እስራኤላዊ ዜግነት ያላቸውን የ80 ዓመት አዛውንት በማገት 1.5 ሚሊዮን ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ በሰው ማገት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ እጅ ከፈንጅ መያዙን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር ፈንታሁን አስፋው እንዳስታወቁት ማሬ መኳንንት የተባለው ግለሰብ እስራኤላዊ ዜግነት ያላቸውን የ80 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑትን አቶ ውዱ አደባባይ የተባሉትን ግለሰብ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሻሁራ ከተማ ወደ ፍንጅት ቀበሌ ጫካ ውስጥ በመውሰድ አግተው 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ድርድር ሲደረግ መቆየቱን አንስተዋል።
በዚህም የአለፋ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ከዞኑ የፖሊስ መምሪያ ጋር ተቀናጅቶ ባደረገው የኦፕሬሽን ስራ የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የሆነውን ማሬ መኳንንትን በቁጥጥር ስር ማድረጉንና 2 ግብረ አበሮቹ ለጊዜው ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡ምክትል ኮማንደሩ አክለውም ኦፕሬሽኑ የተሳካ እንዲሆን ለተባበሩ የህበረተሰብ ክፍሎችና የፖሊስ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበው ህብረተሰቡ ከእንዲህ አይነቱ ወንጀል ራሱን ማራቅ እንዳለበት አሳስበዋል ሲል የወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል፡፡
[ማዕከላዊ ጎንደር ዞን]
@YeneTube @FikerAssefa

👍1
አዲሱ 12ኛ ክልል፤ በሳምንቱ መጨረሻ ከነባሩ ደቡብ ክልል ስልጣን ሊረከብ ነው!
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከመጪው አርብ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሚያደርገው መደበኛ ጉባኤ፤ በህዝበ ውሳኔ ለተመሰረተው 12ኛው አዲስ ክልል ስልጣን እንደሚያስረክብ የምክር ቤቱ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ዘውዱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።ከስልጣን ርክክቡ በኋላ የመዋቅር፣ የህገ መንግስት እና የስያሜ ለውጦችን እንደሚያደርግ የሚጠበቀው የነባሩ የደቡብ ክልል የወደፊት አደረጃጀት ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ላይ እንደማይነሳ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
አዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል የኢፌዴሪ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የወሰነው፤ ከአንድ ወር በፊት ሰኔ መጨረሻ ላይ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ ነበር። ይህ ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር “ነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አዲስ ለተመሰረተው ክልል በአፋጣኝ የስልጣን ርክክብ እንዲያደርግ አቅጣጫ ተቀምጧል” ማለታቸው ይታወሳል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ይህን ቢሉም የደቡብ ክልል የስልጣን ርክክቡን ለማድረግ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉባኤ በኋላ አንድ ወር ፈጅቶበታል። በኢትዮጵያ ካሉ ክልሎች የዚህን ዓመት ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤ ለማካሄድ የመጨረሻ የሆነው የደቡብ ክልል፤ እስከ መጪው እሁድ ሐምሌ 30 በሚቆየው ስብሰባው ከስልጣን ርክክብ በተጨማሪ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት የ2015 ሪፖርት ይገመግማል ተብሏል።የክልሉ ፍርድ ቤቶች እና የኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርትም በምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
Via Ethiopia Insider

ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ ስልሳ ሦስት ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ልዩ ሥሙ ቱሉ ሚልኪ በተባለ አካባቢ ሰኞ ሐምሌ 24/2015 በሸኔ ታጣቂ ቡድን ስልሳ ሦስት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የደጀን ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንዳርጌ ዘውዴ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው 65 ሰዎችን አሳፍሮ ከባህር ዳር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የታጣቂ ቡድኑ አባላት እገታውን የፈጸሙት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ መሆኑን እንዲሁም አቅመ ደካማ ከሆኑ አንዲት ባልቴት እና አንድ ሽማግሌ በስተቀር ሹፌሩን እና ረዳቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 63 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
Via Addis Maleda

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ!
የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ2013 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች፣ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፣ የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች እንዲሁም የህክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ሐምሌ 26 እና 27/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ምዝገባ እንዲያደርጉ ባሳሰበዉ መሰረት በዛሬዉ እለት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዉ መግባት መጀመራቸው ተዘግቧል።ተማሪዎቹ ከሶስት አመታት በኋላ ነዉ ወደ ዩኒቨርስቲው የተመለሱት።
ዩኒቨርስቲው በተመሳሳይ ተመራቂ ላልሆኑ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 04 እና 05/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር ጽ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች ግጭት በላሊበላ በረራ መስተጓጎሉ ተነገረ!
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበለ ከተማ ዙሪያ በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል ግጭት መካሄዱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ::በዚህም ሳቢያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ማክሰኞ እኩለ ቀን ላይ አካባቢ ማረፍ የነበረበት አውሮፕላን መዳረሻውን ለመቀየር ተገዷል ብለዋል።
የታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት ማክሰኞ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም. ከከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ ባሉ አካባቢዎች በአገር መከላከያ ሠራዊት እና በታጣቂዎች መካከል የነበረውን ግጭት “ከባድ” ሲሉ ገልጸውታል።ቢቢሲ በከተማዋ ከሚገኙ ምንጭ ለመረዳት እንደቻለው ማክሰኞ ጠዋት የመጀመሪያው አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ተነስቶ ላሊበላ አርፏል። ከላሊበላም ወደ አዲስ አበባ መንገደኞችን አሳፍሮ ተመልሷል።
ነገር ግን እኩለ ቀን 6፡50 ላይ ማረፍ የነበረበት አውሮፕላን በከተማዋ ዙሪያ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ማረፍ ባለመቻሉ ተመልሷል ብለዋል።ቢቢሲ ያነጋገረው ሌላኛው ነዋሪ በትናንትናው ዕለት ከእኩለ ቀን በፊት የላሊበላ ሹምሸሃ አውሮፕላን ማረፊያ በፋኖ ታጣቂዎች ሥር ገብቶ እንደነበር ገልጿል።
ነዋሪው ተጨማሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በአውሮፕላን ወደ ላሊበላ እየመጡ ነው የሚል መረጃ ከተናፈሰ በኋላ የፋኖ ታጣቂዎች አየር ማረፊያውን ስለመቆጣጠራቸው ሰምቻለሁ ብለዋል።ቢቢሲ በላሊበላ አየር ማረፊያ ስላጋጠመው ክስተት ከተጨማሪ ገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።በላሊበላ አየር ማረፊያ ስለተከሰተው ሁኔታ ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት እና ከአየር መንገድ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልሰመረም።
ነዋሪዎች የላሊበላ አየር ማረፊያ እራሳቸውን ፋኖ ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል ይበሉ እንጂ አየር መንገዱ ነገ ወደ ላሊበላ ለሚደረጉ በረራዎች ቲኬቶችን በድረ-ገጹ አማካይነት እየሸጠ ነው።ታጣቂዎች ከላሊበላ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የላሊበላ ሹምሸሃ አየር ማረፊያ እካባቢ ሲይዙ በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተባል ነገር የለም።
ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ነዋሪ ላሊበላ ከተማ ውስጥ ማክሰኞም ሆነ ዛሬ ረቡዕ ንጋት ላይ ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልጸው፤ በጋሸና እና በሰቆጣ አቅጣጫዎች ግን የተኩስ ድምጽ ይሰማል ብለዋል።በረራ ያስተጓጎለው ግጭት የተሰማው በአገር መከላከያ ሠራዊት እና እራሳቸውን ፋኖ ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች መካከል የሚከሰተው ግጭት እተስፋፋ በመጣበት ወቅት ነው።
Via BBC

❤1👍1
ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ተወያዩ።
በውይይቱም ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፋጠንና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋና ማቅረባቸውን ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 እንዲያጠናቅቁ ማሳሰቢያ ተሠጠ!
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ አሳሰበ።የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አደም ኑሪ ፥ በቤት ወይም በከተማ ቦታ ኪራይና የቤት ግብር አዋጅ መሰረት የጣሪያና ግድግዳ የግብር ክፍያ ሲተገበር መቆየቱን ጠቅሰዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዲስ የገበያ ጥናት በማድረግ በሚያዝያ ወር ላይ ወቅታዊ የማድረግ ስራ መሰራቱን አስታውሰዋል።በዚህም መሰረት እንዲከፍሉ ይጠበቅባቸው የነበሩ ሰዎች እስካሁንም በመክፈል ላይ መሆናቸውን ገልጸው ፥ ከሚጠበቀው አንጻር በርካቶች ገና ናቸው ብለዋል።
Via FBC

ቪዛ 50 ሺሕ ዶላር የሚያስገኝ የፊንቴክ ውድድር በኢትዮጵያ አስጀመረ!
ቪዛ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (ፊንቴክ) ፈጠራን ለማበረታታት፣ የክፍያ እና የግብይት ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንዲሁም አዳዲስ መፍትሄዎችን ለማምጣት ያስችላል ያለውን "ቪዛ በየትኛውም ቦታ (VEI)" የተሰኘ የፊንቴክ ውድድር በይፋ አስጀምሯል፡፡
የቪዛ መካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ፣ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ቢሮ ፕሬዝዳንት አንድሪው ቶሬ፤ በሰኔ ወር በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ቪዛ የዲጂታል ክፍያዎችን ለማስፋፋት ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ የፊንቴክ ፈጠራን ለማስፋፋት እና በሴቶች የሚመሩ አነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶችን ለማገዝ አዳዲስ ውጥኖች መያዙን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
ይህም እቅድ በአገር ውስጥ ለኹለተኛ ጊዜ የቪዛ ለኹሉም ፊንቴክ ውድድርን ለማዘጋጀት እና የቪዛን ‘ቀጣይ እሷ ናት’ የሴቶችን ማጎልበት ፕሮጀክት ማስጀመርን እንደሚያካትት ገልጸዋል።
“የ"ቪዛ በየትኛውም ቦታ" (Visa Everywhere Initiative) ለፊንቴክ እና ለሥራ ፈጣሪዎች በክፍያ እና በንግድ ዓለም ላይ ተጨባጭ እና ውጤታማ መፍትሄዎችን እንዲያስገኙ የሚያስችል መድረክ ነው" ሲሉ የቪዛ የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ ያሬድ እንዳለ ተናግረዋል።
ፊንቴክ እና ሌሎች የክፍያ ስርዓት ፈጣሪዎች፣ ሸማቾች እና ነጋዴዎች ክፍያ የሚፈጽሙበትን መንገድ በመቀየር ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትን ገንዘብ በሚፈልጉበት ጊዜ በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ማድረጉንም አስረድተዋል።
የዘንድሮው "ቪዛ በየትኛውም ቦታ (VEI)" ኢትዮጵያ የፍፃሜ ውድድር በመስከረም ወር የሚካሄድ ሲሆን፤ በድምሩ 50 ሺሕ ዶላር በተለያየ ደረጃ ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች እንደሚሰጥ ተነግሯል።
ይህም 1ኛ ደረጃ 25 ሺሕ ዶላር፣ 2ኛ ደረጃ 15 ሺሕ ዶላር እና 3ኛ ደረጃ 10 ሺሕ ዶላር ተሸላሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ከገንዘብ ሽልማቶች በተጨማሪ፣ አሸናፊዎች ባንኮች፣ ነጋዴዎች፣ ቬንቸር ካፒታሊስቶች እና የመንግሥት አካላት የሚገኙበትን የቪዛን ሰፊ የአጋሮች መረብ ውስጥ የመካተት እና የመታወቅ እድል ያገኛሉ የተባለ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ከሆኑ ታዋቂ ድርጅቶች እውቅና ማግኘት እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡
የ"ቪዛ በየትኛውም ቦታ (VEI)" ውድድር በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ ንግዶች የሚያጋጥሟቸውን የክፍያ እና የግብይት ተግዳሮቶች በመፍታት ማህበረሰቡን የሚያግዙ እና በኹሉም ዘርፍ እና ደረጃ የሚገኙ አዳዲስ እና ትልቅ ሥራ ፈጣሪዎችን እንደሚያሳትፍ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት የቪዛ ለኹሉም ውድድር ምዝገባ የሚጠናቀቀው ነሀሴ 14 መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ተወዳዳሪዎች https://africa.visa.com/visa-everywhere/everywhere-initiative/initiative.html ሊንክን በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል፡፡በ2013 የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሽያጭ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር በመሆን፤ የመጀመሪያውን "ቪዛ በየትኛውም ቦታ" ኢትዮጵያ ውድድርን አሪፍፔይ ማሸነፉ ይታወሳል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FkerAssefa

❤2
የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለሴት ልጃቸው ከፍተኛ ሹመት ሰጡ!
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሴት ልጃቸውን በቢሯቸው ውስጥ ቁልፍ ቦታ ላይ ሾመዋል። የ29 ዓመቷ አንጌ ካጋሜ የስትራቴጂ እና የፖሊሲ ምክር ቤት ሀላፊ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾሟን ፕሬዝዳንት ካጋሜ የመሩት የካቢኔ ስብሰባ ማክሰኞ እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በመግለጫው በኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ፣ ግብፅ እና ጊኒ አዳዲስ አምባሳደሮችን ጨምሮ ሌሎች ሹመቶችን ይፋ አድርጓል። የካጋሜ ሴት ልጅ ከ 2019 ጀምሮ በፕሬዚዳንት ቢሮ ውስጥ በከፍተኛ የፖሊሲ ተንታኝ ሆነና በመስራት ላይ ትገኛለች።
ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ሳይንስ እና የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዲግሪን አግኝታለች። ሌሎች ሁለት የፕሬዚዳንት ካጋሜ ልጆች በመንግስት ስልጣን ውስጥ ቦታ ይዘዋል።
የበኩር ልጃቸው ኢቫን ካጋሜ እ.ኤ.አ. በ2020 የሩዋንዳ ልማት ቦርድ ሰብሳቢ ተደርገው የተሾመ ሲሆን በግሉ ዘርፍ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን የማስመዝገብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ሦስተኛው ልጃቸው ኢያን የሩዋንዳ መከላከያ ኃይል መኮንን ሲሆን ባለፈው ዓመት በፕሬዚዳንቱ ጠባቂነት ተመድበዋል።

በትግራይ ክልል የሚገኙ የሜቴክ ሠራተኞች ለኹለት ዓመታት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የሚገኘው የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሜቴክ ሠራተኞች ለ24 ወራት ደምወዝ እንዳልተከፈላቸው እና በዚሁ ምክንያት ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ለኹለት ዓመት ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች በኢንጂነሪንግ ግሩፑ ሥር ከሚገኙ ፋብሪካዎች መካከል የመቀሌ ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ፣ ውቅሮ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ እና መገጣጠሚያ ፋብሪካ እንዲሁም መቀሌ ኢንጂን ፋብሪካ ከ440 በላይ ሠራተኞች መሆናቸው ተገልጿል።
በፋብሪካዎቹ የሚሰሩት ሠራተኞች አብዛኞቹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና ሌላ የገቢ ምንጭ የሌላቸው በመሆኑ ለከፍተኛ ረሀብ እና ችግር መዳረጋቸውን ነው የገለጹት።
@Yenetube @Fikerassefa

በትግራይ ክልል ትላንት እና ዛሬ ለሶስት ጊዜ ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ንዝረት መከሰቱ ተገለጸ!
በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ትላንት ምሽት እና ዛሬ ጠዋት፤ ለሶስት ጊዜ ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ንዝረት መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በክልሉ ዋና ከተማ መቐለ እና በሌሎች አራት ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ንዝረቱ በአካባቢያቸው ማጋጠሙን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።
ይህን ንዝረት ያስከተለው የመጀመሪያው እና ዋናው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ማክሰኞ ሐምሌ 25፤ 2015 የተከሰተው፤ በኤርትራ ባህር ዳርቻ ዳህላክ ደሴት አካባቢ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። በሬክተር ስኬል 5.4 ሆኖ የተለካው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ የተመዘገበው፤ ትላንት ምሽት ሁለት ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ እንደነበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስር ባለ ኢንስቲትዩት የመሬት መንቀጥቀጥን የሚያጠናውን የትምህርት ክፍል የሚመሩት ፕሮፌሰር አታላይ አስረድተዋል።
የትላንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ “መለስተኛ” (moderate) የሚባል ምድብ ውስጥ የሚወድቅ ቢሆንም “የሚናቅ” እንዳልሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ተመራማሪ እና ባለሙያው ተናግረዋል።“ይህንን ያህል መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ [ከተማ ውስጥ] ቢፈጠር ብዙ ህንጻዎች ይወድማሉ” ሲሉ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ፕሮፌሰር አታላይ አነጻጽረዋል።
[Ethiopia Insider]

👍2
በጋምቤላ ክልል ተጥሎ የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ማሻሻያ ተደረገ!
የክልሉን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በማስመልከት በካቢኔ አባላቱ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ አመሻሹ ላይ ባካሄዱት አስቸኳይ ስብሰባ ነዉ ዉሳኔዉን ያሳለፉት።
በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ብስራት ራዲዮ እና ቴቪ መዘገቡ ይታወሳል። በመሆኑም የክልሉ ካቢኔ የፀጥታ ሁኔታው እየተሻሻለ መምጣቱን በማስመልከት የሰውና ተሽከርካሪን እንቅስቃሴ የሰዓት ማሻሻያ ማድረጉን አሳዉቋል።
በዚህም መሰረት የባለ ሁለትና ባለሶስት እግር ባጃጅና ሞተር ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:30 እንዲሰሩ ማሻሻያ ተደርጓል።
የሰዎችን እንቅስቃሴ በሚመለከትም የካቢኔ አባላቱ ባሳለፉት ውሳኔ እስከ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ እንደሚቻል ተወስኗል።በጋምቤላ ክልል በተከሰተዉ ግጭት ቁጥራቸው ከ 30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ እና በ አራት ቀበሌዎች የሚኖሩ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መፈናቀላቸውን ብስራት ራዲዮ እና ቴቪ መዘገቡ ይታወሳል።

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በዓመቱ ውስጥ ከሩብ ሚሊዮን በላይ የዜጎችን አቤቱታ እንደተቀበለ ገለጸ!
የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ይፋ ባደረገው የ2015 ዓ.ም. የአፈጻጸም ሪፖርቱ፣ በዓመቱ በልዩ ልዩ ዘርፎች “ችግር ደርሶብናል፤” ያሉ፣ ከ277 ሺሕ በላይ ዜጎች፣ ለተቋሙ አቤቱታ እንዳቀረቡ አስታወቀ፡፡
የተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ ዶር. እንዳለ ኀይሌ፣ ስለ ሪፖርቱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ ዘንድሮ በዜጎች የቀረበው የአቤቱታ ብዛት፣ ካለፉት ዓመታት ጋራ ሲነጻጸር፣ ከፍተኛ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ፣ አቤቱታዎችን እየመረመረ ውሳኔ እንደሚሰጥ የጠቀሱት ዋና እንባ ጠባቂው፣ ውሳኔውን ባልተገበሩ የመንግሥት አስፈጻሚዎች ላይ፣ ክሥ እንደመሠረተም አመልክተዋል።
Via VoA

በአማራ ክልል በሚገኙ በርካታ ከተሞች ‹‹ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ›› የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
በክልሉ በመከላከያ ሰራዊትና ራሳቸውን ፋኖ ሲሉ በሚጠሩ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ውግያ ምክንያት ከትናንት ረቡዕ ከምሽት ሦስት ሰዓት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የክልሉ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
ነዋሪዎች እንደሚሉት ዛሬም ድረስ በአንድንድ አካባቢዎች ውግያው የቀጠለ ሲሆን በአንፃሩ እንደ ቆቦና ወልዲያ ባሉ ከተሞች ደግሞ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል፡፡
ለአሻም አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች በቆቦ፣ ወልዲያ፣ ላሊበላ፣ ጎንደርና ደምበጫ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተናግረዋል፡፡የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን በተመለከተ ኢትዮ-ቴሌኮም ከዚህ ቀደም እንደተናገረው ‹‹ ጉዳዩ ከተቋሙ አቅም በላይ መሆኑን ›› አመልክቷል፡፡
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ በባለፈው የሰኔ ወር የተቋማቸውን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን ›› በተመለከተ ከአባላቱ በኩል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡
ፍሬሕይወት በወቅቱ በሰጡት ምላሽ ‹‹ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን የሚመለከተው መንግስት ›› መሆኑን ጠቅሰው ‹‹ ከተቋማቸው አቅም በላይ ›› መሆኑን የሚያሳብቅ ምላሽ መሰጠታቸው ይታወሳል፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ከመንግስት ይበሉ እንጂ የትኛው የመንግስት ተቋም እንደሆነ በወቅቱ አልገለፁም፡፡
[Asham]

በ2015 በጀት ዓመት ለአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከሠራተኞች ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠቅሰዋል። የከተማ አስተዳደሩ አመራር ውይይት አድርጎ አቅም በፈቀደ መጠን ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን ገልጸዋል። ይህም ሠራተኞች ያላቸውን የክፍያ ምጣኔ ታሳቢ ያደረገና እስከ አንድ ሺህ 500ብር እንደሆነ ጠቁመው፤ ይህ አሁን ያለውን መሠረታዊ የቤት ኪራይ ክፍያ ጥያቄ የሚፈታ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ችግሩን ማቃለል ያስቻለ ነው ብለዋል።
ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ሠራተኛው የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊዋ፤ በሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤት ካፍቴሪያዎች ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን በተወሰነ መጠን መንግሥት መደጎም መቻል እንዳለበት ታምኖ በ2015 መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ እንደተገባ አስታውቀዋል።ይህም ሁሉንም ሠራተኛ ታሳቢ የደረገና በአንድ ሠራተኛ የ20 ብር ድጎማ እንደሆነ ገልጸዋል። በሂደቱ መንግሥት ከ20 ብሩ ድጎማ ባሻገር ለካፍቴሪያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራ እንደሚፈጽምም ጠቁመዋል።
ሙሉውን ለማንበብ: https://press.et/?p=106158

❤1
ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ወደ ላሊበላ የሚደረግ የአየር በረራ መቋረጡን የላሊበላ ኤርፖርት ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በጎንደር ከተማ ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ምክንያት በዛሬው ዕለት ወደ ጎንደር የሚደረግ የአየር በረራ አለመኖሩን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።
ዛሬ ረፋድ ላይም በጎንደር አየር ማረፊያ አቅራቢያ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ነው መረዳት የተቻለው።
የላሊበላ አየር ማረፊያ ሠራተኞች ወደ ላሊበላ በቀን ከሚደረጉ ኹለት በረራዎች የመጀመሪያው ማክሰኞ ሐምሌ 25/2015 ጠዋት ላይ መደረጉን ገልጸው፤ “ተጨማሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላሊበላ አየር ማረፊያ ሊገቡ ነው” የሚል ወሬ የሰሙ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ሥፍራው አቅንተው ጥበቃ ላይ ከነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ይህን ተከትሎም በኹለተኛው በረራ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ50 ላይ ላሊበላ ኤርፖርት ማረፍ የነበረበት የመንገደኞች አውሮፕላን ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር ሳያርፍ መመለሱን ገልጸዋል።

‹‹ መንግስት የታገቱት ያሉበትን ያሳውቀን ›› የታጋች ቤተሰቦች
‹‹ ባለፈው ሰኞ የታገቱ 62 ሰዎችን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረግሁ ነው ›› - የፌደራል ፖሊስ
ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ጉዞ የጀመረ ‹‹ ታታ ›› የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በታጣቂዎች እገታ እንደተፈፀመባቸው › አሻም ከቤተሰቦቻቸው ለመረዳት ችላለች፡፡
‹‹ ታናሽ ወንድሜ ነዉ፤ ዘመድ ለመጠየቅ ነበር ባህርዳር የመጣው፡፡ ስራዉ አዲስ አበባ አንድ የግል ት/ቤት ዉስጥ ጥበቃ ነዉ፡፡ ቤተሰቦቻችን በህይወት የሉም፡፡መንግስት ወንድሞቻችንን ያሉበትን ሁኔታ ያሣዉቀን ›› ሲል አንድ የታጋች ቤተሰብ በአሻም በኩል አቤቱታውን አሰምቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጀይላን አብዲ ‹‹ባለፈው ሰኞ የተጋቱት ሰዎች ቁጥር 65 ቢሆንም አሽከርካሪውን ጨምሮ አንድ እናት ልጇ አምልጠው አዲስ አበባ መግባታቸውን›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡
በዚህም የታገቾች ቁጥር 63 መሆናቸውን አመልክተው ከአመለጡት ሰዎች በደረሳቸው ጥቆማ መሠረት የታገቱትን ለማስቀቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ›› ገልፀዋል፡፡የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው እንደሚሉት ‹‹ በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉረቻ ደብረፅጌ አከባቢ ተደጋጋሚ ዕገታ እንደሚፈፀም ›› ጠቅሰዋል፡፡ይህን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቀርበዋል፡፡

በአማራ ክልል የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የክልሉ መንግስት ጠየቀ!
በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ።
በአማራ ክልል የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብአዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ኃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።
ሆኖም በክልሉ ያለው የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር ነው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጠየቀው።
ክልሉ ወደ ቀደመ መረጋጋቱ እንዲመለስ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ ወደ እርሻው ክልሉም ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ መንግስት ያለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባልም በሚል የፌደራል መንግስትን ጠይቋል።
[Walta]

ቅዱስ ሲኖዶስ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖቻችን ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምን በተመለከተ አጀንዳ በመቅረጽ በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ መግለጫ ሰጥቷል ፤ በመግለጫውም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም መደፍረስና የእርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ውድ ሕይወት እያለፈ እና በርካታ የሀገርና የሕዝብ ሀብትና ንብረት እየወደመ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች ብሏል።
ሰላም ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፍጡራን መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ቀድሶ ማቁረብ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ አርሶ ማምረት፣ ተምሮ ማስተማር ወልዶ ማሳደግ፣ ወጥቶ መግባት፣ አገር መምራትና ማስተዳደር አይቻልም ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅሉ ሰላም ሲጠፋ አብረው የሚጠፉ መልካም እሴቶቻችን ብዙ ናቸው፡፡ በቅርብ ጊዜ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ ከመሆኑም በላይ ከሞት የተረፉት ወገኖቻችንም ለስደትና ለረሀብ የዳረገ፣ ለአካልና ለእእምሮ ስብራት ያጋለጠ ከመሆኑም በተጨማሪ በርካታ አድባራትና ገዳማትን እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትን ያፈረሰ እና መተኪያ የሌላቸውን ውድ ቅርሶቻችንን ያወደመ እጅግ በጣም አስከፊ ተግባር መሆኑ ይታወሳል።
በመሆኑም፡-
በሀገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነትና ግጭት ተወግዶ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ልንማጸን ይገባል ሲል የገለጸ ሲሆን በሀገራችን በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም እጦትና የእርስ በርስ ግጭት ወደፊት ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለአገራዊ ሰላም የበኩላቸውን ጥረት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ መልእክቱን አስተላልፏል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጨረሻም በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖቻችን ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ከአደራ ጋር ታስተላልፋለች ሲል መልዕክቱን ማስተላለፉ ተገልጿል።
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወገዙ የትግራይ ክልል አባቶች ውሳኔውን እንደሚቃወሙና ዳግም እንዲያጤነው ጠየቁ!
በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ሓላፊዎች፣ በአክሱም ከተፈጸመው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና ሹመት እንዲሁም፣ ‘መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት’ በሚል ከሚያደርጉት ክልላዊ እንቅስቃሴ ጋራ በተያያዘ፣ ትላንት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈባቸውን ውግዘት፣ “ከንቱ ውግዘት ነው” ሲሉ እንደማይቀበሉት ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአክሱም የተፈጸመውን ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የሰጡ እና የተቀበሉ፣ እንዲሁም ‘መንበረ ሰላማ’ በሚል በክርስቲያናዊ ትውፊት የማይታወቅ እንቅስቃሴ ያመነጩ እና ያስተባበሩ፥ አራት ሿሚ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ዘጠኝ ተሿሚ መነኰሳትንና ሁለት ሌሎች ግለሰቦችን፥ ከማዕርገ ክህነታቸው በመሻር፣ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና አባልነት በመለየት ማውገዙን፣ በትላንትናው መግለጫው አስታውቋል፡፡
ለቅዱስ ሲኖዶሱ የውግዘት መግለጫ መልስ የሰጡት፣ በክልሉ የሚገኙ አባቶች፣ ውግዘቱ፥ የትግራይን ሕዝብ ያለአባት ለማስቀረት የተላለፈ እና በጦርነት ጊዜ የተፈጸመው በደል ቅጥያ ነው፤ ብለዋል።