YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቢሊየነሩ አብራሞቪች በኢስታንቡል የሰላም ንግግር ላይ ተገኝተዋል

ሮማን አብራሞቪች ተመርዘዋል የሚለዉ መረጃ ዉድቅ አድርጓል


ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች በቱርክ አሸማጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተደረገው የሰላም ድርድር ላይ ታይተዋል።በኢስታንቡል በተደረገው ውይይት ላይ ሽምግልና ላይ ከሚገኙት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ ታይተዋል።

አብራሞቪች እና ሁለት የዩክሬን ተደራዳሪዎች በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ካካሄዱት ድርድር በኋላ የመመረዝ ምልክት ታይቆባቸዋል የሚል ሪፖርት ከወጣ ከሰዓታት በኋላ ነው የቢሊየነሩ ምስል ይፋ ተደርጓል፡፡ አብራሞቪች በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል በሽምግልና ሚና ላይ ሳምንታት እንዳሳለፉ ይታወቃል።

የቼልሲው የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት የዓይን እና የቆዳ ህመም አጋጥሟቸው ነበር ቢባልም አሁን ግን አገግመዋል የሚል መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ መሰረት ሮማን አብራሞቪች እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች በሩሲያ አማካይነት ተመርዘዋል ቢልም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለስልጣን ግን ሁለቱ ዩክሬናውያን ደህና እንደሆኑ እና መረጃዉ የውሸት ነው ብሏል።

ሆኖም ግን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውይይቱ ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቲቪ እንደተናገሩት ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ምንም ነገር እንዳይበሉ እና እንዳይጠጡ መክረዋል።የኢስታንቡል ውይይት ማክሰኞ እለት በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የተኩስ ማቆም እና የሰላም ጥሪ በማቅረብ "ግጭቱን ማራዘም ለማንም አይጠቅምም" ሲሉ ለሁለቱ ልዑካን ቡድን በዶልማባቼ ቤተ መንግስት ተናግረዋል፡፡

[ ዳጉ ጆርናል ]
@Yenetube @Fikerassefa
በኮንሶ ዞንና አሌ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ህይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ ተገለጸ!

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙት የኮንሶ ዞንና አሌ ልዩ ወረዳ ከሰሞኑ በተከሰተ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ ቤቶች መቃጠላቸውንና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።መጋቢት 09/2014 ዓ.ም በተነሳውና እስከ ትናንት በስቲያ በቀጠለውም ግጭት በኮንሶ በኩል አስካሁን ቁጥሩ በትክክል ያልታወቀ የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን አቶ ሠራዊት ዲባባ በኮንሶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

"የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ የአካል ጉዳት ተመዝግቧል። ይህ ጉዳት ደግሞ የሁላችንም ህመም ነው። እጅግ በጣም አሳዝኖናል" ብለዋል አቶ ሠራዊት።በአሌ ወረዳ በኩልም እንዲሁ በተመሳሳይ የሰው ህይወት መጥፋትን ጨምሮ፣ የአካል ጉዳትና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የአሌ ልዩ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ገሚሶ ገሳቶ ያስረዳሉ።

ለግጭቱ መነሻ የሆነው በኮንሶ ዞንና አሌ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ባለ የኩታ ገጠም እርሻ መሬት የይገባኛል ጥያቄ እንደሆነም ሁለቱም ባለሥልጣናት ይናገራሉ።የሰሞኑ ግጭት ከእርሻና ግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ የይገባኛል እንዲሁም የከብት ዝርፊያዎችና በሰዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ግጭቱ ማገርሸቱንም ያስረዳሉ።ከሰሞኑም በኮንሶ በኩል የኮልሜ ክላስተር እንዲሁም በአሌ በኩል ደግሞ ገዋዳ ክላስተር የሚባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል የተፈጠረው ግጭት መባባሱን የጠቆሙት አቶ ገሚሶ "የግጭቱ መነሻ በግለሰቦች መካከል የነበረ ቢሆንም ወደ ማኅበረሰቡ መስፋፋቱን" አመልክተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መጋቢት 16 ያሳለፈው ውሳኔ ገቢራዊ ይሆን ዘንድ ህወሓት ከተቆጣጠራቸው ስድስት የአፋር ክልል ወረዳዎች ለቅቆ መውጣት ይገባዋል አለ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ” ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማስቆም ስለመወሰኑ ” መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ” በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ” አስታውቋል፡፡

በዚህም” የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደትግራይ በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ጥረት ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን” መግለፁም አይዘነጋም፡፡ይሁንና ከተጠቀሰው ጊዜ አንስቶ ወደትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታዎች ወደትግራይ ክልል እየገቡ እንደማይገኝ መንግስት ገልጿል፡፡

ከአሻም ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሠ ቱሉ(ዶ/ር) ”ህወሓት ከያዛቸው ስድስት አፋር ክልል ወረዳዎች እስካለቀቀ ድረስ ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ መላክ እንደማይቻል” ተናግረዋል፡፡ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም ”ሰብዓዊ እርዳታዎቹ የሚተላለፉበትን የአስፓልት መንገድ ይዟል፤ ግጭትም አላቆመም” ሲሉ ከስሰዋል፡፡ምንም እንኳን በአፋር ክልል በኩል በየብስ ሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ ክልል ለማጓጓዝ አስቸጋሪ ይሁን እንጂ በአውሮፕላን በየቀኑ በሚደረገው በረራ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ስለመሆኑ ለአሻም ነግረዋታል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!

ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡

በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡

ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡

ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡

“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
👍1
ምርጫ ቦርድ በ2014 ዓ.ም 50 ሚሊዮን ብር ለፓርቲዎች አከፋፍላለሁ አለ!

ቦርዱ ለ35 አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች ገንዘቡን የሚያከፋፍል ሲሆን፤ ከእነዚህም ብልጽግና 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር፣ ኢዜማ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር፣ ኦብነግ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ ኦነግ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ ተብሏል።

ቦርዱ ከምርጫ ቁሳቁስ ሕትመት የተረፈውን 50 ሚሊዮን ብር ነዉ ለፓርቲዎች ድጎማ እንደመደበ የተናገረው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ የጠየቀውን የ230 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ ቢያቀርብም እንዳልተቀበለው ካስታወቀ በኋላ ነው ይህን አማራጭ የተጠቀመው። ቦርዱ ዛሬ ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ፣ አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ገንዘብ ሚንስቴር ገንዘቡን መመደብ እንደማይችል እንዳሳወቀ ገልጧል።የፓርቲዎች የድጎማ ቀመር፣ ፓርቲዎቹ በምርጫ ያገኙትን መቀመጫ፣ የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባላት ብዛት እና ያሰባሰቡትን የገንዘብ አቅም መሠረት ያደረገ እንደሆነ ዋዜማ ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤት ዛሬ የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች አሚር አማን እና ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።

ሆኖም ችሎቱ ዘጋቢዎቹ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ጥሎባቸዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም፣ ችሎቱ ግን የእስካሁኑ ምርመራ ለውጥ አላሳየም በማለት ነው የገንዘብ ዋስትናውን የፈቀደው። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ባለፈው ኅዳር ያሰራቸው፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮችን እና ታጣቂዎችን መስክ ወርደው በማነጋገር እና በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ ወደ ውጭ አገር መረጃዎችን ልከዋል በማለት ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለ2014/15 የምርት ዘመን ከውጭ ሀገር የገዛውን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ።

እስከ ዛሬ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም. ድረስ ሁለት 2 ሚሊየን 863 ሺ 890 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን ኮርፖሬሽኑ አስታዉቋል። ለዘንድሮ የምርት ዘመን የሚውል 12 ሚሊየን 876 ሺ 623 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል።

ለምርት ዘመኑ ከተያዘው የማዳበሪያ መጠን ውስጥ እስከ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም. ድረስ 3 ሚሊየን 724 ሺ 30 ኩንታል ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል ያለው ኮርፖሬሽኑ ሁለት 2 ሚሊየን 863 ሺ 890 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል።

ወደ ሀገር ውስጥ የገባው የአፈር ማዳበሪያ በማህበራት/ዩኒየኖች አማካኝነትም በየክልሉ ለሚገኙ አርሶ አደሮች እየተሰራጨ ይገኛል።በመጋቢት 29/2014 እና ሚያዝያ 1/2014 ዓ.ም. 600,000 ኩንታል በአጠቃላይ አንድ ሚሊየን 180 ሺህ 120 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ እንደሚጠበቅ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/sabinaadvisor

የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።

#ወደ_ሀብት_ጉዞ

ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡

ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡

ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።

ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።

እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት ተመለሱ!

በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።

በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት የተመለሱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት ተመለሱ! በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል። በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 498 ዜጎች ወደ አገር ቤት የተመለሱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል። @YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በሳውዲ አረቢያ በአሰቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራውን ሙሉ በሙሉ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይአምባሳደር ዲና ሚፍቲ ገለጹ።

ቃል አቀባዩ ዛሬ ጧት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ለማስመልስ ሰፊ ሰራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውስው፣ በዛሬው እለት በሳውዲ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ የቅድመ ምዝገባ ስራ ሰርቶ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ የመመለስ ስራውን ጀምሯል ብለዋል።

ከስደት ተመላሾቹ ጊዜያዊ መጠለያ የሚያርፉ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ በቀጣይነት የሚቋቋሙበት መንገድ ይሰራል ሲሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎችን ለመመለስ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ በደረሰ የእሳት አደጋ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለፀ።

በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፈረጀቴ ጎጥ ትናንት እኩለ ቀን ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 35 የሳር ክዳን ቤቶች፣ 5 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶችና 2 መስጂዶች በድምሩ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተገለፀው።2ቱ መስጂዶች በከፊል የወደሙ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በምርትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተጠቁሟል።

በጥንቃቄ ጉድለት በአካባቢው የነበረውን ቁጥቋጦ ለማጥፋት በሚል የተለኮሰ እሳት በወቅቱ በነበረ ከፍተኛ ንፋስ ወደ አካባቢው በመዛመቱ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው።በእሳት አደጋው በቤትና ንብረት ላይ ከደረሰው ውድመት በተጨማሪም በእንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል።በእሳት አደጋው ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በደረሰው አደጋ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጥ ሜዳ ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ለማቋቋም የወረዳውና የዞኑ አስተዳደር፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና መላው ህብረተሰብ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።የቀቤና ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት በበኩሉ ወቅቱ ነፋሻማ በመሆኑ የወረዳው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ገልጿል።አሁን ላይ በአደጋው የወደመው አጠቃላይ ንብረት መጠን ምን ያህል ስለመሆኑ ግብረሃይል ተዋቅሮ እየተጣራ መሆኑን ከወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ያረቀቀውን ኤስ3199 ረቂቅ ሕግ አጸደቀ።

ኮሚቴው በኢትዮጵያ ሰላም እና ዲሞክራሲ ለማበረታታት ወይም 'The Ethiopia Peace and Democracy Promotion Act' በሚል ያረቀቀውንና ኤስ3199 የተሰኘውን ይህን ህግ በትናንትናው እለት መጋቢት 20፣ 2014 ዓ.ም ካጸደቀም በኋላ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት መርቶታል።ማከሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም በከፍተኛ ድምፅ ያለፈው ይህ ረቂቅ ሕግ ለኢትዮጵያ መንግሥት በፀጥታ ጉዳዮች ላይ አሜሪካ የምትሰጠውን ድጋፍ ከማገድ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ፣ ከጦርነቱ የሚያተርፉ እንዲሁም ጦርነቱ እንዲባባስ በገንዘብ እንዲሁም በቀጥታ የተሳተፉ አካላት ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል ነው።

ረቂቅ ሕጉ ከቀረበበት ከወራት በፊት የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መልክ መቀየሩን የተናገሩት የምክር ቤቱ አባል ጂም ሪሽ፣ ሆኖም በዋነኝነት መሠረታዊ ጉዳዮቹ ተመሳሳይ መሆናቸውን መናገራቸውን የሴኔቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል።ረቂቅ ሕጉ የጦርነቱ ተሳታፊ አካላት ለፈጸሟቸው መጠነ ሰፊ ጥሰቶችና አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ ተጠያቂ የሚሆኑበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቸችም አስምረዋል።በተጨማሪም በዚህ ጦርነት ከፍተኛ ስፍራ ያላቸውን የውጭ አገራት ሚናም እትኩሮት እንደሚሰጥ አውስተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንት ሹመት በልዩ ሁኔታ በሚል የሰጠው ይሁንታ ጥያቄ አስነሳ፡፡

ሲንቄ ባንክ በበኩሉ ኢብባ በልዩ ሁኔታ ብሎ መፍቀዱ ለምን እንደሆነ ግራ እንዳጋባው ጠቅሶ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑን የጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከሰሞኑ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንትነት ሹመት ከባንኩ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው የይሁንታ ምላሽ ደብዳቤ እንደጠቀሰው የአቶ ንዋይ መገርሳን ሹመት በልዩ ሁኔታ መፍቀዱን አስታውቋል፡፡

ይህ የኢብባ ውሳኔ በዘርፉ ያሉትን ባለሞያዎች ግራ ያጋባ ሆኖም ተስተውሏል፡፡“ተቆጣጣሪ ሁሉንም በሚያስተናግደው የህግ መሰረት መስራት ሲገባው ለምን በልዩ ሁኔታ ሲል መፍቀድ ፈለገ፡፡ ሁለት አይነት አሰራር ነው የታየው፤ ከጠንካራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የማይጠበቅ ነው፣፣” ሲሉም ውሳኔውን ተችተዋል፡፡

ከኢብባ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ ሆኖም የሲንቄ ባንክ ፕሬዝደንት አቶ ንዋይ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።በምላሻቸውም የብሄራዊ ባንክ ደብዳቤ ግራ እንዳጋባቸው ገልፀው ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ የተጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ ወይም እንዲከለክል ነው ለምን በልዩ ሁኔታ ፈቅጃለሁ እንዳለ እኔም ግራ ገብቶኛል ብለዋል፡፡በማከልም በኢብባ መመሪያ መሰረት በፕሬዝደንትነት ለመስራት የሚያበቃ በቂ የስራ ልምድ አለኝ በማለት አክለዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሉ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ65 ሺ በላይ መድረሱ ተነገረ!

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከአበርገሌ፣ ከዝቋላ፣ ከባዱቢ ፣ከዛታ፣ ከወፍላ እና ኮረም አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር 65 ሺ 757 መድረሱን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ኮምኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ደባሱ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዞኑ በየቀኑ በአማካኝ 2 ሺ የሚሆኑ ሰዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ እንደሚመጡ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሠዓት የተፈናቃዮች ቁጥር ቀንሶ በአስር ቀናት ውስጥ 4 ሺ ሰዎች መፈናቃለቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መጠለያ ጣቢያ ዉስጥ ደግሞ 16 ሺ 748 ተፈናቃዮች መኖራቸዉ ተገልፆል፡፡ በዞኑ የመጠለያ ጣቢያ ችግር ከፍተኛ እንደሆነ እና በዚህም የተነሳ ተፈናቃዮች በየበረንዳው ፣ ከዘመድ ተጠግተው እየኖሩ በመሆኑ ደረጃውን የተጠበቀ መጠለያ ስፍራ ሊዘጋጅላቸው እንደሚገባ ሀላፊዉ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ አሁንም ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎች ቢደረግም የተፈናቃች ቁጥር በመጨመሩ እና የእለት ፍጆታ በመሆኑ የተነሳ በቂ ባለመሆኑ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አና ለተፈናቃዮችም በቂ መጠለያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነዉ ሲሉ አቶ ከፍያለው ደባሱ ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa