YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዮናስ ብርሃነ መዋ ከእስር ተለቀቀ!

ባሳለፍነው አርብ ሰኔ 2/2015 ምሽት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው የፊልም ባለሙያ እና የጉማ የፊልም ሽልማት አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ መዋ ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መፈታቱ ታውቋል።

ዮናስ አርብ ምሽት ከጉማ የፊልም ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በኋላ ሲቪል በለበሱ የመንግሥት ደኅንነት ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።

በማግስቱ ቅዳሜ ጠዋት ፍርድ ቤት የቀረበው ዮናስ በአምስት ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ በፍርድ ቤት ቢወሰንለትም፤ በተመለዶ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ወደሚጠራው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መዘዋወሩም ተገልጾ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሆነ!

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በግጭት በተጎዱ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች በተገኙበት ይፋ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሲደረግ በግጭቱ 28.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመትና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ውድመቱን መልሶ ለመገንባት 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራሙ ይፋ በተደረገበት ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ መንግስት ለፕሮግራሙ ውጤታማነት ከሚያደርገው ሰብአዊ ድጋፍ በተጨማሪ በጀት መድቦ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ተግባር በመንግስት አቅም ብቻ የሚከናወን ተግባር ባለመሆኑ ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋሮች ለፕሮግራሙ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ አተገባበር ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው የፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮችና በግጭት የተጎዱ ክልሎች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎችና የልማት አጋሮች ኃላፊዎች በፕሮግራሙ አተገባበር ላይ ሰፊ ውይይት አድረገው የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ታገዱ!

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ማገዱን አሰታወቀ።ከጥቅምት 14/2015 እስከ ታህሳስ 30/ 2015 ዓ.ም ድረስ 15 ኤጀንሲዎች ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ሪፖርት አለማድረጋቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ በላይ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡በህግ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዜጎችን ለሥራ ስምምነት ወደተደረሰባቸው መዳረሻ ሀገራት ለመላክ ፍቃድ በመውሰድ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችም በአዋጅ ቁጥር 923/08 እና በማስፈፀሚያ መመሪያ መሰረት ሊያሟሉ የሚገባቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡በአዋጅ ቁጥር 923/08 መሰረት ድርጊቱ የሥራ ፈቃድ ስረዛ የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሶ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አልቻሉም፡፡

ስለሆነም ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎ ከድርጊታቸው መማር እንዲችሉ ከግንቦት 11ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለመጨረሻ ጊዜ ለሦስት ወራት ታግደዋል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
👍1
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በአዲስ አበባ ከተማ ወንዝ ዉስጥ የገባው የ45 ዓመት ሰዉ አስከሬን ከ2 ሰዓታት ፍለጋ በኃላ ተገኘ!

-
በሌላ የአደጋ ዜና አንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች ተቃጥለዋል

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ሰኔ 5 ቀን  በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ ተባበር በርታ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 45 ዓመት የተገመተ ሰዉ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ከሁለት ሰዓት ፍለጋ በኋላ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።በሌላ በኩል በዚያዉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች ተቃጥለዋል።የእሳት አደጋዉ ያጋጠመዉ የአንበሳ አዉቶቢስ የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥና የነዳጅ  መቅጃ ማዕከል ላይ ሲሆን የተቃጠሉት አዉቶቢሶች ከቅጥር ጊቢ ዉጭ ቆመዉ  የነበሩ አውቶቡሶች መሆናቸውን አቶ ንጋቱ ማሞ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ እና ሰላሳ አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል።የእሳት አደጋዉ ወደ ነዳጅ ታንከርና ጋራዡ  ላይ ተሳፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል።የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የጠየቀ ሲሆን በሰዉ ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በሞስኮ በአደገኛ የዕፅ ንግድ ተጠርጥሮ የተያዘው አሜሪካዊ ፍ/ቤት ቀረበ!

በሞስኮ፣ በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ተይዞ የተከሠሠው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሙዚቀኛ እና የቀድሞ አየር ወለድ አባል የነበረ አሜሪካዊ፣ ፍርድ ቤት መቅረቡን፣ ሮይተርስ ዘገበ፡፡በመንግሥት ቴሌቪዥን እንደታየው፣ አሜሪካዊው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት፣ የብረት እጥር በኾነ የተከሣሽ መቆሚያ ውስጥ እንዳለ መታየቱ ተዘግቧል፡፡

የሩሲያ ፍርድ ቤት፣ የ51 ዓመቱ አሜሪካዊ ማይክል ትራቪስ ሊክ፣ በማለት የገለጸው ተከሣሹ፣ ቀደም ሲል በሩሲያ “ሎቪ ኖች” ተብሎ በሚጠራው የሮክ ባንድ፣ ሙዚቀኛ እና የዜማ ደራሲ እንደነበር ተወስቷል፡፡“ሩሲያ 24” የተባለው ቴሌቪዥን፣ ባለፈው ቅዳሜ፣ የተከሣሹን ምስል ያሳየው፣ ተከሣሹ፥ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ከተያዘ በኋላ እንደኾነ ተነግሯል፡፡

ወጣቶችን ባሳተፈ የአደገኛ ዕፅ ዝውውር እና ንግድ የተከሠሠው ሊክ፣ እ.አ.አ እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2023 ድረስ በእስር እንደሚቆይ፣ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡ሊክ፣ ጠበቃ ያለው ስለመኾኑ ግልጽ አይደለም፤ ያለው የሮይተርስ ዘገባ፣ በሩሲያውያን ቁጥጥር ሥር ያለውን የተከሣሹን አስተያየት ለማግኘት አለመቻሉን አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ “በቅርቡ ሞስኮ ውስጥ፣ አንድ አሜሪካዊ በቁጥጥር ሥር ስለ መዋሉ የወጡትን ዘገባዎች እናውቃለን፤” ብለዋል፡፡ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ሚኒስቴሩ፥ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ፣ በውጭ አገር በታሰረ ጊዜ፣ ወዲያኑ፣ የዚያን አገር ቆንስል አግኝቶበማነጋገር፣ የሚያስፈልገውን ርዳታ ሁሉ ያገኝ ዘንድ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ይኹን እንጂ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ የቆንስሉ ርዳታ፣ እስከ አሁን ለተከሣሹ ሊክ መስጠት ስለመቻላቸው፣ ቃል አቀባዩ የገለጹት ነገር የለም፡፡የዩክሬኑ ጦርነት ከተጀመረ ካለፈው ዓመት የካቲት አንሥቶ፣ ሩሲያ ውስጥ ሊደርስባቸውን የሚችለውን የዘፈቀደ እስር እና እንግልት ለማስወገድ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች፥ ሩሲያን ለቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ስታሳስብ መቆየቷ ተመልክቷል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
"መንግስት ስልጣን የሰጣቸው የአብን አመራሮች ፓርቲው የተመሰረተበትን ዓላማ በመተው የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል" - የአብን ጽ/ቤት ሃላፊ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የጽህፈት ቤት ሃላፊ ቴዎድሮስ ሀይለማርያም (ዶ/ር) "መንግስት ስልጣን የሰጣቸው የአብን አመራሮች ፓርቲው የተመሰረተበትን ዓላማ በመተው የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል" ሲሉ ለአሻም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል መንግስትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል እየተደረጉ ያሉ ግንኙነቶችን አስመልክቶ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራሮች ለሁለት መከፈላቸውን ሃላፊው ይፋ አድርገዋል።

ሀላፊው እንደሚሉት የሁለቱ አካላት ግንኙነት ሰላም እስካመጣ ድረስ መልካም ነው የሚሉ አመራሮች አሉ በአንፃሩ  ደግሞ ተጠያቂነት ሳይኖር ጦርነቱን በበላይነት ሲመሩ የነበሩ አካላት የሚያደርጉት ውይይት አግባብ አይደለም የሚሉ መኖራቸውን ነግረውናል፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለፅ "ይህ መከፋፈል የመጣውም በመንግስት ሹመት ተደልለው የመንግስት ስራ አስፈፃሚ የሆኑ የንቅናቄው አመራሮች በመኖራቸው ነው፡፡" ሲሉ ተችተዋል።

ግማሹ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በመንግስት ካቢኔ ውስጥ ተቀምጠው የአማራ ህዝብን ሳይሆን የገዢውን ብልፅግና ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል የሚሉት ቴዎድሮስ "በአማራ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምበት ንቅናቄው ከተመሰረተበት ዓላማ ውጭ የመንግስትን ጉዳይ በማስፈፀም የአማራ ህዝብን የሚታገል ድርጅት ሆኗል" ሲሉም አክለዋል።

ሃላፊው  መፍትሔ ብለው በማስቀመጡት ሃሳብም "አብን ይህን ጉዳይ አስታርቆ  ሊቀጥል የሚችለው በመንግስት ስልጣን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከስልጣናቸው ሲለቁ አልያም ፓርቲውን መልቀቅ ሲችሉ ብቻ ነው" ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ሀላፊው አክለውም "ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ እያሉ ለሕዝቡ ጠላት የሆነው መንግስትም አካል ነኝ ማለት ሊሆን አይችልም፤ ምን አልባትም ድርጅቱ ጉባኤውን ካካሄደ እነዚህን ሰዎች ምርጫቸውን ይሰጣቸዋል" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን የማጣራት ስራ መጀመሩን ተከትሎ 67 መምህራን ስራ ጥለው ጠፉ!

በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የማጣራት ስራ ተጀምሮ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ፍተሻ ተደርጓል። ይህንኑ ተከትሎ የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘባቸው የተወሰኑ መምህራን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 67 መምህራን ስራ ጥለው መጥፋታቸው ተነግሯል ።

በተያዘው በጀት ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ 4ሺ 4 መቶ 74 የትምህርት ማስረጃዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልከው በተደረገ የማጣራት ስራ የ82 መምህራን ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱን የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ  አ/ቶ ሽኩራል አወል ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ። ከነዚህ መምህራን መካከል 28 ቱ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ቀሪዎቹ መጥፋታቸው ተገልጿል ። 

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በ15 መምህራን ላይ የፍርድ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን ቀሪ መምህራን በገንዘብ ዋስ ከወጡ በኋላ መጥፋታቸውን አክለዋል። የ67ቱ መምህራን ስራቸውን ጥለው መጥፋት በአንድ ወረዳ ብቻ የ23 መምህራን የትምህርት ማስረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል ። ሀሰተኛ ማስረጃው በተራቀቀ መንገድ የተሰራ መሆኑንና በምርመራ ወቅት ማወቅ እንደተቻለው ደላሎችን ጨምሮ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በዚሁ ተግባር ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ መምህራኑ ተናግረዋል ።

እንዲህ ዓይነት ችግሮች ዳግመኛ እንዳይከሰቱና ለመከላከል እንዲቻል የሚመለከተው አካል ሁሉ በጉዳዩ ዙሪያ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አ/ቶ ሽኩራል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ!

የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ፍፁም ብርሀን እንዳስታወቁት÷ በአክሱም ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለቱሪስቶች ክፍት ተደርገዋል።

ቅርሶቹ ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆኑ ኅብረተሰቡ በጉልበቱ፣ በገንዘቡ እና በሙያው ያደረገው ተሳትፎ የላቀ እንደነበረም ተናግረዋል።

የቱሪዝሙን ዘርፍ ወደነበረበት ለመመለስ እና ኅብረተሰቡ ለቱሪስቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ለፎቶ አንሺዎች፣ አስተርጓሚዎች፣ ለባህላዊ ጌጣጌጦች እና ቅርፃቅርፅ ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለ ሆቴሎች ሥልጠና መሰጠቱን አሰረድተዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ "ሕወሃት" በሚል ስያሜ ትግራይ ውስጥ አዲስ ክልላዊ ፓርቲ ለማቋቋም ያሰቡ ግለሰቦች ያቀረቡን የፓርቲ ቅድመ እውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ዛሬ አስታውቋል።

ቦርዱ፣ የትግራይ ክልል ነዋሪ የኾኑ ሦስት ግለሰቦች የ120 የፓርቲ መስራቾችን ስም ዝርዝር በማያያዝ፣ ቦርዱ ለአዲሱ ፓርቲ የቅድመ እውቅና ፍቃድ እንዲሰጥላቸው ማመልከቻ ማቅረባቸውን ገልጧል። ኾኖም አዲስ የሚቋቋም ማንኛውም ፓርቲ የሚይዘው ስያሜ በምርጫም ኾነ ከምርጫ ውጭ በዜጎች ዘንድ መምታታትና ግርታ የማይፈጥር መኾን እንዳለበት በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ላይ እንደተደነገገ ቦርዱ ጠቅሷል። ከሕጉ አንጻር አዲሱ ፓርቲ ስያሜ ለበርካታ ዓመታት በትግራይና ከትግራይ ውጭ "ሕወሃት" በሚል ሥያሜ ከሚታወቀው ፓርቲ ጋር አንድ ዓይነት መኾኑን የገለጠው ቦርዱ፣ ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው ለጥያቄው አቅራቢዎች በጻፈው ደብዳቤ ገልጧል።

@YebeTube @FikerAssefa
በደንበጫ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች ተቃውሞ ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ ትላንትና እና ከትላንት በስቲያ በነበረ የተኩስ ልውውጥ፣ የሦስት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የደንበጫ እና ፍኖተ ሰላም ሆስፒታሎች ሥራ አስኪያጆች ገለጹ፡፡የየአካባቢው ነዋሪዎች፣ ዛሬ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ በሁለቱ ከተሞች፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት፣ የተገደሉ እና የቆሰሉ ሰዎችን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ትላንት፣ ከዐዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደው ዋናው መንገድ በመዘጋቱ፣ ትራንስፖርት ተስትጓጉሎ እንደነበርና ዛሬ መከፈቱን፣ እንዲሁም በፍኖተ ሰላም ከተማ ሰልፍ ወጥተው በነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አንድ ሆቴል መውደሙን፣ ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በበኩሉ፣ ካለፈው እሑድ ምሽት ጀምሮ፣ በዞኑ ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ ተከሥቶ የነበረው አለመረጋጋት፣ ዛሬ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን አስታውቋል፡፡

ባለፈው እሑድ እና ትላንት ሰኞ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን በደንበጫ እና በፍኖተ ሰላም ከተሞች በነበሩ ግጭቶች፣ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን፣ የደንበጫ እና የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሥራ አስኪያጆች፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።የደንበጫ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዐዲሱ ፍቅሬ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ ማታ፣ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ሰዎች፣ ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውንና በደረሰባቸው ጉዳት የተነሣ፣ ሰዎች ለኅልፈት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በደንበጫ ከተማ፣ መናኸሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ አመሻሽ በሥፍራው ነበርኹ፤ ያሉ፣ ስማቸውን በምሥጢር እንድንይዝ የጠየቁን አንድ ነዋሪ፣ በዕለቱ የነበረውን ኹኔታ ለአሜሪካ ድምፅ እንዲህ አብራርተዋል።ትላንት ሰኞ ከቀትር በኋላ፣ በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች እንደነበሩና ከእነዚኽም መካከል አንድ ሰው እንደ ሞተ የገለጹልን ደግሞ፣ የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ አቶ ማናየ ጤናው ናቸው፡፡

የከተማው ነዋሪዎች፥ መንግሥት፣ በአካባቢው የሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም የሚጠይቅ ሰልፍ ተደርጎ እንደነበርና በሰልፉ ላይ ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡በሰልፉ ወቅት የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የገለጹት እኚኹ የከተማው ነዋሪ የኾኑ አስተያየት ሰጪ፣ ልውውጡ በማንና በእነማን መካከል እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሓላፊ አቶ ዘመኑ ታደለ በበኩሉ፣ ካለፈው እሑድ ምሽት ጀምሮ፣ በዞኑ ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ ተከሥቶ የነበረው አለመረጋጋት፣ ዛሬ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ገልጸዋል፡፡የክልሉ መንግሥት የሰላም እና ጸጥታ ቢሮም፣ በሚያዝያ ወር ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ ማስከበር ርምጃው፣ አጥፊዎች ለሕግ እስኪቀርቡ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ማለቱ ይታወቃል።

በሌላ በኩል፣ በዐማራ ክልል ምክር ቤት፣ የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ተመራጭ የኾኑ 13 የሕዝብ እንደራሴዎች፣ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት፣ ያለክልሉ ምክር ቤት የእገዛ ጥያቄ በሕግ ማስከበር ስም ወደ ዐማራ ክልል ያስገባውን፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ እንዲያስወጣ ጠይቀዋል።ምንም እንኳን መንግሥት፣ በክልሉ እየሰወደ ያለው ርምጃ፣ ሕግ የማስከበር እንደኾነ ቢገልጽም፣ የዐማራ ክልል ምክር ቤት አባል የኾኑ የአብን ተመራጮች ግን፣ ርምጃው፥ ሕግን የተከተለ አይደለም፤ ሲሉ ተቃውመዋል። የፌደራል መንግሥት፣ የመከላከያ ሠራዊቱን ወደ ክልሉ ያስገባው፣ የዐማራ ክልል ምክር ቤት፣ እገዛውን ሳይጠይቅ በመኾኑ፣ ይህም፣ ርምጃውን ሕገ ወጥ እንደሚያደርገው አስረድተዋል፡፡ ይልቁንም፣ እየተወሰደ ያለው ርምጃ፥ በክልሉ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፤ ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
Forwarded from YeneTube
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
መቀለ ፣ አዲግራትና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች በመጪዉ መስከረም ስራ ይጀምራሉ ተባለ!

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው መስከረም ወር 2016 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢፕድ ዘግቧል።

የሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት የምግብ ፣ የመኝታና የህክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን ገልጸው ራያ ዩኒቨርሲቲም ይህንን አሟልቶ በትናንትናው ዕለት የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን ጠቁመዋል።

መቀሌና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በቀጣዮቹ ወራት ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር እንደሚጨርሱና ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነቱ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ እንደሚችልም ገልጸዋል።

አራቱ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከጦርነቱ በፊት 45 ሺሕ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ እንደነበር አስታውሰው ከእነዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት 22 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲወጡና በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ዪኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል ብለዋል።

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችም አሁን ላይ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ 20 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎችን ይሆናል ተብሏል።

በመጪው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ የቆዩ መሆኑን የገለጹት መሪ ስራ አስፈጻሚው ፤ አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹም ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በሱሉልታ ከተማ በታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል በሚል እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በቅርቡ በተዋቀረው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መንግስት ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የሚገልጹ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ሲዘዋወሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የተወሰዱት ሰዎችም ያሉበት እንደማይታወቅ እና አጋቾችም ይህን ያህል ብር አምጡና እንለቃቸዋለን በማለት እየተደራደሩ እንደሚገኙ መዘገቡም ይታወቃል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን ነባራዊ እውነታ እንዲያብራሩ አሃዱ ያነጋገራቸው የሸገር ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ናስር ሁሴን  ከተማ አስተዳድሩ መረጃው ከወጣ በኋላ የማጣራት ስራዎችን እንደሰራ አንስተው ሆኖም በከተማ መስተዳድሩ ውስጥ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ታፍነው የተወሰዱ ዜጎች አለመኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየወጡ ያሉት ዘገባዎች ከእውነት የራቁ እና ተአማኒነት የሌላቸው መሆናቸውን በመግለጽ ህብረተሰቡን በተሳሳቱ ዘገባዎች ማደናገር ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa