YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የዓለም የምግብ ድርጅት የሥራ ሃላፊዎች ቦረና ዞንን እየጎበኙ ነው።

ልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸው ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።በቦረና ዞን ለተከታታይ ወቅቶች ዝናብ ባለመጣሉ የተከሰተው ድርቅ ቁጥሩ ከፍ ያለ የዞኑ ነዋሪን ለምግብ እህል እጥረት የዳረገ ሲሆን፥ በከብት ሀብት ላይ የከፋ ጉዳት አድርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
አጫጭር መረጃ የዩክሬንን ቀዉስ በተመለከተ

🇷🇺የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ምስራቃዊ ክፍል የሚገኙ አማፂ ተገንጣይ ክልሎችን እንደ ገለልተኛ መንግስታት እውቅና ሰጥተዋል፡፡የዶኔትስክ እና የሉሃንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ በሩሲያ የሚደገፉ አማፂያን ሲሆኑ ከ2014 ጀምሮ የዩክሬይን ጦርን ሲዋጉ እንደነበር ይታወሳል፡፡

🇺🇦የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ለሊት በቴሌቭዥን ለህዝቡ ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ሰላም ትፈልጋለች ነገር ግን አንፈራም እና “ሉዓላዊነታችንን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም” ብለዋል። ኪየቭ አሁን ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ "ግልጽ እና ውጤታማ የድጋፍ እርምጃዎች" ያስፈልጋታል ሲሉ ተናግረዋል።

🇦🇺🇺🇸በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የሩሲያ ዉሳኑ ትርጉም የለሽ በሚል ያወገዙት ሲሆን የአዉስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮቲ ሞሪሰን ዉሳኔ ተቀባይነት የሌላዉ ሲሉ አጣጥለዉታል፡፡

🌍🇷🇺የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ለሁለት ተገንጥላ ክልሎች እውቅና ከሰጠች ከሰዓታት በኋላ ነዉ፡፡ሞስኮ "ሰላምን ለማስጠበቅ" ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ተገንጣይ ግዛቶች እንደምታሰማራ አስታዉቃለች፡፡

🇺🇸ዩናይትድ ስቴትስ የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መግለጫ "የዩክሬንን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን መጣስ ነው" ስትል ዩክሬን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ያቀረበችውን ጥሪ ደግፋለች።ስብሰባው በዝግ ሳይሆን ክፍት ስብሰባ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

🇦🇺የአውስትራሊያ ኤምባሲ ሰራተኞች እና ባለስልጣናት ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪሴ ፔይን ገልጸዋል፡፡የሀገሪቱ ኤምባሲ እና በዩክሬን ሉቪቭ ከተማ ያለው ስራ ለጊዜው ተዘግቷል ብለዋል ሚኒስትሩ።

🇺🇿ዩክሬንን ለቀው ለመውጣት የሚሞክሩ አውስትራሊያውያንን ለመርዳት ሰራተኞቹ ወደ ሮማኒያ እና ምስራቃዊ ፖላንድ ተልከዋል።

🇺🇸የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለደህንነት ሲባል በዩክሬን በሉቪቭ የቀሩት የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ሰራተኞች በፖላንድ እንደሚያድሩ አረጋግጠዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች

አባላቱ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ...

👉 አሸባሪው ህወሓት በአፋር ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ለማስቆም መንግስት ምን አስቧል፤
👉 የአምባሳደሮች ሹመት መስፈርት ምንድን ነው፤
👉 የእነ ስብሃት ነጋ ከስር መለቀቅ ከህግ አንጻር ያለው የመንግስት ምላሽ ምንድን ነው፤
👉 በምክር ቤቱ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው ከትህነግ ጋር ድርድር ተጀምሯል የሚባል ነገር አለና በዚህ ዙሪያ የመንግስት መልስ ምንድን ነው፤
👉 በውጭ አገርት በተለይም በሳውዲ አረቢያ ታስረው ያሉ ዜጎች
ጉዳይ፤
👉 የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ መንግስት ምን አስቧል፤
👉 በጦርነት የወደሙ ከተሞችንን ኣነ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የተያዘው በጀት አነስተኛ ስለመሆኑ፤
👉 የክልሎች ልዩ ሀይሎች አቅም መከላከያን የሚገዳደር አይነት መሆኑለአገር አንድነት ያለው ስጋት
👉 የድሬደዋ አስተዳደር ቻርተር ሲዋቀር የድሬደዋን ሁነታ ታሳቢ ያላደረገ በመሆኑ 39 ቀበሌዎችን እውቅና አይሰጥም፤ ሌሎች በርካታ ከመዋቅር ጋት የተያያዘ ችግሮችም ያሉበት በመሆኑ መንግስት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ፤
👉 የሙርሌ ታጣቂዎች እያደረሱት ያለው ጥቃትን ለማስቆም መንግስት ምን አስቧል፤
👉 በጋምቤላ ክልል በህወሓት ዘመን በኢንቨስትመንት ስም የገቡ ባለሀብቶች በርካታ ሀብት ዘርፈዋል ይህ ሀብት እንዲመለስ ቢደረግ፤
👉 የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነትን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ምን የታሰበ ነገር አለ፤
👉ሀይቆችን አልምቶ ለልማት ለማዋል መንግስት ምን አስቧል፤
👉 የኦሞ ኩራዝ 1 እና 5 የስኳር ፋብሪካዎች ባለፉት ሁለት አመታት ስራቸው ተቋርጦ ቆሟል። ስለሆነም መንግስት እነዚህን ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ምን አስቧል፤
👉 በሶማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ ባለፉት 40 አመታት ያልተከሰተ ከባድ ድርቅ ነው፤ በዚህም አርብቶ አደሩ ችግር ውስጥ ነው። ድርቁ ወደ ረሀብ ተሸጋግሮ ከባድ ጉዳት እንዳይደርስ መንግስት ምን አቅዷል፤ በዘላቂነትስ አርብቶ አደሩ ከዚህ ችግር እንዲወጣ ምን ታስቧል፤
👉 ወደ ስራ ያልገቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አሉና መንግስት ካላቸው ፋይዳ አንጻር መንግስት ምን አቅዷል፤
👉 የፌዴራልና የክልል መንግስታት በሙስና ላይ በአንድ ላይ ተባብረው የሚዘምቱት መቼ ነው፤
በአሁኑ ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እየሰጡ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት 297 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ!

በጦርነትና ሌሎች ውስብስብ ችግሮች ውስጥ በከረመችው ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ገቢ ቢሰበሰብም መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት 297 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

የባለፉት 6 ወራት አገራዊ ወጪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 39 በመቶ እድገት እንዳለውም አመላክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ነው።

ያለፉት ስድስት ወራት የጦርነት ወቅት በመሆናቸው ምጣኔ ሃብቱ ላይ በዘርፈ ብዙ ፈተናዎች የታጠረ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

በጠርነት ወቅት ብድር የሚሰጡ አገራት እና ተቋማት ብድር መስጠቱን፤ እርዳታ የሚያደርጉ ደግሞ እርዳታን ያዝ የማድረግ ሁኔታቸው ከፍ ያ ስለሚሆን ምጣኔ ሃብቱን በእጅጉ ይጎዱታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አምራቹ ኃይል በሙሉ ኃይሉ ከማምረት ይልቅ አንድም በአካል አሊያም በሐሳብ ወደ ጦርነቱ መግባቱ፣ የዜጎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ በስፋት መኖሩ ያለፉት ስድስት ወራት የምጣኔ ሃብቱ ተግዳሮቶች እንደነበሩም አስረድተዋል፡፡

ይህም ሆኖ ባለፉት 6 ወራት 185 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 171 ነጥብ 3 ቢሊዩኑን መሰብሰብ ወይም የእቅዱን 92 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህ ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲታይ የ15 በመቶ እድገት እንዳለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

ይሁንና የመንግሥት ወጪ 297 ቢሊዮን ብር በላይ እንደነበረም ነው ያሳወቁት።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባህር ትራነዚት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ያወጣውን ጨረታ ሰረዘ!

ኢባትሎአድ ለሚሰጠው የጭነት ግልጋሎት የተጨማሪ 150 ተሽከርካሪ ግዥ አለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ የጨረታ ሂደቱም ከሳምንታት በፊት ተከፍቶ የቴክኒክ ግምገማ የተደረገ ሲሆን፡፡ የጨረታ ኮሚቴው የፋይናንስ ሰነዱን ሳከፍት ጨረታው እንዲሰረዝ መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ለዚህም በዋንኛነት የተጠቀሰው የተጫራቾች ተሳሰትፎ ዝቅተኛ መሆን ነው፡፡

ካፒታል ባገኘችው መረጃ 150 የጭነት ተስከርካሪዎች ግዥ በጨረታው የተሳተፈው የቻይናው ግዙፍ የተሽከርካሪ አምራች ዢያን ሳይኖትራክ ብቻ ነው፡፡ እንደሚታወሰው ይህ ኩባንያ አምና ወጥቶ የነበረውን የ150 ተሽከርካሪዎች ግዥ ጨረታ ያሸነፈ ነው፡፡በቅርቡ በተከፈተው ጨረታ አንድ ተሳታፊ ብቻ በመቅረቡ ጨረታው መሰረዙን የአገልግሎቱ ሃላፊዎች ተናግረው የጨረታ ሰነዱን በመከለስ በቅርቡ ድጋሚ ጨረታ ይወጣል ብለዋል፡፡የ150 ጭነት ተሽከርካሪዎች ጨረታ የወጣው የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ባመቻቸው የ70 በመቶ የዱቤ ዋስትና ግዥ (ዲፈርድ ኤልሲ) መሰረት ነው፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
“እስረኞች በመፈታታቸው ኢትዮጵያ በእጅጉ ተጠቃሚ ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ይህን ያደረግነው ለኢትዮጵያ ጥቅም ነው የምንሞተውም የምንኖረውም ለሃገር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እስረኞችን ለመፍታት የተገደድነው በሶስት ምክንያቶች ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ፊት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፓርላማ አባላት በቅርቡ በምህረት ስለተለቀቁት እስረኞች በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እስረኞችን የፈታነው በሶስት ምክንያቶች ነው ሲሉም ምላሽ ሰተዋል፡፡

ለዘላቂ ሰላም፤የታሳሪዎችን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ያገኘነውን ድል ለማፅናት እስረኞችን ፈተናል ብለዋል፡፡

ጦርነት አስከፊ ነገር እንደሆነ ከራሳችንም ሆነ ከአለም ታሪክ ተምረናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፡፡

ከህወሃት ጋር በተያያዘም እስካሁን ምንም አይነት ድርድር አልተደገም ሲሉም ምላሽ ሰተዋል፡፡

ነገር ግን ይህ ማለት እስከመጨረሻው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት የውጭ ባንኮችን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት የፖሊሲ ማሻሻያ እንደሚያደርግ ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምለሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራያቸው የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን፤ ከእነዚህም የባንኮች ጉዳይ አንዱ ነበር።

በዚህም የኢትዮጵያ ባንኮች ሀብት እያደረገ መምጣቱን አንስተው፤ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የባንኮች የሀብት ከነበረበት 1.8 ትሪሊየን ብር ወደ በ2 ትሪሊየን ማደጉን አስታውቀዋል።የባንኮች ተቀማጭ ሀብትም ባለፈው ዓመት ከነበረበት 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ባለፈው ስድስት ወራት ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ማደጉን አስታውቀዋል።የባለድርሻዎች የሀብት መጠንም እንዲሁ ጭማሪ አሳይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህም የአክሲዮች ባለድርሻዎች ሀብት 159 ቢሊየን ብር መድረሱንም አስታውቀዋል።የባንኮች የቅርጫፍ መጠን ባለፈው ስድስት ወር በተሰራው ስራ ከ6 ሺህ 700 ወደ 7 ሺህ 400 መድረሱንም ከፍ ማት መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

የኢትዮጵያ ባንኮች ላለፉት 20 ዓመታት ብቻቸውን የሚሰሩበትን እድል አግኝተው ቆይተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ፤ አሁን ግን ይህንን ማስቀጠል አይቻልም፤ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ፣ ተጨማሪ ሀብት ስለሚያስፈልግ የውጭ ባንኮች መምጣታቸው አይቀርም ብለዋል።“ባንኮች በቴክኖሎጂ እና በዘመናዊ አሰራር ራሳቸውን በማደራጀት ከፍ ላለ ውድድር ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው” ያሉ ሲሆን፤ መንግስት የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑንም አስታውቀዋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

👉 የፌዴራል መንግስት ከአፋር ክልል መንግስት ጋር በቅርበት ነው የሚሰራው
👉 የአፋር ጥቃት የኢትዮጵያ ጥቃት ነው፤ የአማራ ጥቃት የኢትዮጵያ ጥቃት ነው፤
👉 የሰሞኑ የህወሓት ጥቃት ዓላማው አፋር አይደለም፤
👉 የዓለም መንግስታት ኢትዮጵያን የሚከሱበት ክስ በሙሉ አለቀ፤ ምን ቀራቸው ሰብአዊ ርዳታ የሚል፤
👉 ይሄ እንዳይሳካ ደግሞ ህወሓት ወደ ትግራይ የሚሄድ ርዳታን አስተጓጎለ ከዛ አማራ አፋር ትግራይን አስራበ ይባላል፤
👉የአማራ ገበሬ የትግራይ ቁስለኞችን ወተት አልቦ አጥቶ አክሞ ወደ ትግራይ ልኳል፤
👉 አፋር ላይም የግመል ወተት የሚጠጡት አፋሮች ብቻ አይደሉም፤ የህወሓት ቁስለኞችም ጭምር እንጂ፤
👉 በዚህ ውጊያ እንደ ትግራይ ክልል የተጎዳ የደቀቀ ክልል የለም፤ የምንገነባው እኛው ነን የእኛው እዳ ነው፤ ህወሓት መስራት አይችልም፤
👉 በአፋርም በአማራም የሚደረገው ጥቃት የጋራ ጥቃት ስለሆነ በጋራ ነው የምንከላከለው
👉 ሸኔ ለምን ዓላማ እንደሚዋጋ የማይታወቅ፤ ዓላማ የሌለው ቡድን ነው፤
👉 ሸኔ ከምን አይነት ስብስብ የተሰራ እንደሆነ ግራ የሚያጋባ ነው፤
👉 የፌዴራል መንግስት ከዚህ እኩይ ቡድን ጋር ከፍተኛ ትግል አድርጓል፤
👉 ይሄ ቡድን በየስራቸው ተደብቆ ያለ ሀይል ነው፤
👉 ህዝቡ ለምንድን ነው የደበቀው የሚለውን መነጋገር ያስፈልጋል፤ እኛ ጋር ችግር ካለ ማየት አለብን፤
👉 ለምን የሆነ ወረዳ ይህንን ቡድን ቀለበው ብሎ መፈተሽ ያስፈልጋል፤
👉 ይህ ቡድን ሰው ሊገል ይችላል ግን አያሸንፍም፤
👉 ልዩ ሀይሎች ኢትዮጵያ ስትጠቃ ባላቸው ሀይል ሁሉ ተጋድሎ አድርገዋል፤
👉 ልዩ ሀይሎችን በተመለከተ ጥናት ያስፈልገናል፤
👉 በዚያ እንመልሰዋለን፤ ተነጋግረን እናደርገዋለን፤

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዋጋ ግሽበት እና ለኑሮ ውድነት ጥያቄው ምን ምላሽ ሰጡ?

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የምክር ቤት አባላት ካነሷቸው አንኳር የሕዝብ ጥያቄዎች መካከል የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት አንዱ ነው፡፡ የምክር ቤት አባላቱ እንዳሉት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት ሕዝቡን በከፍተኛ ደረጃ ምሬት ውስጥ አስገብቶታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽም ይሕንኑ ነው ያረጋገጡት፡፡ በተለይ ከምግብ ነክ ሸቀጦች ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መፈጠሩን አመላክተዋል፡፡ ይህም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ሰዎች በልቶ ማደር እንዳይችሉ አድርጓል፤ እንዲማረሩም ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት፡፡

የዋጋ ግሽበት በአንድ ምክንያት ብቻ የሚፈጠር አለመኾኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሑራን በርካታ ምክንያቶች ያነሳሉ ብለዋል፡፡ ከነዚህ ምክንያቶች መካከል በሕዝብ ቁጥር እድገት የተፈጠረው የፍላጎት መጨመር አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሌላኛው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት ምክንያት የአቅርቦት እድገቱ ከፍላጎት ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑ ነው፡፡ ነጋዴው የዋጋ ጭማሬን በመጠበቅ ምርትን መሸሸግ እና ሸማቾች ውድነቱን በመስጋት ለመግዛት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሌላኛው ምክንያት ተደርጎ ተነስቷል፡፡ በነጋዴና ሸማቾች የተዛባ አመለካከት ምክንያት ምርት እያለ እንኳን የዋጋ መናር እያጋጠመ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የዓለም የሸቀጥ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩም ለችግሩ መባባስ አንዱ ነው፡፡ የኮሮናቫይረስ በዓለም የንግድ ሥርዓት ላይ በፈጠረው ተጽዕኖ መሠረት የዓለም ኢኮኖሚ መቀነሱንም አመላክተዋል፡፡ በሀገር ውስጥ ሸማችን ከምርት ጋር የማገናኘት ችግሩ የዋጋ ግሽበቱን እንዳናረው ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ሕዝቡ ገዝቶ መብላት ስላልቻለ በከፍተኛ ደረጃ ተማርሯል ነው ያሉት፡፡ የዋጋ ግሽበቱ የፈጠረውን መዛባት ለመቀነስ መንግሥት በግምጃ ቤት ሰነድ እንዲሟላ አድርጓል ብለዋል፡፡ ይህንን ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያትም ገንዘብ በገበያ ውስጥ በተሰራጨ መጠን ግሽበቱ ስለሚባባስ 80 በመቶ በግምጃ ቤት ሰነድ ለመተካት ጥረት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቅ ቢሆንም የተሠራው ሥራ ቀላል እንዳልሆነ ነው ለምክር ቤት አባላቱ ያብራሩት፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት የምግብ ሸቀጥ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ኮታ መሰጠቱንም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለነዳጅና ለአፈር ማዳበሪያ መንግሥት ድጎማ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ የከተማ ግብርና እንዲያድግም ተደርጓል ብለዋል፡፡ አሁንም በከተሞች የጓሮ አትክልት መልማት የሚችል ከሆነ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ነው ያሉት፡፡ ለዋጋ ግሽበቱ ዋንኛው የችግር መሠረት የምግብ ሸቀጥ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን በመሰረታዊነት ለመፍታት እንደ ሀገር የምግብ እህል ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ ለዚህም የሁሉንም ርብርብ ይሻል ነው ያሉት፡፡

Via AMC
@YeneTube @FikerAssefa
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በ+2517 ኮድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል!

በቀጣይ አሥር ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ1 ነጥብ 5ሚሊየን ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት መዕዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱበት በኢትዮጵያ አዲስ ጅማሮ የሆነው የቴሌኮም ዘርፍ ላይ ኢትዮጵያዊያንን የሚመጥን ዘመናዊ የኔትዎርክ ዝርጋታ እንደሚያካሂድ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ሃላፊ ማቲው ሀሪሰን ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በአዳማ በመቶ ሚሊየን ዶላር ወጪ የዳታ ማዕከል መገንባቱን ያነሱት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ክፍል ዋና ሃላፊ ፔድሮ ራቫካል በዚህ ዓመት በሁለቱም ከተሞች ሁለት ተጨማሪ የዳታ ማዕከል እንደሚገነቡ ገልጸዋል፡፡በቀጣይ አሥር ዓመታት 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በማፍሰስም የዘርፉን ተጠቃሚነት የማሻሻል ዕቅድ እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በ (+2517) ኮድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ነው የተባለው፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአውሮፓ ህብረት በሩስያ ላይ ማዕቀብ ሊጥል ነው።

ጀርመንም ከሩሲያ ጋር ልታደርግ የነበረውን የንግድ ስምምነት መሰረዟን በዛሬው ዕለት ገልፃለች።የጀርመን የዜና ወኪል /DPA/ እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት ማዕቀቡን የሚጥለው ራሳችንን ችለን እንገነጠላለን ላሉት ሁለት የዩክሬን ክልሎች ሩሲያ እውቅና በመስጠቷ እና ወታደሮቿን በቦታው በማሰማራቷ ነው። የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባም የሩሲያን እርምጃዎች ዝርዝር ማውሳታቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እንደገለፁት ዛሬ ከስዓት በኋላ የማዕቀቡ ምክረ ሀሳብ ማጠቃለያ ያገኛል።ርምጃዎቹ ደግሞ በነገው እለት ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።እንደ ዘገባ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን ትናንት ሰኞ፤ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክ በተባሉ የዩክሬን ግዛቶች ሩስያ ወታደሮቿን ለማሰማራት በወጣው አዋጅ ላይ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

ወታደሮቹንም "ሰላም አስከባሪዎች" በማለት ጠርተዋቸዋል። ይህ እርምጃም በሩሲያ ላይ ዓለም አቀፍ ውግዘትን አስከትሏል።የማዕቀቡ ረቂቁ ሀሳብ በዩክሬን "ህገ-ወጥ ውሳኔ" በግላቸው የተሳተፉትን ሁሉ የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል።ከከዩክሬን ተገንጣይ ክልሎች ከዶኔትስክ እና ሉሃንስክ ጋር ወታደራዊ እና ሌሎች ሥራዎችን በገንዘብ የሚደግፉ ባንኮችም በማዕቀቡ የተካተቱ ሲሆን፤ በክልሎቹ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚደረግ የንግድ ልውውጥም ዒላማ ይሆናል ተብሏል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ቀደም ሲል ከመረጣቸው 42 ዕጩዎች ውጭ ሌሎች ሁለት ኮሚሽነሮች ትናንት ሹሟል እያሉ አንዳንድ አካላት የሚያሰራጩት መረጃ አሳሳች ነው ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል። ምክር ቤቱ አንዳንድ ዕጩዎች ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደሌላቸው በመረጋገጡ እና አንዳንዶችም በኮሚሽነርነት ለመስራት ፍላጎት እንደሌላቸው በማሳወቃቸው፣ ከ42ቱ ዕጩዎች ዝርዝር እንደተሰረዙ እና በምትካቸው በሁለተኛ ምድብ ከተያዙት 75 ዕጩዎች መካከል ሌሎች ዕጩዎች አስተያየት ተሰጥቶባቸው እንደተመረጡ ገልጧል። ብዝኀነትን፣ ጾታን እና ዕድሜን መሠረት ያደረገ ማስተካከያ ማድረጉን እና ማስተካከያው የሕዝብን አስተያየት መሠረት ያደረገ እንደሆነም ምክር ቤቱ ጨምሮ አብራርቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ማዕድን ለማውጣት ሲሉ አፈር ተደርምሶባቸው 7 ወጣቶች ህይወታቸው አለፈ።

በምስራቅ ባሌ ዞን ጎሎልቻ ወረዳ ማዕድን በማውጣት ላይ በነበሩ ወጣቶች ላይ አፈር ተንዶባቸው የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገለጸ። ሕይወታቸው ካለፈው 7 ሰዎች በተጨማሪ በ11 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው።

የዞኑ የማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሐኑ ጆቢራ እንደገለጹት ወጣቶቹ የማዕድን ሚኒስቴር እንዲሁም የክልሉ የማዕድን ልማት ቢሮ ጥናት አድርጎ ባልጨረሰበት ቦታ በግላቸው ሲሳተፉ እንደነበር ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስትም በደረሰው አደጋ የተሰማውን ኃዘን ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁


🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
https://youtu.be/sG0S6CNbmvw

Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.

የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።


https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
https://youtu.be/G-fzeN_xbRk
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
በየኔ ትዩብ ላይ ማስታወቂያችንን ዐይቶ ተመዝግቦ አሁን ላይ በአሜሪካ ትምህርት የጀመረ ተማሪ ምስክርነት በላይ ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ!

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinaadvisor
ሌተናንት ጀነራል አስራት ዴኒሮ የደቡብ ሱዳን የሰላም ተቆጣጣሪ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ!

በኢትዮጵያ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ የነበሩት ሌተናንት ጀነራል አስራት ዴኒሮ የደቡብ ሱዳንን ሰላም አስከባሪ አዛዥ ተደርገው ተሹመዋል።የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምድር ኃይል ዋና አዛዥ እና የመተከል ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ የነብሩት ጀነራል አስራት ዴኒሮ ይህ ሹመት የተሰጣቸው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሲሆን በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ማስፈን እና የሽግግር ወቅት ፀጥታን መቆጣጠር የጀነራሉ ኃላፊነት መሆኑ ተገልጿል።

የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ቢሮ ቃል አቀባይ የሆኑት ኑር መሐመድ ሼህ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት “በጣም ብቁ እና የውትድርና እውቀት ያለው በመላው ዓለም የተከበሩ ባለሙያ ናቸው” ሲሉ ስለ ጀነራል አስራት ዴኒሮ መፃፋቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም እንዲሰፍን ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም በሁለት ጎራ የተከፈለውን የሀገሪቱንወታደራዊ ኃይል ወደ አንድ ወታደራዊ አመራር ማምጣት በጀነራል አስራት ላይ ከተጣሉ ኃላፊነቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።ሌተናንት ጀነራል አስራት የተተኩት በኢጋድ የደቡብ ሱዳንን ተልዕኮ ለሁለት ዓመታት በመሩት ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ቦታ ነው።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ በጀመረው ስብሰባው በወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa