የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመላው ሀገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች “ያላንዳች ቅደመ ሁኔታ ቆመው” “በአስቸኳይ” በምክክር እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ ባለድርሻ አካላትን “በማቀራረብ፣ የልዩነት አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለማወያየት እና ለማመካከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን” አስታውቋል።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የሚመለከታቸው አካላት ልዩነቶቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ የጠየቀው፤ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 2፤ 2015 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ በንባብ ባሰሙት መግለጫ፤ ለሀገራዊ ምክክሩ የተሳታፊዎች የተሳታፊዎች ልየታ እየተከናወነ ባለበት ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አየታዩ ያሉ “ደም አፋሳሽ ግጭቶች” የኮሚሽኑን ስራ “አዳጋች እያደረጉበት ይገኛሉ” ብለዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa

‹‹በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ድንገቴ ሳይሆን ለዓመታት የታመቀ ብሶት፣ የመጠቃት ስሜትና ተስፋ መቁረጥ የወለደው ነው›› - ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ(ኢዜማ) ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ‹‹ በዚህ ወቅት በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ድንገት የተከሰተ ሳይሆን መንግሥት ሃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ባለመወጣቱ የተከማቹ ሀገራዊ የፖለቲካ ትኩሳቶች የግለታቸው ጫፍ ላይ ሲደርሱ የተፈጠረ ነው ›› ሲል ገልፀለታል፡፡ፓርቲው በመግለጫው ‹‹ ይህ ለዓመታት የታመቀው ብሶት፣ የመጠቃት ስሜት እና ተስፋ መቁረጥ ገደፉን አልፎ ክልሉን አሁን ላለበት ሁኔታ ዳርጎታል ›› ሲልም አመልክቷል፡፡
‹‹ የዚህ ቀውስ መሠረታዊ ምክንያት በብልፅግና ውስጥ ያለው የጋራ ርዕይ መጥፋት፣ በየክልሉ እርስ በእርስ በመጓተት ላይ ያሉ ካድሬዎች የሚመሩት የመንግሥት የአስተዳደር ድክመትና በደል እንደኾነ ሊታወቅ ይገባል ›› ባይ ነው - ኢዜማ፡፡
‹‹ችግሩን ለማባባስ ፅንፈኛ የዘውጌ ፖለቲካ አስተሳስብን የሚያቀነቅኑ ታጣቂ ኃይሎች በጠራራ ፀሀይ ሰዎችን በመግደል ሽብርና ፍርሃት በመንዛት እንዲሁም ከግል ትርፋቸው ውጪ አንድ ስንዝር አርቀው ማሰብ የማይችሉ ያላቸው ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋቸው መሆኑን ›› አመልክቷል፡፡ፓርቲው በመግለጫው እነዚህ ‹‹ ፅንፈኛ ›› እና ‹‹ አርቀው ማሰብ የማይችሉ ›› ያላቸው ባለሃብቶች እነማን እንደሆኑ ግን በግልፅ አላስቀመጠም፡፡
‹‹ በሰላማዊ መንገድ የሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ባልተሰጣቸው ቁጥር መፍትሔዎች ከጉልበት ይመነጫሉ!›› የሚል አስተሳስብ መሬት እየያዙ እየመጡ መሆኑ ያሰጋኛል የሚለው ኢዜማ ‹‹ በክልሉ የተከሰተውን ቀውስ ከማርገብ ጎን ለጎን መዋቅራዊ የሆነ ሀገር አቀፍ የዘላቂ ሰላም መላ እንዲበጅ ›› ጠይቋል፡፡‹‹ይህ ቀውስ መንግስት ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ የመጣ መሆኑን ተገንዝቦ በግልጽ ራሱን ተጠያቂ በማድረግ ማህበረሰቡን በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ ›› ሲልም አበክሮ አሳስቧል፡፡
‹‹መንግስት የሚዘውራቸው ›› ያላቸውና በስም የጠራቸው ‹‹ እንደ ፋናና ዋልታ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የመንግስት ብቻ ሳይሆን የችግሩን ምንጭን ከመሰረቱ በማሳየት በደሎች ተዳፍነው እንዳይቀሩ የመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ›› ሲልም ጠይቋል፡፡‹‹መንግሥት ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን አገናዝቦ ሀገርአቀፍ የዘላቂ ሰላም ፍኖተ-ካርታ በማዘጋጀት መዋቅራዊ እና ሕጋዊ የሰላም ግንባታ በአስቸኳይ ሊተገብር እንደሚገባም ›› ገልጿል፡፡
የፌደራልና የክልል መንግስታት ላለፉት አምሥት ዓመታት የፈጸሟቸውን ‹‹ የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያጠብቡ ›› ያላቸው ተግባራት በመፈተሽ የሀገሪቱን የፖለቲካ ብዝኃነት የሚያንፀባርቅ የአሳታፊነት መርህን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውን አስታውሷል፡፡መንግስት በሁሉም አካባቢዎች ማኅበረሰቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማኅበራት፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለማዳመጥ የሚያስችል መድረክ ማመቻቸት ይተበቅበታል ሲልም አሳስቧል፡፡
‹‹ ህዝቡም በበደል ስሜትና በቁጭት ተነሳስቶ አውዳሚ ወደሆነ መንገድ እንዳይጓዝ ደግሞ ደጋግሞ እንዲያስተውል ›› ሲል የጠየቀው ፓርቲው ‹‹ ከአብራኩ የወጣውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሚገባው ክብር ልክ በመረዳት አላስፈላጊ መስዋዕትነቶች እንዳይከፈሉ የሚቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ ›› ጠይቋል፡፡በአራት ገፅ የተቀነበበው የኢዜማ መግለጫ ለታጠቁ አካላት ባስተላለፈው መልዕክት ‹‹ ታጣቂ ኃይሎች እንታገልለታለን ለምትሉት ማህበረሰብም ሆነ ክልል ከመሳሪያ አፈሙዝ የሚወጣ ዘላቂ ሰላም እንደማይገኝ በመረዳት ወደሰላማዊ መንገድ እንድትመጡ ›› ሲልም ጥሪውን ምክረ ሀሳቡን አቅርቧል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረዉ ግጭት ምክንያት የልማት ባንክ የተበላሸ ብድር 11 ቢሊዮን ብር ደርሶ እንደነበር ተገለፀ።
በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ብሔራዊ ባንክ የእፎይታ መመሪያ እስኪያወጣ ድረስ፣ ወደ 11 ቢሊዮን ብር የተበላሸ ብድር እንደነበረዉ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ዩሐንስ አያሌዉ አስታዉቀዋል።በትግራይ የነበሩ ፕሮጀክቶች ከጦርነቱ በፊት በአብዛኛው ጤናማ የሚባሉ እንደነበሩ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ባንኩ 43 በመቶ የተበላሸ ብድር በነበረበት ወቅት 10 በመቶ ብቻ ድርሻ እንደነበራቸዉ ተናግረዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኃላ ግን ግንኙነቱ ስለተቋረጠ ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ ተበላሸ ብድር ገብተዋል ብለዋል በማብራሪያቸው።የተበላሸ ብድር የሚባለዉ ብድር መክፈያ ጊዜዉ እየተቆጠረ ሲሆን ሶስት ደረጃዎች አሉት፣ ያንን መተግበር ሳይቻል በሶስት ዓመት መክፈል ካልተቻለ ወደ ተበላሸ ብድር ዉስጥ እንደሚገባ አንስተዋል።
ከፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት በኃላ በትግራይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉበትን መገምገሙን የተናገሩት አቶ ዩሐንስ፣ ብዙዎቹ ሙሉ ለሙሉ ያልተጎዱበትና ጥሩ ሁኔታ ላይ መኖራቸዉን ገልጸዋል።አሁን ላይ በትግራይ ያሉ ፕሮጀክቶች 80 በመቶ ወደ ስራ የገቡና ብድር በማግኝት ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸዉን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር የፎይታ ግዜ እንደሰጣቸዉ የሚገልፁት አቶ ዩሐንስ፣ በዚህ ዓመት ዉስጥ ባንኩም ድጋፍ እያደረገላቸዉ ወደ ጤናማ መንገድ ለማስገባት እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል።ባለፈዉ ዓመት በአማራ እና አፋር ክልሎች በተመሳሳይ መንገድ ተሰርቶ በርካታ ፕሮጀክቶች ከተበላሸ ብድር ወጥተዉ ወደ ጤናማ መንገድ መግባታቸዉንም ገልፀዋል።
[Ethio FM]

👍2
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጦት የከረመውን እርዳታ ‹‹ ከብዙ ትችት ›› በኋላ በዝግታ መጀመሩን ይፋ አደረገ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአምስት ወራት ገደማ በኢትዮጵያ አቋርጦት የቆየውን ሰብዓዊ ረድዔት ‹‹ በአነስተኛ መጠን ›› መጀመሩን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ ከግብረሰናይ ድርጅቶችና የጤና ባለሙያዎች በኩል ‹‹ በመቶዎች የሚቆጠሩት በረሃብ በሚሞቱበት ሀገር እርዳተውን ማቋረጡን ኢ-ሞራላዊ ›› በማለት ሲተቹ መክረማቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡ድርጅቱ ይህን ‹‹ በዝግታና አነስተኛ መጠን ›› የጀመረው እርዳታ ‹‹ ለሙከራ ›› መሆኑን ጠቅሶ ለዚህም መንግስት በሂደቱ ላይ ሚናውን ስለመወጣቱ ዕውቅና ችሯል፡፡
ልክ እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ሁሉ ሰብዓዊ ረድዔቷን ያቋረጠችው ዩናይትድ ስቴትስ፣ እርዳታው በተቋረጠበት እንደሚቀጥል ገልፃ፣ ጎን ለጎን ‹‹ ለረዥም ጊዜ በክልል ባለስልጣናት ቁጥጥር ስር የሚገኘው አሰራርን ለማሻሻል የሚደረገው ድርድርን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንደምታካሄድ ›› አመልክታለች፡፡
ሁለቱ ተቋማት እርዳታ በማቋረጣቸው ምክንያት ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀጥር አንድ ስድስተኛው ወይም 20 ሚሊዮኑ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ የጠቀሰው የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ከዚህ በተጨማሪ ስምንት መቶ ሺህ ያህሉ ስደተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአሶሼትድ ፕሬስ በፅሑፍ በሠጠው ምላሽ ‹‹ በትግራይ ክልል በአራት ቅርንጫፎች፣ ለ100ሺህ ያህል ሰዎች እ.አ.አ. ከሐምሌ 31 2023 ወዲህ መጀመሩን ›› አመልክቷል፡፡
ድርጅቱ በአዲ አሰራሩ ምዝገባዎችን የሚያከናውነው ‹‹ በዲጂታል ›› መሆኑን ጠቅሷል፡ ለሰብዓዊ ረድዔት ሰራተኞችም ስልጣና ሰጥቼያለሁ ብሏል፡፡ ይህ አዲስ ያለው አሰራር በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍልም እንደሚጀምር የገለፀው ድርጅቱ ‹‹ ሰብዓዊ ረድዔቶች ›› ለሚያስፈልጋቸው ብቻ እንዲደርሱ ያደርጋል የሚል ተስፋ መሰንቁንም ገልጧል፡፡
✍Asham

👍1
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ስለተፈጠረው የስርጭት መስተጓጎል ያለው:
1.
የአሚኮ ቴሌቪዥን በመጠነኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የስርጭት የጥራት መጓደል ነበር ባለሙያዎቻችን እንዲስተካከል ማድረግ ችለዋል።
2.
በውስን የራዲዮ ማሰራጫዎች(ትራንስሚተር)ላይ በኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት ስርጭታቸው መቆራረጥ ያጋጠመ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሟላ ስርጭት እንዲኖር አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ ነው።

አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ!
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የፓርላማ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር በጠበቆቻቸው አማካኝነት “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ። አቤቱታው የቀረበለት ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፤ የፌደራል ፖሊስ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጥ አዝዟል።
የአቶ ክርስቲያን እና ዶ/ር ካሳ ጠበቆች አቤቱታቸውን ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 2፤ 2015 ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ ያለመከሰስ መብት ያላቸው ደንበኞቻቸውን ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ “ያለምንም ፍርድ በእስር ላይ ያቆያቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው። በጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እና ሰለሞን ገዛኸኝ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታ፤ በምክር ቤት የህዝብ ተወካዮቹ የተያዙበትን መንገድ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።
በአንድ ገጽ የተዘጋጀው ይህ አቤቱታ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ባለፈው ሳምንት አርብ ከመኖሪያ ቤታቸው “እየተደበደቡ ተይዘው” በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን አትቷል። ዶ/ር ካሳ ተሻገርም በዚሁ ቀን ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው፤ በተመሳሳይ ቦታ ታስረው እንደሚገኙ በአቤቱታው ላይ ሰፍሯል። የፌደራል ፖሊስ ሁለቱንም ግለሰቦች የያዛቸው “ለጥያቄ እፈልጋቸዋለሁ” በሚል መሆኑንም በአቤቱታው ተመላክቷል።
Via Ethiopia Insider

✅✅✅ "Do or Die..!" ✅✅✅
የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!
ቤት ...❓
መሬት...❓
መካዝን...❓
ኢንዳስትሪ...❓
ኢንቨስትመንት...❓
ሪል ስቴት ..❓
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..❓❓❓
አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው
..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..
መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!
+251937736408
https://tttttt.me/shger21
Inbox @FikreabAmanu
ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0

"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665

Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

በመዲናዋ በሞተር ብስክሌቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ!
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማዋ ጥሎት የነበረውን የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እግድ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን አስታውቋል፡፡ቢሮው ሐምሌ 27/2015 ባወጣው መመሪያ፤ እስከ ዛሬ ነሐሴ 3/2015 ድረስ የሞተር ብስክሌቶችን በከተማዋ ማሽከርከር እንደማይቻል መግለጹ ይታወሳል፡፡
እገዳው ዛሬ ማብቂያ ጊዜ መሆኑን ተከትሎ ቢሮው ባሰራጨው መልዕክት፤ እግዱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።ክልከላው የጸጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን እንደሚያካትት የተገለጸ ሲሆን፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እግዱ እስኪነሳ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ይህንን መልዕክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ በከተማዋ እገዳው የተጣለበትን ምክንያት አስመልክቶ እስካሁን የሰጠው ማብራሪያም ይሁን ገለጻ የለም።
[Addis Maleda]

አየር መንገዱ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ እንደሚጀምር ገለጸ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4/2015 የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ መንገደኞች በአቅራቢያቸ በሚገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከሉ (6787/+251116179900) በመደወል መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከተታይ ቀናት፤ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎችን መሰረዙን በትናንትናው ዕለት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

‹‹ መላው የአማራ ሕዝብ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚያጠለሹ መልዕክቶችን ይፀየፍ ›› - አብን
ማህበራዊ መሠረቱ የአማራ ሕዝብ መሆኑን የሚገልፅው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ለአማራ ሕዝብ የተለያዩ ጥሪዎችን አቅርቧል፡፡
በዚህም ‹‹ መላው የአማራ ህዝብ ከሌላው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነት እሴቶች ከሚንዱ ቅስቀሳዎች፤ በራሱ እና በልጅቹ የተመሰረቱ ተቋማትን በተለይም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሚያጠለሹ መልዕክቶች እንዲሁም የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ረፍት እንዲያጣ ከሚመኙ አካላት በስልት የሚሰጡትን አጀንዳዎች እንዲፀየፍ ›› ጠይቋል፡፡
አክሎም ‹‹ ወደ ሰላም መድረክ የሚያመሩ መንገዶችን ሁሉ ለመጥረግ አቅሙ የፈቀደውን ርብርብ እንዲያደርግ በአደራ ጭምር ›› አሳስባለሁ ብሏል፡፡አብን በክልሉ ላይ አለኝ ያለውን አቋም በ16 ነጥቦች ዘርዝሮ አንፀባርቋል፡፡
በዚህም ‹‹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአጭር ግዜ እንዲያልቅ፣ አዋጁን ለማስፈፀም የተሰማሩ አካላትም ከማንነት ተኮር ፍረጃዎች፣ ወከባዎች፣ ከዘፈቀደ እስራትና አካላዊ ጥቃቶችን ›› እንዳይፈፅሙ አሳስቧል፡፡
‹‹ የፌደራሉ መንግስት አካላት ሚና ለህዝቡ የሚመጥን አስተዳደር እንዲዋቀር መደላድል በመፍጠር እንዲወሰን፣ ህዝባዊ የውይይት መድረኮችም እንዲፈጠሩ፣ ህዝቡም የሰላም ጥረቶችን እንዲደግፍ ›› ጥሪ አቅርቧል። አክሎም ‹‹ ክልሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተዳደር በአፋጣኝ እንዲወጣም ›› ጠይቋል፡፡መግለጫው ‹‹ መንግስት ለድርድር እና ንግግር ጥሪ እንዲያደርግ ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡

በጎንደር በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው እና ሆስፒታሉ የመድኃኒት እና የኦክሲጂን እጥረት እንዳጋጠመው ተገለጸ!
በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ሆስፒታል ውስጥ የደም፣ ኦክስጂን እና የተወሰኑ መድኃኒቶች እጥረት ማጋጠሙን የሆስፒታሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ።በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ግጭት እና የተኩስ ልውውጥ ከገጠማቸው የአማራ ክልል ከተሞች መካከል የጎንደር ከተማ አንዷ ስትሆን፣ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በከተማዋ እና በዙሪያዋ ባለፉት ቀናት በነበረው ግጭት አብዛኞቹ ሰላማዊ የሆኑ ወደ 20 የሚደርሱ ሰዎች እንደሞቱ እና ከ200 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጎንደር ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ወደ ጎንደር ሆስፒታል በጥይት ተመትተው ከመጡ ሰዎች መካከል የ16 ዓመት ታዳጊ እንደሚገኝበት እና ተጎድተው ከመጡት መካከል በእድሜ ትልቅ የሆኑት ደግሞ የ50 ዓመት ሴት መሆናቸውን አንድ ዶክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ በኋላ የሞቱ ሰዎች አብዛኛዎቹ “ሰላማዊ ሰዎች እና ተዋጊዎች” መሆናቸውን የሕክምና ባለሙያዎቹ ጠቅሰው፣ እስካሁን ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ የመጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አለመኖራቸውን ተናግረዋል።በግጭቱ የተነሳ በከተማዋ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በመስተጓጎላቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚገኙ ህሙማን እጅግ አስፈላጊ የሆኑት የደም፣ የኦክስጂንእና የመድኃኒት አቅርቦቶች እጥረት ማጋጠሙን የጎንደር ሆስፒታል ምንጮች ተናግረዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሆስፒታሉ ባጋጠመው የኦክስጂን እጥረት ምክንያት ምንም ዓይነት ቀዶ ሕክምና ማከናወን አለመቻሉን የሆስፒታሉ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።የቢቢሲ ምንጮች ጨምረውም ለቀናት በከተማዋ ባጋጠመው አለመረጋጋት የተነሳ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለመኖሩ በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የሚቀርብ ምግብ እጥረት ማጋጠሙንም ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንዳሉት በከተማዋ ለሦስት ቀናት በዘለቀው ግጭት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል ለማድረስ ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩ የተጎዱ ሰዎች በቃሬዛ መምጣታቸውን አመልክተዋል።
Via BBC

አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!
አርቲስት አብነት ዳግም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ተዋናይ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
አርቲስት አብነት ዳግም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ተዋናይ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፊታችን ነሐሴ 8 አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ የፊታችን ነሐሴ 8 ቀን ለአባላት የአስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ሰሞኑን በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ የሚኒስትሮች ም/ቤት በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ) መሰረት ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 መደንገጉ ይታወሳል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 2 (ሀ) እና (ለ) መሠረት በሚኒስትሮች ም/ቤት የሀገሪቷን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ቢደነገግም ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡
በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 58 (4) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 (1) ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሠረት ለምክር ቤቱ አማካሪ ኮሚቴ አጀንዳው ቀርቦ በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን÷ ምክር ቤቱ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡
የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው።
በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ የተማረረ በመሆኑ፣ የህግ አስካባሪ አካላት ተልዕኮዋቸውን በስኬት እንዲወጡ ተገቢውን ድጋፍ አድርጓል። ጠቅላይ መመሪያ እዙም የክልሉ ህዝብ ላደረገለት ትብብር ምስጋናውን ያቀርባል።
በአሁኑ ሰዓት ከተሞቹ ከዘረፊዉ መንጋ ስጋት ነጻ ሆነዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት በየሥርቻው የተራረፈውን ዘራፊ በማጽዳት ላይ ናቸው። ማኅበረሰቡም መረጃ በመስጠት፣ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ለዚህ ስራ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሽንፈት የተከናነበው የፅንፈኞች ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ቅርስ ቦታዎችና የእምነት ተቋማት በመግባት ለመደበቅ እየሞከረ ነው።
የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት ህግ፣ ሥርዓትና ሞራልን ባከበረ መንገድ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛል። በቀጣይም የመጨረሻውን የማጽዳት እና የመልቀም ተግባር በማከናወን ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ይደረጋል።
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የጠቅላይ መምሪያ ዕዙ እስካሁን 14 ተጠርጣሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ወደፊትም እንደሁኔታው በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ ዕቅድ የተያዘው ከተሞቹን ከዘራፊ የጥፋት ቡድን የማጽዳቱ ተግባር እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣
1. ከሐሙስ ነሐሴ 4 ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች መደበኛ የአውሮፕላን በረራ ይጀመራል፤
2. ከባጃጅና ከሞተር ሳይክል በስተቀር ሁሉም ዓይነት የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፤
3. የመንግሥት፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የንግድ፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ. ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።
በዚሁ አጋጣሚ የክልሉ ሕዝብ ራሱን ከዘራፊውና ከጽንፈኛው መንጋ በመነጠልና በመከላከል፣ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመሰለፍ ላደረገው ተጋድሎ ዕዙ በድጋሚ ምስጋናውን ያቀርባል።
ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓም
አዲስ አበባ