሆን ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

👍7
የአፋር ክልል በድንገተኛ ህክምና ከፍተኛ የሞት ምጣኔ የተመዘገበበት ክልል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የአፋር ከልል ከፍተኛ ድንገተኛ ታካሚዎችን በማስተናገድም ግምባር ቀደም መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ኢሊባቡር ቡኖ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ ያለው የድንገተኛ ህክምና ሞት ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ድንገተኛ የጤና እክሎች ከክልል ክልል ከፍያለ መሆኑን የሚገልፁት ዶክተር ኢሊባቡር አንድ አንድ የዪኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ላይ በድንገተኛ ክፍሎች የሚሞቱ ታካሚዎች ከ197 በመቶ በላይ የሚደርስበት ወቅት መኖሩን ያነሳሉ፡፡
የሞት ምጣኔው ከፍ የሚለው በቂ የህክምና ባለሙያ ባለመኖሩ፣በቂ የህክምና ክፍል ያለመኖሩ፣በቶሎ ሪፈር ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ሪፈር ያለማድረግ ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ስራ አስፈፃሚው በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የድንገተኛ ህክምና ውስጥ በርካታ ታካሚዎች ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ለጣብያችን አስረድተዋል፡፡
በዚህም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 37 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ሆስፒታሎች ከሆስፒታል ጋር ጥምረት በመፍጠር ትልልቅ የሆኑ ሆስፒታሎች አነስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህክምና ተቋማት የሚረዱበት ሲስተም መፈጠሩ ተገልፃል፡፡የድገተኛ ክፍል ሞትን ለመቀነስ፣ሰርጀሪ በአግባቡ እንዲሰራና ያለባቸውን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ የሚሰራ ሲስተም መሆኑም ተናግረዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

👍18🔥1
ዳሸን ባንክ ከሁለት የአውሮፓ ተቋማት የ40 ሚሊየን ዶላር ብድር ማግኘቱን ተናገረ፡፡
ባንኩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ያገኘው ከእንግሊዙ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ('ቢ አይ አይ') እና ከኔዘርላንድሱ የስራ ፈጠራና ልማት ባንክ ከሆነው ኤፍ ኤም ኦ መሆኑ በላከው መግለጫ አስረድቷል፡፡ሁለቱ ተቋመት እያንዳንዳቸው 20 ሚሊየን ዶላር በድምሩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ለዳሸን ባንክ ማቅረባቸውን ተነግሯል፡፡
የብድር ገንዘቡ ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምታቀርበውን የግብርና ምርት ለማሳደግ እና በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ለማሻሻል ያስችላል ተብሎለታል፡፡በተለይ በእርሻ ስራ ላይ ለተሰማሩ ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሟላት ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ አስተዋጽኦ ያበረክታል መባሉን ሰምተናል፡፡
ዳሸን ባንክ ብድሩን በማግነቱ ዓይነተ-ብዙ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንደሚያግዘው ጠቅሷል፡፡ይህም በአመራረት፣ በማጓጓዝ እና በማቀናበር ሂደቶች ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ ማቅረብን ይጨምራል ተብሏል፡፡
በዚህ ትብብር 'ቢ አይ አይ' እና 'ኤፍ ኤ ምኦ' የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በ2021 አዲስ ባወጣው የውጭ ማንዛሪ ማቀላጠፊያ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ለሚገኝ የፋይናንስ ተቋም በውጭ ምንዛሪ የቀረበ የረዥም ጊዜ ብድር ሲሰጡ የመጀመሪያዎቹ ናቸው ሲል ባንኩ አስታውሷል፡፡
በግብርና ለተሰማሩ የንግድ ተቋማት የሚቀርብ ፋይናንስ ከአበባ እስከ ቡና እና የቁም ከብት ድረስ የተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችን ለማስተዋወቅ፣ ጥራትን ለማሳደግ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለማሟላት እና እሴት ለመጨመር የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ የ40 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በእጅጉ እነደሚያስፈልግ አንስተው ለተገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አለን" ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ዳሸን ባንክ ያገኘው የ40 ሚሊዮን ዶላር ብድር በ3 ዓመት ውስጥ የሚመለስ መሆኑን ባንኩ ነግሯል፡፡

👍31❤12👎1
በኢትዮጵያ 35 ነጥብ 8 በመቶ የህክምና መስጫ ማሽኖች አገልግሎት እንደማይሰጡ ተገለጸ፡፡
ጤና ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት በድንገተኛ እና ጽኑ ህምክና መስጫ ክፍሎች ላይ ያለው የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ምን ይመስል እንደነበር መገምገሙን የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢልባቡር ቡኖ ናቸው፡፡
በሃገሪቱ የሚገኙ የጽኑ ህሙማን ህክምና መስጫ ክፍሎች ምን ደረጃ ላይ እንደሆኑ ገምግመናል፤ በዚህም 35.8 በመቶ የሚሆኑት የመተንፈሻ ማሽኖች ተበላሽተዋል ወይም በአግባቡ አገልግሎት አይሰጡም ብለዋል፡፡እነዚህ ማሽኖች ራሱን ለሳተ ታካሚ በጊዜያዊነት የሳንባ ቦታን ተክተው የሚሰሩ በመሆናቸው ለጽኑ ታማሚዎች እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የድንገተኛ ህክምና ክፍሎች ላይ በተደረገው ግምገማም የተወሰኑ ተቋማት መሰረታዊ የሚባለውን ደረጃ የማያሟሉ እንዳሉ ገልጸው በቂ ባለሙያ፣ የመስሪያ ቦታ፣ የመድሃኒት አቅርቦት እና የህክምና መሳሪያ እንደሌላቸው እና ተገቢውን አሰራር ተከትለው በመስራት ላይ ውስንነት እንደታየባቸው ገልጸዋል፡፡
[Ahadu]

👍20🔥2
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ!
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ጭማሪ ማድረግ ማስፈለጉ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተደረገው የዋጋ ጭማሪ መሰረትም የ1 ሊትር ዋጋ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፤
1. ቤንዚን 74 ብር ከ85 ሳንቲም
2. ነጭ ናፍጣ 76 ብር ከ34 ሳንቲም
3. ኬሮሲን 76 ብር ከ34 ሳንቲም
4. የአውሮፕላን ነዳጅ 68 ብር ከ58 ሳንቲም
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ 62 ብር ከ22 ሳንቲም
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ 61 ብር 07 ሳንቲም

👎86👍35❤4
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

👍5❤2🔥1
በደብረማረቆስ ከተማ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!
በምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረማረቆስ ከአርብ ነሐሴ 19/2015 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ በመከላከያ ሠራዊትና እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከመቶ በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አዲስ ማለዳ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከጤና ባለሙያዎች ሰምታለች።
ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የደብረማርቆስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታል ሐኪም በከተማዋ ቦሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከመቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሰው፤ የሟቾቹ አስክሬን ከኹለት ቀን በላይ ሳይነሳ መንገድ ላይ ወድቆ መታየቱን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
"በቦታው የወደቁትን አስከሬኖች፤ አንዳንድ ሰዎች ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኹሉንም እያነሱ ማሪያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እና በአካባቢ ቀብረዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ሰኞ ድረስ ያልተቀበሩም ነበሩ።" ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
በከተማው ለሦስት ቀናት በተደረገው ውጊያ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የሄዱ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩም፤ የትራንሰፖርት እና የሰው እንቅስቃሴ ባለመኖሩ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚወስዳቸው ጠፍቶ ሕይወታቸው ያለፉ ብዙዎች መሆናቸውንም ሐኪሟ ገልጸዋል።
የደብረማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አንዷለም ገረመው፤ ከአርብ ነሐሴ 19 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ 25 ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን በመጥቀስ፤ "ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ "በተኩስ ልውውጡ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የገቡትና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች እድሜያቸው ከ17 እስከ 50 ዓመት የሆናቸውና ሰዎች ናቸው።" ካሉ በኋላ፤ በሆስፒታሉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ወጊያ "ባለሙያዎቻችን ሥራቸውን እንደፈለጉ ተንቀሳቅሰው መስራት አልቻሉም፤ ታካሚዎችም ወደ ሆስፒታል ገብተው እየታከሙ አይደለም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህን ተከትሎም በተለይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ታካሚ የሆኑ ሰዎች ወደ ተቋሙ መጥተው እየታከሙ አይደለም ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ "የመድኃኒት እጥረት እያጋጠመን በመሆኑ፣ የጸጥታ ችግሩ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሆስፒታሉ ትልቅ ችግር ውስጥ ይገባል።" ሲሉ አክለዋል።
ከደብረማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተጨማሪ አጎራባች የሆኑ ስምንት የመጀመሪያ ደረጃ ሆሰፒታሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የሪፈር ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩና ወደ እኛ ሆስፒታል መምጣት ባለመቻላቸው ችግር ላይ ወደቀዋል ነው ያሉት።በደብረማርቆስ ባለፉት አራት ቀናት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በከተማዋ የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አለመኖሩም ተጠቁሟል።
Via Addis Maleda

👍28❤3👎1🔥1
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ቢሮ በምዕራብ ትግራይ የአማራ ክልል ፖሊስ፣ የካባቢው ባለሥልጣናት፣ የአካባቢው ሚሊሺያና የታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች 250 የትግራይ ተወላጆች እንዳሠሩ መስማቱን ገልጧል።
የታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች በቁጥጥር ስር የዋሉትን ግለሰቦች የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደሚቆጣጠረው ቦታ ሲወስዷቸው፣ መከላከያ ሠራዊት መንገድ ላይ እንዳገኛቸው ቢሮው ጠቅሷል። ቢሮው፣ ሠራዊቱ ለግለሰቦቹ ወደ ምዕራብ ትግራይ የመመለስ ወይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር በሚገኙ አካባቢዎች የመቆየት ምርጫ እንደሰጣቸው መስማቱንም ገልጧል።
[Wazema]

👍26❤3🔥3👎1
የሶማሌ ክልል ካቢኔ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ!
የሶማሌ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 114 አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 23፤ 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የጉባኤውን ስልጣን እና ኃላፊነት የሚዘረዝረውን አዋጅ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።
የጉባኤው አባላት የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ዋነኛ ስራቸው “የማማከር ስራ” መሆኑን የሶማሌ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲቃድር ረሺድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። “በአንዳንድ አዳዲስ የሰፈራ ፕሮግራሞች ግጭት ስለሚከሰቱ፤ በግጭት ዙሪያ፣ በጎሳ ግጭት ዙሪያ፣ በልማት ዙሪያ የሚያማክሩን ይሆናል” ሲሉ የቢሮው ኃላፊው አስረድተዋል።
የጉባኤው አባላት በመሆን የሚመረጡት የሀገር ሽማግሌዎች የተለያዩ የጎሳ ማህበረሰብ ቅንርጫፎችን የሚወክሉ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አብዲቃድር፤ “ከአዋጁ መጽደቅ በኋላ በሚወጣ መመሪያ የአባላት ምርጫ በግልጽ የሚቀመጥ ይሆናል” ብለዋል። በዚህ መመሪያ መሰረት የሚመረጡት የጉባኤው አባላት በሚያደርጉት ስብሰባ፤ የጉባኤውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመርጡም አመልክተዋል። የጉባኤው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር በበኩላቸው፤ በአዋጁ በተቀመጠላቸው ስልጣን መሰረት “አስፈላጊ የሆኑ ሹመቶችን” እንደሚሰጡ የቢሮ ኃላፊው አክለዋል።
Via Ethiopia Insider

👍23❤4🔥1
የጋቦን ጦር ሠራዊት የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ከሥልጣን አስወገደ!
ጋቦን አጨቃጫቂ የምክር ቤት እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦር ኃይሉ በመፈንቅለ መንግስት ፕሬዚዳንት ዓሊ ቦንጎ ኦንዲምባን ከሥልጣን አባረረ።ምርጫው ተጭበርብሯል ያሉ የጦር ሠራዊቱ ባለ ከፍተኛ ማእረጎች ሥልጣኑን መቆጣጠራቸውን ይፋ አድርገዋል።የቀድሞው ፕሬዚደንት ይመሩት የነበረው መንግሥት፦ «ኃላፊነት የጎደለው፤ እንዲህ ተብሎ የሚጨበጥ ነገር የሌለው ነበር» ሲሉም ኮንነዋል ። ዓሊ ቦንጎ ሀገሪቱን «ወደ ቀውስ መርተዋታል» ሲሉም ከሰዋል ።
በዋና ከተማዪቱ ሊብሬቪል የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም የዐይን እማኞች ተናግረዋል።ከአንድ ወር ግድም በፊትም በሌላኛዋ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገር ኒጀር ወታደራዊ ኹንታ ሥልጣኑን በኃይል መቆጣጠሩ ይታወሳል።የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ECOWAS) መፈንቅለ መንግሥት ከፈጸሙት ወታደራዊ ኹንታዎች ጋር ለመደራደር እንደሚሞክር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ካልተመለሰም ጦር እንደሚልክ አስጠንቅቆ ነበር።እስካሁን ከጋቦን ውጪ፤ ኒዤር፤ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ-ኮናክሪ፣ ቻድ፣ ሱዳንና ማሊ ውስጥ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሲፈጸም ኤኮዋስም ሆነ የአፍሪቃ ኅብረት ጥርስ አልባ አንበሳ ሆኖ ከማስጠንቀቁ ውጪ የፈጠሩት ነገር የለም።
[DW]

👍58❤3👎2🔥2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር ዛሬ ከሰዓት መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
👎88👍32❤7
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል
@YeneTube @FikerAssefa
👍16👎14❤5
በቅርቡ በቻይና መንግስት የተሰጠው የአንድ አመት የእዳ ክፍያ ማቋረጥ ውሳኔ ቢያንስ ከጠቅላላ የውጭ እዳ ክፍያ እሩብ ያህሉን የሚሸፍን ሊሆን እደሚችል ይጠበቃል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በነበረው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በንግግራቸው ጋገኙት ውጤት መካከል የእዳ ሽግሽግ እስኪደረግ ለቻይና በዚህ አመት የሚከፈል እዳ ለአንድ አመት እፎይታ እንዲያገኝ መደረጉ ነው፡፡ይህም ትልቅ ውሳኔ ነው ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡በውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያ ከጠቃላላ የውጭ እዳ ክፍያዋ ቢያንስ አንድ አራተኛ የሚሆነውን ማዳን እንደሚትችል ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡
ለምሳሌ በተጠናቀቀው የ2015 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ከተከፈለ ጠቅላላ የውጭ እዳ 1.24 ቢሊየን ዶላር ውስጥ በመንግስት ዋስትና ከግል አበዳሪዎች እንዲሁም ያለ መንግስት ዋስትና ለተወሰዱ ብድሮች የተከፈለውን ሳይጨምር የቻይና ድርሻ 24 በመቶ ወይም ወደ 300 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ነው፡፡በዚህ መሰረት መንግስት ለአንድ አመት ያገኘው የእዳ ክፍያ እፎይታ ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው ባለሞያዎች እየገለጹ ነው፡፡
Via Capital

👍27❤2👎2
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ!
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሠረት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ነፃነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ቦረዱም ዩኒቨርሲቲውን በኃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

👍49👎44❤7🔥2
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ530 በላይ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ህይወታቸው ያልፋል!
በዓለም ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ስርጭት ያለው የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቂ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስቴር የማህፀን በር ካንሰር አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቦጋለ ለብስራት ሬድዮና ቲቪ እንደተናገሩት ከካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ በሚያደርሰው ጉዳይ 30 በመቶ ሽፍን በመያዝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲቀመጠ የማህፀን በር ካንሰር ከ13 በመቶ በላይ በመሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ያለ የካንሰር ዓይነት መሆኑን ተናግረዋል።
በየዓመቱ 7ሺ 445 አዲስ የማህፀን በር ካንሰር ተጠቂ ሴቶች የሚመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 533 የሚሆኑት ህይወታቸው ያልፋል።የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ከሌሎች የካንሰር አይነቶች የሚለየው መነሻው ይታወቃል ያሉን አቶ መንግስቱ መነሻውም HPV በሚባል ቫይረስ ነው።
መነሻው መታወቁ አስቀድሞ ክትባት ለመስጠት የሚስችል እና በሽታው አስቀድሞ በመመርመር ህክምና ማድረግ ይቻላል።ሆኖም የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ህመም የሌለው በመሆኑ ሰዎች ቫይረሱ ተስፋፍቶ ህመም ሲጀምራቸው እና ወደ ካንሰር ከተቀየረ በኃላ ወደ ጤና ተቋም መምጣታቸው ህክምናውን አስቸገሪ አድርጎቷል።
በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆኑት የማህፀን በር ካንሰር ህመምተኞች የሚመጡት የማይድን ደረጃ ላይ ከደረሰ በኃላ ነው ።የማህፀን በር ካንሰር ያለእድሜ በሚደረግ የፆታ ግንኙነት፤ ወንዶችም ሆነ ሴቶች በፆታዊ ግንኙነት ከአንድ ሰው ጋር አለመወስን ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው።የማህፀን በር ካንሰር አስቀድም ለመከላከል ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።
Via Bisrat FM

👍15❤6👎2
ፍሬሕይወት ታምሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቦርድ ሊቀመንር ሆነው ተሾሙ!
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ለተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ ቴሌኮም ወና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን ፍሬህይወት ታምሩ የየኒቨርስቲው የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 ዓም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም ፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ከተዘጋጁ በኋላ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
Via Reporter

👍43👎21❤3

👍6🔥1