YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ናይጄሪያ አቡጃ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ናይጄሪያ አቡጃ ገብተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አብን በስራ አስፈፃሚው ደሳለኝ ጫኔ ከአባልነት መነሳት ዙሪያ አልተወያየሁም አለ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ስራ አስፈፃሚ አባሉና የቀድሞው የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ማምሻውን በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በገዛ ፍቃዳቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

ዶክተር ” ንቅናቄው ባለፈው የካቲት ወር ባካሄደው የአስፈፃሚ ተሃድሶ በቀጣይ ሦስት ወራት ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ባልበለጠ ጊዜ ወደ ስራ አስፈፃሚ እንደመለስ ፓርቲው ወስኖ ነበር” ብለዋል፡፡

ለመመለሱ ፍላጎት ባይኖረኝም የፓርቲው ውሳኔ በመሆኑ ተቀብዬው ቆይቻላሁ ያሉት ስራ አስፈፃሚ አባሉ ወደፊት በምገልጸው ባሉትና አሁን ባልዘረዘሩት ምክንያት ከስራ አስፈፃሚ አባልነቴ ራሴን አግልያለሁ ሲሉ ፅፈዋል፡፡

በንቅናቄው አባልነት እንደሚወጥሉ ግን ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል፡፡ አሻም ይህን በመያዝ የንቅናቄው ጽ/ቤት ሃለፊ ዶክተር ቴዎድሮስ ሀይለማርያምን ያነጋገረች ሲሆን ሃለፊው በሰጡት ምላሽ ፓርቲው በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ውይይት አላካሄደበትም ብለዋል፡፡

ከአንድ ወር ገደማ አብን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባሉ ክስርስቲያን ታደለ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

እንደ ጣሂር መሀመድ፣ ዩሱፍ ኢብራሂም ያሉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና በአማራ ክልል የተለያዩ የስራ ሃለፊነቶች ከመንግስት እንደተሠጣቸው ይታወቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ተመድ በየመን የታሰሩ 6 ሺ 750 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ሊመልስ ነው!

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ በመጪዎቹ ወራት ቢያንስ 6 ሺ 750 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በጦርነት በመታመስ ላይ ካለቸው የመን ለማስመለስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ድርጅቱ ስደተኞቹን ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጠይቋል።ባለፉት ወራት በሶስት በረራዎች ከ600 በላይ ስደተኞችንና ቤተሰብ የሌላቸው 60 ህጻናትን ወደ ኢትዮጵያ ማዘዋወሩን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቋል።በደቡብ የመን የወደብ ከተማ ኤደን እና በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መካከል ተጨማሪ በረራዎች ለማድረግ እቅድ እንዳለም ገልጿል ድርጅቱ፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ገቡ!

የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።ለአምስተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ የምግብ ድጋፎችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችንና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ይዘው መቀሌ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ አሰታውቋል።በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሁለት መጠለያ ጣቢያዎች ለሚኖሩ 9 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን ኮሚቴው ጨምሮ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት አዳዲስ ቦይንግ 777 ካርጎ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን ዛሬ ቦይንግ በድረገጹ አስታውቋል።

አየር መንገዱ አምስት ተጨማሪ ካርጎ አውሮፕላኖችን ማዘዙ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሄደውን የካርጎ ገበያ ለማሟላት ያግዘዋል ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። አየር መንገዱ ባሁኑ ወቅት 9 ቦይንግ ካርጎ አውሮፕላኖች አሉት።

@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የሚገኙ ከ400 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በአስቸኳይ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ጠየቀ፡፡

በክልሉ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩ ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በካምፕና በተለያዩ ቦታዎች መኖራቸውንና ክረምት ከመግባቱ በፊት ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ፓርቲው ጠይቋል። ተፈናቃዮቹ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ፣ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ብርሃኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል።በክልሉ በተወሰደ የሰላም ማስከበር ዘመቻ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን ገልጸው፣ ነገር ግን ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው የመመለሱ ሒደት መዘግየቱንና በአስቸኳይ የመመለስ ሥራው ሊከናወን ይገባል ብለዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች የሚገኙ ተፈናቃዮችን በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ተሲሳ፣ በክልሉ በአጠቃላይ 442 ሺሕ ተፈናቃዮች መኖራቸውንና ይህም ቁጥር ከክልሉ ሕዝብ አንድ ሦስተኛ እንደሚሆን ገልጸዋል።

በመተከል፣ በካማሺና በአሶሳ ዞኖች ተፈናቃዮች በብዛት እንደሚገኙ ገልጸው፣ እስካሁን የሰባዓዊ ዕርዳታ በበቂ ሁኔታ እየደረሰ ነው ብለዋል። ለዚህም በተለይም መንግሥት እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ዕርዳታ እየሸፈነ መሆኑን፣ ለእያንዳንዱ ተፈናቃዮች በወር 15 ኪሎ ምግብ ነክ ዕርዳታ እየደረሰ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን ዕርዳታውን በማድረስ በኩል ምዕራብ ወለጋ አካባቢ መንገድ በመዘጋቱ መቸገራቸውን ገልጸዋል። በግጭቱ በርካታ የግል ንብረቶች፣ እንዲሁም 189 የጤና ተቋማትና ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው መልሶ ለማቋቋም ፈታኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ሁሉም የበኩሉን ዕገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በክልሉ የእርሻ ወቅት ከመድረሱ ጋር ተያይዞ ማዳበሪያና ሌሎች ግብዓቶች በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም መገኘቱን ገልጸው፣ ሥርጭት እየተደረገ ነው ብለዋል። ተፈናቅለው የሚገኙ ሰዎችን መጪው የክረምት ወቅት ከመግባቱ በፊት፣ ወደ ቀዬአቸው እንደሚመለሱ አቶ ታረቀኝ አክለዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የፖለቲካ አመራር የገቡበትን ማወቅ እንዳልቻለ እናት ፓርቲ ገለፀ።

ፓርቲው ከሰሞኑ በአማራ ክልል ቀጥሏል ባለው መንግሥታዊ አፈና በሰቆጣ፣ በአዊ ዞን ቲሊሊ እና በሞጣ ከተሞች የሚገኙ ሁለት አመራሩ የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻለና አንደኛው በፖሊስ መታሰሩራቸውን ማረጋገጡን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።

በተመሳሳይ በወላይታ ዞን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑ ሴት ከሥራ ቦታቸው ተወስደው ቤተሰብም ሊጠይቃቸው እንዳልቻለ ማወቁን የእናት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይፈ ሥላሴ አያሌው ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል።

«እዚህም እዚያም በማናቃቸው ምክንያቶች ሰው በቁጥጥር ስርበሚውልበት ጊዜ በሕጉ መሠረት ከሚታሰርበት ምክንያት፣ አሳሪው የመሳሰሉ ነገሮች ግልጽ መደረግ አለባቸው። ይኼንን ባላመላከተ ወይንም ደግሞ ባላገናዘበ አይነት መልኩ እስካሁን ድረስ በምናውቀው አራት አባሎቻችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።ይኼ በጣም እያሳሰበን ያለ ጉዳይ ነው።

የሚያሳስበን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ብቻ አይደለም። አንዳንዶቹ በአግባብም ቤተሰብ ሊያገኛቸው አለመቻሉ ትንሽ ስጋታችን የሚጨምር ነገር አለው።»ፓርቲው «እነዚህ አፈናዎች ፍጹም ፖለቲካዊና አምባገነናዊ ሥርዓትን ለማዋለድ የሚደረግ ነው ብሎ ያምናል» ብሏል በመግለጫው።

መንግሥት ግለሰቦቹን ቢጠረጥራቸው እንኳን ያሉበትን ቦታ የማሳወቅ፣ ቤተዘመድ እንዲጠይቃቸውና ከሥጋት ነጻ እንዲሆን የማድረግ፣ ሕጋዊነትንና ሥርዓትን በተከተለ መልኩ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸውን ማክበር ብሎም ጠበቃ እንዲያቆሙ መፍቀድ ነበረበት ብሏል። ጉዳዩን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና መሰል ተቋማት ጋር እንደሚከታተለው የያስታወቀው እናት ፓርቲ መንግሥት «የዜሮ ድምር ፖለቲካዊ» ያለውን አካሄዱን በአፋጣኝ እንዲያርም ጠይቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የተፈጥሮ ጋዝና የማዕድን ፈቃድ ወስደው ውጤት ላላሳዩ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ!

በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ እንዲሁም ወርቅ ምርት እና ፍለጋ ላይ ተሠማርተው ለረጅም ዓመታት ውጤት ላላሳዩ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የማዕድን ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በዚህ ሳምንት መባቻ የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንደገለፁት፤ በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ እንዲሁም ወርቅ ምርት እና ፍለጋ ላይ ተሠማርተው ለረጅም ዓመታት ውጤት ላላሳዩ ሁለት ኩባንያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተገለጸ!

በባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቡልቱማ ቂጣታ÷ለባቡር በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል የሃገርን ኢኮኖሚ ወደኋላ ከማስቀረቱም በተጨማሪ በከተማዋ ያለውን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እያስተጓጎለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ 16 ሺህ 402 ሜትር የሚረዝም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል ስርቆት መፈጸሙን ጠቁመው፥ በዚህም 26 ሚሊየን 94 ሺህ 75 ብር የሚገመት ኪሳራ በተቋሙ ላይ መድረሱን አስረድተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚውለዱ ተነገረ!

ዮንሴ የተሰኘው አለም አቀፉ ተቋም በኢትዮጵያ ውስጥ የተመጣጠነ ደስተኛ እና ውጤታማ የሆነ የቤተሰብ ፕሮጀክት ሁለተኛውን ክፍል ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ተነግሯል።ዳሰሳዊ ጥናቱ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ ከአማራ ፣ ኦሮሚያ ፣ ሲዳማ ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች በተውጣጡ የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን አዘጋጅቶታል ተብሏል።

በእነዚህ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በተደረገው ዳሰሳዊ ጥናት በተገኘው ግኝት መሰረት በ 54 .1 የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ለቤተሰብ እቅድ ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ ነው ተብሏል።ከእዚህ በተጨማሪ 49 ከመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለወሊድ መቆጣጠሪያ ያላቸው ግምት አናሳ መሆኑን በኢትዮጵያ የዮንሴ ዓለም አቀፍ ጥናት የጤና ማዕከል ዶ/ር ጆንግ ኢን ሊ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በአማካይ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚወለዱ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ ተናግረዋል።

በከተሞች ደረጃ በአንድ ቤተሰብ እስከ ሶስት ልጆች እንደሚኖሩ ያነሱት ሚኒስትር ድኤታው ይህ ቁጥር በክልሎች በእጥፍ ይጨምራል ብለዋል ፣ በሶማሊያ ክልል ደግሞ በአማካይ እስከ 7 ልጆች እንደሚወለዱ በጥናት መረጋገጡን ገልፀዋል።ይህንን ቁጥር በመቀነስ በቤተሰብ እስከ ሶስት ልጆች ለማውረድ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።የተመጣጠነ ደስተኛ እና ውጤታማ የሆነ የቤተሰብ ፕሮጀክት ሁለተኛውን ክፍል 22.6 ሚሊዮን ኢትዮጲያውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር ዋለ!

የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ አረጋገጡ።

ተመስገን ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ከሥራ ቦታው በሁለት መኪና በመጡ የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ባልደረቦቹ ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር ያዋሉት ኃይሎች መሳሪያ የታጠቁ ይሁኑ እንጂ የሲቪል ልብስ የለበሱ መሆናቸውንም አክለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮንጎ ኪንሻሣ በቅርቡ በኢቦላ ቫይረስ መታመማቸው የተረጋገጠ 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡

ሰዎቹ በኢቦላ መያዛቸው የተረጋገጠው ባለፈው ቅዳሜ እንደነበር አናዶሉ ፅፏል፡፡በሰሜናዊ ምዕራብ ኮንጎ ኪንሻሣ የኢቦላ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ሰንብቷል፡፡እስካሁን በበሽታው ከተያዙት እና ከሞቱት ጋር ቅርርብ የነበራቸው ከ200 በላይ ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ለበሽታው ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ የሆነ ከሺህ በላይ ሰዎች የኢቦላ በሽታ መከላከያ መከተባቸው ታውቋል፡፡በኮንጎ ኪንሻሣ ከ40 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ኢቦላ ሲከሰት የአሁኑ ለ14ኛ ጊዜ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ኢኳቶሪያል ጊኒ ርእሰ ከተማ ማላቦ ገብተዋል፡፡

በናይጄሪያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝቱን አጠናቀው በአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው ከልኡካን ቡድናቸው ጋር ማላቦ የገቡት፡፡

በቆይታቸውም በሰብዓዊ እርዳታ፣ ፀረ ሽብር ጉዳዮች ላይ እና ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል ላይ በሚያተኩረው በሕብረቱ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማላቦ ሲደርሱ በአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢቢሲ ዘግቧል፡

@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ከተማ ሰዎችን በማገት የተጠረጠሩ 36 ግለሰቦች በቁጥጥ ስር መዋላቸውን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ በሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በሰጡት መግለጫ÷ በከተማዋ የእገታ፣ የመሬት ወረራ እና የጥይት ተኩስ መበራከት ለከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታ ፈጥሯል፡፡

የከተማዋን ነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስም የሕግ ማስከበር ሥራ መጀመሩን ገልጸው÷ ከፍረጃ በፀዳ ሁኔታ የሕግ ማስከበር ስራዎች መከናወናቸውን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡በዚህም መሰረት ሰዎችን በማገት ወንጀል የተጠረጠሩ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

ከሕግ ማስከበሩ ጋር በተያያዘ 10 የመንግስት ቤቶችን በኃይል ሰብረው የገቡ ግለሰቦች ቤቱን አስረክበው እንዲወጡ መደረጉን÷ በሕገ ወጥ መንገድ የተገነቡ 103 ቤቶች መፍረሳቸውን እንዲሁም 102 በሕገ ወጥ መንገድ ታጥረው የነበሩ የመንግስት ቦታዎችን ማፍረስ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም በሕገ ወጥ መንገድ የተገነቡ 106 ሸዶችና ኮንቲነሮችን ማስነሳት መቻሉን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡የሕግ ማስከበር ሥራው ፋኖን ለመያዝ እና ትጥቅ ለማስፈታት ነው እየተባለ የሚይናፈሰው አሉባልታ ከእውነት የራቀ መሆኑን ያወሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው÷ ከእውነተኛ ፋኖዎች ጋር በጋራ በሕግ ማስከበር ሥራው ተስማምተን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን ተወካዮች መንግሥት በሕግ ማስከበር ዘመቻ ስም በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመረምር አቤቱታ ማስገባታቸውን የአብን የምክር ቤት ተወካይ ክርስቲያን ታደለ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። አብን መንግሥት በተለይ በአማራ ክልል የፓርቲውን አመራሮች እና አባላትን ጨምሮ እያካሄደ ያለውን የጅምላ እስር ባስቸኳይ እንዲያቆም ከትናንት ወዲያ ባወጣው መግለጫ መጠየቁ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ እንዲቀጥል ወሰነ!

በአውሮፓውያኑ 2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ የጣለው ማዕቀብ እንዲራዘም መወሰኑን አስታወቀ።ሀገሪቱ ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ባደረገችው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ነበር ማዕቀብ ተጥሎባት የነበረው። የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብሰባ በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ባለበት እንዲቀጥል ውሳኔ ማስተላለፉን ሲጂቲኤንን ጠቅሶ አልአይን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ትናንት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት 24 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው የደረሰው፡፡በደረሰው አደጋ የሁለት ሰወች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፥ በሁለት ሰወች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ ( ሻላዬ) በተጠረጠረበት የግድያ ወንጀል ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ።

ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ በግድያ ወንጀል መጠርጠሩን ተከትሎ መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰራውን ስራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

በዚህም የሟች አስከሬን ምርመራ ለማከናወን ለህክምና ተቋም ደብዳቤ መላኩን እና በሟች ላይ የደረሰ አካላዊ ጉዳት ካለ ለማጣራት የህክምና ማስረጃ እየተጠባበቀ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።

ድምጻዊ አብርሀም ከሟች ጋር ያደረገውን የስልክ ለማጣራት ለኢትዮ ቴሌኮም ደብዳቤ መላኩንና ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ በበኩሉ ከዚህ በፊት 14 ቀን የተሰጠ በመሆኑ አሁንም 14 ቀን ሊሰጥ እንደማይጠባ በመግለጽ ምርመራቸውን ለመጨረስ አጭር ቀጠሮ ይሰጣቸው ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ፖሊስ የጀመረውን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ተጨማሪ 12 ቀን በመፍቀድ ለሰኔ 1ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በምዕራብ ጎጃም ዞን ከ595 በላይ ተጠርጣሪዎች ለሕግ መቅረባቸው ተገለጸ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን በተለያዩ ህገ-ወጥ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩ 595 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ በሰጡት መግለጫ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴው ውስጥ በማናቸውም ዓይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የሚጠረጠር ሰው ያለ ምንም ልዩነት በእኩል ወደ ህግ እንዲቀርብ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።በዚህም በዞኑ እስካሁን በድምሩ 595 የሚሆኑ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል።በህግ ማስከበር ስራው አንዳንድ ያጋጠሙ መስተጓጉሎች እንደተጠበቁ ሆነው ከሞላ ጎደል በሰላማዊ መንገድ በመፈፀም ላይ ነው ብለዋል ሀላፊው።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ በትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ፡፡

በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡የትራፊክ አደጋው የደረሰው ትናንት ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ፡፡


የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 30262 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ከጀሞ 1 አቅጣጫ ወደ ሚካኤል አደባባይ እየተጓዘ 67 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነዳጅ ሊቀዳ መግባቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ ገልፀዋል፡፡

አሽከርካሪው ነዳጅ ከቀዳ በኋላ አምስት ባለ 100 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሰጥቶ በሚሄድበት ወቅት ነዳጅ ቀጂው የብሮቹን ትክክለኛነት በመጠራጠሩ ሊያስቆመው መሞከሩን ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ጠቅሰዋል፡፡

አሽከርካሪው ግን በፍጥነት በማሽከርከር ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ዳር ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3A- 60203 አ.አ ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ አብረውት ተሳፍረው የነበሩ 2 ግለሰቦች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ አስረድተዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa