YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ከሚያዚያ በፊት ዝናብ አያገኙም ተባለ!

በኢትዮጵያ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ከሚያዚያ በፊት ዝናብ እንደማያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡በኢትዮጵያ በሶማሊ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያጋጠማቸው ሲሆን እጥረቱ ከክልሎቹ አቅም በላይ በመሆኑ ድርቁ በሰው እና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባሳለፍነው ሳምንት ማሳወቁ ይታወሳል።

በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ መነሻው ባሳለፍነው ክረምት ወራት ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመዝነቡ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ ምንም ዝናብ አለመዝነቡ ቢሆንም፤ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት ውስጥ ዝናቡ አለመዝነቡ ጉዳቱን አባብሶታልም ተብሏል።

በኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትት የአየር ሁኔታ እና ትንበያ ባለሙያው አቶ ታምሩ ለአል ዐይን አማርኛ እንገለጹት አሁን ላይ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባዎች ከሚያዝያ በፊት ዝናብ እንደማያገኙ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ለማንበብ :- https://am.al-ain.com/article/ethiopian-drought-stricken-areas-will-remain-arid-untill-march

@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በአፋር ክልል ባንድ የስደተኞች መጠለያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ አምስት ስደተኞች እንደተገደሉ አስታውቋል። ይኼው ጥቃት ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጸመው እና አምስት ስደተኞች የተገደሉት የኤርትራ ስደተኞች በተጠለሉበት በርሃሌ መጠለያ ነው። ከመጠለያው በርካታ ሴት ስደተኞችም በታጣቂዎች ታፍነው እንደተወሰዱ ኮሚሽኑ ገልጧል። በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጥቃቱን ተከትሎ ወደ ሠመራ፣ አፍዴራ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች ሸሽተዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube pinned «https://youtu.be/sG0S6CNbmvw Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows. የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ። https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb»
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/sabinaadvisor
👇👇👇👇👇👇👇👇
🇹🇷#Turkey_visa

የቱርክ ኢምባሲ አሁን ላይ ስራ ስለጀመረ ፕሮሰስ ለመጀመር ለምትፈልጉ ደንበኞቻችን አሁኑኑ ያናግሩን

👇
የሥራ ቪዛ ወደ ቱርክ

የሆቴል ሥራዎች

ጾታ፡ ወንድ እና ሴት

1. Cleaners
2. Dishwashers
3. Janitors

#Benefits
1. Food and accommodation
2. One way flight ticket
3.Training
4. Salary
5. Service bus

#Process_time = 2 months

#Work_in_Turkey

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

Contact:
@Sabinavisa
@Sabinavisa2
+251118683939
0936363639
0936363680
https://tttttt.me/sabinavisaa
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁


🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
https://youtu.be/sG0S6CNbmvw

Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.

የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።


https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb
የየካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ስነ ስርዓት ላይ ጀግኖች አባት አርበኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የስካውት አባላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በአፋር በከባድ መሣሪያ ጥቃት አስር የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸው ተነገረ!

ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 08/2014 ዓ.ም ምሽት ላይ ተፈፀመ በተባለው የከባድ መሳሪያ ጥቃት አስር የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውንና ሌሎች 13 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ከአካባቢው የወጡ ሰዎችና የበጎ ፈቃደኛ ለቢቢሲ ገልጸዋል።በጥቃቱ አስር የቤተሰብ አባሎቻቸው የተገደሉባቸው አቶ ሁሞ እና ቤተሰባቸው ይኖሩ የነበረው በአፋር ክልል ውስጥ በምትገኘው አዳ የምትባል ትንሽ ከተማ ነበር።

ከተማዋ ከበርሃሌ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ እንደሆነች በሰመራ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሁሞ የቅርብ ዘመድ አቶ ያሲን ከድር ለቢቢሲ ገልጸው፤ አጠቃላይ ዘመድ በከባድ ሐዘን ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።በጥቃቱ ልጆቻቸውን ይዘው በመሸሽ ላይ ከነበሩት የቤተሰብ አባላት መካከል አምስት ህጻናት፣ እናት፣ የእናት እናት [አያት]፣ የእናት ወንድም እና የአባት እህት ሁለት ልጆች መሆናቸው ተገልጿል።አባወራው አቶ ሁሞ ቀድመው ከአካባቢው ተፈናቅለው ወጥተው ስለነበር በቤተሰባቸው ላይ ከደረሰው አደጋ ሊተርፉ ችለዋል።ሙሉ ቤተሰባቸውን ያጡት አባት ሐዘኑን ሊቋቋሙ በማይችሉት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴው ግድብ ነገ ዕሁድ የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተነገረ።

በሁለት የኋይል ማመንጫ ተርባይኖች በውሀ የመሞከር ስራ በስኬት የተከናወነ ሲሆን አሁን ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የኤሌክትሪክ ኋይል ማመንጨት የሚጀምርበት ዕለት በግድቡ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ይሆናል፤ዋዜማ ራዲዮና ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገቡት።

@YeneTube @FikerAssefa
የምግብ ዘይት በቅርብ ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳየ!

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች አንድ ሊትር የምግብ ዘይት እስከ 170 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።የዋጋ ጭማሪው ከጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የተከሠተ መሆኑን አዲስ ማለዳ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውራ ያነጋገረቻቸው የምግብ ዘይት ሻጮች ተናግረዋል።ከውጭ ገበያ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ከሱፍ የሚመረተው አንድ ሊትር የምግብ ዘይት በተለያዩ መሸጫ ቦታዎች የተለያዬ ዋጋ ያለው ሲሆን፣ በመገናኛ አካባቢ ከ150 እስከ 160 ብር ሲሸጥ፣ በአየር ጤና አካባቢ ደግሞ ከ150 እስከ 170 ብር እየተሸጠ መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋግጫለሁ ብላለች።

@YeneTube @FikerAssefa
እየተደረገ ባለው የሰላም ጥረት ውስጥ ለድርድር በማይቀርቡት አምስት የትግራይ ሕዝብ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ሰጥቶ መቀበል እንደማይኖር የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።

ደብረ ጽዮን ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 47ኛ ዓመት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ከመንግሥት ጋር በተለያዩ ወገኖች አማካይነት ንግግር እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፣ ነገር ግን ለድርድር የማይቀርቡ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረታዊ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው ያሏቸውን አምስት ጉዳዮችን ዘርዝረዋል።"በመጀመሪያ ደረጃ በሠራዊታችን ላይ አንደራደርም።

አሁን ያለው ብቻ ሳይሆን ገና እንጨምርበታለን ስለዚህ በሠራዊታችን ጉዳይ ላይ አንደራደርም።ከዚህ በኋላም ኃይላችንን ይዘን ነው የምንኖረው" በማለት ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የታወቁ የትግራይ ክልል ወሰን ጉዳይ፣ የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ መውጣት፣ የትግራይ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብት ጉዳይ እና በትግራይ ሕዝብ ላይ በደል የፈፀሙ ግለሰቦች ተጠያቂነት ለድርድር አይቀርብም ብለዋል።

ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ጨምረውም እየተደረጉ ባሉት የድርድር ጥረቶች ውስጥ እነዚህ አምስት ቅድመ ሁኔታዎች ዋነኞቹና ሊጣሱ የማይገቡ የድርድር ነጥቦች መሆናቸውን ጠቅሰው "ሰጥቶ መቀበል የሚባለው ጉዳይ እዚህ ላይ አይሰራም" ብለዋል።

ነገር ግን ጦርነቱ በድርድር መፍትሔ እንዲያገኝ የተለያዩ ወገኖች የማሸማገል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ የአፍሪካ ሕብረትን በመወከል የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት፣ በተመሳሳይ የኬንያው ፕሬዚዳንት፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን የበኩላቸውን እየሞከሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ6 ወጣትና አንጋፋ ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሕዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምእሸት ተሾመ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲ ው አስተዳደር ቦርድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎቹ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ለማሽላ ደጀኔ ወልደሚካኤል (ዶ/ር) በዕፅዋት በሽታ ጥናት "ፕላንት ፓቶሎጂ"፣ ለዋሱ መሐመድ አሊ (ዶ/ር) በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል "ፕላንት ብሪዲንግ" እና ለንጉሴ ቡሳ ፌዳሳ (ዶ/ር) በ"ባዮኬሚስትሪ እና ፊዚዮሎጂ" የሙሉ ፕሮፌሴርነት ማዕረግ እንደተሰጠ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለአቢ ታደሰ (ዶ/ር) በ"ኢንኦርጋኒክ ኬሚስትሪ"፣ ለምትኩ እሸቱ ጉያ (ዶ/ር) በእንስሳት እርባታ እና ለተስፋሕይወት ዘሪሁን (ዶ/ር) በቨተርነሪ ክሊኒካል ፓቶሎጂ (ስነ ደዌ) የሙሉ ፕሮፈሴርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ተመራማሪዎቹ ባከናወኗቸው የምርምር ሥራዎች፣ በዓለም ዐቀፍ ጆርናሎች ላይ የህትመት ውጤቶችን በማሣተማቸውና በማኅበረሰብ አገልግሎት ባበረከቱት አስተዋፅዖ የሙሉ ፕሮፌስርነት ማዕረጉ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ሀብት_ያለው_አእምሮህ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የእለት ጉርስህን ለማግኘት እየተጣጣርክ ወይም ያለህ ሀብት እንዲበዛ የምታደርግበትን መንገድ እየፈለግክ ነው?

እንግዲያውስ ሀብት ያለው አእምሮህ የተሰኘው አዲሱ የዶ/ር ጆሴፍ መርፊ መጽሀፍ ይረዳሀል፡፡ መጽሐፉ “የሁሉም ሀብት መነሻ አእምሮ ነው” ይለናል፡፡

“የምትኖረው በአእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ሀብታም ወይም ደሀ፣ ለማኝ ወይም ሌባ የምትሆነው እዚያ ነው፡፡ በህይወት ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የመፍጠር ኃይል እንዳለህ ስትገነዘብ ታላቅ ዋጋ ያለው እንቁ እንዳለህ ታውቃለህ፡፡ በውስጥህ ያለው ሀብት እና ኃይል በጭራሽ የሚቀንስ ስላልሆነ አንተ ከምታስቀምጠው ገደብ በስተቀር የአእምሮህ ሀብት ገደብ አያውቅም፡፡”

ከዝቅታ ህይወት ወደ ከፍታ ህይወት ተሸጋግረህ አንገትህን ቀና ለማድረግም ሆነ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚገባህን ብልጽግና ለማግኘት ይህ መጽሐፍ እንዴት የድብቁን አእምሮህን ኃይል መጠቀም እንዳለብህ ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
የብዝሃ ሕይወት ብሄራዊ አማካሪ ምክር ቤት ልውጥ ዘረ መል የድንች እና ጥጥ ዘሮችን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ እያሰበ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በሁለቱ ልውጥ ዘረ መሎች ላይ የሙከራ ምርት እና ምርምር ለማድረግ እንዲፈቀድለት ለመንግሥት ጥያቄ እንዳቀረበ ዘገባው ጠቅሷል። መንግሥት ልውጦቹ የድንች እና ጥጥ ዘረ መሎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመረቱ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ግን ሕዝብ በጉዳዩ ላይ እንዲወያይበት ይደረጋል ተብሏል። የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ልውጦቹን የድንች እና ጥጥ ዘረ መሎች ለማስተዋወቅ ያሰበው፣ በሽታን የመቋቋም እና ከፍተኛ ምርት የመስጠት አቅም አላቸው በሚል መነሻ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ተመድ በኢትዮጵያ በጥቅምት ወር ታስረው የነበሩ 16 ሠራተኞቹ በሙሉ ከእስር እንደተፈቱ በቃል አቀባዩ ስቴፈን ዱጃሪች በኩል አስታውቋል። ከ16ቱ ሠራተኞች አብዛኞቹ ቀደም ባሉት ወራት የተለቀቁ ሲሆን፣ ሦስቱ ደሞ የተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና ሞሐመድ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በተመለሱ ማግስት እንደተፈቱ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል ሰሞኑን የክልሉ ገዢ ፓርቲ ብልፅግና ለሁለት ተከፍሏል በሚል በስፋት የሚናፈሰውን መረጃ በተመለከተ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ዑስማን ከዶይቼ ቬሌ ጋር ባደረጉት ቆይታ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዚህ በፊት በክልሉ የሚከሰት ድርቅ ለአንዳንዶች የጥቅም ምንጭ ይሆን እንደነበር ያነሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሁን በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ መንግስት እያከናወነ ያለው አሰራር ያልተመቻቸው ግለሰቦች የሶማሌ ክልል ብልፅግና ለሁለት ተከፍሏል በሚል ውዥንብሩን እንዲፈጥሩ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።በድርጊቱ እየተሳተፉ ባሉ አካላት ላይ የክልሉ መንግስት እርምጃ የመውሰድ ሀሳብ አለው ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ እንቅስቃሴው የክልሉን ህዝብ በተለያየ መልኩ ወደ ግጭት የሚያስገባ እና ወደ ህግ ጥሰት ከተሸጋገረ የክልሉ መንግስት ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል መስጠት ይጀምራል!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደቱን አጠናቆ በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ መስጠት ይጀምራል።ግድቡ ወደ ኃይል ማመንጨት የገባው በአንድ ተርባይን ነው።ኃይል የማመንጫ ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች ዩኒት ውሰጥ አንዱን በመጠቀም ነው ወደ መደበኛ ኃይል የማመንጨቱ ሂደት የተሸጋገረው፡፡አንዱን ተርንባይን በመጠቀም ወደ ስራ የሚገባው ግድቡ 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው የወጡት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻውን ከጊቤ ሶስት እና ጣና በለስ ኅይል ማመንጫዎች ቀጥሎ ሶስተኛው ከፍተኛ የሚመነጭ የኤልክትሪክ ኃይል ያደርገዋል።በተጨማሪነትም ሁለት ተርባይኖች በቅርብ ኅይል ለመስጠት የሚያስችላችው ስራም እየተጠናቀቀ ተመልክቷል።ግድቡ አሁን ላይ በሁሉም ስራዎች ፈጣን እድገት እያሳየ በመሆኑ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።እስካሁን ለግድቡ ግንባታ ከ163ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ወጥቶበታል፤ከዚህ ውስጥ 16.3 ቢሊየን ብሩ ከህዝብ ተሳትፎ የተገኘ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግድቡን ኃይል ማመንጫ ቁልፍ ተጭነው ኃይል ማመንጨት አስጀምረዋል!

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በጉባ ይገኛሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓባይ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችለውን ቁልፍ ተጭነው ዓባይ ለኢትዮጵያ ኃይል እንዲያመነጭ አድርገዋል።አሁን ዓባይ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ኃይል በአንደኛው ተርባይኑ ብቻ 375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨቱን ተቃወሙ!

ግብፅ እና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን ተቃውመዋል።ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግንባተው መሰረተ የተጣለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጉባ ተገኝተው ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች አንዱ ማለትም ዩኒት 10 በመባልየሚጠራው ተርባይን 375 ሜጋዋት ሀይል የማመንጨት ስራን አስጀምረዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨት ተከትሎ የግብጽ እና ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ሰጥተዋል።የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ እንዳሉት የኢትዮጵያ አካሄድ ግብጽ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2015 በካርቱም ያደረጉትን የመርህ ስምምነት የሚጥስ ነው ብለዋል።

በሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዳሴው ግድብ ተወካይ አምባሳደር ኦማር አልፋሩቅ ለአል ዐይን ኒውስ እንደተናገሩት፤ ግድቡ ሀይል ማመንጨቱ ሶስቱ ሀገራት የተናጥል እርምጃ እንዳይወስዱ በሚል የፈረሙትን የካርቱም ስምምነትን የሚጥስ እና ወዳጅነታቸውን የሚጎዳ ነው።

ሙሉ ዘገባው:
https://am.al-ain.com/article/egypt-sudan-oppose-ethiopian-mega-dam-power-production

@YeneTube @FikerAssefa