YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"ሰላምና ደኅንነትን የማስጠበቅ እንቅስቃሴዎች ሰብዓዊ መብቶችን እንዳይጥሱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል!" ኢሰመጉ

ሰላምና ደኅንነትን የማስጠበቅ እንቅስቃሴዎች ሰብዓዊ መብቶችን እንዳይጥሱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ።ኢሰመጉ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ የከተማዋን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚል መንግሥት ከአዲስ አበባና ከፌደራል ፖሊስ የተዋቀረ የጋራ ግብረ ሃይል በማቋቋም ደኅንነት የማስከበር ሥራዎችን እንደሚሰራ ማስታወቁን አስታውሷል።

እነዚህ ሰላምና ደኅንነትን ለማስከበር ተብለው በመንግሥት የሚሰሩ ሥራዎችና የሚከተሏቸው ስነ-ዘዴዎች አንዳንድ ጊዜ የሕግ ሥነ ስርዓትን ያልተከተሉ እና የሰዎች ሰብዓዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚጥሉ ሆነው እንደሚገኙም ገልጿል።አምስት አካላትን የያዘው የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፤ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ በመግለጽ፤ በአዲስ አበባ ውስጥ ተከታታይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ሊያካሄድ መሆኑን ባወጣው መግለጫ መግለጹን ያስታወሰው ኢሰመጉ፤ ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱ አግባብ መሆኑን ገልጿል።

ነገር ግን "የእዚህን አይነት ይዘት ያላቸው ለሕግ አስፈጻሚው አካል ከፍ ያለ ስልጣን የሚሰጡ እርምጃዎች በሕግ ከተደነገገው ውጪ በሚፈጸሙበት ወቅት በሂደቱ የሚሳተፉ አካላት የሕግ ሥነ ስርዓትን ያልተከተሉ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና ሰዎች ሕጋዊ፣ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲገደቡባቸው ሲያደርጉ የሚስተዋል በመሆኑ፤ ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ሂደቱ ላይ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ህግና ስርአትን የተከተለ አሰራር እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡" ሲልም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አሳስቧል።ኦፕሬሽኑን ተከትሎ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ በጸጥታ አካላት የሕግን ሥነ ስርዓት ያልተከተሉ የመንገድ ላይ ፍተሻዎች፣ እስሮች፣ ማዋከቦች እና እንግልቶች በሰዎች ላይ እየተፈጸሙ መሆኑን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉንም ገልጿል፡፡

ይህ የጋራ ግብረ ኃይል መደበኛውን የሕግ ሥነ ስርዓት በመከተል ሊንቀሳቀስ የሚገባው ቢሆንም፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ከመደበኛው የሕግ ሥነ ስርዓት ከፍ ያለ ስልጣን እንዳለው በማሰብ ስልጣንን አላግባብ የመጠቀም ሁኔታዎች መስታዋላቸውን አመላክቷል፡፡በዚህም መሠረት፤ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል በአዲስ አበባ ውስጥ እያካሄደ ያለው ተከታታይና የተቀናጀ ኦፕሬሽን የታሰበለትን ሰላምና ደሕንነት ማስከበር እንዲችል የሕግ ሥነ ስርዓትን የተከተለ እንዲሆን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም የጸጥታ አካላት ይህንን ኦፕሬሽን በሚፈጽሙበት ወቅት የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች አላግባብ እንዳይገድቡ እና እንዳይጥሱ ተገቢውን የሕግ ሥነ ስርዓት እንዲከተሉና ያልተመጣጠነ እና አላስፈላጊ የሆኑ ኃይሎችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡም ጠይቋል።እንዲሁም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል በሚያካሄደው ኦፕሬሽን ስልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ በሂደቱ የሚሳተፉ አካላትን የሚቆጣጠርበት እና በሕግ ተጠያቂ የሚያደርግበትን ስርዓት እንዲዘረጋ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ተፈጽሟል የተባለዉን የሰብዓዊ እርዳታ ስርቆት በብዛት የፌደራል ሀይሎች የፈጸሙት ነዉ ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ!

በትግራይ የሰብአዊ ርዳታ ስርቆትን እንዲያጣራ በክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር የተመራው የትግራይ ግብረ ሃይል ኮሚቴ እስካሁን የሰብአዊ እርዳታ ማጭበርበርን የሚያሳዩ ግኝቶችን እና ተጠርጣሪዎችን ማግኘቱን የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ (ማንጁስ) ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

እንደ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዉ ገለጻ በሰብአዊ እርዳታው ስርቆት እና ምዝበራ ላይ የተሳተፉት አምስት ዋና ዋና ተዋናዮች ነበሩ ብለዋል። እኚህም የትግራይ ክልል መዋቅር ፣ የኤርትራ ሰራዊት ፣ የፌደራል መንግስት መዋቅር እና የተፈናቃዮች አስተባባሪዎች እና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።በምርመራው ውጤት መሰረት በደቡብ ትግራይ ፣ ደቡብ ምስራቅ ፣ ምስራቅ ፣ መካከለኛ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች 186 ተጠርጣሪዎች ተለይተው በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

የተመዘበሩ የሰብዓዊ ድጋፎችን በሚመለከትም በፌዴራል ሀይሎች እና በኤርትራ ስራዊት ከፍተኛዉን ድርሻ ይይዛሉ ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በክልሉ መዋቅር ዉስጥ ባሉ ሰዎች ስርቆት መፈጸሙን ተናግረዋል።በዚህም መሰረት በትግራይ መንግስት መዋቅር ስር ባሉ ግለሰቦች14 ሺህ 317 ኩንታል ስንዴ ፣ 42 ሺህ 759 ሊትር ዘይት እና 1ሺህ 424 ኩንታል ኦቾሎኒ (አልሚ ምግብ) ላይ ስርቆት መፈጸሙን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ፌዴራል መዋቅር ባሉ ሰዎች 43 ሺህ 196 ኩንታል ስንዴ ፣129 ሺህ 585  ሊትር ዘይት እና 4ሺህ 184 ኩንታል ኦቾሎኒ መሰረቁን በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል። ይህም በጊዜያዊ መስተዳድሩ ምርመራ መሰረት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል።እስካሁን በክልሉ ጊዜያዊ በተደረገው ምርመራ በኤርትራ ጦር  28 ሺህ 880 ኩንታል ስንዴ ፣ 43 ሺህ200 ሊትር ዘይት እና1 ሺህ 440 ኩንታል ኦቾሎኒ ላይ ስርቆት መፈጸሙን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከረድኤት ድርጅቶች የተላከው ሰብዓዊ እርዳታ መጥፋቱንም ነግረዉኛል ሲል የቴሌቪዥን ጣቢያዉ ዘግቧል።ሌ/ጀነራል ፍስሃ ማንጁስ ግብረ ሀይሉ የማጣራት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የምርመራ ውጤቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። የእርዳታ ድርጅቶች ለትግራይ ህዝብ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ችግር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ የማይሰጥባቸው ት/ቤቶች እንዳሉ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ችግር ባሉባቸው የገጠር አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች፣ ትምህርት ካቋረጡ ከሦስት ዓመታት በላይ እንደኾናቸው፣ የቤተሰቦቻቸው አባላት ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በክልል ደረጃ፣ በቅርቡ የሚሰጠውን የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱትም፣ በከተማ እና በወረዳ ከተሞች ውስጥ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች እንደኾኑና እነርሱን እንደማያካትት፣ እነኚኹ የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ገልጸዋል።የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሓላፊ ዶክተር ቡልቶሳ ሂርኮ፣ በሁሉም ወረዳዎች፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱንና ከ400ሺሕ በላይ ተማሪዎች፣ በዘንድሮው ዓመት በሚሰጠው የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

በኦሮሚያ ክልል፣ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪ እና የተማሪ ወላጅ እንደኾኑ ጠቅሰው፣ ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ፣ “ቀደም ሲል በወረዳችን፣ ብዙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ፥ ጎደጃባ፣ ሻካኬ፣ ቃሬ ቶከ፣ ኛኣ እና ቶሌንና አልዴራ የሚባሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይጠቀሳሉ፡፡ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ግን፣ በእነዚኽ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጧል።” በማለት በወረዳቸው ያለውን የመማር ማስተማር ሒደት አስመልክቶ አስተያየት ሰጥተዋል።

አክለውም፤ “ከሦስት ዓመት በፊት፣ ስምንተኛ ክፍል ደርሰው የነበሩ፣ አሁንም እዚያው ስምንተኛ ናቸው፡፡ ከአንድ እስከ ስምንት የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች፣ ባሉበት ነው ያሉት። በተለይ፣ በቆላማ አካባቢው በሚገኙ 10 ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች፣ ምንም የመማር ዕድል አላገኙም። ምክንያቱም፣ በጸጥታ ችግር ትምህርት ቤቶቹ ሥራ በማቆማቸው ነው። በመኾኑም፣ በዘንድሮው የስምንተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡት፣ በወረዳው ከተማ ያሉ ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለወደፊቱ፣ የልጆቻችን ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ ነው።” ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በዋናነት የጸጥታ ችግር የተፈጠረው በክልሉ በሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎችና በመንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ባለው ግጭችት ምክኒያት ሲኾን፤ ነዋሪዎቹ ሌሎች መደበኛ ያልኾኑ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሳሉ በሚሉበት አካባቢም በስጋት ምክኒያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን መማር እንደተሳናቸው ያነጋገርናቸው ቤተሰቦች ገልፀዋል።በሌላ በኩል የያያ ጉለሌ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በወረዳው፥ 400 ተማሪዎች፣ በስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ ይቀመጣሉ።

የአሙሩ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዓለማየሁ ዋቅጅራ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በወረዳቸው፥ ዘጠኝ የሚደርሱ የአንደኛ ትምህርት ቤቶች፣ በጸጥታው ምክንያት የመማር ማስተማር ሒደቱን መቋረጡን፤ ገለፀው “በ21 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 640 ወንድ ተማሪዎችንና 635 ሴት ተማሪዎችን፣ በአጠቃላይ 1ሺሕ275 ተማሪዎችን፣ በኦቦራ እና አገምሳ ክላስተር ላይ ለመፈተን ተዘጋጅተናል። በወረዳችን ዘጠኝ ትምህርት ቤቶች፣ በጸጥታ ችግር ሳቢያ ትምህርት እየተሰጠባቸው አልነበረም። በተቻለ መጠን፣ ተማሪዎች፥ ወደ ወረዳው ከተማ ተቃርበው እንዲማሩ ተደርጓል። አሁንም፣ ለፈተናው የሚቀመጡት እነርሱ ናቸው።” ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፣ በሁሉም ወረዳዎች፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ፣ የተናገሩት የቢሮው ምክትል ሓላፊ ዶክተር ቡልቶሳ ህርኮ፣ “ፈተናውን፣ በሁሉም ወረዳዎች እንሰጣለን። ከጸጥታው ችግር ጋራ በተያያዘ፣ የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጦ በቆየባቸው ትምህርት ቤቶች ግን፣ ፈተና አይሰጡም። ቁጥራቸውን ለመግለጽ አሁን ዳታቸው የለኝም። በዚኽ ዓመት ለመፈተን ካቀድናቸው ተማሪዎች መካከል፣ 97ነጥብ2 የሚኾኑቱ ናቸው ለፈተናው የሚቀመጡት። ቀሪዎቹ፣ በጸጥታው ምክንያት እና በሌሎችም ችግሮች፣ ለፈተናው አይቀመጡም።” ብለዋል።

አሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው፣ የአንዳንድ ተማሪዎች ወላጆች፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ ትምህርት መቋረጡን፤ ሲገልጹ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ትምህርት ስለተቋረጠባቸው አካባቢዎች በአሀዝ አስደግፎ ከመግለጽ ተቆጥቧል።በኦሮሚያ ክልል በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ ከትምህርት በተጨማሪ ሌሎች የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እንደተሳናቸው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ሲገልጹ ቆይተዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ!

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ።በኢትዮጵያ በተለይም የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው በተለያየ መልኩ ሲገለጹ ቆይቷል።የባንክ ደንበኞችም ለአገልግሎት ባመሩባቸው የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ሲጠይቁ እንዳልሰጧቸው በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተሰተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል።የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት "በኢትዮጵያ በግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል እሚባለው መረጃ ሀሰት ነው" ብለዋል።

የጥሬ ገንዘብ እትረት ገጥሟቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ናቸው መባሉን ሰምተናል ፣ "ነገር ግን በሶስት ባንኮች ላይ የተወሰነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞ ነበር፣ ብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በወሰዷቸው ማስተካከያዎች አሁን ላይ ከአንድ ባንክ በስተቀር የጥሬ ገንዘብ እጥረት ያጋጠመው ባንክ የለም" ሲሉም ምክትል ገዢው አክለዋል።

በኢትዮጵያ የገንዘብ አቅርቦቱ እና ፍላጎቱ የተጣጣመ አይደለም ያሉት አቶ ሰለሞን አሁን ያጋጠመው ክስተትም ጦርነት ውስጥ በነበርንበት የቆመው የፋይናንስ እንቅስቃሴ አሁን የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የፋይናንስ ፍላጎቱ በመጨመሩ ብቻ የተፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎቶችን ለዓለም አቀፍ ተቋማት በሯን ክፍት ማድረጓን ተከትሎ ይህ ሂደት የት ደረሰ? በሚል ለምክትል ገዢው ለቀረበላቸው ጥያቄም " ስራው ሰፊ ዝግጅቶችን የሚጠይቅ ነው፣ ከዓለም ባንክ ጋርም አብረን እየሰራን ነው በአንድ ዓመት ውስጥም ስራውን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

" የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱን ተከትሎ የአገር ውስጥ ባንኮች ራሳቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ውህደት ለመፈጸም በሂደት ላይ ያሉ ባንኮች አሉ" ያሉት አቶ ሰለሞን የኢትዮጵያ ባንኮች በቴክኖሎጂ ፣ ፋይናንስ አቅም እና ሰው ሀይል የበለጠ እንዲዘጋጁም ጥሪ አቅርበዋል።

ስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው ይህ ትኩረቱን በካፒታል ማርኬት ላይ ያደረገ ሲሆን የየፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶች እና ውይይቶች እየተደረጉበት ይገኛል።በጉባኤው ላይ የባንክ ስራ አስኪያጆች፣ ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች ተሳትፈውበታል።

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
#የቻናል_ጥቆማ

🔔 የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
🔔 በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

🔥 እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ
     ቻናል እንጠቁመዎት 👇👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

📚 በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
👉 የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
👉 በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

Join us on Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
https://tttttt.me/ethioengineers1
ቢዮንሴ በስዊዲን ያዘጋጀችዉ ኮንሰርት በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ

የስዊድን የዋጋ ግሽበት በግንቦት ወር ከ10 በመቶ በታች ማሽቆልቆሉን አሀዛዊ መረጃዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡ ነገር ግን በተወሰኑ እቃዎች እና የአገልግሎት ዋጋ ወጪዎች በድንገት ጨምሯል፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ቢዮንሴ ወደ ስዊዲን በመምጣቷ የተነሳ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በግንቦት ወር የሸማቾች የምርት ዋጋ በ9.7 በመቶ ጨምሯል፣ በሚያዝያ ወር ከነበረው 10.5 በመቶ ቀንሷል፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ከስድስት ወራት በኃላ ከ10 በመቶ በታች ደርሷል።"የቀጠለው የኤሌትሪክ እና የምግብ ዋጋ መቀነስ በግንቦት ወር ዝቅተኛ የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ አድርጓል" ሲሉ የስታስቲክስ ስዊድን የስታስቲክስ ባለሙያ የሆኑት ሚካኤል ኖርዲን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ሆኖም ግን የአንዳንድ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ወጪዎች ጨምረዋል፣ “ለአብነት የሆቴልና ሬስቶራንት ጉብኝቶች፣ የመዝናኛ አገልግሎቶች እና አልባሳት” ላይ ጭማሪ መታየቱን የስታስቲክስ ኤጀንሲው ገልጿል።በዳንስኬ ባንክ የስዊድን ዋና ኢኮኖሚስት ማይክል ግራህን እንዳሉት “ቢዮንሴ በስዊድን የዓለም የሙዚቃ ስራዎቿን የማቅረብ ጉዞ በግንቦት ወር የጀመረች ሲሆን ግሽበትን አስከትሏል ፣ ምን ያህል ለሚለዉ እርግጠኛ አይደለንም” ብለዋል።

በግንቦት ብዙ የተነገረላቸው ኮንሰርቶች በሆቴሎች እና በሬስቶራንቶች የዋጋ ግሽበት አስከትለዋል፡፡በሰባት አመታት ውስጥ የመጀመሪያውን የሙዚቃ ጉዞ የጀመረችው ድምጻዊቷ ሁለቱን ኮንሰርቶች ለማየት በግንቦት ወር አጋማሽ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ስቶክሆልም ከተማ ጎርፈዋል።


ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @fikerassefa
አየር መንገዱ 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 13 ነጥብ 7 ሚሊየን መንገደኞች ማጓጓዙን ተናግረዋል፡፡

በኮቪድ-19 ወቅት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎችን ከመመለስ በተጨማሪ ወደ ሰባት አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩንም አንስተዋል፡፡

የአውሮፕላን ቁጥርን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 12 አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡በአየር መንገዱ የጥገና እና ምህንድስና ማዕከል ከመንገደኛ ወደ ጭነት አገልግሎት ሰጪነት የተቀየሩ ሁለት አውሮፕላኖች የካርጎ ስራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰማኮ በደሞዝ ማሻሻያ ጉዳይ ላይ ባነሳቸው ጥያቄዎች የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ጠርቶ እስኪያነጋግራቸው እየጠበቁ መሆናቸው ተገለጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ዳግም የደሞዝ ማሻሺያን እና ዝቅተኛ የደሞዝ እርከን እንዲወጣ የሚሉ ጥያቄዎችን በላባዳሮች ቀን አከባበር ላይ በሰለማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንቅስቃሴ ከተደረገ በኃላ ሰልፉ መከልከሉ የሚታወስ ነው ፣ ታዳይ አሁን ላይ ጥያቄያችሁ ከምን ደረሰ ሲል አሐዱ ኢሰማኮን ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው አህመድ ለአሐዱ እንደገለጹት በወቅቱ ከነበረው የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር የአዲስ አበባ ፀጥታ ቢሮ ሰልፉን ማድረግ ቢከለከልም በሰልፉ ላይ ልንጠይቃቸው በነበሩ ሁሉም ጥያቄዎች ላይ እንዲያነጋግሩን በኮንፈዴሬሽኑ ስር በሴክተር ከተደራጁ ሌሎች 9 የኢንዱስትሪ ፌደሬሽኖች ጋር በጋራ በመሆን ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ደብዳቤ አስገብተናል ብለዋል፡፡

ከደሞዝ የሚቆረጥ ታክስን መቀነስ በተመለከተ ደግሞ ጥያቄያችንን ለገንዘብ ሚኒስቴር አስገብተናል ብለዋል፡፡በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ላይ የተደነገጉ አሰሪ ፣ ሰራተኛ እና መንግስት እንደዚህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት የሶስትዮሽ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ ይደነግግጋል ፡፡በዚህም መሰረት ደብዳቤ አስገብተን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ውይይቱን በማዋቀር ላይ ፣ በቅርቡ ይጠሩናል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በጊዜያዊነት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታገደ!

በቻይና ሀገር የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በቻይና ሀገር ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ የሚገኘው ቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሕጋዊ የሆነ ፈቃድ አለመኖሩን የጀርመኑ ኩባንያ በኤንባሲው በኩል በደብዳቤ ለሚኒስቴሩ ማሳወቁ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በቻይና ሀገር የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከኩባንያው ሕጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስከሚረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል በማድረግና የሕጋዊነት ማረጋገጫ መረጃዎችን የማጥራት ስራም በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሠራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲመረቱ፣ እንዲገጣጠሙና ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ለይቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ ለማስቀየር እየተንቀሳቀስኩ ነው አለ!

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን ለማስቀየር ዲፕሎማስያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ሕጋዊነት ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ፣ የሰላም ስምምነቱን የሚጎዳ ነው ሲል ፓርቲው ገልጿል።በሌላ በኩል ህወሓት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው ወደ ፍርድቤት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረመው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት አስቀድሞ ተሰርዞ የነበረው ሕጋዊ ሰውነቱ ለማስመለስ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማስያዊ ጥረት ማድረጉ እንደሚቀጥል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በትላንትናው የህወሓት መግለጫ እና በህወሓት እና የምርጫ ቦርድ ውዝግብ ዙርያ አስተያየታቸው ያጋሩን የሕግ ምሁሩ ሙስጠፋ ዓብዱ፣ ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ለመቀልበስ እንደሚፈልግ ማሳያ ብለውታል።

ምርጫ ቦርድ በህወሓት የሕጋዊ ሰውነት ዙርያ ያስተላለፈው ውሳኔ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ የሚገልፁት የሕግ ሙሁሩ ሙስጠፋ ዓብዱ፥ በመሰረቱም ጉዳዮ የአንድ ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ ውዝግብ አድርጎ መመልከት እንደማይገባ፣ ሊያስከትለው የሚችል ችግርም ታሳቢ በማድረግ ተገቢ ምላሽ ልያገኝ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ።

ከዚህ ውጭ ህወሓት በትላንትናው መግለጫው የፌደራሉ መንግስት የትግራይ ሕገመንግስታዊ ግዛት እንዲያስከብር፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የበኩሉ እንዲወጣ የጠየቀ ሲሆን ወደ ትግራይ የተቋረጠው ሰብአዊ እርዳታም እንዲቀጥል ጥሪ ከቅርቧል። ህወሓት በመግለጫው መጨረሻ 'ያለንበት ምዕራፍ የተወሳሰበ ነው' ያለ ሲሆን፣ ህወሓትን ለማፍረስ እንቅስቃሴ መኖሩንም በመግለጫው አስታውቋል። ይህም በላቀ ጥበብ እንደሚታገለው ገልጿል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሓት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም የቀረበ የቅድመ እውቅና ጥያቄ አለመቀበሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ዕለት ባሰራጨው ደብዳቤ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ ብሎ ባሰራጨው ደብዳቤ በህወሓት ስም ለረዥም ግዜ የሚታወቅ ፓርቲ በመኖሩ ይህም በህዝብ ዘንድ መደናገር የሚፈጥር በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ አለመቀበሉ አስረድቷል። ጥያቄው ያቀረቡ አካላት የቦርዱ ውሳኔ ይቃወማሉ። ጥያቄው ካቀረቡት መካከል ከሆኑት አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ " እኛ ከታሪክ ጋር መያያዝ የለብንም። እኛ መብታችን ነው የጠየቅነው።ህወሓት የሚባል ፓርቲ ደግሞ የለም ተሰርዟል። ምርጫ ቦርድ ራሱ ነው የሰረዘው። ከተሰረዘ ስሙ ነፃ ነው" የሚሉ ሲሆን፣ መደናገር ይፈጥራል ለሚለው ደግሞ "ለህዝቡ ማስረዳት የኛ ስራ ነው፣ ምርጫ ቦርድ አይመለከተውም" ሲሉ አክለዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ገብረሚካኤል በቀጣይ ጉዳዮን ወደ ፍርድቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል።

[ዶቼ ቬለ]
@YeneTube @FikerAssefa
1
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
#የቻናል_ጥቆማ

🔔 የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
🔔 በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

🔥 እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ
     ቻናል እንጠቁመዎት 👇👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

📚 በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
👉 የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
👉 በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

Join us on Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
https://tttttt.me/ethioengineers1
ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!

የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!

Download Tuba: https://tuba.et

@tuba_books @tuba_books
በሃዋሳ ከተማ በተፈጸመው ከተማሪ ሜላት መሃመድ ጠለፋ ጋር በተገናኘ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ተማሪ ሜላት መሃመድ ከትምህርት ቤት ተመልሳ ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት በሁለት ተሽከርካሪ መጠለፏን ቤተሰቦቿ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ከዚህ የጠለፋ ድርጊት ጋር በተገናኘ 8 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንና እየተደረገ በሚገኘው ክትትልም ጠላፊውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዘን ይፋ እናደርጋለን ሲሉ የተናገሩት የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ናቸው፡፡

በቅርቡ ተጠልፋ የነበረችውና ከቀናቶች በኃላ ነጻ የሆነችው ጸጋ በላቸውም ይሁን በተማሪ ሜላት መሃመድ ላይ የተፈጸሙት ጠለፋዎች በምርመራ በተረጋገጠው መሰረት ከዚህ በፊት በነበሩ ትውውቆች ላይ የተመሰረቱ እንጂ በማያውቁት ሰው የተፈጸመ እገታ አይደለምም ብለዋል፡፡

በከተማው በግለሰብ ደረጃ ከሚያጋጥሙ ጥቃቅን ወንጀሎች በስተቀር በክልሉ በሚነገረው ልክ የዝርፊያ እና እገታ ወንጀሎች እየተፈጸሙ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ችግሮችም ለዜጎች የመኖር ዋስትናን ሊያሳጡ የሚችሉ ጉዳዮች አይደሉም ሲሉ ነዉ ሃሳባቸዉን የገለጹት፡፡

መንግስት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ግዴታው በመሆኑ የክልሉ የጸጥታ ሃይል አስፈላጊውን ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ህወሓት በጦርነቱ ለማገዳቸው ታጣቂዎች ሰብዓዊ እርዳታዎችን አሳልፎ በመስጠት የራሱን ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያስጠብቅ ለማድረጉ ዋነኛ ተጠያቂው የፌደራል መንግሥት ነዉ ሲል ኢዜማ ከሰሰ

👉🏼ኢዜማ ፤ ብልጽግና ሰብዓዊ እርዳታዎችን ለፖለቲካዊ ትርፍ ይጠቀምበታል
ብሏል

ኢዜማ ፤ ከሰሞኑ የመንግስት የሞራል ማጣት ልጓም እጅጉኑ በመክፋቱ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የሚያቀርቧቸው ሰብዓዊ ዕርዳታዎች በመንግሥት ኃይሎች እየተዘረፉ ለችግሩ ተጠቂዎች ከመድረሳቸዉ ይልቅ ለሌላ ዓላማ እየዋሉ መኾኑን ጠቅሰው ፤ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የዕርዳታ መርኃ ግብር ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል ብሏል።

መንግሥት በቂ የሆነ ምርት እንዲኖር የማስቻል ስራውን በተገቢው ሁኔታ አለመወጣቱ ሃገሪቱን ለእርዳታ መዳረጉ እና በዜጎች ላይ የተረጂነት እና ጥገኝነት መንፈስ እንዲሰፍን ማድረጉ ሳያንስ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ህይወታቸውን ማቆያ የሚሆንን የእርዳታ እህል መዝረፍ እና እንደ ሃገር መከላከያ ያሉ ተቋማትን ስም በሚያጠለሽ ሁኔታ እንዲነሳ ማድረጉ የመንግሥት የሞራል ዝቅጠትን ጥግ ያሳያል ሲል ኮንኗል።

ይህ የተረጂነት መንፈስ የሚፈጥረው የመንፈስ ስብራት እንዳለ ሆኖ በባሰ መልኩ ለዜጎች መዋል የነበረበትን ፍጆታ ለግል ጥቅም ማዋል ባስ ሲልም በአደባባይ ለሽያጭ ማቅረብ፣ የተጋነነ የተረጂዎችን ቁጥር በማቅረብ በሌሉ ሰዎች ስም እርዳታን መቀበል እና የእርዳታው ተጠቃሚዎችን ከተተመነላቸው ድጋፍ በታች በመስጠት ትርፍን መውሰድ አይነት አሳፋሪ ተግባሮች ሲፈጸሙ ይስተዋላል ሲል ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡

ሌላኛው በተደጋጋሚ እንደታዘብነው መንግሥታዊ ተቋማት ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እና ድጋፎችን እርዳታ የሚደረሳቸውን ዜጎች ነፃነት በሚነጥቅ ሁኔታ  ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ አድርገው ይጠቀሙበታል ያለዉ ኢዜማ ፤ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚኾነው ብልፅግና ፓርቲ ከኢሕአዴግ በወረሰው መጥፎ ጠባይ ፤ ባለፈው ሃገራዊ ምርጫ የገጠር እና የከተማ ሴፍቲኔት መርኃግብሮችን ለምርጫ ድምፅ መግዣ አድርጎ በስፋት ተጠቅሞበታል ሲል ከሷል፡፡ “ብልፅግናን ካልመረጣችሁ የሴፍቲኔት ድጋፉን እናቋርጣለን” በሚል ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማስፈራሪያ እንዲሁም ለሴፍቲኔት ፕግራም የተመደቡ በጀቶችን ለምርጫ ቅስቀሳ ጥቅም ላይ የማዋል ተግባራት ሲፈጸሙ እንደነበር የአደባባይ ሀቅየ ነው ብሏል፡፡

በምጽዋት የሚሰጥን ፍጆታ ከዜጎች ጉሮሮ የመንጠቅ ሞራል ካለው ሃገሪቱ የምታመርታቸውን ምርቶች ዋጋ ሆነ ብሎ እንዲያጋሽብ የማያደርግበት፣ ፍጆታዎች ሆነ ተብለው በየማከማቸው የማይደበቁበት፣ ለአርሷደሮች የሚመጣ ማዳበሪያ ሆነ ተብሎ እንዲነፈግ የማይደረግበት እና በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ በየትኛውም መልኩ የሚፈጠር ትርምስ አትራፊ ያደርገኛል ብሎ ካመነ ምንም አይነት ነገር ከማድረግ እንደማያቆም ማሳያ ግልጽ ተግባር ነው ሲል ጠንከር ያለ መግለጫ አዉጥቷል።

እንዲህ አይነት መልካም አስተዳደር የጎደለበት ሥርዓት በምጽዋት የሚሰጥን ፍጆታ ከዜጎች ጉሮሮ የመንጠቅ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ዝቅጠት እና ወንጀል የማኅበረሠባችንን እሴት እጅጉን የሚፈታተን አፀያፊ ተግባር እንደሆነ ሊታወቅ ይገባልም ብሏል።

መንግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ የፌደራል መንግሥቱ ሊኖረው የሚገባውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው  ለህወሓት ያልተገደበ ነፃነት ሰጥቶ ትንፋሽ እንዲዘራ እና ትግራይ ክልልን መልሶ እንዲቆጣጠር በማድረጉ ምክንያት ከአንድ ወር በፊት በክልሉ ሰብዓዊ ዕርዳታዎች ላልተገባ ዓላማ እየዋሉ መኾኑን በመጥቀስ የዕርዳታ ድርጅቶች ድጋፋቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡ የትግራይ ህዝብ አሁንም ተመልሶ ለከፋ ርሃብና እጦት ሲጋለጥና ህወሓት በተመቻቸለት ነፍስ የመዝራት ዕድል ተጠቅሞ ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እየደረሱበት ያሉ ተቃውሞዎችን ለመከላከል  በጦርነቱ ለማገዳቸው ታጣቂዎች አሳልፎ በመስጠት የራሱን ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያስጠብቅ ለማድረጉ ዋነኛ ተጠያቂው የፌደራል መንግሥት መኾኑ ሊሰመርበት ይገባል ብሏል፡፡

በመኾኑም፤ መንግሥት በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚቀርብ ድጋፍን ከብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ እንዲያከናውን የተጣለበትን ግዴታን እንዲሁም በረዥም ጊዜ ሂደት ሃገሪቱን ከተመጽዋችነት የምትላቀቅበትን ምርታማነትን የማሳደግ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጠይቋል፡፡ በየትኛውም ደረጃ የሚደረግን ሰብዓዊ ዕርዳታ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለምርጫ ቅስቀሳ እና ለገፅታ ግንባታ የመጠቀም አባዜም በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስቧል፡፡

ዓለምአቀፍ የተራድዖ ድርጅቶችም በስግብግብ መንታፊ መንግሥታዊ አሠራር ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን የሚጎዳ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተገንዝበው ከመንግሥት ጋር በጋራ የጀመሩትን እነዚህን ወንጀለኞች ሕግ ፊት የማቅረብ ጥረት ማጠናከር እና የእርዳታው ተደራሽነት ላይ ቀደም ካለው ጊዜ በበለጠ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ከእርዛት እና መከራ እንዲያወጡ ሲል ጠይቋል።

መንግሥት ይህን አሳፋሪ እና አፀያፊ ተግባር  ከዚህ ቀደም ተድበስብሰው እንደቀሩ ሌብነቶች በአንድ ሰሞን ግርግር እንዳያልፍ ይልቁንም  ከምንም ነገር አስቀድሞ መንግሥት በይፋ ወጥቶ ይህንን ቆሻሻ ተግባር ከማመን በተጨማሪ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ የድርጊቱ ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ገለልተኛ አካል ታክሎበት እንዲታይ፣ ሂደቱም በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን እና በመጨረሻም ፍትህ ሲሰፍን በግልጽ ሊያሳይ ይገባል ሲል ፓርቲዉ ባወጣዉ መግለጫ አሳስቧል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa