ፕሮፐርቲ ታክስ በኢትዮጵያ አለመጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ!
ፕሮፐርቲ ታክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ መደረግ አለመጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋገጡ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከፕሮፐርቲ ታክስ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ አዲስ አበባ የራሱ ገቢ ያለው እና በራሱ የሚተዳደር ከተማ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ፕሮፐርቲ ታክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለመጀመሩ በአዲስ አበባም እንዳልተጀመረ ገልጸው፤ ከተማው የጀመረው ከዚህ ቀደም የነበረውን የጣሪያ እና ግርግዳ ግብር ህግ ዘንድሮም በማሻሻል እየተገበረ እንደሆነ ጠቁመዋል።
[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa

Forwarded from YeneTube
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

ኢሰመኮ በእስር ላይ በሚገኙ የኦነግ አመራሮች ዙሪያ ለመወያያት ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር ቀጠሮ መያዙን ገለጸ!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በእስር ላይ በሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች ዙሪያ ለመወያያት ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር ቀጠሮ መያዙን ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በዳሳ ለሜሳ፤ ኮሚሽኑ በእስር ላይ ስለሚገኙ የግንባሩ አመራር፣ አባላት እና ደጋፊዎችን ኹኔታ ሲከታተል እንደነበር አውስተዋል።
ኃላፊው አክለውም፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባላት እና ደጋፊዎች ከሕግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ በጅምላ ተይዘው በእስር ቤት እንደሚገኙ በመጠቆም፤ ኮሚሽኑ ባደረገው ብርቱ ክትትል ከእስር የተፈቱ ቢኖሩም፣ አሁንም ሰባት የሚሆኑ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች በማረሚያ ቤት ውስጥ ናቸው ብለዋል። ለዚህም እልባት ለመስጠት ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅርቡ ውይይት እንደሚደረግ ነው የገለጹት፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚያወጣቸው መግለጫዎች እና በሚያዘጋጃቸው መድረኮች አመራሮቼ፣ አባላት እና ደጋፊዎቼ ከሕግ አጋባብ ውጭ በእስር ላይ ይገኛሉ በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጸ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል፤ በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች እና በሕግ ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሱ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጨምሮ ገልጿል።
የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይም በክልሉ ፖሊስ እና ሚሊሻ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚፈጸም እና ሰብዓዊ መብታቸው እንደሚጣስ ነው የተጠቀሰው።
ፍርድ ቤት የዋስ መብት አክብሮላቸው ወይም "ነጻ ናችሁ" ተብለው ከተበየነላቸው በኋላ ፖሊስ ታራሚዎችን ከእስር ያለመልቀቅ ሁኔታ በስፋት የሚስተዋል መሆኑም ተመላክቷል።
የኮሚሽኑ የጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሰዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዛ ይዞ በጅምላ ማሰር የተለመደ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፤ "በተለያዩ መድረኮች እንደዚህ አይነት ተግባር እንዲቆም አሳስበን የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል።" ነው ያሉት።
ስለሆነም በንጹሃን ዜጎችና በሕግ ታራሚዎች ላይ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አንስተው፤ "የሚመለከተው አካል የመፍትሄ እርምጃ ሊወስድበት ይገባል።" ሲሉ አሳስበዋል፡፡

👍1
የኦዲት ግኝቶችን ተከትሎ ክስ የመመስረት ስልጣን እንደሌለው የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
በየአመቱ በፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት አማካኝነት በሚቀርቡ ሪፖርቶች የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የኦዲት ክፍተት እንደተገኘ ይፋ የሚደረግ ቢሆንም ከሪፖርት ባለፈ መልኩ ግን ተቋማቱም ሆነ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ተጠያቂ ሲደረጉ አይስተዋልም፡፡
አሐዱ ለምን ተጠያቂ ማድረግ አልተቻለም ሲል የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበበ አለሙን ጠይቋል፡፡በምላሻቸውም ባለስልጣኑ የተገኘውን ክፍተት ተከታትሎ ለሚመለከታቸው ተቋማት ከማቅረብ ባለፈ ክስ የመመስረት ስልጣን የለውም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው የተቋማቱን አሰራር በመከታተል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ለገንዘብ ሚንስቴር እና ለፍትህ ሚንስቴር ከማሳወቅ ባለፈም እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
[አሐዱ]

ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ!
በሱዳን ያለውን ግጭት በመሸሽ ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በጋምቤላ ክልሎች በኩል ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገልጿል።
በአጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት መካከልም ከ30 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሱዳናውያን ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ ከ13 ሺሕ የሚበልጡት ደግሞ የሌላ አገር ዜጎች መሆናቸው ተጠቁሟል።
የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት በአገሪቱ በተቀሰቀሰው ግጭት ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን፤ በአገሪቱ ጾታዊ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።
እንዲሁም ጦርነቱ ከተጀመረበት ባለፈው ሚያዚያ ወር አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን፣ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውና ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁት ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት መሰደዳቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ ያመላክታል።
የአገሪቱ ወጣቶች ጦሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ያቀረቡት የሱዳን ጦር መሪ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን፤ የግጭቱ ዋነኛ ተፋላሚ ኃይል ከሆነው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ጋር "መቼም ቢሆን ቁጭ ብዬ አልነጋገርም" ማለታቸው ይታወሳል።
ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ በበኩላቸው፤ በአንድ ሰሞን ከጄነራል አል ቡርሃ ጋር መነጋገር ዋጋ የለውም ብለው የነበረ ሲሆን፣ ቆይተው ደግሞ "ጄኔራል አል ቡርሃ ጦርነቱን ካቆመ የመነጋገር እድል ይኖራል" ሲሉ ተደምጠዋል።
ሆኖም የተለያዩ አገራት በተለይም አሜሪካና ሳውዲ አረቢያ የሱዳኑ ግጭት ያበቃ ዘንድ ኹለቱን ተፋላሚ ኃይሎች ለማደራደር ሲያደርጉት የነበረው ጥረት ፍሬ ሳይፈራ ቀርቶ፣ ግጭቱ ሦስተኛ ወሩን አስቆጥሯል።

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric

❤1
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ለኢትዮጵያ የተቋረጠው ርዳታ እንዲቀጥል ጥሪ አደረገ!
ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን(ሜዲሳን ሳን ፍራንቴር) ወይም በእንግሊዘኛው ምኅጻሩ MSF፣ ተቋርጦ የነበረውና ለኢትዮጵያ ሲሰጥ የነበረው የምግብ ርዳታ በአፋጣኝ መልሶ እንዲቀጥል፣ ዛሬ ዐርብ ጥሪ አስተላልፏል።
ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን፣ የምግብ ርዳታው እንዲቋረጥ የተወሰነው፣ “እጅግ አሳሳቢ” የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት ባለበት ወቅት ነው፤ ብሏል።
ለተጎጂዎች የተላከው ርዳታ፣ ላልታሰበለት ዓላማ ውሏል፡፡ በዚኽም፣ የመንግሥት አካላት፥ ተሳታፊ እና ተጠያቂ ናቸው፤ በሚል፣ የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም(WFP) እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት(USAID)፣ ከአንድ ወር በፊት የምግብ ርዳታውን አቋርጠው ነበር። በቅርቡ ግን፣ ውሱን ዐይነት ርዳታዎች መልሰው መለቀቅ እንደሚጀምሩ፣ የአሜሪካ መንግሥት አስታውቋል።
የምግብ ርዳታው ከመቋረጡም በፊት፣ በኢትዮጵያ፣ 20 ሚሊዮን ሰዎች በርዳታ ላይ ጥገኛ ኾነው ይኖሩ እንደነበርና በአንዳንድ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረቱ “እጅግ አሳሳቢ” እንደኾነ፣ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን ገልጿል።
“የምግብ ርዳታው መቋረጡ አሳሳቢ ነው፤ ምክንያቱም፣ እንዲቋረጥ የተወሰነው፣ ወትሮውንም በቂ ያልኾነ የርዳታ ምግብ ሥርጭት በነበረበትና በመላ አገሪቱ ያለው ሰብአዊ ኹኔታ አሳሳቢ በኾነበት ወቅት ነው፤” ሲሉ፣ የቡድኑ የኢትዮጵያ ዲሬክተር ካራ ብሩክስ መናገራቸውን፣ የኤኤፍፒ ዘገባ ጠቅሷል።
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(OCHA) በበኩሉ፣ በዚኽ ሳምንት እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል፣ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፣ ብሏል። ርዳታው በመቋረጡ ምክንያት፣ ወትሮውንም ተጋላጭ የነበሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ለተጨማሪ ሥቃይ እንደተዳረጉ አክሎ ገልጿል።
Via VoA

በጅግጅጋ ከተማ በእሳት አደጋ ከ900 በላይ ሱቆች ወደሙ!
በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ትናንት ሌሊት በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።በጅግጅጋ ከተማ ‘ታይዋን’ ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማእከል ትናንት ሌሊት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተከሰተው ከፍተኛ የእሳት አደጋ በገበያው በሚገኙ የንግድ ሱቆችና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል።
እሳቱን ለመቆጣጠር የክልሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ግብረ ሀይልና ከሐርጌሳ ከተማ የተላከለ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን የእሳት አደጋውን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብ እሳት አደጋውን መቆጣጠር መቻሉን የክልሉ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።
በእሳት አደጋው ሳቢያ 932 ሱቆች ሲወድሙ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱም ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ!
ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ 9 ሰዉ ህይወት አለፈ!
በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡
ከዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ እንደተገኘው መረጃ ከሆነ፤ አደጋው የደረሰው መነሻውን ያቤሎ አድርጎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው መኪና በመገልበጡ እንደሆነ የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ የገለፁት።
በተከሰተው የመኪና አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የገለፁት ኢንስፔክተር ታምራት ከሞት በተጨማሪ 12 ከባድና 19 ቀላል አደጋ ማስከተሉን ነዉ የገለፁት።
የአደጋ መንስኤ በማጣራት ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ በአደጋ ምክንያት ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በዲላ ሪፈራል አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት 140.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት 140.29 ቢሊዮን ብር ሆኖ በከተማዋ ምክር ቤት ጸደቀ፡፡ በዘንድሮው የ2016 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ የተያዘው በጀት ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ40.2 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን በጀት ያጸደቀው ዛሬ እሁድ ሐምሌ 2፤ 2015 ለሁለተኛ ቀን ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው፡፡ በዛሬው የምክር ቤቱ ውሎ ትላንት ለተጀመረው የ2016 በጀት ዓመት የሚውል የበጀት ዝርዝር የያዘ አዋጅ ለምክር ቤት አባላቱ ቀርቧል፡፡ የከተማ ምክር ቤቱ በበጀት አዋጁ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በ87 ድጋፍ እና በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ የ2016ን በጀት ጸድቋል፡፡
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት 140.29 ቢሊዮን ብር ሆኖ በከተማዋ ምክር ቤት ጸደቀ፡፡ በዘንድሮው የ2016 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ የተያዘው በጀት ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ40.2 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን በጀት ያጸደቀው ዛሬ እሁድ ሐምሌ 2፤ 2015 ለሁለተኛ ቀን ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው፡፡ በዛሬው የምክር ቤቱ ውሎ ትላንት ለተጀመረው የ2016 በጀት ዓመት የሚውል የበጀት ዝርዝር የያዘ አዋጅ ለምክር ቤት አባላቱ ቀርቧል፡፡ የከተማ ምክር ቤቱ በበጀት አዋጁ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በ87 ድጋፍ እና በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ የ2016ን በጀት ጸድቋል፡፡
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ አመሩ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የተመራ የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ከተማ አምርቷል።
የሰላም ልኡኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአገር ሽማግሌዎች ያካተተ መሆኑን የቤተክርስቲያኒቷ የመገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

በአዲስ አበባ በእሳት አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በአንድ ሆቴል ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ።የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ እንደገለፁት፥ አደጋው ትናንት ምሽት 3:30 ላይ ነው የተከሰተው።

ፆታዊ ጥቃት የሚያደርሱ ተጠርጣሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል መተግበሪያ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አማካኝነት ለማስጀመር መታቀዱ ተገለፅ፡፡
በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ሀገራትን ልምድ በመዉሰድ እና ኮሚቴዎችን በማቋቋም ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በዚህም ፌደራል ፖሊስ፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፣ የመረጃ መረብ ደህንነት እና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አንድ ላይ በመሆን ያስፈፀሙታል፡፡
ይህ አሰራር ወንጀሎችን በመከላከል ላይ የሚያተኩር ሲሆን በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ስርአት እና ምላሽ ስራ አስፈፃሚ አቶ ስለሽ ታደሰ ናቸዉ፡፡
አክለዉም አሰራሩ ጥቆማዎች ወደ ፍትህ አካላት በሚደርሱበት ጊዜ የመመዝገብ ስራ የሚሰራበት ሲሆን ባለዉ የፍትህ ስርአት ዉስጥ የሚካተት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቤተክርስትያኗ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖች 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በትግራይ ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስታን ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ድጋፉን ዛሬ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።
ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት ድጋፉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው።
“የሃይማኖት መሪዎች ግጭት ሳይሆን ሰላም፣ ውድመት ሳይሆን ልማት ለማረጋገጥ ሃላፊነት አለብን” ያሉት ብፁእነታቸው ወደፊትም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የሃይማኖት መሪዎች ለሰላምና ልማት መረጋገጥ ሚናቸው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ለ6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አስታወቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉን አስተዳደሩ አስታውሷል፡፡
በቀጣይም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን መገለጹን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ውስጥ ባለፈው አርብ ማምሻውን ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች 13 መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
17 የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለው የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል፡፡ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች የሰላም ተመላሽ ተብሎ ከወር በፊት የተመለሱ እና ከግልገል በለሰ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የቻይና ካምፕ የሚባል ቦታ የሚኖሩ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ጉዳት ያደረሱ ታጣቂዎች በጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ስም (ጉ.ህ.ዴ.ን) የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ናቸው የተባለ ሲሆን በጉባና ዳንጉር ወረዳ እና ሱዳን ድምበር አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በበኩሉ በጥቃቱ ሁለት የታጣቂ ቡድን አበላት እና አራት ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን መረጃ እንደደረሰው ገልጾ ጥቃት አድራሾች ለህግ መቅብ እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡ የሟቶችን ቁጥር በተመለከተ ከተለያየ ነዋሪዎች የተለያዩ መረጃ የተገኘ ሲሆን በመንግስት በኩል ስለ ጉዳዩ የተባለ ነገር የለም፡፡
በፓዌ ሆስፒታል የተጎዱ ሰዎችን በማሳከም ላይ የሚገኙ አንድ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት ባለፈው አርብ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም በግልገል በለስ ከተማ በደረሰው ጥቃት የጸጥታ ሐይሎችን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡
እስከ ትናትናው ዕለት ድረስ የጠፉ ሰዎች እየማፈላለግ ሥራ እየቀጠለ ሲሆን አራት ሰዎች በጫካ ሞተው መገኘታቸውንታውቋል።የጉዳት መጠኑ በየዕለቱ እየጨመረ እንደሚገኝ የአይን እማኙ አክለዋል፡፡ ብዙ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎችም ወደ አጎራባች ወረዳዎች መሸሻቸውን ገልጸዋል ሲል DW ዘግቧል፡፡