YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ!

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።ፑቲን፤ ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ ካሉ በኋላ፤ “እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን” ብለዋል።የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም የሶሪያ ወታደሮች በሩሲያ መንግሥት እየተከፋላቸው በዩክሬን ሊዋጉ ይችላሉ የሚል መረጃ በስፋት ሲሰራጭ ነበር።ባሻር አል-አሳድ ሕዝባዊ ተቃውሞ በተነሳባቸው ወቅት ከሩሲያ መንግሥት ጠንካራ ድጋፋ አግኝተው በሥልጣናቸው ላይ አሁንም ይገኛሉ።ፑቲን ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን “በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስጋዊ እረፍትን ተከትሎ የሽኝትና አስክሬናቸውን የማሳረፍ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

የሽኝቱና የቀብር ስነ-ስርዓቱ በሰላም እንዲከናወን የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በመስቀል አደባባይ የፓትርያኩ አስከሬን ሽኝት የሚካሄድና የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ሲሆን፡-
ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-

*ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ
-ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
-ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
-ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መብራት
-ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር
-ከጦር ኃይሎች ፣ በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 12:30 ጀምሮ ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በእለቱ የብፁእነታቸው አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ (ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን) በሚንቀሳቀስበት ወቅት ከመስቀል አደባባይ ፣ በብሔራዊ ቤተ መንግስት፣ ውጭ ጉዳይ ፣ አራት ኪሎ ፣ ቅድስት ማርያም የሚወስደው መንገድ፣

መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ-ስርዓት የሚፈፀም በመሆኑ የቀብር ስነ-ስርዓቱ እስከሚፈፀም ወደ ቅድስት ማርያም ፣ አራት ኪሎ እና ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሰጡት አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ግብረ ኃይሉ እያስታወቀ ለጋራ ደህንነት ሲባል በሽኝቱ እና በቀብር ስነ-ስርአቶች ወቅት ፍተሻ መኖሩን የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
አሶሴትድ ፕሬስ እስር ላይ ያሉ ዘጋቢዎቹ እንዲለቀቁለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በድጋሚ ጠይቋል።

አሚር ከሦስት ወራት በላይ እስር ላይ ቢቆይም የወንጀል ክስ እንዳልተመሠረተበት የገለጠው ድርጅቱ፣ አሚር የታሠረው በጋዜጠኛነት ሥራው ብቻ ነው ብሏል። ፖሊስ አሚርን ያሰረው ወደ ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር ተጉዞ፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ እና አመራሮቹን እና ታጣቂዎችን በማናገር ያሰባሰበውን መረጃ ኢትዮጵያ ጠል ወደሆኑ አገሮች ልኳል በሚል ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct

📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ለሴት እና ለወንድ እንዲሁም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ 👇
shein.com SHEIN.COM shein.com

ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን (SHEIN.COM)

Contact @kiru04
☎️ 0931607806

Join 👇👇👇
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

በሽኝት መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ብፁዓን አባቶች እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እጅግ አሰቃቂና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ገለፀ!

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ገለፀ።
 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት መፈጸሙን አንስቷል።
 
በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተንቀሳቃሽ ምስል ሲዘዋወር በቆየው እጅግ አሰቃቂ ድርጊት ንፁሃን ዜጎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ሲደረግ መታየቱ በመግለጫው ተመላክቷል።
 
ይህ ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል፣ እሴትና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው ያለው አገልግሎቱ፥ ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ እንደማይችልም አስገንዝቧል።

በመሆኑም ድርጊቱ ሊኮነንና ሊወገዝ ይገባል፤መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን መንግስት ይህን አይነት ፍፁም ከሰብዓዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
 
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከልም ከክልሉና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
 
የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን መንግስት ከዚህ በኋላ አይታገስም ያለው መግለጫው÷እነዚህ በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም በጥብቅ አሳስቧል።
 
@YeneTube @FikerAssefa
የሕንድ ጦር በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳየል መተኮሱን አመነ፡፡

የሕንድ የመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚሳየሉ በስህተት በመተኮሴ አዝኛለሁ ማለቱን ዴይሊ ሞኒተር ፅፏል፡፡ቀደም ሲል የፓኪስታን ጦር ወደ አገሪቱ የተወነጨፈውን ተምዘግዛጊ በሚመለከት ሕንድን ማብራሪያ ለመጠየቅ እንዳላረፈደ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ሕንድ እና ፓኪስታን ግንኙነታቸው በቋፍ ላይ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡አነስተኛዎቹን ቁርቋሶዎች ሳይጨምር ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው ቢያንስ 3 ታላላቅ ጦርነቶችን ማድጋቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡በተለይም በካሽሚር ግዛት ጉዳይ ስሜተ ስሱዎች ናቸው ይባላል፡፡

Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከነ ቀኖናዋ፣ ከነ ትውፊቷ እና ማንነቷ ለትውልድ እንድትሸጋገር በታማኝነት አገልግለዋል-ጠ/ሚ ዐቢይ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚያምኑትን አምላክ እና የሚወዷትን ቤተክርስቲያን በታማኝነት ያገለገሉ አባት ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
 
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስክሬን የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።በሽኝት መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ብፁዓን አባቶች እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሽኝት መርሃ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እንደ ጥሩ አባት ሩጫቸውን ጨርሰው ወደ ሚወዱት አባታቸው ሄደዋል” ብለዋል፡፡“አባታችን እድለኛ ናቸው፤ እድሜያቸውን በሙሉ የሚወዷት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግለዋል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
 
ብፁዕነታቸው መናገር ሲገባቸው ተናግረው፤ መጸለይ ሲገባቸው ጸልየው፤ መምከር ሲገባቸው መክረው ፤ በአርምሞ እና በጸጥታ መኖር ሲገባቸው እንዲሁ አድርገው በብዙ ያስተማሩን አባት ናቸውም ብለዋል፡፡“አባታችን በጸሎት እና በምክር ያግዙኝ ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፥ ሃሳባቸውንም በጹሑፍ በተደጋጋሚ ልከውልኛል ብለዋል፡፡
 
“ከአባታችን ልንማር የሚገባን ኦርቶዶክስ ከነ ቀኖናዋ፣ ከነ ትውፊቷ እና ማንነቷ ወደ ትውልድ እንድትሸጋገር ከግጭት እርስ በርስ ከመሰዳደብ ወጥተን በመተባበር መንፈስ አብርን መስራት እንዳለበን ነው” ሲሉም መክረዋል፡፡አሁን ወቅቱ የጸሎት ጊዜ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ምዕመናን ለአገራቸው ኢትዮጵያ ሰላም እና ለአባታችን እረፍት እንዲጸልዩም ጠይቀዋል፡፡
 
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ የአሰራር መመሪያ ጥናት እየተዘጋጀ ነው!

የነዳጅ ውጤቶች መሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም እና የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሠራር መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

ከነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ በዋናነት ኹለት መመሪያዎች ተዘጋጅተው ታኀሣሥ 20/2014 በሚኒስትሮች ምክርቤት የጸደቁ ሲሆን፣ መመሪያዎቹ የተዘጋጁት ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀ ጥናት መሆኑንና ጥናቱ የተጠናው ከተለያዩ ሰባት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሆነ የባለስልጣኑ ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ቁምነገረ እውነቱ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባው : https://bit.ly/3J5YgQf

@YeneTube @FikerAssefa
ከህወሓት ጋር ያለውን ችግር በየትኛውም የሰላም አማራጭ ለመፍታት መስማማቱን ብልጽግና አስታወቀ!

የትኛውንም የሰላም አማራጭ ተጠቅሞ ከህወሓት ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት መስማማቱን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡አንደኛ ድርጅታዊ ጉባዔን በማካሄድ ላይ ያለው ፓርቲው የትግራይ ህዝብ በህወሓት ጸብ አጫሪ ድርጊት ምክንያት ያልተገባ ዋጋ እየከፈለ ነው ብሏል፡፡የትግራይ ህዝብ ጉዳት የሌላውም ኢትዮጵያዊ ጉዳት ነው ሲሉ የድርጅታዊ ጉባዔውን የመጀመሪያ ቀን ውሎ የተመለከተ መግለጫን የሰጡት የፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)ህዝቡ እያጋጠመው ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሰላም አማራጮችን ተጠቅሞ መስራት እንደሚጠበቅ ተስማምተናል ብለዋል፡፡

ህወሓት እያደረገው ካለው ትንኮሳና ዳግም ወረራ አንጻር በተለይም የሃገርን ሉዓላዊነትና ክብርን ለመቀልበስ ለመጉዳት የነበረው ፍላጎት የተቀለበሰ ቢሆንም በድጋሚ የመውረር ፍላጎቱ ዜሮ ሆኗል ለማለት አይቻልም ያሉት ኃላፊው ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጅት ማድረግና ራስን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይህን በማድረግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር እንዲሁም ህልውና ዳግም አደጋ ላይ የሚጥል ነገር በሚያጋጥምበት ጊዜ አስፈላጊው እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ነው የገለጹት፡፡የብልጽግና አመራርና አባላትም ይህን በአንክሮ እንዲከታተሉና ንቁ ሆኖ ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት እንዲያደርጉ ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል ዶ/ር ቢቂላ፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሩፒያህ ባንዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሩፒያህ ባንዳ በ85 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሩፒያህ ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2011 የዛምቢያ ፕሬዚዳንት በመሆን ሃገራቸውን መርተዋል። ከዚያ ቀደም ብሎ በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ህይወታቸው ያለፈው የሃገሪቱ መሪ ሌቨየ ምዋንዋሳ ምክትል በመሆን አገልግለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር በራሺያ ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች የአለምን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ያደርጋሉ አሉ!

የቻይናው ጠ/ሚር ሊ ኬኪያንግ በራሺያ ላይ የሚጣሉ እቀባዎች ቀድሞውንም በኮቪድ ምክንያት ችግር ውስጥ የገባውን የአለም ኢኮኖሚ እንዲያገግም ይጫነዋል ብለዋል። ቀጥለውም ቻይና አለምአቀፍ ሰላም በሚረጋገጥበት መንገድ በመሥራት እድገት እና ብልፅግና እየመጣ ትሰራለች ብለዋል። ለዚህም ጦርነት ውስጥ ያሉትን ራሺያ እና ዩክሬን ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር እንዲመጡ እናበረታታለን ብለዋል። ዘገባው የራፕትሊ ነዉ

@YeneTube @FikerAssefa
The dates are getting closer to witness one of Largest Global Hybrid Expo, which shall be taking place at the newly built state of the art library, Abrehot Library.

Exhibitors can take part either Onsite or Virtual, form any part of the globe.

List of Exhibitors:

Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.

To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
Book online via:
www.backtoschoolafrica.com
👍1
ሩሲያ፤ ኪቭን ለመክበብ የሚያስችል ግዙፍ ወታደራዊ ኮንቮይ በማንቀሳቀስ ላይ መሆኗ ተገለጸ

እንቅስቃሴው የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ መጠጋታቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል ሩሲያ፤ ኪቭን ለመክበብ የሚያስችል ግዙፍ ወታደራዊ ኮንቮይ በማንቀሳቀስ ላይ መሆኗ ተገለጸ፡፡

በእንቅስቃሴው የዬክሬን ዋና ከተማ ኪቭ ዳግም በሩሲያ ወታደሮች ከበባ ስር ልትወድቅ ትችላለች ተብሏል፡፡

60 ያህል ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን አንድ ግዙፍ የሩሲያ ወታደራዊ ኮንቮይ ወደ ዩክሬኗ መዲና ኪቭ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ወታደራዊ የሳታላይት ምስሎች አመልክተዋል፡፡
ኮንቮዩ ወደ በቀላሉ ወደ ከተማዋ ለመግባት የሚችል ከሆነ ፕሬዝዳንት ዜለንስኪን ጨምሮ ሌሎች የሃገሪቱ በለስልጣን አለን የሚሉባት ኪቭ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ኃይሎች እጅ የምትወድቅ ይሆናል፡፡

የሩሲያ ወታደሮች በተለያዩ አቅጣጫዎች ማጥቃት መጀመራቸውም ነው የተነገረው፡፡ ሊሰነዘር የሚችልባቸውን የትኛውንም ዐይነት ጥቃት ለመከላከል ይችሉ ዘንድ በስብጥር መሰማራታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች በቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ እንዲቀመጡ መደረጋቸውን የሚያሳዩት ምስሎቹ ኪቭ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ልታስተናግድ የመጨረሻው ሰዓት ላይ ለመድረሷ ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው ተብሏል፡፡

የሩሲያ የእግረኛ ጦር አባላት ከኪቭ በ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኙም የብሪታኒያ የደህንነት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ከሳምንት በፊት ተመሳሳይ የወታደራዊ ኮንቮይ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳዩ ምስሎች ይፋ ሆነው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይህ በአዲስ መልክ የተነቃቃ የሚመስለው የሩሲያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያለ ስኬት ከተጠናቀቀው የአንታልያው ውይይት በኋላ የሆነ ነው፡፡

በቱርክ አንታልያ ከተማ የተገናኙት የሃገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተኩስ ለማቆም ከሚያስችል ስምምነት መድረስ ሳይችሉ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ብልፅግና ፓርቲ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የፓርቲው ፕሬዘዳንት አድርጎ የመረጠ ሲሆን አቶ አደም ፋራ እና አቶ ደመቀ መኮነንን ምክትል ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ጫንጮ ከተማ የኦኑግ ሸኔ ታጣቂዎች ካገቷቸው የኢትዮ ስሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች 18 ኢትዮጵያዊያን ሐሙስ ዕለት በአገር ሽማግሌዎች ጥረት እንደተለቀቁ ዋዜማ ሰምታለች። ታጣቂዎቹ ካገቷቸው የፋብሪካው ሠራተኞች መካከል 6ቱ ሕንዳዊያን ሲሆኑ፣ ሕንዳዊያኑ እና ሦስት አስተርጓሚዎቻቸው አሁንም በታጣቂዎች እገታ ስር ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ታጋች ባልደረቦቻቸውን ገንዘብ ከፍለው ለማስለቀቅ ከታጣቂዎቹ ጋር የተደራደሩ 4 የፋብሪካው ሠራተኞችን አስሯል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ግን 18ቱ ታጋቾች ስለመለቀቃቸው እንዳልሰሙ ለዋዜማ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa