YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዋግነር መሪ ላይ የተከፈተው ክስ ይቀጥላል ተባለ!

የታጠቁ ወንጀለኞችን በማደራጀት የተከሰሰው የዋግነር የግል ወታደራዊ ኩባንያ (PMC) መስራች በሆነው የቭጀኒ ፕሪጎዝኒ ላይ የተከፈተው የወንጀል ክስ ምርመራ አልተዘጋም ሲል የሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ምንጭ  ለሩሲያው የዜና ወኪል ታስ አረጋግጧል። "በፕሮጎዝኒ ላይ ያለው የወንጀል ክስ አልተዘጋም ምርመራው ቀጥሏል" ሲል ምንጩ ተናግሯል።

ኮሜርሳት የተሰኘው የሩሲያ ጋዜጣ በበኩሉ በሰኞ ማለዳ እትሙ ላይ ፕሪጎዝሂን እና የታጠቁ የቡድኑ አባላትን የሚመለከተው የወንጀል ክስ እንዳልተዘጋ እና በሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) ምርመራ መጀመሩን እንደቀጠለበት ዘግቧል። ቅዳሜ እለት የሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽ / ቤት የታጠቁ ወንጀለኞችን በማደራጀት በሩሲያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 279 በየቭጅኒ ፕሪጎዝሂን ላይ የወንጀል ክስ መከፈቱን አስታውቆ ነበር።

ጉዳዩ የተጀመረው ፕሪጎዝሂን በቴሌግራም ቻናል ላይ በወታደሮቼ ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚል መግለጫን ካጋራ በኋላ ሲሆን የዋግነር ደጋፊዎች በሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች ላይ እንዲነሱ ጥሪ በማቅረቡ የተነሳ ነው። በወንጀሉ ከ12 እስከ 20 ዓመታት እስራት ሊቀጣም እንደሚችል ተመላክቷል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቭዥን ባስተላለፉት መልዕክት አመፁን  ከባድ ወንጀ፤ የአገር ክህደት እና ሽብርተኝነት ሲሉ አውጀው ነበር። ሆኖም ግን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ፣ ከፕሪጎዝሂን ጋር በተደረገው ስምምነት፣ በዋግነር መሪ ላይ የተመሰረቱት ሁሉም የወንጀል ክሶች የተቋረጡ መሆናቸው ተገለጸ። በድጋሚ ደግሞ ክሱ ይቀጥላል መባሩ አነጋጋሪ አድርጎታል።

[ዳጉ ጆርናል]
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማ በአጠቃላይ 297 ያክል ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4 ቦታዎች ለጨረታ ብቁ እንዳልሆኑ በባለሙያዎች መለየታቸው እና ሌሎች 6 ቦታዎች ደሞ በቂ ተጫራች ሳያገኙ መቅረታቸውን አቶ ሃብታሙ ተናግረዋል።

በድምሩ13 ሄክታር ገደማ ስፋት ባላቸው በቀሪዎቹ 287 ቦታዎች ላይ በቂ ተጫራቾች ተገኝተው አሸናፊዎች የተለዩ ሲሆን አሁን ላይ ወደ ውል ማሰር እና ሌሎች ሂደቶች እንደተገባ ገልጸዋል።


በሊዝ ለጨረታ ከቀረቡት ቦታዎች 7.7 ቢሊዮን ብሩን ተጫራቾች ቦታውን እንደተረከቡ ክፍያ የሚፈጽሙበት ሲሆን ቀሪው 4.5 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ በሰጠው የሊዝ መክፈያ የ5 ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚከፈል ነው።

በተደረገው ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ ሂደት በአራዳ ክፍለ ከተማ 1 ካሬ በ414 ሺህ ብር በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ20 ሺህ ብር የተሸጠው መሆኑ ተነግሯል።

አቶ ሀብታሙ የጨረታ ሂደቱ ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለ ግልጽነት የተስተዋለበት እና ተጫራቾች እያንዳንዱን ሂደት በአካል እንዲከታተሉ የተደረገበት እንደሆነም ገልጸዋል።

ነገር ግን በጨረታው ሂደት ላይ ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዙ አሰራሮች  ስህተቶች ተፈጥረው እንደነበር ጠቅሰው፤ በችግሮቹ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ነው የተናገሩት።

ተጫራቾችም ምንም አይነት ቅሬታ ካላቸው መስሪያ ቤቱ ይህንን ለማስተናገድ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል።

ላለፉት አምስት ዓመታት መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ሂደት ተቋርጦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሀብታሙ፤ ለዚህ ምክንያቱ በመሬት አያያዝ ስረዓቱ ላይ ክፍተት እና ህገ ወጥነት ይስተዋል ስለነበር መሬት ኦዲት እየተደረገ በመቆየቱ ነው ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ያለ ሪፈር እንደሚያስተናግድ ገለጸ።

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ያለ ሪፈር የጭንቅላት ቀዶ ህክምና እየሰጠ መሆኑን የሆስፒታሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ክፍል አስታውቋል።

የክፍሉ ሀላፊ ዶ/ር አብዲ ኤርሜሎ እንደገለጹት የህጻናት ጭንቅላት ቀዶ ህክምና ብቻ ላይ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት የአዋቂዎችንም የህክምና አገልግሎት ጨምሮ እየተሰጠ ይገኛል።

በህጻናት የህክምና አገልግሎት በኩል የሃይድሮሴፋለስ (የጭንቅላት ውሃ መቋጠር) ህመም  ህክምና ፣ የኤምኤንሲ ቀዶ ህክምና፣ በአከርካሪ ላይ የሚወጡ ዕጢዎች ህክምና እና ከወሊድ ጋር  በተገናኘ የሚፈጠሩ የተለያዩ የጭንቅላት ችግሮች ህክምና የሚሰጥባቸው ናቸው።

በአዋቂዎች ህክምና ደግሞ የአንጎልና አከርካሪ ዕጢዎች፣ የዲስክ መንሸራተት ከአደጋ ጋር በተገናኘ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ህክምናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ዶ/ር አብዲ ተናግረዋል።

#ከሁለት_ወር በፊት የኢንዶስኮፒክ ቀዶ ህክምና መጀመሩ በተለይ ለህጻናት የሚደረገውን ህክምና በማሻሻል የጭንቅላት ውሃ መቋጠርን ለማከም ከጭንቅላት ወደ ሆድ የሚሄድ ቱቦ (vp shunt) በመጠቀም ይሰጥ የነበረውን ህክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች በኢንዶስኮፒክ ሰርጀሪ ማስቀረት እንደተቻለም ገልጸዋል።

የህክምና አገልግሎቱ በሳምንት አምስት ቀን እየተሰጠ በወር ከ50 እስከ 60 ቀዶ ህክምናዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን  በቀጣይ የሲአር ማሽን ግዢ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ የአከርካሪ  አጥንት ስብራት ህክምናን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች በሰፊው እንደሚሰጡ ዶክተሩ ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና በከፍተኛ ደረጃ እንዲሰጥ የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አባላት ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ያሉት ዶክተሩ ህብረተሰቡም የህክምና አገልግሎቶቹን ያለ ሪፈር እንደሚሰጡ አውቆ ህክምና ማግኘት እንደሚችል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
#ADVERTISEMENT

👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ

📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠

💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ

ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፀጥታ ሀይሎች ተወሰደ!

ዛሬ ጠዋት 12:30 ላይ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሀይሎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት በመሄድ  "ለጥያቄ እንፈልግሃለን" ብለው እንደወሰዱት ሰምተናል:: ቤተሰቦቹ ለዋዜማ እንደገለፁት የፀጥታ ሀይሎቹ ተመስገንን ወዴት እንደወሰዱት እና ለምን እንደሚፈልጉት የታወቀ ነገር የለም።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ - የተመድ ድርጅቶች

የአየር ንብረት ለውጥ እና ግጭትን ጨምሮ በተደራራቢ አደጋዎች ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካ ቀንድ ነዋሪዎች በአስቸኳይ የረሃብ አደጋ እና የጤና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ገለጹ።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚገኙ ሰባት ሀገራት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የምግብ ዋስትና እጦት ውስጥ መሆናቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። ስልሳ ሚሊዮን የሚሆን ህዝብም ንቁ እና ጤናማ ሆነው ለመቆየት የሚያስፈልገውን በቂ ምግብ እንደማያገኙም ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

የተቋሙ ከፍተኛ የአደጋ ጊዜ ኃላፊ ዶምኒክ ፌሬቲ፣ የረሃብ ቀውሱ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እንዲጨምር ማድረጉን ገልፀው፣ በአፍሪካ ቀንድ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጡ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አስታውቀዋል። ከነዚህ፣ የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ካለባቸው ህፃናት መካከልም 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ልዩ የምግብ ድጋፍ ካላገኙ ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

"ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ምስራቅ አፍሪካ ኮቪድ 19፣ የኢቦላ ወረርሽኝ እና ሌሎች እንደ ኮሌራ እና ኩፍኝ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎችን እንዲሁም ደንጊ የተሰኘውና በትንኝ አማካኝነት የሚተላለፈው በሽታ አስተናግዷል። የበረሀ አንበጣ ወረርሽኝም በአካባቢው የሚገኘውን ሰብሎች እና መተዳደሪያ አውድሟል" ያሉት ፌሬቲ፣ "ከሁሉ የከፋው ደግሞ በቀጠናው ያለው ሰፊ ግጭት እና አለመረጋጋት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እና እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና አለመታደል ሆኖ ሱዳንም አዳዲስ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች እንዲፈጠሩ ማድረጉ ነው" ሲሉ እነዚህ አስደንጋጭ አኃዞች በአንድ ድንገተኛ አደጋ ብቻ የተከሰቱ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

በአፍሪካ ቀንድ መጣል የጀመረው ዝናብ፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ረጅም ጊዜን ላስቆጠረው የድርቅ አደጋ እፎይታን ቢያስገኝም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ግን ዝናብ ብቻውን ቀውሱን ለማስቆም በቂ እንዳልሆነ እያስጠነቀቁ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት፣ የአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ የጤና አደጋዎችን እየተጋፈጡ መሆኑን ያመለክታል። በጤና ተቋሙ የአስቸኳይ አደጋ ዋና ኃላፊ የሆኑት ሊዝቤት አልብሬችት እንደሚያስረዱት፣ አምስት አመታትን በዘለቀው ድርቅ ሳቢያ በርካታ የጤና ችግሮች ተከስተዋል።

"በቅርቡ በአፍሪካ ቀንድ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ፣ ባለፈው አመት እና በዚህ አመት እንደ ኮሌራ እና ኩፍኝ የመሳሰሉ ወረርሽኞችን እያየን ነው። ቁጥር በጣም ከፍተኛ የሆነ የወባ በሽታም አለ። ስለዚህ በጎርፍ ተፅእኖ ምክንያት እነዚህ በሽታዎች እየተባባሱ ሲሄዱ እያየን ነው" ሲሉም፣ በከፍተኛ ዝናብ እና ከባድ የጎርፍ አደጋዎች በተጎዱ አካባቢዎች የጤና ችግር እየተባባሰ እንደሚሄድ አስጠንቅቀዋል።

በምዕራቡ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ከድርቁ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሁኔታ በቀጠለበት ወቅት፣ በምስራቁ አካባቢ ተጨማሪ ዝናብ የሚጠበቅ መሆኑ፣ የዓለም ጤና ድርጅት አዳዲስ ፈተናዎችን እንዲጋፈጥ እያደረገው መሆኑን አልብሬችት ጨምረው ገልፀዋል። ሁለቱም ከባድ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የንጹህ ውሃ አቅርቦትን እንደሚቀንሱም አስረድተዋል። አልብሬችት አክለውም፣ ይህ ሁኔታ የወባ እና ሌሎች ውሃ ውለድ በሽታዎች እንዲስፋፉ እንደሚያደርግና በሰዎች የአመጋገብ እና የጤና ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያሳድርም አክለው ገልጸዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ማለዳ 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል

የኢድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ማለዳ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ነገ የሚከበረውን የኢድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ማለዳ 12 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ በመከላከያ ሚኒስቴር ሥነ ልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በሌተናል ጄኔራል ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በካርቱም የሚገኘውን የሱዳን ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን ተቆጣጠርኩት አለ፡፡

RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በካርቱም የሚገኘውን የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መያዙን አስመልክቶ መግለጫ እንዳወጣ ሜኸር ድረ ገፅ ፅፏል፡፡ፈጥኖ ደራሹ ታጣቂዎቹ ጠቅላይ መምሪያውን መቆጣጠራቸውን የሚያስተማምኑ ፎቶ ግራፎችን እዩልኝ ማለቱም ታውቋል፡፡

RSF የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያውን የተቆጣጠረው ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ሲካሄድ በነበረው ከባድ ውጊያ ነው ተብሏል፡፡

የፈጥኖ ደራሹ ሀይል የተቆጣጠረው የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የበርካታ ጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች መገኛ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡በሱዳን መንግስት ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ሀይል መካከል ውጊያው ከ11 ሳምንታት በላይ ሆኖታል፡፡

Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በቡራዩ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ የመጣ የጅምላ እስር መኖሩ ተገለጸ!

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተዋቀረው ሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ የጅምላ እስር ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መምጣቱን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።በዚህም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደዚህ ዓይነት ተግባራት እየተበራከቱ ነው ሲሉ ገልጸዋል።ድርጊቱን የሚፈጽሙት የኦሮሚያ ፖሊስ እና የአካባቢው ሚሊሻ አባላት መሆናቸን የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ወጣቶች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በየዕለቱ ወደ እስር ቤት በጅምላ እየተጋዙ ነው ብለዋል።

በከተማው ያሉ ወጣቶች ለእስር የሚዳረጉበት ዋነኛ ምክንያት፤ በብዛት ከወለጋ እንዲሁም ከተለያዩ የምዕራብ ሸዋ እና የሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በጸጥታ ችግሮች ተፈናቅለው የመጡ በመሆናቸው፣ “ከኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ” በሚል ጥርጣሬ ነው ተብሏል።ወጣቶቹን ከተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎች ጭምር እንደሚታፍሱ እና ሲያዙም ኃይል የተቀላቀለበት ድርጊት እንዲሁም ሌሎች የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸምባቸው ተመላክቷል።

ድርጊቱ በከተማዋ ባሉ ድሬ፣ ከታ እና ማርያም በተባሉ ሰፈሮች በስፋት እንደሚፈጸምም ተጠቁሟል።በዚህ የተነሳ በከተማው ያሉ እስር ቤቶች ከእስረኞች መሙላታቸው እና ቀሪዎቹ ደግሞ በክፍለ ከተማው የመሬት አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ ነው የተገለጸው።

ወጣቶቹ ወደ እስር ቤት ከገቡ በኋላም ወደ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሦስት እስከ አራት ወራት እንደሚቆዩ ብሎም ዛቻ እና ከፍተኛ ድብደባ እንደሚያደርሱባቸውም ተጠቁሟል።የክፍለ ከተማው መታወቂያ የሌለው ሰው በከተማዋ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስቸጋሪ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፤ በዚህም ምክንያት ለእስር የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በተጨማሪም ራሳቸው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ያሰሯቸውን ሰዎች ጉቦ እየተቀበሉ እንደሚለቋቸው እና የመክፈል አቅም የሌላቸው ታሳሪዎች ደግሞ ለወራት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆኖ በእስር እንደሚቆዩ ተጠቅሷል።ጉዳዩን በተመለከተ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በኩሪፍቱ ሀይቅ ለመዋኘት የገባው የሩሲያ ዜጋ ህይወቱ አለፈ!

በቢሾፍቱ ኩርፊቱ ሀይቅ በመዝናናት ላይ ከነበሩት የዉጭ ሀገር ዜጎች መካከል አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለዉ የ 55 ዓመት ህይወቱ ማለፉን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተያገሩት ግለሰቡን ለሞት ያበቃዉ በኩሪፍቱ ሀይቅ 1መቶ 50 ሜትር ድረስ ርቀት ሀይቁን ዘልቆ በመዋኘት ላይ ሳለ መመለስ ሳይችል ቀርቶ ነው ብለዋል።

ዋና ለመዋኘት የገባዉ እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን የኮሚሽን መ/ቤቱ ጠላቂ ዋናተኞች ትላንት ሰኔ 19 እለት ከሁለት ሰዓት ፍለጋ በኋላ አስከሬኑን አግኝተዉታል ሲሉ ጨምረዉ ተናግረዋል።

Via Bisrat
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ድብደባ ደርሶባቸዉ አካል ጉዳተኛ የሆኑ የፓርቲ አባላት እንዳሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገልጿል፡፡

የተለያየ የፓርቲ አባል ናችሁ በሚል ከሚደርሰዉ አፈናና ማስፈራሪያ ባሻገር ድብደባ ደርሶባቸዉ አካል ጉዳተኛ የሆኑ፤ የስነ ልቦና ቀዉስ የደረሰባቸዉና ፓርቲዎችን እንዳይቀላቀሉ የተደረጉ ግለሰቦች መኖራቸውን የተናገሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ዶክተር ራሄል ባፌ ናቸዉ፡፡

ካለፈዉ አምስት አመት ወዲህ እያንዳንዱ ፓርቲና ፖለቲከኛ የራሱን ርዕዮት ይዞ በመምጣት የተሻለ ስርአት ይኖራል የሚል ተስፋ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም መልሶ ወደ ቀድሞው ስርአት እንዲመለስ ሆኗልም ብለዋል፡፡በተለይም በክልሎች በፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት አደገኛ እንደሆነ እና እየደረሰ ያለዉ ጫናም ቢሆን የፖለቲካ ስርአቱን የሚያዛባ ነዉ ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ አብራርተዋል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
በእሳት ቀልጦ የጠቆረ ስኳር ሰውነቱ ላይ በማፍሰስ ቁስል አስመስሎ ሲለምን የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ!

በእሳት ቀልጦ የጠቆረ ስኳር ሰውነቱ ላይ በማፍሰስ ቁስል አስመስሎ ሲለምን የነበረ ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ልዩ ቦታው መሳለሚያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፤ በእሳት ቀልጦ የጠቆረ ስኳር ሆዱ ላይ በማፍሰስ እና ቁስል እንዲመስል አድርጎ በፕላስተር በማሸግ መንገድ ላይ ተኝቶ የልመና ተግባር ሲያከናውን የተመለከቱ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃውን ለፖሊስ ማድረሳቸው ተገልጿል።

በየካ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ግለሰቡ ምንም አይነት የጤና ዕክል ሳይኖርበት በማታለል ገንዘብ ለመሠብሰብ የተጠቀመበት ዘዴ መሆኑን ፕላስተሩን ከሆዱ ላይ በማስላጥ ማረጋገጥ መቻላቸውም ተነግሯል።

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ድጋፍ የሚጠይቁ ግለሰቦች ቢኖሩም፤ ልዩ ልዩ የማታለያ ዘዴዎችን ተጠቅመው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ገንዘብ የሚለምኑ ሰዎች እያጋጠሙ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢውን የማረጋገጥ ሥራ በመስራት አታላዮችን ሊያጋልጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአንዋር ሶሳ ምትክ ዊም ቫንሄሌፑቴ ነሀሴ 1, 2023 ጀምሮ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ። ዊም በአሁኑ ጊዜ የኤምቲኤን ዩጋንዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆኖ እየሰራ ነው።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች:

-  ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ዋናው መንገድ ቴድሮስ አደባባይ 

-  ከጎተራ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ሪቼ የሚወስደው መንገድ  ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች  ጥላሁን አደባባይ ወይም የቀድሞ 4ኛ ክፍለ ጦር  ጋር

-  ከኬኬር ህንፃ ጀርባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ የድሮ ለገሃር ግምሩክ

-  ከከፍተኛ ፍርድ ቤት  ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አል ሳም ጨለቅለቅ በስርና በላይ መንገድ

-  ከጎማ ቁጠባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

-  ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ መብራት

-  ከሜትሮሎጂ በጥቁር አንበሳ ወደ ፖስታ ቤት የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መ/ቤት

-  ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ኦርማ ጋራዥ  የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት

-  ከአራት ኪሎ  እና ከእሪ በከንቱ የሚመጡ መንገዶች  ፓርላማ መብራት ጋር

-  ከሲግናል ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

-  ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ስታዲዩም የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም  ደንበል ሲቲ ሴንተር  

-  ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅድስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ ከላይና ከታች

-  ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ  ጥቁር አንበሳ ሼል 
-  ከተክለ ሃይማኖት ጎላ ሚካኤል የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

-  ከጎፋ ፣ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር የሚወስደው አዲሱ መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው  ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ 

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላፈ ሲሆን፤ ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆን በፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ሥም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም እንዲከበር እያከናወነ ላለው ተግባር ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እና የእምነቱ አባቶች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥመው ወይም የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልኮች 011-1 11-01-11 ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 መረጃ መስጠት እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ

ዛሬ ጠዋት ሰኔ 20 ቀን፣ 2015 ዓ.ም. ጠዋት 12: 30 ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከመኖር ቤቱ እንደተወሰደ የተነገረለት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዳግም መፈታቱ ተገለጸ ። ተመስገን በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ አካባቢ በሚገኘው በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለ6 ሰዓታት ታስሮ እንደነበረም ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጾ ነበር።

ከዚህ ቀደም ተከሶ ነጻ በተባለበት ክስ ለሐምሌ 7 ዳግም ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ እንደሰጠበትም ተዘግቧል ።

@Yenetube @Fikerassefa
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች፤ እንኳን ለ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!
አዋጭ ላልሆኑ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ለማዳረስ በጀት መመደብ ኃላፊነቱ እንዳልሆነ ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ

የቴሌኮም ዘርፉ ለውድድር ገበያ በመከፈቱ የቴሌኮም አገልግሎት ላልተዳረሰባቸውና አዋጭ ላልሆኑ የገጠር አካባቢዎች በጀት መመደብ ኃላፊነቱ እንዳልሆነ፣ ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ያስታወቀው የሁሉን አቀፍ ተደራሽነት ኃላፊነትን ለመወጣት በጀት መበጀቱን አስመልክቶ፣ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ላነሱት ጥያቄ ነው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋማቸው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በፓርላማው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዓርብ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲገመገም ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ የቴሌኮም አገልግሎት ያልተዳረሰባቸው አካባቢዎችን ለማዳረስ ተፈላጊው በጀት ተበጅቷል ወይ? ካልተበጀተ ምን ታስቧል? የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለውድድር ክፍት በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት ለማረጋገጥ በገጠር አካባቢዎችና አዋጭ ባልሆኑ አካባቢዎች በጀት መበጀት የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ ድርሻ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ እንደማይገባ፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለቀረቡት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ አስረድተዋል፡፡

ዘርፉን የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን በመሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ከመንግሥትም ሆነ ከሌሎች አካላት በጀት አፈላልጎ በኢንዱስትሪው አሠራር መሠረት ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች እንደሚያቀርብ፣ እስካሁን ውይይቶች ከመደረጋቸው ውጪ የቀረበ ነገር አለመኖሩን ወ/ሪት ፍሬሕይወት ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አብራርተዋል፡፡

Source: Reporter
@Yenetube @Fikerassefa