የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ እየገቡ መሆናቸውን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የቡድኑ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ሰምተናል።የወረዳው ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ታጣቂዎቹ ከሰሞኑ በስፋት መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ወረዳው የገጠር ቀበሌዎች እየገቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በወረዳው በተደጋጋሚ ባደረሱት ጥቃት በርካታ ዜጎች መገደላቸውንም ነዋሪዎቹ አስታውሰዋል።በተጨማሪም በወረዳው የገጠር ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ታጣቂዎችን ሸሽት ወደ ወረዳዋ ከተማ ጉንዶ መስቀልና ወደሌሎች አካባቢዎች መሰደዳቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ ታጣቂውች በወረዳው የገጠር ቀበሌ በሆኑ ባቡ ድሬ፣ ራቾና ድሬ መንቃታ አካባቢዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ነው የተነገረው።ኦነግ ሸኔ ከ ሁለት አመት በፊት ጀምሮ ወደ ወረዳው በመግባት ዜጎችን በማገት ገንዘብ መቀበል እንዲሁም ግድያና ማፈናቀል እያደረሰ ነው ተብሏል።
በተለይም የደራ ወረዳን ከሰላሌ ጋር የሚያገናኘውን የጀማን ድልድይ በመቆጣጠሩ የወረዳዋ ነዋሪዎች በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ በኩል ወደ አዲስ አበባ እንዲሚመጡ ተገደዋል።የደራ ወረዳ ከአዲስ አበባ 2 መቶ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ወረዳ መሆኑ ይታወቃል።እኛም ወቅታዊውን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማናገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካም።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

👍1😁1
በጅማ ዞን በሞቱ ሰዎች ስም የአፈር ማዳበሪያ እንደሚሸጥ ተነገረ!
በጅማ ዞን ቀርሳ እና አሰንዳቦ ወረዳዎች በተደረገ ቁጥጥር በህገወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ዉስጥ ተከማችቶ በዉድ ዋጋ ሊሸጥ የተዘጋጀ 1 ሺህ 47 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ መያዙ ተነግሯል።የአፈር ማዳበሪያዉ ግምታዊ ዋጋዉ 5 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር የሚገመት መሆኑን የጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና የኮሚኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ወንድሙ ሞቲ ተናግረዋል።የቀርሳ ወረዳ የህብረት ስራ ማህበር ማስፋፊያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነዚብ አባተማም ፤ በዞኑ ህገወጥ የፈር ማዳበሪያ ዝዉዉር እና ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዉ ፤ በመዋቅር የተደራጀ ሌብነት ፈተና መሆኑን አክለዋል።
በዚህም አመራሮችን አሳታፊ ባደረገዉ ህገወጥ ድርጊት ፤ በህይወት በሌሉ ሰዎች ስም ጭምር ማዳበሪያ እንደሚወጣ እና እንደሚሸጥ ገልጸዋል። በቀርሳ ወረዳ 314 ኩንታል ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉንም አክለዋል። በወረዳዉ በህገወጥ መንገድ የሚሸጥ አንድ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከ 10 ሺህ ብር በላይ እንደሚጠይቅ ሀላፊዉ ጠቁመዋል።በጅማ ዞን በርበሬ የሚዘሩ አርሶ አደሮች ወቅቱ እንዳያልፍባቸዉ በሚልም በህገወጥ የማዳበሪያ ግዢ ላይ ተሳታፊ ለመሆን እንደተገገዱም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ሰንዳቦ እና ጊቤ ኬላ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 428 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ተጭኖ ሲጓጓዝ መያዙን ኮማንደር ወንድሙ ሞቲ ተናግረዋል። በተጨማሪም ከቦነያ የህብረት ስራ ማህበር በ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ 95 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መያዙንም አክለዋል።
በተመሳሳይ በኦሞ ናዳ ወረዳ ዋቅቶላ ቀበሌ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ዉስጥ 210 ኩንታል ማዳበሪያ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል። የአፈር ማዳበሪያዉ ሲያጓጉዙ የነበሩ እና አራት የህብረት ስራ ማህበራት ሰራተኞችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና የኮሚኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ወንድሙ ሞቲ ጨምረዉ ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]

🔥1
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።
ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።
ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!
ለዛሬ ምሽት የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
https://www.betsket.com/man-utd-atletico-hoffenheim-cremonese-betting-tips/

ተቋርጦ የነበረው የደሴ-ኮምቦልቻ-ከሚሴ-ደብረብርሐን አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት በዛሬው እለት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለፀ።
በአንድአንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት በተጠቀሱት አካባቢዎች በተወሰነ መልኩ አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአንድአንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት በተጠቀሱት አካባቢዎች በተወሰነ መልኩ አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
😁1
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት ሹመት ፀደቀ!
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ፡፡
ሹመቱ የጸደቀው በውሳኔ ቁጥር 17/2015 በ1 ድምፅ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህ መሰረትም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ አባላት ፡-
1. አዝመራው አንዴሞ --- ሰብሳቢ
2. ነጃት ግርማ (ዶ/ር) ምክትል --- ሰብሳቢ
3. አቶ ሣዲቅ አደም --- አባል
4. አቶ መስፍን እርካቤ --- አባል
5. አብርሃም በርታ ዶ/ር) --- አባል
6. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ተሾመ --- አባል
7. አቶ ወንድሙ ግዛው --- አባል
በመሆን የተሰየሙ ሲሆን÷ የቦርዱ አባላትም በጉባዔው ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከስሕተት ያለመማር ውጤት እንደኾነ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ!
በዐማራ ክልል፣ እስከ ስድስት ወር ተፈጻሚ እንዲኾን በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀውና ዛሬ ሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ “ካለፉት አምስት ዓመታት ስሕተቶቻችን ያለመማራችን ውጤት ነው፤” ሲሉ፣ የቀድሞው የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ተቃውሟቸውን ገለጹ፡፡
በአሁኑ ወቅት፣ በዐማራ ክልል የተስፋፋው ችግር መሠረታዊ ምክንያት፣ የብልጽግና መንግሥት የፖለቲካ አመራር ክፍተት ነው፤ ያሉት አንዱ የፓርቲው መሥራች አቶ ገዱ፣ ራሱ የሚፈጥራቸውን ፖለቲካዊ ችግሮች፣ በወታደራዊ ኀይል መፍታት የመንግሥት ባሕርይ ኾኗል፤ ሲሉ ተችተዋል፡፡
አቶ ገዱ ይህን ተቃውሟቸውን ያሰሙት፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ረቂቅ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የምክር ቤቱ አባላት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን በመደገፍ እና በመቃወም ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፤ ስድስት የምክር ቤቱ አባላት ያሉበት፣ “የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መርማሪ ቦርድ”ም ሠይሟል፡፡
Via VoA

👍1
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

መንግሥት በአማራ ክልል የሚወስዳቸው እርምጃዎች በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸውን ሰዎች እንዲለይ ተጠየቀ!
መንግሥት በአማራ ክልል ያለውን ግጭት ለመቆጣጠር የሚወስዳቸው እርምጃዎች በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸውን ሰዎች በመለየት እንዲፈጸሙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጠየቀ።
በመከላከያ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ውጊያ የሰላማዊ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን ተከትሎም ነው ኢሰመጉ መንግሥት “የሚወስዳቸው ሰላም የማስከበር እርምጃዎች ተመጣጣኝ እና በግጭቱ ተሳታፊዎች ላይ” ተፈጻሚ እንዲሆኑ ነሐሴ 8/2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የጠየቀው።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ነሐሴ 7/2015 ዓ.ም የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ እና በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ሳይለዩ ጥቃት መፈጸማቸውን ኢሰመጉ በመግለጫው አትቷል።ከፍኖተ ሰላም በተጨማሪ በቡሬ ከተማም ነሐሴ 6/2015 ዓ.ም ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱን ገልጾ በዚህም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንደሞቱና የአካል ጉዳት እና ንብረት መውደሙንም ኢሰመጉ በመግለጫው አስፍሯል።
በነዚህ ጥቃቶች የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መግለጫው ባያትትም በፍኖተ ሰላም ከተማ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 25 ሰዎች መገደላቸውንና ከ50 በላይ ሰዎችም እንደቆሰሉ የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሱ ተናግረዋል።ጥቃቶቹን በተመለከተ አንዳንዶች የደረሰው በከባድ መሳሪያ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የተፈጸመ መሆኑንም ነው ለቢበሲ የገለጹት።
በአማራ ክልል እንደ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ሸዋ ሮቢት፣ ደብረ ብርሃን፣ ላሊበላ እና ሌሎችም ከተሞች በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ከሰሞኑ የተኩስ ልውውጦች የነበሩ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ላይ ከባድ መሳሪያዎች ጭምር ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ኢሰመጉ አስታውቋል።ኢሰመጉ በዚህም በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱንም በትናንትናው መግለጫው አስፍሯል። በተጨማሪም የማረሚያ ቤቶችና የፖሊስ ጣቢያዎች ሰበራ ተፈጽሞባቸው የመሳሪያዎች ዝርፊያ እና ከፍተኛ የንብረት መውደም ደርሷል ብሏል።በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት የንጹሃን ሕይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን እና ዘረፋ መፈጸሙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከሰሞኑ አስታውቋል።
በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለቀናት በዘለቀው ግጭት በአማራ ክልል ከተሞች እና የተለያዩ አካባቢዎች እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸው መዘገቡ ይታወሳል።በአማራ ክልል ያሉ ከተሞችን ከፋኖ ታጣቂዎች ነጻ ማድረጉን መንግሥት ከሰሞኑ ማስታወቁንም ተከተሎ በአንዳንድ አካባቢዎች አንጻራዊ መረጋጋት መታየቱን የጠቆመው የኢሰመጉ መግለጫ አሁንም ውጥረት እና ስጋት ያለባቸው አካባቢዎችም አሉ ብሏል።
Via BBC

ከምርት ጥራት በታች የሚያመርቱ 32 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ!
በ2015 በጀት ዓመት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ 382 ፋብሪካዎች ላይ ባተደረገ የኢንስፔክሽን ሥራ የ32 ፋብሪካ ምርቶች ጥራት ከደረጃ በታች ሆኖ በመገኘቱ እርምጃ መውሰዱንየንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
እርምጃ የተወሰደባቸው 25 የልብስ ሳሙና፣ ውኃ፣ ሽንሽን ቆርቆሮ፣ ሚስማር፣ አርማታ ብርት፣ non-carbonated fruit juice፣ ሶኬት እና ዋይን ፋብሪካዎች የማምረት ሂደቱን አቁመው የማስተካከያ ሥራዎችን እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን፤ 7 አኩሪ አተር ማከፋፋያ፣ የውኃ እና የሳሙና የፋብሪካዎች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተነግሯል።
ሸማቹን ህብረተሰብ ጥራታቸውና ደህንነታቸው ካልተረጋገጡ ምርቶች በመከላከል ጤናና ደህንነቱ እንዲጠበቅ ለማድረግ በቀጣይም በየፋብሪካዎቹ ላይ የሚደረገው የምርት ጥራት ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።ሚኒስቴሩ በፋብሪካዎቹ ላይ እርምጃ መውሰዱን ይግለጽ እንጂ፤ በየትኞቹ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃው እንደተወሰደ በዝርዝር ይፋ አላደረገም፡፡

በአማራ ክልል የባጃጅ ትራንስፖርት ክልከላ በተጣለባቸው ከተሞች አገልግሎቱ ነገ እንዲጀመር ዕዙ ፈቀደ!
በአማራ ክልል ክልከላ በተጣለባቸው ስድስት ከተሞች ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀምሩ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፈቀደ።ዕዙ በሰጠው ቁጥር ሁለት ወቅታዊ መረጃ ዛሬ ማለዳ ላይ ባደረገዉ ግምገማ የሁለተኛዉ ዙር ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቁና እየተወሰደ ባለዉ ርምጃ አብዛኞቹ አካባቢዎች ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሱ መሆናቸዉን አረጋግጧል፡፡
በሁሉም አካባቢዎች ከልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ዉይይት መጀመሩን፣ የመንግሥት፣ የግልና የማኅበረሰብ አገልግሎቶች ወደ መደበኛ ሥራቸዉ እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊታችን እያሳየ ያለው አቀባበል፣ የስንቅና የማበረታቻ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን፣ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ሥራ እንዲጀምሩ ያለው ፍላጎትና እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ዕዙ አረጋግጧል፡፡
አርሶ አደሩ ወደ መኸር አዝመራ ሥራዉ እየተመለሰ እንዲሁም የግብርና ግብአቶችን ወደየአካባቢዎቹ ለማጓጓዝ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን ዕዙ ገምግሟል።የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥብቅ መመሪያ የሰጠው ዕዙ፤ ክልከላ በተደረገባቸው ከተሞች የባጃጅ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት እንዲጀምሩ ከኅብረተሰቡ የቀረበዉን ጥያቄ መርምሮ ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡
ከዚህም ጋር በማያያዝ ክልከላዉ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ የባጃጅ ባለቤቶችና አሽካርካሪዎች የጽንፈኛ ቡድኑን አባላት፣ የዘረፉትን ንብረቶችና የትኛዉንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ከማጓጓዝ እንዲቆጠቡና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ይህንን ተላልፈዉ በተገኙት ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማሕቀፍ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ መስጠቱን በመግለጫው አመልክቷል።

👍2
ከተበተኑ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላት መካከል፤ “አብዛኛዎቹ” ታጣቂ ቡድኖችን መቀላቀላቸውን የሰላም ሚኒስትሩ ገለጹ!
በአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ስራ ከተጀመረ በኋላ 50 በመቶ የሚሆኑ የልዩ ኃይል አባላት “እንደተበተኑ” እና ከእነዚህ ውስጥ “አብዛኛዎቹ” ታጣቂ ቡድኖችን እንደተቀላቀሉ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ። በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት የተጀመረው፤ ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ “ዘግናኝ የሚባል ጥቃት መክፈታቸውን” ተከትሎ እንደሆነም ገልጸዋል።
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ ይህንን የተናገሩት፤ በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ትላንት ሰኞ ነሐሴ 8፤ 2015 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባው ካፒታል ሆቴል በተደረገ ውይይት ላይ ነው። አቶ ብናልፍ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በመሩት በዚህ ስብሰባ 16 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
አቶ ብናልፍ በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ባቀረቡት ማብራሪያ፤ መንግስት በአማራ ክልል ያጋጠመው ግጭት “ዝም ብሎ በድንገት የተፈጠረ” ነው የሚል እምነት እንደሌለው እና “በተለያዩ ጊዜ የሚነሱ እና እየተደመሩ የመጡ ችግሮች የፈጠሩት” እንደሆነ አስረድተዋል። የሰላም ሚኒስትሩ በዚሁ ማብራሪያቸው ላይ በአማራ ክልል ለተፈጠረው ችግር ምክንያት የሆኑ ካሏቸው “የህዝብ ጥያቄዎች” ውስጥ፤ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ፣ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና የእኩልነት ጥያቄ እንዲሁም “የፈለጉትን የፖለቲካ ሀሳብ ለማራመድ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖር” የሚሉት ይገኙበታል።
ዝርዝሩ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11795/
Via Ethiopia Insider

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን አቅጣጫ ተሰጠ::
በ2016 የትምህርት ዘመን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ነሃሴ 09/2015ዓ. ም በተጻፈ ደብዳቤ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
እስካሁን በመሰጠት ላይ ያሉ የቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በ2016 ዓ.ም በዝርዝር ተፈትሸውና ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ልየታ ጋር መጣጣማቸውን የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በጻፉት ደብዳቤ የታቀዱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ለመክፈት የሚደረጉ ጥናቶች ባሉበት እንዲቆዩ፣ መጪው የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ እንዲሁም በቦርድ በጸደቁና በትምህርት ሚኒስቴር በተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ አሳስበዋል።
አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች ባሉበት እንዲቆዩ የተወሰነው የትምህርት ፕሮግራሞች ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮና ትኩረት ጋር መጣጣማቸው እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን የመክፈት ስራ መግታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በ2016 የትምህርት ዘመን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ነሃሴ 09/2015ዓ. ም በተጻፈ ደብዳቤ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
እስካሁን በመሰጠት ላይ ያሉ የቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በ2016 ዓ.ም በዝርዝር ተፈትሸውና ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ልየታ ጋር መጣጣማቸውን የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በጻፉት ደብዳቤ የታቀዱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ለመክፈት የሚደረጉ ጥናቶች ባሉበት እንዲቆዩ፣ መጪው የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ እንዲሁም በቦርድ በጸደቁና በትምህርት ሚኒስቴር በተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ አሳስበዋል።
አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች ባሉበት እንዲቆዩ የተወሰነው የትምህርት ፕሮግራሞች ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮና ትኩረት ጋር መጣጣማቸው እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን የመክፈት ስራ መግታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
Betስኬት ለስፖርታዊ ውርርዶች የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይዞ ወደናንተ መጥቷል።
ስፖርታዊ ውርርድ(ቤቲንግ) መጫወት ሚያዘወትሩ ከሆነ ይህ ዌብሳይት ጨዋታዎችን ከቁጥራዊ መረጃዎች በመነሳት በጥልቀት በመተንተን የትኛውን ቡድን ወይም Possibility መምረጥ እንዳለብዎ ስራዎን እናቀልሎታለን፤ ትንተናዎቻችንን ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ።
ወደፊትን መገመት ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለእርሶ ለማቅለል ተግተን እንሰራልን!
ለዛሬ ምሽት የመረጥንላችሁ ጨዋታዎች:
👇👇
https://rb.gy/d76bx

በትግራይ ክልል 16 ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መታየቱ እና በአዝርእትና የተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።
የትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው መነሻው የአፋር ክልል በረሃዎች ያደረገ የበርሃ አንበጣ መንጋ በትግራይ ሶስት ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች መንሰራፋት የጀመረው ካለፈው ሐምሌ 20 ጀምሮ ሲሆን እስካሁን ባለው በ79 የክልሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚገኝ 35 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈኑ ተነግሯል።
የትግራይ ምስራቃዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች የበርሃ አምበጣ መንጋ እየታየባቸው መሆኑ የገለፁት በትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የአዝርእት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት አቶ ገብረህይወት ሃይለስላሴ ከሐምሌ መጨረሻ ወዲህ ባለው ግዜ የበርሃ አንበጣ መንጋው ሽፋን እየሰፋ እና አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ገልጸዋል።
የክልሉ ባለስልጣናት የበርሃ አንበጣ መንጋው ለመከላከል ህዝብ እያደረገው ካለ እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ የፌደራል መንግስቱም በኬሚካል አቅርቦት እና ሌሎች መንገዶች እየደገፈ መሆኑ የገለጹ ሲሆን፥ በቀጣይነት ግን የበርሃ አንበጣ መንጋው ከምንጩ የማድረቅ ስራ በሚፈለፈልበት አፋር ክልል ሊከናወን እንደሚገባ፣ ይህም ለፌደራሉ መንግስት እና ለFAO ማሳወቃቸውን በትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የአዝርእት ጥበቃ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ሲል ዶይቸ ቨለ ዘግቧል።

🌼 🎁የአዲስ አመት ገጸበረከት ከ ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር የ15% ቅናሽ ጋር እና ከልዩ ልዩ ስጦታዎች ጋር ይዞላችሁ ከተፍ ብሏል 🌼🎁🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🎁ቴዲ አበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር ሀዋሳ 🌼🎁እጅግ ውብና ማራኪ የ2016 የፋሽን ጥግ የሆኑ የፈርኒቸር ውጤቶች አቅርበንሎታል 🤗
ስለሆነም ከወዲሁ ለበአሉ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ልዩ ዝግጅት አድርገን ለውድ ደንበኞቻችን እነሆ ብለናል 🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
ከ ምናቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ፡-
🌼የሌዘር እና የጨርቅ ሶፋዎች
🌼 የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን
🌼 ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን
🌼 የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር
🌼የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን
🌼 ዘመናዊ ኪችኖች
🌼 የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን፡፡
ልዩነታችን
❤ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን ማደሳችን፣
❤ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኀላ ከአነስተኛ የገንዘብ ጭማሪ ጋር በአዲስ እቃ መለወጣችን ከሌሎች ልዩ ያደርገናል
❤ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
❤ በማንኛውም በዓላት ወቅት 15% የዋጋ ቅናሽ የምናደርግ መሆናችን፣
❤አድራሻችን፡-ሀዋሳ ከአረብ ሰፈር ወደ እርሻ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ከራስ ጤና ሆቴል ፊትለፊት ከንግድ ባንክ አንደኛ ህንጳ ለይ እንገኛለን
በስልክ ቁጥሮቻችን ፡0924711168 /0912340763 ሀሎ ይበሉን
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገጳችንን ይጎብኙ
: 👇👇👇👇 https://tttttt.me/tedyaberalanganofurniturehawassa

የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከ3 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ!
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ የአዋሽ ወንዝ ከልክ በላይ መሙላቱን ተከትሎ፤ 657 አባወራዎች ወይም 3 ሺሕ 156 ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የምዕራብ ሸዋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ መምሪያ አደጋው የደረሰው ነሐሴ 05/2015 ሌሊት ላይ መሆኑን ገልጾ፤ ነዋሪው ከቤቱ ወጥቶ በመሸሹ በሰው ሕይወት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳላደረሰ አስታውቋል፡፡
ነዋሪው ነፍሱን ለማዳን ባደረገው ሽሽት ከቤት ባዶ እጁን በመውጣቱና፤ መኖሪያ ቤቱ በወንዙ መሙላት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ አሁን ላይ ከፍተኛ ለሆነ የምግብ እና መጠለያ ችግር መዳረጉ ተጠቅሷል፡፡የወረዳው አስተዳደር እና የምዕራብ ሸዋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ መምሪያ፤ ተጎጂዎቹን ለመርዳት ጥረት ቢያደርጉም ከችግሩ ስፋት አንጻር በበቂ አለመሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ጎርፉ በ500 ሄክታር መሬት ላይ የለማን ሰብል ሙሉ ለሙሉ ያወደመ ሲሆን፤ በአርሶ አደሮች የወደፊት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀና እና መሬቱን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ እንደሆነም ተነግሯል፡፡አደጋው ከተከሰተ አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ አስቸኳይ ድጋፍ ለተፈናቃዮቹ ለማድረግ ቸልተኝነት ታይቷልም ነው የተባለው።
በተጨማሪም ሰዎች ከአደጋው ሸሽተው በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያሉ በመሆኑ፤ ለተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩም ተጠቁሟል።ለተጎጂዎቹ ምግብ፣ ልብስ፣ ጊዜያዊ መጠለያ፣ የንጽሕንና መጠበቂያ እና ሉሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶች የሚያስፈልግ በመሆኑም ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።