YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጥቁር አንበሳ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ኮሌጅ በተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ ጉዳይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል ።

ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ ከ2010 ጀምሮ በህክምና ኮሌጁ ትምህርቱን ይከታተል እንደነበር ተገልጿል።

ነገር ግን የአራተኛ አመት ተማሪ እያለ በተፈጥሮ በግራ እጁ ላይ ጉዳት እንዳለበት በመምህራኖቹ ታይቶ ይህ ጉዳት የህክምና ትምህርቱን መቀጠል እንደሚያስችለውና እንደማያስችለው ለመወሰን ጉዳዩ ወደ ፕረዝደንት ፅ/ቤት መመራቱንም ዶክተር አንዷለም ተናግረዋል።

በዚህም ላለፉት 8 ወራት ውይይት ሲካሄድበት ጉዳዩ መቆየቱ በመግለጫው ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት በተላላፈው ውሳኔ አንድ የህክምና ተማሪ ግዴታ ሊከውናቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተብለው ከተቀመጡ መስፈርቶች ማለትም የቆመ የልብ ምት ማስነሳት ፣ መለስተኛ ቁስል መስፋት ፣ኦክሲጅን መስጠት ፣ማወለድ እንዲሁም ቱቦ በሰውነት ውስጥ ማስገባት ሲሆኑ እነዚህን ለማድረግ ደግሞ የግድ ሁለት እጆች እንደሚያስፈልጉም ነው የተገለፀው።

ይህን ተከትሎ በተማሪ ቢኒያም ላይ በተካሄዱት ስብሰባዎች ውሳኔ መሰረት በፋርማሲ ፣ህክምና ላቦራቶሪ ሳይንስ ፣የህክምና ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂን መማር እንደሚችል እና ወደ እነዚህ የትምህርት ዘርፎችም ሲዘዋወር ትምህርቶቹ ተዛማጅ በመሆናቸው እስከዛሬ የተማራቸው ተያያዥ ትምህርቶች በሙሉ እንዲመዘገቡለት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም በተማሪ ቢኒያም የቅበላ ሁኔታ ላይ ለተፈጠረው ስህተት ዩኒቨርስቲው ሙሉ ሀላፊነት እንደሚወስድ አረጋግጧል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው አምባ ጊዎርጊስ ከተማ ከ 31ኛ ክፍለ ጦር እንደመጣ በመግለፅ ሶስት ኤርትራውያንን የጫነ ኮድ 06580 መ.ከ ሰሌዳ የመከላከያ ሰራዊት መኪና ለመፈተሽ ፈቃደኛ ባለመሆንና ኬላ በመጣስ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ወደ ጎንደር ከተማ እየገባ የነበረው ይህ መኪና የአካባቢው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያስቆሙት በሚሞክሩበት ጊዜ በቦታው የነበሩ እንስሳትን በመግጨት ሊያመልጥ ሙከራ አድርጓል።በማምለጥ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ከጎንደር ከተማ በ 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወለቃ ቀበሌ ላይ 3 ኤርትራዊያን የጫነው ሹፌር ከነመኪናው በመከላከያ ሰራዊት ኃይል ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ኤርትራውያንና የመኪናው አሽከርካሪ በጎንደር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል።

የኮሚቴው አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባ ማካሄዱን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን እንዳሉት ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሰራርና ሥነ ምግባር አካሄድ ተወያይቶ ወስኗል።

በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጀት ኃላፊነት ተከፋፍሎ ሥራውን እንደጀመረም አስታውቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት በአጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ተሰደዱ!

የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ወደ ማልዴቪስ ተሰድደዋል።

በእስያዋ ስሪላንካ በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ላለፉት ሳምንታት ህዝባዊ ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ጎታብያ ራጃፓክሳ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡

ተቃዋሚዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ በሀገሪቱ መዲና በሆነችው ኮሎምቦ ከተማ የሚገኘውን ቤተመንግስት የተቆጣጠሩ ሲሆን የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ድርጊቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ራጃፓክሳም ወደ ጎረቤት ሀገር ማልዴቪስ እንደተሰደዱ ሮይተርስን ጠቅሶ አል አይን ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል በ2014 በጀት ዓመት በፀጥታና በድርቅ ምክንያት ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መሰተጓጎላቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሰታወቀ።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተሮ ቶላ በሪሶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ የትምህር ከ10 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት የገቡ መሆኑን ገልፀው በዚህም ከእቅዱ 92 በመቶ ማሳካቱን ተናግረዋል።

የ2014 ዓ.ም በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ስራና ለውጥ የታየበት ነው ያሉት ቢሮው ኃላፊ በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ የታየና በትምህርት ዘመኑ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 52 ነጥብ 8 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን ውጤት ማስመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

በፀጥታና በድርቅ ምክንያት ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መሰተጓጎላቸውን ጠቅሰው፣ በተሰራው ሰፋፊ ስራ አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተመልሰው የሚጠበቅባቸውን ትምህርት መውሰዳቸውን አውስተዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የህክምና ስህተት ቅሬታዎች እየጨመሩ መምጣታቸው ተገለጸ!

የህክምና ስህተት ቅሬታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን የጤና ባለሙያዎች የስነ-ምግባር ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ ተናገሩ።የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒት፣ ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለሥልጣን በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት በሚያጋጥሙ የሕክምና ስህተቶችና የስነ-ምግባር ግድፈቶች ዙሪያ ከጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

የጤና ባለሙያዎች የስነ-ምግባር ኮሚቴ ከተቋቋመበት 2007 ዓ.ም ጀምሮ 216 የሕክምና አገልግሎት ስህተትን የተመለከቱ ቅሬታዎችን መቀበላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።ከእነዚህ ውስጥ 131 በግል ጤና ተቋማት 74 ደግሞ በመንግሥት ጤና ተቋማት ላይ የቀረቡ ሲሆኑ 116 ቅሬታዎች ውሳኔ ማግኘታቸውን ጨምረዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
“ግሪን ትራንስፖርት” የተሰኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ስራ ጀምረዋል።

ተሽከርካሪዎቹ “ግሪን ቴክ አፍሪካ” በተሰኘ ኩባንያ የተመረቱ ሲሆን÷ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሽከርካሪዎቹን ስራ ዛሬ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ አስጀምረዋል።በማስጀመሪያ መርሐግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ የትራንስፓርት ዘርፉን ተደራሽና ፈጣን በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የትራንስፖርት ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው።በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣውን የበካይ ጋዝ ለመቀነስ መንግስታት እየሰሩ እንደሚገኙና ኢትዮጵያም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስተዋወቅ ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሆነች ገልጸዋል።ስራ የጀመሩት ተሽከርካሪዎች ለመዲናዋ ነዋሪዎች ለአንድ ወር ያህል ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው በዛሬው ዕለት በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቢሲ እንዳሉት፣ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉት "ኤልሻዳይ" ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ጭማሪ ማድረጉን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ጀመሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል።የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ለውጥን ብቻ መሰረት በማድረግ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎች የአገልግሎት ታሪፍ ማስተካከያ ከነገ ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ጭማሪ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮው አስታውቋል።በዚህም በሚዲ-ባስ 0.50 ሳንቲም እስከ 2.00 ብር የተጨመረ ሲሆን በሚኒ-ባስ 0.50 እስከ 6 ብር ተጨምሯል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ እና በጃፓን መንግስት መካከል 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት “የምግብ እርዳታ ፕሮግራም” ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተፈራርመዋል።ዕርዳታው 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች በተከሰተው ድርቅና በሰሜኑ ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው ተብሏል።ጃፓን በመሠረተ ልማት ፣በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመጠንም ሆነ በስርጭት ብዙ አካባቢዎችን የሚሸፍን እርጥበት እንደሚኖር እና በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ፡፡

ባለፉት ቀናት በተከታታይ ዝናብ እያገኙ ያሉና ውሃ የመሸከም አቅማቸው ከፍተኛ የሆነ የአፈር አይነት ያላቸው አካባቢዎች የአፈር ውስጥ እርጥበት መብዛት እንዲሁም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ከአፈር መሸርሸርም ሆነ ከመሬት መንሸራተት ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡

ከእርጥበት መብዛት ጋር ተያይዞ የአረም መጨመር ሊከሰት ስለሚችል አርሶ አደሩ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ተጠይቋል፡፡

በአንጻሩ በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚጠበቀው እርጥበት በተለይም ባሳለፍናቸው ቀናት አካባቢዎቹ ካገኙት የተሻለ እርጥበት ጋር ተዳምሮ የመጠጥ ውሀ አቅርቦትና የግጦሽ ሳር ልምላሜ ከማሻሻል አንጻር ጥሩ ጎን እንደሚኖረው የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በትንበያው ላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች በአብዛኛው ከመደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን ይህም የአፈር ውስጥ እርጥበትን ከማሻሻል አንፃር አስቀድመው የተዘሩና በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግም ሆነ የመኸር ሰብሎች እንዲሁም ለተለያዩ የቋሚ ተክሎችና የጓሮ አትክልቶች የውሀ ፍላጎታቸውን ከማሟላት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ነው ያለው፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ሥር ዋሉ! የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው በዛሬው ዕለት በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ። በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቢሲ እንዳሉት፣ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉት…
ኤልሻዳይ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ጋር በመመሳጠር የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀሎች ፖሊስ ይፋ አደረገ!

ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን መንግሥትዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት በተረጂዎች ስም ከብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለእርዳታ የተዘጋጀን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን አላግባብ ወስዶ ለግልጥቅም አውሏል በሚል ተጠርጥረው ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ፖሊስ ባደረገው የማጣራት ሥራ የተሰበሰበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በተለይ ለኢቲቪ አስታውቋል።

በምርመራ ሂደቱ የተገኙ ግኝቶችም፦

1ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን በየጊዜው አሉ ተብሎ እርዳታ የሚጠየቅላቸው ዜጎች በትክክል ስለመኖራቸው እና አለመኖራቸው በተደረገ ምርመራ፡-

ድርጀቱ በክልል ካሉት ማዕከል ውስጥ በ3 ማዕከላት ማለትም በአማራ ክልል ቁጭት ለልማት ማዕከልከ 2010 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር፤ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2019 ማእከሉ 14 ተረጂዎች ብቻ እያለው ዓመቱን ሙሉ በ2 ሺህ 631 ተረጂዎች ስም የእርዳታ ስንዴ ጠይቆ ከኮሚሽኑ የተሰጠው መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል።

ድርጅቱ በአፋር እና ደቡብ ክልል ማዕከል የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር የጠየቀ እና የወሰደ መሆኑን፣ በጋምቤላ ክልል ማዕከል ስም የጠየቀው ተፈቅዶለት ያልወሰደ እና በሙከራ ደረጃ የቀረ መሆኑን በማስረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
2ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን በተለይ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ አለአግባብ ከኮሚሽኑ ጠይቆ የተሰጠውን የእርዳታ ስንዴ ምን እንደሚያደረገው በተደረገ ምርመራ፡-

ድርጅቱ ከመንግስት የወሰደውን ስንዴ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ለሚገኝ ኪያ የዲቄት ፋብሪካ (ሶሮሮ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር) 66 ሺህ ኩንታል ስንዴ በ66 ሚሊዮን ብር ሸጦ ግንዘቡን የወሰደ መሆኑን፣ 6 ሺህ ኩንታል ስንዴ በብር 6 ሚሊዮን ግምት በ4 ተሸከርካሪ በአይነት ከሶሮሮ ትሬዲግ የተለዋወጠ መሆኑን፤

ኤልሻዳይ ድርጅት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አዋሽ መልካ የሚገኝ ነጃኼ ሬዲን የድቄት ፋብሪካ ባለቤት እና ሰራተኛ ስም 27 ሚሊዮን ብር የገባለት በመሆኑ ነጃሄ ትሬዲን ተጠይቆ 15 ሚሊዮን ብር ያስገባው ከኤልሻዳይ ስንዴ ገዝቶ መሆኑን በሰነድ በማስደገፍ ቃሉን የሰጠ ሲሆን ቀሪው 12 ሚሊዮን ብር ቢሆን የሰነድ አያያዝ ችግር ነው እንጂ የስንዴ ግዥ ብር ነው በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል።

3ኛ- በኤልሻዳይ ድርጅት የበላይ አመራር አቶ የማነ ገ/ማሪያም እና በኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መካከል መመሳጠር መኖር እና አለመኖሩን በተደረገ ምርመራ፡-

ኤልሻዳይ ኮሚሽኑን እርዳታ ለመጠየቅ ያዘጋጀው የአንድ ጊዜ በእጅ ፁሕፍ የረቀቀ መጠይቅ ሰነድ ተገኝቶ በፎረንሲክ ምርመራ ረቂቂ የእጅ ፁህፍ ተመርምሮ የብሔራዊ አደጋ መከላከል ስራ አመራር ከሚሽን ኮሚሽነር በኤልሻዳይ ስም የተዘጋ መሆኑ ተረጋግጧል።

በተጨማሪም በኮሚሽነሩ ቤተሰቦች ላይ በተደረገ ማጣራት፦
1ኛ - የኮሚሽነሩ ወንድ ልጅ ኢያሱ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት በተላለፈ ገንዘብ መኪና ተገዝቶለት ይህንኑ መኪና መልሶ ኤልሻዳይ የገዛው መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን፤ እንዲሁም ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በኤልሻዳይ ድርጅት ፀሀፊ ስም በወር 15 ሺህ ብር በተከራየው ሙሉ ጊቢ ውስጥ የሚኖር መሆኑን መረጃ ደርሶ፤ በቤቱ ውስጥ የተባለው የኮሚሽነሩ ልጅ መኖሩን ወርሃዊ ክፍያውንም ኤልሳሻዳይ ድርጅት እንደሚከፍልለት በሰውና በሰነድ ተረጋግጧል፣

2ኛ- የኮሚሽነሩ ሴት ልጅ ወ/ሮ ሚኪያ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጣሪ ሳትሆን በኤልሻዳይ ድርጅት ፔሮል ውስጥ ስሟ ተካቶ ለ1 ዓመት ያክል በወር አምስት ሺህ ብር ደመወዝ በባንከ በኩል ሲከፈላት እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል። እንዲሁም ከኤልሻዳይ ድርጅት የባንክ ሂሳብ ብር 800 ሺህ ብር ወደ ሚኪያ ምትኩ በተለያዩ ጊዚያት ገቢ መሆኑን በሰነድ ማረጋገጥ ተችሏል፤ እንዲሁም ተጨማሪ ማጣራም በማጣራት ላይ ይገኛል

3ኛ- የኮሚሽነሩ ባለቤት በወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ስም ከእንይ ጀኔራል ቢዝነስ ሪል እስቴት (በወኪል የማነ ወ/ማሪያም በርሄ አማካኝነት (የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ) ከኤልሻዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ጥቆማዎች ላይም ማጣራት እየተካሄደ ስለመሆኑ

4ኛ- የኮሚሽነሩ ወላጅ እናት ወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ከኤልሻዳይ ድርጅት 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ብር በሲፒ.ኦ ገቢ በሆነላት ብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ብቻ በተደረገ ማጣራት በኤልሻ ድርጅት እና የኮሚሽነሩ የቅርብ ጉዳይ አስፈፃሚ በሆኑ ግለሰቦችና የወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት 7 ቤቶች የገዛች መሆኑ በተጨማሪም ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ስም የተገዙ ቤቶችን በተመለከተ ሙሉ ውክልና ለኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ የማነ ገ/ማሪያም ውክልና ሰጥተው የተገኙ መሆኑን ይህ ቀሪ የማጥራት ስራ የሚቀረው ቢሆንም መመሳጠር መኖሩን ያስረዳል። እንዲሁም ከእነዚህ ሰባት ቤቶች መካከል አንዱን አቶ የማነህ ገ/ማሪያም በተሰጠው ውክልና መሰረት ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ለአቶ ምትኩ ካሳ መሸጡን ይህ ሽያጭ ሲፈፀም አቶ የማነ ገ/ማሪያም ሀሰተኛ መታወቂያ፣ ሀሰተኛ ፎቶ መጠቀሙን ተረጋግጧል።

አቶ ምትኩ ካሳ ሚኖሩበት ቤት ቁጥር በማስመዝገብ እና የሌላን ሰው ፎቶግራፍ በመጠቀም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በስማቸው አሰርተው የተገኙ መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል፣

በምርመራ መዝገቡ ላይ ተጠርጣሪ የሆኑት፡-
1. የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ እና ቤተሰቦቻቸው ፤
2. የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ የማነ ወ/ማሪያም፤
3. የኤልሻዳይድርጅት ኦፕሬሽናል ዘርፍ ምክትል ስ/አስኪያጅ ዶ/ር ዮናስ ወ/ትንሳይ እና
4. የኤልሻዳይ ድርጅት የፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ስ/አስኪያጅ ደመወዝ ኃይሉ መሆናቸውን ከፖሊስ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ኢቲቪ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የወጣው እጣ ውድቅ ተደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውድቅ አደረገ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ25 ሺሕ 491 ያወጣው የ20/80 እና 40/6 ላይ እጣ የወጣበት ሲስተም ላይ የተአማኒነት ጉድለት እንደነበር በመረጋገጡ ነው የወጣውን ዕጣ ውድቅ ያደረገው፡፡

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ የጀመረው ከተማ አስተዳደሩ በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች መገኘታቸውን መግለጹ ይታወሳል::

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 18 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች መካከል 1 ሺህ 12 ወንዶችና ስድስት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ነው የተገለፀው፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 50 ሺህ 672 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የወጣው እጣ ውድቅ ተደረገ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውድቅ አደረገ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ25 ሺሕ 491 ያወጣው የ20/80 እና 40/6 ላይ እጣ የወጣበት ሲስተም ላይ የተአማኒነት ጉድለት እንደነበር በመረጋገጡ ነው የወጣውን ዕጣ ውድቅ ያደረገው፡፡ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ…
ዝርዝር ማብራሪያ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

በመግለጫው የአስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ቀጥሎ ቀርበዋል፦

👉 በጋዜጣዊ መግለጫው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡

👉 በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

👉 ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፡፡

👉 የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፡ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል ብለዋል፡፡
 የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው በማለት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

👉 በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡

👉 ህብረተሰቡም መብቱን ለማስጠበቅ ያደረግነውን ጥረት ተረድቶናል፡፡ እኛም ድሃውን ማህበረሰብ መታደግ በመቻላችን ያስደስተናል፡፡

👉 የቀረበልን ሪፖርት በሚገባ ሲስተሙ ተቆጣጣሪ ጭምር እንዳለውና አስተማማኝ እንደነበረ ነበር፡፡ ይህንንም ለማመን ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚህ ቡድን የለሙና ጥቅም ላይ የዋሉ ሲስተሞች ነበሩ፡፡

👉 ማረጋገጫ ለማግኘት የተሄደበትና ተቋም ለተቋም የተደረጉ ግንኙነቶችም ችግር ነበረባቸው፡፡ ሰዎች ለሰዎች የተደረጉ ግንኙነቶች አይነት የተደረጉ ግንኙነቶችም መመልከት ተችሏል፡፡

👉 ኢንሳ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደነበርም በወቅቱ ተገልፆ ነበር ነገር ግን ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ ኢንሳ ያረጋገጠው እንዳለሆነ ታይቷል፡፡

👉 ዳታው በሰዎች አጅ ለአምስት ቀን ያህል መቆየቱና ይህም የተከናወነው በሃላፊዎች ትእዛዝ እንደነበር ገልፀዋል

👉 ነገር ግን የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ መታወቁን

👉 በሂደቱም እጣ ቁጠባ ያቋረጡ ሰዎች ፤ቁጠባቸውን ከረሱበት ቦታ ጭምር እጣ እንዲወጣላቸው መደረጉን

👉 የማጣራት ሂደቱን እጣ የወጣ እለት ከሰዓታት በኋላ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

👉 ይህ የማጣራት ሂደት ኢንሳ አራት ባለሙያዎች መወከሉንና ከዚህ በተጨማሪም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት የተዋቀረ ኮሚቴ በኢንሳ አስተባባሪነት ስራውን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

👉 ቴክኖሎጂዎች ለመጠቀም ያደረግነውን ጥረት ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለማው ሰው ቢሆንም ወደፊት በረቀቀ የሙያ ስልት እጣ አወጣጡን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እናድርጋለን

👉 እዚህ በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ ከእውነቱ የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ጭምር ተረጋግጧል፡፡

👉 ባለሙያዎችና አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሃላፊና አንድ ምክትል ሃላፊ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

👉 ሌሎች እርምጃዎች እንደ ሚዛኑ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
👉 የከተማ አስተዳደሩ አሁንም ቆራጥ አቋሙ ህዝቡን መብት ማስከበር መሆኑን ይህንን ቤት ለህዝብ ለማቅረብ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ጭምር የጎደለውን መሰረተ ልማት በሟሟላት ለህዝብ ማድረሱን

👉 በፍትሃዊነት ህዝብን ሃብት ለማድረስና የኋላ የኮንዶሚኒየም መጥፎ ታሪክን ላለመድገም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፡፡ አሁንም ይቀጥላል፡፡

👉 አሁንም ተቋም ግንባታ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

👉 ስለሆነም በዚህ ሁሉ ችግር እና ሂደት የወጣን እጣ ተዓማኒነት ስለሌለው እጣው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲሆን አድርገናል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
የሳሙና አምራች ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃ እጥረትና እስከ 480 በመቶ በደረሰ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት በቂ ምርት እያመረቱ አለመሆናቸው ተገለጸ።

ለሳሙና ምርት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እያሳዩ መሆናቸውንና በቂ አቅርቦትም አለመኖሩን፣ የቲቲኬ ኢንዱስትሪስ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛው መጨጊያው ገልጸዋል።

ለሳሙና ምርት የሚውሉ በርካታ ግብዓቶች በአብዛኛው ከውጭ የሚመጡ ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችም አሉ። በተለይ ‹‹ኑዱልስ›› የተባለው ጥሬ ዕቃ በአንድ ዓመት ውስጥ 480 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የታየበት መሆኑን የገለጹት አቶ ግዛው፣ ይህም በኪሎ ግራም 50 ብር ከነበረበት ወደ 240 ብር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡ በየቀኑ ጭማሪ እያሳየ ይገኛልም ብለዋል።

በአገር ውስጥ ከሚገኙት ግብዓቶች ውስጥ ‹‹ዶኖማይት›› የተባለው ጥሬ ዕቃ አሶሳ አካባቢ እንደሚገኝ፣ በተለይም በፀጥታ ችግር ምክንያት በበቂ መጠን ማግኘት አለመቻሉን ገልጸው፣ በዋጋውም ላይ ከነበረበት በኪሎ ግራም ከሦስት ብር ወደ አሥር ብር ከፍ ማለቱን አክለዋል።

በጥሬ ዕቃ እጥረት ምክንያት በአምራቾች ላይ የሚደርሰው ጫና በተጠቃሚዎች ላይም የዋጋ ጭማሪ እንዲኖር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በአንድ የሳሙና ምርት ላይም እስከ 70 በመቶ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስረድተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/108232/

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo
Forwarded from YeneTube
🎁 #ArtLand_gifts 🎁 Best Gifts


✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት(MDF) እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን

"እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በፖስታ ቤት እንልካለን 📦✉️

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
@artlandengraving
@artlandengraving
Forwarded from YeneTube
Room.et

ከ 200 ብር ጀምሮ ጥራት ያላችውን የሆቴል ክፍሎችን ባሉበት ቦታ ሆነው ይያዙ።

Room.et ተጠቅመው ሲይዙ፣ የሆቴል እና የገስት ሃውስ ክፍሎች በጥራት ፤ በዋጋ፤ ርቀት እና አገልግሎት አይነት አነጻጽረው በካሽ፤ በቴሌብር እና አሞሌ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ።

በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች እንገኛለን። 9883 ይደውሉ ወይንም

Download Room.et 👉🏻 https://bit.ly/3bMJou0
ትክክለኛውን የሩም ማዕበራዊ ገፆች ይከታተሉ።
TelegramTiktokInstagram
በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ የሕዝብ ተሳትፎና የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ ይፈጸማል ተባለ!

በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ሂደት የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡

ኃላፊው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት በ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሐምሌ 01 ቀን 2014 እጣ አወጣጥ ላይ የተገኘውን ግኝት ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ የወሰደው ፈጣን እርምጃ ፍትሕን ከማስፈን አኳያ ተገቢነት ያለው ውሳኔ ነው፡፡

የማጣራት ሥራው በሚመለከታቸው ተቋማት እና ከፍተኛ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የተከናወነ ሥራ መሆኑም የግኝቶቹን ተአማኒነት ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡በቀጣይ ለሚከናወኑ የእጣ አወጣጥ ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባ ገልጸው ለተግባራዊነቱም እንተጋለን ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa