YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የደቡብ ሱዳን የውሀና መስኖ ሚኒስትር በግብፅ ጉብኝት ላይ እያሉ ህይወታቸው ማለፉ ተዘገበ።

@Yenetube @Fikerassefa
ኢሰመኮ በምዕራብ ወለጋ በሲቪል ሰዎች ላይ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱን ገለጸ!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮማሽን(ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ በመግስት እና መንግስት በሽብር በፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ቡድን መካከል ከነበረውን ውጊያ ጋር በተያያዘ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል።ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው በሚኖሩ ሲቪል ሰዎች ላይ የህይወት፣ የአካል እና የንብረት ጉዳት ማድረሱን የገለጸው ኢሰመኮ የጸጥታ ሰጋት በመኖሩ ነዋሪዎቹ አሁንም ድጋፍ እየጠየቁ ነው ብሏል።

ኢሰመኮ በትናንትናው እለት በባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል አሮሞ ብሄረሰብ ዞን የመንግስት የጸጥታ ኃይሎት የኦነግ ሸኔ አባላት ናቸው በተበሉ ሰዎች ላይ ከህግ ውጭ የሆነ ግድያ ፈጽመዋል ብሏል።ይህን ከህግ ውጭ የሆነ ግድያ መጋቢት 2፣2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርቱ ማካተቱን የገለጸው ኢሰመኮ ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲሰፍን አሳስቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤ በቀለ"መንግሥት በሲቪል ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስድ"እና ሐችግሩ ዘለቂ መፍትሄ ኦንዲሰጥ አሳስበዋል።ኢሰመኮ በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት እና በታጠቁ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ጥቃት እየተከታተልኩት ነው ብሏል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
አብን በለጠ ሞላ ከሊቀመንበርነታቸው ለመነሣት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ኃላፊነታቸው ለመነሣት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።ፓርቲው አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

በዋናነት ፓርቲውን የተሻለ ለማድረግ እና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የተሰየመው ማዕከላዊ ኮሚቴው ሊቀመንበሩ “4 ዓመት የቆዩ አመራሮች ይቀየሩ ወይም በሌላ ይተኩ” በሚል ባቀረቡት ሐሳብ ላይ ረዥም ጊዜ የፈጀ ክርክር ካደረገ በኋላ የቀረበውን ሐሳብ ውድቅ በማድረግ አመራሩ እስከ ድርጅቱ አጠቃላይ ጉባኤ ድረስ እንዲቆይ ወስኗል።

ፓርቲውን ለማሻሻል እና ተቋማዊ አንድነቱን አስጠብቆ ለመንቀሳቀስ ሊሠራ እንደሚገባ እና ለዚህም ከ1 ወር በኋላ ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም አብን ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያካሂድ ማዕከላዊ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ወስኗል።ለዚህ የሚሆን አመቻች እና የቴክኒክ ኮሚቴ የሚሰየም መሆኑንም የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ መግለፃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕገ ወጥና ኢመደበኛ በሆኑ ሃይሎች በንጹሀን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።ንጹሀንን የመግደልና ማህበረሰቡን የማሸበሩ የዚህ አይነቱ ዘግናኝ ድርጊትን መንግስት እንደማይታገስም ገልጸዋል።ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታን መመለስ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል በድርቅ የተራቡ ጦጣዎች ሕጻናትን ማጥቃት መጀመራቸው ተገለጸ!

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ከፍተኛ ድርቅ የተራቡ ጦጣዎች ሕጻናትን ማጥቃት መጀመራቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን ሪፖርት እንደደረሰው አስታወቀ።ሴቭ ዘ ችልድረን ሰኔ 9/2014 የዱር እንሰሳት ሕጻናትን ማጥቃት ስለመጀመራቸው ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የዱር እንሰሳት ‹ከተፈጥሮ ውጪ› ሕጻናትን እንዲተናኮሉ ምክንያት ሆኗል ብሏል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በትላንትናው ዕለት ኹለት ታዳጊዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ!

በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ኳስ ለማወጣት ወደ ወንዝ የገቡ ኹለት ታዳጊዎች ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስር በተለምዶ ቀይ አፈር በሚባለው አካባቢ አደጋው ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ መድረሱ ነው የተነገረው።

የዘጠኝ እና የአስራ አራት ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎቹ ኳስ እየተጫወቱ ሳለ ኳሱ ወደ ወንዝ ሲገባባቸው ለማውጣት በሚያርጉት ጥረት በውሃው ታፍነው መወሰዳቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

አንዱ ታዳጊ ወዲያው ህይወት ሲያልፍ ኹለተኛው ደግሞ ሆስፒታል ከገባ በኃላ ህይወቱ ማለፉን ተነግሯል፡፡ምክትል ኢንስፔክተር ማርቆስ የተያዘው የክረምት ወቅት በርካታ ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ መሆናቸውን እና የወንዞች ዳርቻ ጥንቃቄ ካልተደረገባቸው በርካታ ችግር ሊፈጥሩ እንሚችል በመግለፅ፤ ወላጆች እና ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
"መንግስት ለሚረግፉ ዜጎቻችን ህይወት ተጠያቂ ነው" ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ጭፍጨፋዎች በፅኑ ያወግዛል፡፡ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋዎች እንዳይፈጠሩ አስቀድሞ መስራት ያለበት መንግስት ለሚረግፉ ዜጎቻችን ህይወት ተጠያቂ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ ሲሆን በዚህ ወቅት መንግስት የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ ስራውን በጥንቃቄ እዲሰራ እንጠይቃለን፡፡ እንዲህ ህዝብን በሚያሸብሩ እና የዜጎችን ህይወት እንደዋዛ በሚቀጥፉ ነፍሰ በሎች ላይ እርምጃ ሲወስድ በማያዳግም መንገድ እንዲሆን አልያ እንደተለመደው ነካክቶ መተው በየጊዜው የወገኖቻችንን ውድ ህይወት እያስገበረን እንደሚቀጥል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ የሚወሰዱ እርምጃዎች ተመልሰው ለህብረተሰቡ የደህንንነት ስጋት መሆን በማይችሉበት ደረጃ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲፈፀሙም እንጠይቃለን፡፡

በወለጋ፣ በጋምቤላ እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከፍተኛ ግፍና መከራ ለደረሰባቸው እንዲሁም ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡

የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ።ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው፤ "በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሸባሪው ሸኔ በንጹሐን ወገኖች ላይ በፈጸመውን ግድያ የተሰማኝን ሀዘን እየገለጽኩ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁ" ብለዋል።

"ድርጊቱ አገራችንን ከአሸባሪዎች ለማጽዳት የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክረን ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለን ማሳያ ነው" ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከ260 እስከ 320 እንደሚደርሱ የአይን ምስክሮችን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።

ከጥቃቱ በኋላ የሟቾችን አስክሬን በጅምላ በመቅበር የተሳተፉ ሁለት ግለሰቦችን እንዳነጋገረ የጠቀሰው ዘገባው አንደኛው የአይን ምስክር የሟቾች ቁጥር 260 እንደሆነ ሲገልጹ ሌላኛው ደግሞ ቁጥሩን 320 ያደርሱታል።

በወቅቱ በተፈጸመው ጉዳት እና በደረሰው የጉዳት መጠን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሃይሉ አዱኛም ሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱ ቃል አቃባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ወዲያው መልስ አለመስጠታቸውን የዜና ምንጩ ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ትናንት ባወጣው መግለጫ «የኦሮሞ ነጻነት ጦር» የተባለ ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን ማድረሱን ገልጾ «በሲቪል ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስድ» ጠይቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በእግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ እቃ ያስቀመጡ ድርጅቶች የግንባታ ፈቃዳቸዉ ሊሰረዝ ይችላል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በእግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ እቃዎች ያስቀመጡ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ለአንድም ቀን ይሁን ይህ ማድረግ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡ያለ ይዞታቸው የእግረኛ መንገድን የሚያጨናንቁ ድርጅቶች መኖራቸውን ደርሸበታለሁ ያለዉ ባለስልጣኑ፣ በአስቸኳይ እንዲያነሱ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በባለስልጣኑ የግንባታ ክትትል እና ቁጥጥር ዳሬክትር አቶ ሙሉጌታ ሊክዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከተሰጣቸው የግንባታ ቦታ ውጪ የሚጠቀሙና የግንባታ እቃ የሚያስቀመጡ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ ነግረዉናል፡፡

ለእግረኛ ተብሎ በተሰራ ቦታ ላይ በማን አለብኝነት የግንባታ እቃዎች ማለትም አሸዋ፣ድንጋይ፣ ፌሮ እና ሌሎችም እቃዎች ያስቀመጡ ድርቶች የግንባታ ፈቃዳቸዉን እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድባቸዉ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡በእግረኛ መንገዶች ላይ የሚቀመጡ የግንባታ ግብዓቶች ዓይነስውራን እና አካል ጉዳታኞች ለከፍተኛ ችግር እንዲጋለጡ እያደረጉ መሆናቸዉንም ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በተጠረጠረበት ወንጀል የ10 ሺህ ብር ዋስ አሲዞ ከእስር እንዲፈታ ተፈቀደ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀድሞ የኢትዮፎረም አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል በ10 ሺህ ብር ዋስ አሲዞ ከስር እንዲፈታ በዛሬ ፈቃድ መስጠቱ ታዉቋል።

Via :- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
እናት ፓርቲ መንግሥት ታጣቂ ቡድኖች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን ዘግናኝ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ማስቆም ካልቻለ በይፋ ዓለማቀፍ እገዛ ይጠይቅ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

መንግሥት የንጹሃንን ጭፍጨፋ በቸልታ ያለፉ የክልልና የአካባቢ አስተዳደር ኃላፊዎችን በሕግ እንዲጠይቅና በምትካቸው ከጥላቻ የጸዱ አመራሮችን እንዲሾም እና ሕዝብን ለከፋ ጥቃት ከማጋለጥ እንዲቆጠብም ፓርቲው አሳስቧል። ፓርቲው ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች በግፍ ለተጨፈጨፉ ዜጎች ብሄራዊ የሐዘን ቀን እንዲታወጅም ጠይቋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
አብን የፌደራል፣ የኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥታት በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ለመከላከል እና ጭፍጨፋውን የሚያስቆሙ ተጨባጭ ርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁነትና ፍቃደኝነት ሊያሳዩ አልቻሉም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል።

አብን መንግሥት በአማራዎች ላይ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን እንደ ተፈጥሯዊ እና መደበኛ ክስተት ቆጥሯቸዋል በማለትም ወቅሷል። መንግሥት ጭፍጨፋውን ማስቆም ካልቻለ የጥቃት ተጋላጭ ዜጎችን ጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ራሳቸውን ከጭፍጨፋ የሚከላከሉበትን ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈጥር፣ ጭፍጨፋውን የፈጸሙና ተባባሪ የመንግሥት አካላትን ለሕግ እንዲያቀርብ እና በሕይወት ለተረፉት አስተማማኝ ጥበቃ እንዲያደርግ አብን ጨምሮ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለቤቱን እና የ 8 ዓመት ልጁን በእንጨትና በዱላ የገደለዉ ግለሰብ የሞት ፍርድ ተፈረደበት!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ነዋሪ የሆነዉ ግለሰብ በጥርጣሬ ባለቤቱ በተኛችበትና ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ በእንጨት ዱላ ጭንቅላቷን ደጋግሞ በመምታት እንዲሁም በስለት በመዉጋት እና በመቁረጥ ለህልፈት እንድትዳረግ ማድረጉ ተነግሯል።በተመሳሳይ ሰዓት ድርጊቱን ስትመለከት የነበረችዉ የ8 ዓመት ልጁን በዱላ ጭንቅላቷን በተደጋጋሚ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

በጉራጌ ዞን አኖር ኤነር መገር ወረዳ አንዘች ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ አይሱ በድር የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት በጥርጣሬ ድርጊቱን ሊፈፅም መቻሉ የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. የዋለዉ የጉራጌ ዞን የወልቂጤ አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ አይሱ በድር ዐቃቤ ህግ ባቀረበበት ሁለት ክስ በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ የተቀመጠውን በመተላለፍ ባለቤቱን እና የ ስምንት ዓመት ልጁን በመግደል ወንጀል ጥፋተኛ በማለት በሞት ፍርድ እንዲቀጣ ዉሳኔ አሳልፏል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በጎዳና ከሚኖሩ ልጆች 93 በመቶ የሚሆኑት ከክልል ከተሞች እንደሚመጡ ተነገረ!

በአዲስ አበባ ከተማ በጎዳና ላይ ከሚኖሩ ልጆች የአዲስ አበባ ተወላጅ የሆኑት 7 በመቶ ሲሆኑ ሌሎች 93 በመቶ የሚሆኑት ከክልል የሚመጡ መሆናቸውን በጥናት መረጋገጡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል ።ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ከተማ በልመና ስራ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ስለመኖራቸው እውቅና እንዳላቸው በማንሳት ችግሩን ለመፍታት ቅንጅታዊ ስራ እንደሚፈልግ በቢሮው የህፃናት ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ የሆኑት አ/ቶ አናንያ ያዕቆብ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደር ማድረግ የሚቻለው ህፃናትን በተቋም ማቆየት ፣ የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት ማሟላት ፣ ስልጠና መስጠት ፣የስነልቦና ድጋፍ ማድረግና ቤተሰቦቻቸዉን አፈላልጎ የተረጋጋ ሁኔታ በተፈጠረበት አካባቢ መልሶ የማቀላቀል ስራውን ይሰራል ብለዋል ። ነገር ግን ሚዛን ከአቅማቸው በላይ ተሸክመው ዳቦ እንኳን ማግኘት የማይችሉ ህፃናት መኖራቸውን ብናውቅም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው በመሆኑ ከጎዳና ላይ ስለተገኙ ብቻ ስለ ልጆቹ ሙሉ መረጃ ሳይኖርና ህጋዊነት ሳይጠበቅ እንዲሁ ተነስተው ወደ ተቋም አይገቡም ብለዋል ።

በአንድ ወቅት ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ጎዳና ላይ ሚዛን የሚሰሩ ታዳጊዎችን ማንሳት ተጀምሮ የነበረ መሆኑንና ለልጆች ሚዛን በመስጠት የሚያሰሩ ግለሰቦች ተይዘዉ ክስ ተጀምሮ ሊመሰክር የሚችል አካል ባለመገኘቱ ግለሰቦች ተለቀዋል ሲሉ አክለዋል፡፡ በዚህ የተነሳ ልጆችን ከጎዳና የማንሳቱ ስራ መቋረጡን ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬድዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሂዳል!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት፤ በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ፣ 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለትያካሂዳል።ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው በዋናነት የፌዴራል መንግስት መሥሪያ ቤቶችን የ2013 በጀት ዓመት ሒሳብ፤ የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ያዳምጣል።

እንዲሁም፤ የምክር ቤቱን 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ መርምሮ እንደሚያጸድቅ፣ ለዕለቱ የተያዘው አጀንዳ ይጠቁማል።በዚህ የምክር ቤት ጉባዔ፤ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ የፌዴራል ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ወይም ወኪሎቻቸው እንደሚገኙ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፈው ሳምንት በታጠቁ ኃይሎች ድንገተኛ ተኩስ ሰላሟ ተናግቶ የነበረችው የጋምቤላ ከተማ አሁን ላይ ወደ ሙሉ መረጋጋት ተመልሳለች ተብሏል፡፡

ድንገተኛ ተኩስ ከከፈቱ ታጣቂዎች 117ቱ መገደላቸውንም የጋምቤላ ፖሊስ ኮምሽን ለሸገር ተናግሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቂ ትኩረት አለመስጠታቸው ለደረሰው ጥቃት ምክንያት ሆኗል ሲል ኢሰመጉ ገለፀ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በታጣቂዎች የሚደርሱ ጥቃቶች በፌደራል እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስታት በቂ ትኩረት አለመስጠት እና ጥቃት አድራሾች ላይ ህጋዊ ተጠያቂነት አለመመስረት በጊምቢ ወረዳ ለተከሰተው ድርጊት ምክንያት ነው አለ።

ኢሰመጉ በጊምቢ ወረዳ ጥቃት እና በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ አካባቢ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በነቀምቴ አካባቢ “በመንግስት የፀጥታ አካላት ከሸኔ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከህግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶች እየተፈፀሙ ነው” ሲል አስታውቋል።

ጉባኤው መንግስት ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች በቂ የፀጥታ አካላትን በማሰማራት መሰል ጥቃቶች ዳግም እንዳይፈፀሙ መከላከል አለበት ሲል አሳሰቧል።

ኢሰመጉ በመግለጫው የፌደራል እና የክልል መንግስታት የዜጎችን ደህንነት የማስከበር ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እንዲሁም በምዕራብ ወለጋና አካባቢው ከሸኔ ጋር በሚደረገው ዉጊያ ሁለቱም ኃይሎች ንፁሀንን እንዳያጠቁ ጠይቋል።

“በዚህ ጥቃት የተሳተፉ ማንኛውንም አካላት ምርመራ በማድረግ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ” ሲልም ጉባኤው ለመንግስት ጥሪ አቅርቧል።ኢሰመጉ በመግለጫው በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ያለ ሲሆን መንግስት ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲቆጣጠር አሳስቧል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስብሰባ ረግጠው ወጡ!

ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን አባላት ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል። ረግጠው የወጡበች ምክንያት በዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አማካኝነት ቀዳሚ አጀንዳ ወለጋ ጊምቢ ስለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ብሄራዊ የሃዘን ቀን እንዲታወጅ፣ ስብሰባውም በህሊና ጸሎት እንዲጀመርና ጠቅላይ ሚኒስትሩም በም/ቤቱ ቀርበው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለአፈ-ጉባኤው ቀርቦ እንደነበር እና ነገር ግን አፈ-ጉባኤው ግን አጀንዳው እንዲያዝ አለመፍቀዳቸው ታውቋል።

በዘር-ተኮር በሆነው ጭፍጨፋ ከ400 በላይ ዜጎቻችንን ባጣንበት ወቅት ስብሰባውን እንደ አዘቦት ቀን መታደም ለህሊናችን ስለከበደን የሚከተሉት የአብን አባላት የም/ቤቱን ጉባኤ አቋርጠን ለመውጣት እንደተገደዱ ከዚህ በታች ያሉ የምክር ቤት አባላት መረጃውን አድርሰውኛል።

1. ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ (የባህር ዳር ተወካይ)
2. አቶ አበባው ደሳለው (የጅጋ /ምዕራብ ጎጃም ተወካይ)
3. አቶ ሙሉቀን አሰፋ (የሸበል በረንታ- ዕድ ውሃ ተወካይ)
4.አቶ ዘመነ ሃይሉ (የጭስ አባይ ተወካይ)

መረጃ ያደረሱኝ የምክር ቤት አባሉ አክለውም አቶ ክርስቲያን ታደለ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ስለሆኑና የሳቸው ኮሚቴ ሪፖርት ስለሚያቀርብ ስብሰባውን አቋርጠው መውጣት እንዳልቻሉም ገልፀዋል::

ምንጭ ፡- ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ዋና ኦዲተር ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ 24 ተቋማት መገኘታቸውን አስታውቋል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስርያ ቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ እያቀረበ ባለው ሪፖርት በ24 መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ የሒሳብ መደቦች ሳያስፈቅዱ እና በጀት ሳያዘዋውሩ ከተደለደለው በጀት በላይ ወጪ የሆነ ሒሳብ መገኘቱን አረጋግጧል፡፡

ከመደበኛ በጀት 645,198,927 ነጥብ 44 በላይ ሆኖ መገኘቱን ነው ያረጋገጠው።

በልዩ ልዩ የሒሳብ መደቦች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ ከተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶች መካከል፡- የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተካተዋል።

ተቋማቱ በየሒሳብ ኮዶቹ ከተፈቀደው በጀት ከ10 በመቶ በላይ ያልተጠቀሙበትን ብቻ በመውሰድ፤ በድምሩ ብር 21,012,778,873.67 ያልተሠራበት በጀት ተገኝቷል ማለቱን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa