በቀድሞ የደርግ ባለሥልጣን ላይ የተወሰነው የእድሜ ልክ እስራት እንዲጸና ተበየነ
የደች ዜግነትን ያገኙትና የቀድሞ የደርግ መንግሥት ባለሥልጣን የነበሩት መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ ላይ የዓለም ዐቀፉ የጦር ወንጀለኞች በሚዳኙበት በሄጉ ፍርድ ቤት ተወስኖ የነበረው የእድሜ ልክ እስራት እንዲጸና የደች ፍርድ ቤት መወሰኑ ተዘግቧል።
የ67 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ጉዳይን ሲመለከት የነበረው የሄጉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ በጦር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩትን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ይግባኝ ጥያቄ ባለፈው ረቡዕ ውድቅ አድርጓል።
የቀይ ሽብር ዘመቻ ተካሂዶበታል በሚባለው በ70ዎቹ መጀመሪያ በነበራቸው ተሳትፎ ከአምስት ዓመት በፊት ጥፋተኛ ተብለው የነበሩት ይግባኝ ባይ፣ ውሳኔው ውድቅ እንዲደረግላቸው አመልክተው ክሱን ግን በነበረባቸው ከፍተኛ ሕመም ምክንያት በአካል ተገኝተው መከታተል አለመቻላቸውን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa

YeneTube
Photo
**ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 300 ሺህ ቶን ስንዴ እና በቆሎ እንደተበላሸባት ገለጸች
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 107 ቀናት ሆኖታል**
ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 300 ሺህ ቶን ስንዴ እና በቆሎ እንደተበላሸባት ገልጸች፡፡
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ይፋዊ ጦርነት ከጀመረች 107 ቀናት ተቆጥረዋል።
ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ብቻ የሩሲ ጦር ባደረሰው ጉዳት ምክንያት 300 ሺህ ቶን ስንዴ እና በቆሎ ከጥቅም ውጪ መሆኑን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ታራስ ቬሶቲክዬ ለሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን እንዳሉት የዩክሬን በጥቁር ባህር ባለ የጥራጥሬ ማከማቻ ውስጥ ያጠራቀመችው 300 ሺህ ቶን ስንዴ እና በቆሎ በሩሲያ ጦር ወድሟል ብለዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ጦርነት በተቀረው ዓለም ላይ ጉዳት በማድረስ ላይ ሲሆን በተለይም የምግብ እና ነዳጅ ዋጋ እንዲያሻቅብ እያደረገ ይገኛል፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዩክሬናውያን መኖሪያቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት ሲሰደዱ 20 በመቶ የዩክሬን ክፍልም በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር መውደቁን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት መሰረት መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት ከተሰደዱ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዩክሬናውያን መካከል 2 ነጥብ 5 ያህሉ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡በጦርነቱ እስካሁን ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ5 ሺህ በላይ ንጹሃን ደግሞ እንደቆሰሉ የዚሁ ተቋም ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በዚህ ጦርነት ምክንያት የምግብ ዋጋ ካሻቀበባቸው ሀገራት መካከል አፍሪካ አንዷ ስትሆን ከሰሞኑ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ወደ ሞስኮ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መምከራቸው ይታወሳል፡፤
ዩክሬን በኦዴሳ ወደብ ላይ ያጠመደቻቸውን ፈንጂዎች ካላነሳች ከሩሲያ እና ዩክሬን በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ የሆነችው አፍሪካ ወደ ከፋ ረሃብ ልታመራ ትችላለች ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ክጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል፡፡

308 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በዚህ ሳምንት ትግራይ ክልል ገብተዋል ሲል የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ
በዚህ ሳምንት ወደ ትግራይ ክልል 308 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መድረሳቸዉን የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታዉቋል።
ይህም 800 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ተደራሽ ይደረጋልም ብሏል በትዊተር ገጹ።
በተመሳሳይም በአማራ እና አፋር ክልሎች በቀጣይ የምግብ አቅርቦቱን እንደሚጀምር የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታዉቋል።

በፋና ላምሮት የድምፃውያን ውድድር ያለምወርቅ ጀምበሩ አሸነፈች
ዛሬ በተካሄደው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 10 የፍጻሜ ውድድር ድምፃዊት ያለምወርቅ ጀምበሩ አሸነፈች፡፡
በውድድሩ ምዕራፍ የመጨረሻ ዙር የቀረቡት ድምፃውያን ዳንኤል አዱኛ ፣ ደሳለኝ አበበ፣ያለምወርቅ ጀምበሩ እና ገረመው ገብረፃዲቅ በሦስት ዙር የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ለዳኞችና ለተመልካቾች በቀጥታ አቅርበዋል፡፡
ዳኞችም በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የየራሳቸውን ነጥብ የሰጡ ሲሆን፥ ያለምወርቅ ጀምበሩ የተጋባዥ እንግዳው የድምፃዊ ተሾመ አሰግድ ነጥብና የተመልካቾችን ነጥብ በማካተት 104 ሺህ 263 ነጥብ በማግኘት የምዕራፉ የማጠቃለያ ውድድር አሸናፊ በመሆን የ200 ሺህ ብር አሸናፊ ሆናለች፡፡
ዳንኤል አዱኛ 99 ሺህ 247 ነጥብ በማምጣት ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የ150 ሺህ ብር አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
ደሳለኝ አበበ እና ገረመው ገብረፃዲቅ 3ኛ እና 4ኛ በመውጣት በቅደም ተከተል የ100 ሺህ ብር እና የ50 ሺህ ብር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
Via :- Fbc
@Yenetube @Fikeeassefa

ኮርፖሬሽኑ የተጨማሪ ቤቶች ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ❗️
➯የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያስገነባቸውን የቀበናና የገርጂ ሳይቶች ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ፕሮጀክቶች ዛሬ ያስመረቀ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በምርቃቱ ወቅት እንደገለፁት በድርጅቱ ምዕራፍ ሶስትና አራት እቅድ መሰረት በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች በጥቂት ወራት ውስጥ የቤቶች ግንባታ ይጀመራል ብለዋል።
➯ግንባታው በ30 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ኃላፊው ጠቅሰው፤ ስራውን ለማስጀመር የሚያስፈልገውን መሬትና ሀብት የማፈላለግ ስራም ተጠናቋል ብለዋል። የቤቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ በሀገሪቱ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው አቶ ረሻድ የተናገሩት።
➯ግንባታው መንግሥት በ10 ዓመት የከተማ ቤቶች ልማት ፕሮግራሙ ያስቀመጠው ከ4 ሚሊዮን በላይ ቤቶች የመገንባት እቅድ አካል ነው።

277 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት የቀበና ወንዝ ዳር ልማት በቀጣይ ዓመት ይጀመራል ተባለ
ከኹለት ዓመት በፊት ይጀመራል ተብሎ 277 ሚሊዮን ብር በጀት ተይዞለት እስከ አሁን የዘገየው የቀበና ወንዝ ዳር ልማት በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀመር ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ከተማው (ኢ/ር)፣ ፕሮጀክቱ ከጣሊያን መንግሥት በተገኘ 277 ሚሊዮን ብር እንደሚሠራ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ከኹለት ዓመት በላይ ሊጓተት የቻለው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችን የማልማት ፕሮጀክት በአገራችን አዲስ ስለሆነ እና ሥራውም ውስብስብ በመሆኑ ባህሪውን ተላምዶ ቶሎ ወደ ሥራ ለመግባት አስቸጋሪ መሆኑን ተከትሎ ነው ብለዋል።
Via:- Addis Maleda

ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች!
ኢትዮጵያ በሞሪሸስ በተካሄደው 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናናቀቀች፡፡ከሰኔ 1 እስከ 5 በተካሄደው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ 4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሐስ በድምሩ 14 ሜዳልያዎችን በማግኘት ነው 5ኛ ሆና ያጠናቀቀችው፡፡
በ5000 ሜትር እና በ3000 ሜትር የወንዶች መሰናክል የተወዳደረው አትሌት ኃይለማርያም አማረ 2 የወርቅ ሜዳልያዎችን ለሀገሩ በማስገኘት ትልቅ ገድል ሰርቷል፡፡በወንዶች 10000 ሜትር አትሌት ሞገስ ጥኡማይ በ29:19.01 በመግባት የመጀመሪያውን ወርቅ ለኢትዮጵያ አምጥቷል፡፡
አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው ደግሞ በ3000 ሜትር የሴቶች መሰናክል 1ኛ ሆና በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ማስገኘቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa

ዘዊደሮ በሚለው የትግረኛ ዘፈኑ የሚታወቀው ወጣት ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ዛሬ ማረፉ ተሰምቷል።
ዘፋኙ አዲስ አበባ በሚገኘው በአዲስ ሒወት ሆስፒታል ላለፉት አራት ቀን ህክምና ሲከታተል ነበር ሲሉ ከዘፋኙ ጋር ቅርበት ያላቸው ወዳጆች ገልፅዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ዘፋኙ አዲስ አበባ በሚገኘው በአዲስ ሒወት ሆስፒታል ላለፉት አራት ቀን ህክምና ሲከታተል ነበር ሲሉ ከዘፋኙ ጋር ቅርበት ያላቸው ወዳጆች ገልፅዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
መስከረም አበራ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንድትፈታ ፍርድ ቤቱ ወሰነ!
መምህርት እና የፖለቲካ ተንታኝ መስከረም አበራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ ፍርድ ቤቱ ወሰነ።የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ የዋስትና መብቷ ተከብሮ በ30 ሺህ ብር የዋስትና ክፍያ ትለቀቅ ብሏል።
መርማሪ ፖሊስ በዛሬው ችሎት የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቢጠይቅም በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። የተጠርጣሪዋ ጠበቃዎች የዋስትና ጥያቄም ተቀባይነት አግኝቷል።
መምህርትና የፖለቲካ ተንታኝ መስከረም አበራ ግንቦት 13 ቀን በቁጥጥር ስር ውላ በግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ፍርድ ቤት መቅረቧ ይታወሳል።
[Addis Zeybe]

አማራ ባንክ ሰኔ 11 ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።
በባንኩ የምረቃ ዕለትም 70 የተሟሉ ቅርጫፎች የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ይኾናል ተብሏል።እሰከ ሰኔ 30 ባሉት ቀናቶች ባንኩ ቅርንጫፎቹን ወደ ከ100 በላይ የሚያሳድግ መኾኑንም ገልጿል።
የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ እንዳሉት ባንኩ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የተከፈተ ነው፤ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ የተጀመረ ባንክ ነው ብለዋል።
ባንኩ የሕዝብ ባንክ መኾኑን አንስተው እሰካሁን በብሔራዊ ባንክ ደንብ መሠረት የአክሲዮን ሸያጭ መከናወኑን አንስተዉ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች አክሲዮኖች ተሽጠዋል ብለዋል።
የካቲት 2/2014 ዓ.ም ዋና እና ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችን ማስመረጡንም አንስተዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸዉ እስከ ሰኔ 30 አጠቃላይ 100 ቅርጫፎች ሥራ እንደሚጀምሩ ጠቅሰዉ ሰኔ 11 ላይ በመክፈቻዉ 70 ቅርጫፎች ሥራ ይጀምራሉ ብለዋል።
የሠራተኛ እና የሥራ ቁሳቁስ ግብዓት የማሟላት ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት።ዋና መሪ ቃሉን "ከባንክ ባሻገር "ብሎ የጀመረዉ አማራ ባንክ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በሥራዎቹ እንደሚወጣ አስታውቋል።
እስከ ሰኔ 11 ባሉት ቀኖችም ባንኩ የፓናል ዉይይት፣ የደም ልገሳ እና ሌሎችም መርኃግብሮች እንደሚኖሩት አመላክቷል።
ባንኩ የማኅበራዊ አገልግሎቱን ለመወጣት እንዲያስችለው ሥራ በሚጀምርበት ሰኔ 11 ቀን ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ የአምበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎችን ወጭ መሸፈኑን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ከፓርላማው ለሚነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ!
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቃል የሚሰጡትን ምላሽ ያዳምጣል።ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በሚካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተያዘው አጀንዳ መሠረትም፥ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጥያቄዎችን ያቀርባሉ፤ እንዲሁም አስተያየቶችን እንደሚሰጡም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት 114 ባለሀብቶች ጠፍተዋል አለ!
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 114 የፕሮጀክት ባለቤቶች መጥፋታቸውን ተከትሎ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ግብር ማጣቱን የክልሉ መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመት ቢሮ ኃላፊ አመንቴ ገሽ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በክልሉ በእርሻ፣ በማዕድን እና በሌሎች ኢንቨስትመንቶች ከዘጠኝ መቶ በላይ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ይገኛሉ።
ከእነዚህ መካከል ከ2010 ጀምሮ እስከ 2014 ባለው ጊዜ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኹለት ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ ገብተው የነበሩ 114 የኘሮጀክት ባለቤቶች ጠፍተዋል። ለዚህም ዋናው ምክንያት በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት መሥራት አልቻልንም በማለት እና በፍላጎታቸው ሥራ አቁመው መጥፋታቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ -> https://bit.ly/3mF3SHu

በአዲስ አበባ እየተቋቋሙ ያሉ 10 መለስተኛ ፋብሪካዎች ስራ ሲጀምሩ 3.4 ሚሊየን ዳቦ በቀን እንደሚመረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማካሄድ ላይ ነው።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ለአባላቱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዋጋ ግሽበትን በተመለከተ በሰጡት ምላሽ ግሽበቱ የሚጎዳው በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎችን ነው ብለዋል።ይህንን ለመቆጣጠር የተለያዩ ርምጃዎችን እየተወሰዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕድ ማጋራት በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ቤተሰቦች መጥቀሙን አመላክተዋል።
ለአቅመ ደካሞች 8000 ቤቶች መታደሳቸውንና ተጨማሪም እየታደሰ መሆኑንም አስታውቀዋል።የእሁድ ገበያ ማዕከላት ለማህበረሰቡ ተደራሽነትን መጨመሩን ጠቁመዋል።በአዲስ አበባ የዳቦ ምርት በቀን 20 ሺህ ብቻ እንደነበር በማስታወስ አሁን በሸገርና በብርሀን ዳቦ ቤቶች በቀን ከ2 ሚሊየን ዳቦ በላይ የሚመረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
10 መለስተኛ ፋብሪካዎች በከተማ ደረጃ እየተቋቋሙ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስራ ሲጀምሩም 3.4 ሚሊየን ዳቦ በቀን በአዲስ አበባ ይመረታል ብለዋል።በየሁለት ሳምንቱ ከቤተመንግሥት ግቢ የጓሮ ግብርና ብቻ 200 እናቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን በመጠቆም ተቋማትም የጓሮ ግብርናን እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰረት ትዕዛዝ ሰጠ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፤ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ዐቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰረት ትዕዛዝ ሰጠ።ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ ላይ ለሚያደርገው ምርመራ ተጨማሪ አምስት ቀናትም ፈቅዷል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ የያዘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራውን አጠናቅቆ ለዐቃቤ ህግ ማስተላለፉን ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ለፍርድ ቤቱ በጽሁፍ አስታውቋል።ከፖሊስ የምርመራ መዝገቡን መረከቡን በጽሁፍ ያረጋገጠው ዐቃቤ ህግ የክስ መመስረቻ 15 ቀናት እንዲሰጡት ችሎቱን ጠይቋል።
ጋዜጠኛ ተመስገንን ወክለው በችሎት የተገኙት ጠበቃው ሔኖክ አክሊሉ የዐቃቤ ህግን ጥያቄ ተቃውመው፤ ፍርድ ቤቱ የደንበኛቸውን የዋስትና መብት እንዲያስከብርላቸው ጠይቀዋል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የጠበቃውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ህግ የክስ መመስረቻ 15 ቀናትን መፍቀዱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጋዜጠኛ ተመስገንን ጉዳይ ዛሬ የተመለከተው፤ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የፈቀደው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሽሮ መዝገቡ አንዲመለስ በመደረጉ ምክንያት ሲሆን፤ የዋስትና ትዕዛዙን የሻረው፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በትዕዛዙ ላይ ያቀረበውን ይግባኝ በመቀበል ነው።

በአጎዋ እግድ ምክንያት አርቪንድ ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለውን ማምረቻ ወደ ህንድ እያዞረ መሆኑን ገለፀ!
አርቪንድ በመባል የሚታወቀው የጅንስ፣ ሸሚዝ እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቅ አምራች ኩባንያ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለውን የጨርቅ ምርት ማሽነሪዎችን ወደ ህንድ እያዞረ መሆኑን ገለፀ። የኩባንያው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ወደ አሜሪካ ያለቀረጥ ምርቶችን የመላክ ዕድል (አጎዋ) በመሰረዙ እንደሆነ ተጠቅሷል።
የአርቪንድ ዋና የስራ ዕቅድ አመራር ሳሚር አግራዋል “በያዝነው ዓመት ውስጥ በህንድ ውስጥ አንዳንድ መሰረቶቻችንን በማዋቀር ያለንን አቅም ካጠናከርን በኋላ ሙሉ ለሙሉ ኩባንያችንን ወደዛ ለማዞር በኢትዮጵያ ያለውን አቅማችንን ቀስ በቀስ መቀነስ ጀምረናል” ሲሉ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሳሚር የአጎዋ ውል ለጊዜው መሰረዙን እና ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚላከው ከቀረጥ ነፃ ምርት እንዲቆም መደረጉን ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ መቀነሱ ለዚህ ውሳኔ እንደዳረጋቸው ገልፀዋል።
አጎዋ የተወሰኑ የብቃት መሥፈርቶች የሚያሟሉ ከሰሐራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከ1 ሺሕ 800 በላይ የሸቀጥ አይነቶችን ቀረጥ ሳይከፍሉ በአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ የግብይት ሥርዓት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት "የአጎዋን ደንብ የሚጥሱ እርምጃዎች ወስዷል" በማለት ከታኅሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከአጎዋ የንግድ ሥምምነት ውጪ ኢትዮጵያ እንድትሆን መወሰኑን የፕሬዚደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ማስታወቁ ይታወሳል።

ደምቢዶሎ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ!
በምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢዶሎ ውስጥ በመንግሥት ኃይሎች እና በሸኔ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።መንግሥት በሽብርተኝነት የሰየመውና ኦነግ-ሸኔ የሚለው፣ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገጻቸው ላይ በደምቢዶሎ እና በጊምቢ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን አስፍረዋል።ቢቢሲ ያነጋገራቸው የደምቢዶሎ ነዋሪዎች በከተማዋ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የከተማዋ ነዋሪ “አሁን የመሳሪያ ተኩስ እየተሰማ ነው። ከጠዋት 12፡30 ጀምሮ እስከ አሁን (5፡00) ከባድ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው። ሰው ወደ ውጪ መውጣት አይችልም። ቤታችንን ዘግተን ነው ያለነው” ብለዋል።እኚህ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የከተማው ነዋሪ ተኩሱ በብዙ የከተማዋ ቀበሌዎች ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል።ሌላ የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።ታጣቂዎቹ በደንቢዶሎ ውስጥ እንደታዩና “በመላ ከተማዋ እየተተኮሰ፣ በበራችን ደጃፍ ሲያልፉ አይተናቸዋል (ታጣቂዎች)።”
የፌደራል መንግሥት እና የክልሉ ኃይሎች፤ ማለትም መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የኦሮምያ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ ከታጣቂዎቹ ጋር ተኩስ ሲለዋወጡ እንደነበር እኚህ ነዋሪ ለቢቢሲ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።“በከተማዋ ምንም እንቅስቃሴ የለም። ሁሉም ሰው ቤቱን ዘግቶ ነው ያለው። በመንገድ ላይም ምንም ነገር የለም። ወታደሮች ብቻ ናቸው እየተሯሯጡ ያሉት” በማለት በደምቢዶሎ ከተማ ስላለችበት ሁኔታ ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ታጣቂዎቻቸው በደምቢዶሎ እና ጊምቢ ከተሞች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር እየተዋጉ መሆናቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።በዚህ ጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ቢቢሲ የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ገመቹ ጉርሜሳን ለማግኘት ሞክሮ፣ ሥራ ላይ መሆናቸውን እና በኋላ እንዲደወልላቸው በመንገር ተጨማሪ ማብራርያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
Via BBC

ወልድያና አካባቢዋ በጭጋግ በታገዘ ለከፍተኛ አቧራ ብናኝ ተዳርጋለች፤ ከተማ አስተዳደሩ ማሰሰቢያ ሰጥቷል።
ወልድያ ከተማና አካባቢዋ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10:00 ሰዓት በኋላ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የአቧራ ብናኝ ተከስቷል።
ጫጋጋማው ብናኝ አዳሩንም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፤ ክስተቱ ለጊዜው መነሻው በትክክል ባይታወቅም በአስፋልት ግንባታ ምክንያት ተቆፎሮ ሲነሳ የነበረው አቧራ ጋር ተዳምሮ አካባቢውን በከፍተኛ ሁኔታ በክሎታል።
ይኽ ከፍተኛ የአቧራ ብናኝ ለተለያዬ የጤና እክል የሚዳርግ በመሆኑ ሕዝቡ ማስክ በመልበስ የተለየ ጥንቃቄ በማድረግ የእራሱንም የአካባቢውንም ጤና በመከላከል የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።
[ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

የትግራይ ኃይሎች ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ!
የትግራይ ኃይሎች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከ18 ወራት በላይ ሲያደርጉት የነበረውን ጦርነት ለማብቃት በኬንያ መንግሥት አሸማጋይነት በሚካሄድ ድርድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።
በህወሓት ሊቀመንበር እና በክልሉ ፕሬዝዳንት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተፈርሞ የተሰራጨው ደብዳቤ የወጣው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው መንግሥታቸው ጦርነቱን በሰላም ለማብቃት ፍላጎት እንዳለው ካሳወቁ በኋላ ነው።
ከህወሓት በኩል የወጣው ደብዳቤ ከዚህ በፊት ቡድኑ ለድርድር ያቀረባቸውን ቅድመ ኹኔታዎች አላካተተም።
የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላደረጉት ጥረት አድናቆቱን የገለፀው ህወሓት፣ በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚችል ከፍተኛ የመልዕክተኞች ቡድን ወደ ኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል።
ደብዳቤው የአፍሪካ ሕብረት የሚጠበቅበትን ያህል አለማከናወኑን በመግለጽ አጥብቆ የተቸ ሲሆን፣ ባለፉት ወራት ሰላም ለማውረድ ከመቀለ አዲስ አበባ ሲመላለሱ በነበሩት የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ላይም ጥያቄ አንስቷል።
ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውንም በተመለከተ “ለሰላም ተጨማሪ ርቀት ለመሄድ ዝግጁ መሆናችን ከደካማነት ወይም ከስግብግብነት በመነጨ የቆምንለትን መርህ ለመተው እንደ መዘጋጀት ተደርጎ መታየት የለበትም” ብሏል።
በዚህ ድርድርም በኬንያ መንግሥት መሪነት የአፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ተሳታፊ እንዲሆኑም መጠየቁንም ቢቢሲ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማክሰኞ ትናንት ሰኔ 07 ቀን 2014 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው እንደተናገሩት፣ መንግሥታቸው ከየትኛውም ወገን ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚፈልግ ለዚህም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮሚቴው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ እንደሆነና በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ መሰየሙን አመልክተው፤ ሰላሙን በተመለከተ መሳካት ያለባቸው ተግባራትን፣ እንዲሁም ስለሚጠበቁ ነገሮች እያጠና መሆኑን አመልክተዋል።
“ከህወሓትም ይሁን ከማንኛውም ሰላም ፈላጊ ጋር የምንፈልገው ሰላም ነው፤ የሚቻል ከሆነ ለሰላም መቆም ችግር የለውም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጦርነት እንደማያተርፍና ከኹለቱም ጎን የሚያለማ ወጣት እየረገፈና አገሪቱም የምታወጣው ገንዘብ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሓት ጋር በሚደረገው ድርድር ይኸው ኮሚቴ ተደራዳሪ መሆኑን እና ኮሚቴው በቅርቡ የደረሰበትን ለፓርቲው ሲያቀርብ በይፋ ለሕዝብ በዝርዝር የሚቀርብ ይሆናል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከሚገኙ 13 መድሃኒት ፋብሪካዎች ሶስቱ ስራ ማቆማቸው ተነገረ!
በኢትዮጵያ ካሉት አስራ ሶስት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ፋበሪካዎች ውስጥ ሶስቱ በውጪ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ስራ ማቆማቸው ተገልጿል፡፡ ፋብሪካዎች በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የሚባሉ እና መሰረታዊ የነፍስ አድን መድሃኒቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ሲሆኑ ሰራተኞቹ ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆማቸውን የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾች እና የህክምና መገልገያ ፋብሪካዎች ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዳንኤል ዋቅቶሌ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡
ፋብሪካዎች በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙት ሳንሸንግ ፣ ካዲላ ፣ ሰሚድ ሲሆኑ ሙሉ ለሙሉ ስራ ያቆሙት ፋብሪካዎቹ የማሽን ፣የሰው ሃይል እንዲሁም የተሞላ ሰራተኛ ያሏቸዉ ሲሆን ፋብሪካው እንዲዘጋ ብቸኛ ምክንያት የሆነው የውጭ ምንዛሬ እጥረት መሆኑም ተገልጿል፡፡
አያይዘውም አቶ ዳንኤል ዋቅቶሌ እንደገጹት መድሃኒቶችን በውጪ ምንዛሬ ምክንያት በሚፈለገው መጠን ከውጪ ማስገባትም ሆነ ማምረትም አለመቻሉን ለሚመለከተው አካል ያሳወቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት መልስ ማግኘት አለመቻላቸውን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡
Via Bisrat FM