YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቻይና ÷ኢትዮጵያ ብሪክስን በመቀላቀሏ የደስታ መልዕክት አስተላለፈች

ቻይና ÷ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን በመቀላቀሏ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡

የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ጉዳዩን አስመልክቶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ÷ ቻይና ለብሪክስ መስፋፋት በተለይም የኢትዮጵያን በአባልነት መቀላቀል እንደምትደግፍ አስታውቋል፡፡

ቻይና ሁሉን አካታች እና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓት ለመፍጠር የብሪክስ አባል ሀገራትን መስፋፋት እንደምትደግፍ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ በጉባዔው ብሪክስን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሀገራት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውም ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢያን÷ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን በመቀላቀሏ ለኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቻይና በብሪክስ ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትብብር ለማጠናቀር ቁርጠኛ መሆኗንም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia #BRIKS

@Yenetube @Fikerassefa
1👍1
የስልጤ ዞን የኩተሬ ከተማ ነዋሪዎች በወረዳ እንደራጅ የሚል ጥያቄን አንግበው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

መንግስት በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በክላስተር አደረጃጀት ካዋቀራቸው አራት ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስር የተካተተው ስልጤ ዞን ውስጥ የምትገኘው የኩተሬ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በወረዳ እንደራጅ ጥያቄያቸውን ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ለአሻም እንደነገሯት ‹‹ የወረዳነት የጥያቄያቸው መነሻ የእድገት፣ የመልካም አስተዳደርና የመሰረተ ልማት መስፋፈት ፍላጎቶች እንዲሟሉላቸው ታስቦ መሆኑን ›› አስረድተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ‹‹ ከአምስት አመታት በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸውን ሲያነሱ የፌደራል፣ የክልሉና የዞን አመራሮች በተገኙበት ብልፅግና ፓርቲ ምርጫን ካሸነፈ የመጀመሪያ የሚመለሰው ጥያቄ የኩተሬ የወረዳነት ጥያቄ መሆኑን ቃል መግባቱን ›› አስታውሰው ‹‹ ይህ ግን ተፈፃሚ አለመሆኑን ›› በመጥቀስ ይወቅሳሉ፡፡

አሻም የሰልፈኞችን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አማን ከድርን እንዲሁም የስልጤ ዞን አስተዳዳሪ አሊ ከድር ምላሽ በዘገባው ለማካተት ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡የሥራ ሃላፊዎች ምላሽ በሰጡበት አፍታ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
👍21
Forwarded from YeneTube
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
👍1
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር ልትዘረጋ መሆኑ ተገለጸ!

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር በ13 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ልትዘረጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ኬንያ የምትዘረጋው ይህ ፈጣን የባቡር መስመር በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆን፤ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ ላሙ ወደብ በማድረግ ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳንን እንደሚያገናኝ ብሉምበርግ ዘግቧል።

በዓይነቱ ልዩ ነው የተባለው ይህ የባቡር መስመር በፈረንጆቹ 2025 ሥራ እንደሚጀመር እና 3 ሺሕ ከሎ ሜትር ወይም 1 ሺሕ 864 ማይል እንደሚረዝም ታውቋል፡፡

የባቡር መስመሩ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ አድርጎ፣ በኬንያዋ ማዕከላዊ ከተማ ኦሲዮሎን በኩል፣ ናይሮቢን እና አዲስ አበባን በማገናኘት የመጨረሻም መዳረሻውን ደቡብ ሱዳን ጁባ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

ይህ ፈጣን የባቡር መስመር “ኢትዮጵያ በአሰብ እና ምጽዋ እንዲሁም ጅቡቲ ወደቦች ላይ ያላትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው” የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉትም ተገልጿል፡፡

በዚሁ ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታ አማካኝነት ደቡብ ሱዳን ኹለተኛ ወደብ እንደሚኖራትም ተመላክቷል።

የባቡር መስመር ዝርጋታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠጥ በሚጀምርበት ወቅት፣ ከላሞ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ውል የፈጸመው ላፕሴት፣ በዓመት ከ29 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት እና 700 ሺሕ ተጓዦችን እንደሚያመላልስ አስታውቋል። 

🖋Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
1👍1
የቻይና መንግስት በሰጠው የነፃ ትምህርት እድል አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች ሽኝት ተደረገ።

የቻይና መንግስት  በሰጠው የነጻ የትምህርት እድል አሸናፊ ለሆኑ 26 ተማሪዎች አዲስ አበባ በሚገኘው የቻይና ኢምባሲ  ትናንት ሽኝት ተደርጓል።በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የቻይና አምባስደር ዣዎ ዚዩአን  ሀገራቸው በኢትዮጵያ የሚደረገውን የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን  በዘላቂነት እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

አምባሳደሩ አያይዘውም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ ትብብር  የጋራ በሆኑ ጉዳዮች በዘላቂነት ለመስራት እንደሚያስችል አብራርተዋል።በትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት አለማቀፋዊነትና ስኮላርሺፕ ዴስክ ሀላፊ ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ በበኩላቸው  በኢትዮጵያ የሰለጠነ የሰው ሀይል ግንባታ ሂደት ውስጥ የቻይና መንግስት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ተማሪዎች ተጨባጭ እውቀት በመቅሰምና ወደ ሀገራቸው በመመለስ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር  ግምባታ የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።በተደረገው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎችና ቀደም ሲል በቻይና ትምህርታቸውን ተከታትለው የተመለሱ ምሁራን ልምዳቸውን አካፍለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ!

ለአንድ ቀን በባሕር ዳር ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

የቀድሞውን ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ የአቶ አረጋ ከበደን ርእሰ መሥተዳድርነት ሹመት ያጸደቀው ምክር ቤቱ በአዲሱ ርእሰ መሥተዳድር በእጩነት የቀረቡትን የተለያዩ ሹመቶች ተወያይቶ አጽዷል፡፡

በዚሁ መሠረት፤

1.አቶ አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር
2.ዶክተር አህመዲን መሐመድ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ
3.ዶክተር ድረስ ሳህሉ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኅላፊ
4.ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የማሕበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኅላፊ
5.አቶ ደሳለኝ ጣሰው በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊ
6.ዶክተር ጋሻው አወቀ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኅላፊ
7.አቶ ብርሃኑ ጎሽም የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኅላፊ
8.ዶክተር መንገሻ ፈንታው የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኅላፊ
9.ዶክተር ስቡህ ገበያው የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ኅላፊ
10.አቶ ክብረት አህመድ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኅላፊ
11.አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኅላፊ
12. ዶክተር ደመቀ ቦሩ የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ኅላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ከላይ የተጠቀሱት ተሿሚዎች በእጩነት የቀረቡ ሲሆን ሌሎቹ ተቋማት ባሉበት እንደሚቀጥሉ ርእሰ መሥተዳድሩ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል። የምክር ቤት አባላቱ በእጩ ተሿሚዎች ላይ ሰፊ ውይይት እና ምክክር ካደረጉ በኋላ ሹመታቸውን አጽድቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍21
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።

ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።

ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!

ለዛሬ የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
👇👇👇

https://www.betsket.com/ቼልሲ፤-ሪያል-ማድሪድንና-አርጀንቲኒዮስ/
1
ሩሲያ 42 የዩክሬን ድሮኖችን መትታ መጣሏን አስታወቀች!

ሩሲያ ከዩክሬን የተላኩ በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) መደምሰሳቸውን ዛሬ ዓርብ አስታወቀች፡፡የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳመለከተው 42ቱ ድሮኖች የተደመሰሱት ክሬይሚያ ላይ ነው፡፡

ከእነዚህ ዘጠኙ በአየር መከላከያ ተመተው የወደቁ ሲሆን 33ቱ ደግሞ በኤሌክትሮኒክ የጦር መሳሪያዎች መውደማቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት መኖሩ አልተገለጸም፡፡

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) ኤፍ 16 የተባሉ ተዋጊ ጀቶችን የሚያበሩ እና የሚጠግኑ ዩክሬናውያንን እንደሚያሰለጥን ትናንት ሐሙስ አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአሪዞና ክፍለ ግዛት ይሰጣል የተባለው ሥልጠና "የዩክሬንን የረዥም ጊዜ መከላከያን ለማዳበር እና ለማጠናከር የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት ለመደገፍ የሚሰጥ ነው" ሲሉ የፔንታገን ቃል አቀባይ የአየር ኃይሉ ብርጊዴየር ጄኔራል ፓት ራይደር ተናግረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኖርዌይ የኤፍ 16 ተዋጊ ጀቶችን ለዩክሬን እየሰጠች መሆኑን ትናንት ሐሙስ ኪቭን የጎበኙት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶሬ ተናግረዋል፡፡

የተዋጊ ጀቶቹ ብዛት ባይገለጽም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምናልባት ከአስር ያልበለጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለምታካሂደው ውጊያ ተዋጊ ጀቶችን በመለገስ ከኔዘርላንድ እና ዴንማርክ ቀጥሎ ኖርዌይ ሶስተኛዋ የአውሮፓ አገር መሆኗ ተነግሯል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
1👍1
ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ውድድር የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አገኘች!

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት አማኔ በሪሶ የወርቅ እና አትሌት ጎይቲቶም ገብረስላሴ የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።

እንኳን ደስ አለን!

@YeneTube @FikerAssefa
ኡጋንዳ "የሞቱ ምዕራባውያን" ልብስ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እግድ ጣለች!

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሰቨኒ የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን እድገት ያቀጭጫሉ ያሏቸውን "የሞቱ ምዕራባውያን" ልብሶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እገዳ ጥለዋል።ኡጋንዳ ከፍተኛ መጠን ያለው ያገለገለ ልብስ ስታስገባ የቆየች ሲሆን የዋጋ ቅናሽ ስላላቸው በተወሰኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ናቸው።

ነገርግን የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ድርጅቶች ያገለገሉ ልብሶች ገበያው ላይ መብዛት የሀገሪቱን የጥጥ እና የጨርቃጨርቅ እንዱስትሪ እድገት ይገታዋል የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።ፕሬዝደንት ሙሰቨኒ"እነዚህ ለሞቱ ሰዎች የሚሆኑ ናቸው። ነጭ ሰው በሚሞትበት ጊዜ፣ ልብሶቹን ይሰበስቡና ወደ አፍሪካ ይልኳቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የእንግሊዙ ግበረሰናይ ድርጅት ኦክስፋም እንደገለጸው ከሆነ የእርዳታ ድርጅቶች ከሜሪካ እና አውሮፖ ከሚሰበስቡት 70 በመቶ የሚሆነው ልብስ ወደ አፍሪካ ይላካል።ሮይተርስ ከሞቱ ሰዎች የሚመጣው ልብስ ምን ያህል ድርሻ እንዳለው ማረጋገጥ እንደማይችል ገልጿል።"አዲስ ምርት የሚያመርቱ ሰዎች እዚህ አሉን ነገረግን ገበያውን ሰብረው መግባት አልቻሉም" ብለዋል ሙሰቨኒ።

ኡጋንዳ ከፍተኛ የጥጥ አምራች ሀገር ብትሆንም አብዛኛው ምርት በተወሰኑ ደረጃ እሴት ተጨምሮበት ወደ ውጭ የሚላክ ነው። ኡጋንዳ አባል የሆነችበት የምስራቅ አፍሪካ ቡድን ያገለገሉ ልብሶች እንዳይገቡ በፈረንጆቹ 2016 ተስማምተው ነበር። ነገርግን አስካሁን ተግባራዊ ያደረገችው ሩዋንዳ ነች።

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የዛሬ ከሰአት በኋላ ጨዋታዎች:-

ማንችስተር ዩናይትድ፤ ፍሬይቡርግን እና ብሬንትፎርድን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት

ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇

https://www.betsket.com/ማንችስተር-ዩናይትድ፤-ፍሬይቡርግን-እና/


ምሽት በሚደረጉ ጨዋታዎችም እንመለሳለን። ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett